Jara Travelers

Jara Travelers Welcome to Jara Travelers, an adventurous and culturally immersive traveling group based in Ethiopia'
(3)

Jaarraan isinidha !Imala Jaarraa keessatti waan nu gargaartaniif Tokkoon tokkoon keessaniif galata gahaa galchuu hin dan...
14/11/2023

Jaarraan isinidha !

Imala Jaarraa keessatti waan nu gargaartaniif Tokkoon tokkoon keessaniif galata gahaa galchuu hin dandeenye.har'a garuu Carraa argame kanatti isin galateeeffachuu barbaanna.

Eyyeen Jaarraan Isinidha !

Maatiiwwan keenya jaallatamoo hojiin nu deeggartan, asitti seenaan hin mul'anne jira, achitti immoo kan seenaa hojjetetu jira;Bakka kana aadaan jira nuun jechaa ;Biyya jirtan keessaa laphee keessan kan nuuf kennitan, yaada Jaarraa osoo isinitti hin mul'isin kan hubattan,akkasumas immoo yaada Jaarraa erga isiniif ibsinee booda kan hubattan, beekunis ta'e osoo hin beekiin karaa biraatiin kan nu hubattan hundi keessan galata guddaa nu biraa qabdu.Isin jechuun dhiiga lubbuu dhaabbata keenyati.galatoomaa !

Jaarraan keenya.....

ji'a 4 keessatti

*Imala aadaa fi seenaa adda addaa saddeet( 8 ) seenaa hin himamne, bakka turistii fi seenaa dhuunfaa waliin qorachuu dandeenyerra.

* Miseensota lakkoofsaan 16 hin caallerraa gara miseensota maatii 165 ol uumuu dandeenyeerra.

* waa'ee naannoolee daawwanne Barreeffamoota 33 ol barreessinee afaanota 3n hawaasa miidiyaa bira akka dhaqqabu taasifneerra.

* Miidiyaa biyyatti 2 (Faanaa fi Walta) waliin gaaffii fi deebii gochuun sagantaa ayyaanaa isaan waliin hojjechuu dandeenyeerra.

* Hojii yeroo gabaabaa keessatti hojjenne ilaalcha keessa galchuun zoonii fi aanaalee Oromiyaa lama waliin kallattiin qunnamtii uumuudhaan waliin hojjechuu eegallee jirra;akkasumas immoo Guutuu Itiyoophiyaa irraa waamichi adda addaa nu qaqqabaa jira.

* dhalattooni Itiyoophiyaa biyyoota adda addaa jiraatan yommuu gara biyyaa isaanitti deebi'an sagantaa daawwi akka qopheessinuuf irra deddeebiin nu gaafataniiru.

*Yeroo gabaabaa kana keessatti fuula Facebook Jaarraa irratti hordoftoota 5000 arganne jirra.

Kun hundi kan ta'e isinini waan ta'eef isinumtii galata isaa fudhadhaa.
Eyyeen Jaarraan isinidha

galatoomaa 🙏

Jara  እናንተ ናችሁ...!እጅግ የምንወዳችሁ ቤተሰቦቻችን በስራ የምታበረቱን ፣ "እዚህ ቦታ ያልታየ ታሪክ አለ ፣ እዚያ ቦታ ታሪክ ሰሪ አለ፤ እዚህ ቦታ ባህል አለ..." እያላችሁ ፤ ካላ...
14/11/2023

Jara እናንተ ናችሁ...!

እጅግ የምንወዳችሁ ቤተሰቦቻችን በስራ የምታበረቱን ፣ "እዚህ ቦታ ያልታየ ታሪክ አለ ፣ እዚያ ቦታ ታሪክ ሰሪ አለ፤ እዚህ ቦታ ባህል አለ..." እያላችሁ ፤ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ልባችሁን የሠጣችሁን ፣ የጃራን ሀሳብ ሳንገልጥላችሁ የገባችሁ ፣ የጃራን ሀሳብ ገልጠን አስረድተናችሁ ያልገባችሁ ወይም በሌላ መንገድ የተረዳችሁ ሁላችሁንም እጅግ በጣም እናመሠግናለን ።

ጃራችን

በ 4 ወር ውስጥ

* ስምንት እጅግ የተለዩ ባህላዊ እና ታሪካዊ ጉዞዎችን ካልተሰሙ ታሪኮች፣ የቱሪስት መዳረሻዎች እና የግለሰብ ታሪኮች ጋር ለመዳሰስ ችለናል።

* ከ16 አባላት ብቻ ተነስተን 165 የቤተሰብ አባል መፍጠር ችለናል።

* ከ33 በላይ ፅሁፎች ስለሄድንባቸው አካባቢዎች በሶስት ቋንቋዎች ፅፈን ለ Social media ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ ችለናል።

* በ 2 ሚዲያ (Fana እና Walta ) ቃለመጠይቆችን ማድረግ እና የበአል ፕሮግራም አብረን መስራት ችለናል።

* በአጭር ጊዜ ውስጥ የሠራነውን ስራ ግምት ውስጥ በማስገባት ከሁለት የኦሮሚያ ዞን እና ወረዳዎች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ፈጥረን አብረን መስራት ጀምረናል፤ የተለያዩ ጥሪዎች ከመላው ኢትዮጵያ እየቀረበልን ይገኛል ።

* የተለያዩ አለማት ላይ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገር ቤት ሲገቡ በኢትዮጵያ ምድር የጉብኝት መርሀ ግብራቸውን እንድናሰናዳላቸው በተደጋጋሚ ጠይቀውናል ፤

*በዚህች አጭር ጊዜ በ Jara page 5000 Followers አግኝተናል እናመሰግናለን 🙏🙏

ስለ ጃራ ትራቭለርስ የታዘብኩትለማለት ያህል ብቻ ማለት ልክ አይመስለኝም ፤ ጃራ እንደወሊድ ሆስፒታል ነው ፤ ሁሌም ራሱን እየወለደ የሚመጣ የአዲስ ሀሳብ ፅንስ የሚላውስበት ነው፤ ጃራ ውስጥ ...
13/11/2023

ስለ ጃራ ትራቭለርስ የታዘብኩት

ለማለት ያህል ብቻ ማለት ልክ አይመስለኝም ፤ ጃራ እንደወሊድ ሆስፒታል ነው ፤ ሁሌም ራሱን እየወለደ የሚመጣ የአዲስ ሀሳብ ፅንስ የሚላውስበት ነው፤ ጃራ ውስጥ ስለ ገንቢ ታሪኮች ፣ ስለሚያንፁ ባህሎች ፣ ስለ ዘመን ተሻጋሪ መፃህፍት ይነገራል ፤ ደስ የሚሉ ወጣቶች ከመኪናችን የሚወጣውን የኦሮምኛ ሙዚቃ ተከትለው ሲፈሱ ታያላችሁ ፤ ሀገር የሚቀይር ህልማቸውን ሲያጋቡ ትመለከታላችሁ ፤ ተፈጥሮን እያዩ የሚያምር ትንፋሽ የሚያወጡ እና ለ አዲስ ሀሳብ ውልደት ምጥ ላይ ሲሆኑ አዲስ ነገር አይደለም ፤

ህልም አለን

የት እንሂድ? እንላለን ፤ የቱ ኦሮሚያ (ኢትዮጵያ) አልተነገረለትም ? የቱ ሞራል እና እሴት ወደ አደባባይ አልወጣም ? የህዝባችን ልህቀት እንዴት እንሰብካለን ? ለኦሮሞና ለኢትዮጵያ ሀገራችን የደሙ ፣ የሠሩ እና ላባቸው ያፈሰሱ ጉምቱ ሠዎች ን እንዴት እናመስግን ? ታክስ ከፍሎ ላስተማረን የገጠር ገበሬ በምን መድረስ እንችላለን ?

እዉነት ለመናገር ኦሮሚያ ያልተገለጠች ምድር ፣
እዉነት ለመናገር ኦሮሚያ የተዘጋች ቤት ፣
እዉነት ለመናገር ኦሮሚያ መቃብር ላይ የተፃፈች ፅሁፍ አይደለችም የሚል ቁጭት ነበረን ፤ እንደ ወጣቶች ሰብሰብ ራዕይ አለን ፤

የባህል ሰባኪዎች ነን ፤ እኛ ህልማችን ሀዋርያዊነት ነው ፤

ታውቂያለሽ ? ህልም አለን ፤

ህልማችን ጫጉላ ሞምባሳ ሄዶ የሚዝናና ሳይሆን በወንጪ የሚደግስ ኢትዮጵያዊ መፍጠር ነው ፤ ህልማችን ከቪክቶሪያ ሀይቅ ይልቅ ጭስ አባይን የሚመርጥ ትውልድ ማብቃት ነው ፤ ህልማችን አመት ፈቃድ ሞልቶ ከዱባይ ይልቅ በላንጋኖ ወይም በሶር የሚዝናና ኦሮሞ መፍጠር ነው።

ታውቃለህ ? ህልማችን

ቢሾፍቱ ወይም አዳማ ወይም ድሬዳዋ መጥቶ የሆነ ሬስቶራንት የፈረንጅ ምግብ በልቶ የሚያገሳ፣ ዋይን ከሚስቱ ጋር እየጠጣ Bishoftu ኦሮሚያ የሚል ፎቶ የሚለጥፍ ፣ ናይት ክለብ አዳር ጠጥቶ Live ገብቶ ፣ ቺክ ቀምሶ ኦሮሙማ የሚል ፣ በአፍ ኦሮሞ የሚል በልቡ ለኦሮሞ ማድረግ የማይሻ ጉራውን የሚቸረችር ትውልድ አይደለም ፤

ህልማችን

በከተማ የሚንጠራወዝ ወጣት ሳይሆን ሬስቶራንት ውስጥ እንደ ጭሮርሳ ያሉ ባህላዊ ምግቦችን የሚጠይቅ ፣ ገጠሪቱ ኦሮሚያ ያሉ ህፃናት ጋር ሄዶ ህመማቸውን የሚሰማ ፣ እስኪርቢቶ የሚገዛላቸው ፣ ገጠር ገበያ ወርዶ በግ ወይም ፍየል ገዝቶ ከእናቶች ጋር ገጠር ማዕድ የሚጋራ እና ለዚች እናት በማህረቧ የምትቋጥረው ፍራንካ የሚሸጉጥላት ፣ ፈረስ ጋልቦ ለጋለበበት የሚከፍል
፣ ቡነ ቀላ የሚቀምስ ፣ ጉጂ፣ ቦረና እና ከሚሴ የገዳ ስርዓት ሲከወን አብሮነቱን የሚያሳይ ሠው መፍጠር ነው ፤

ታዉቃላችሁ ? ህልማችን

የውጪ ፊልም የሚያደንቅ ፣ የውጪ ምሁር የሚያደንቅ ፣ ለንደን ብሪጅን ለማየት የሚጓጓ ፣ ኤይፍል ታወርን የሚያመልክ ትውልድ አይደለም ፤

ህልማችን

ገቢሳ እጄታን ፣ ቡልቻ ደመቅሳን ፣ ለማ ጉያን ፣ አብዲሣ አጋን ፣ ታደሰ ብሩን የሚያደንቅ ፣ ሶፍ ኡመርን ደጋግሞ የሚያይ ፣ እንደ ናይጄሪያ ከያኒያን በመላው አፍሪካ የሚተረጎሙ ኦሮምኛ ፊልሞችን የሚፅፉ እና ዳይሬክት የሚያደርጉ ኢትዮጵያዊያን መፍጠር ነው።
ጃራ እንደ
በዕሉ ግርማ ፣ ፀጋዬ ገ/መድህን ፣ አሊ ቢራ ፣ ሳህሌ ደጋጎ ፣ አያና ብሩ ፣ ተስፋዬ ለሜሣ አይነት ብሩሃን ኦሮሚያ ላይ ዳግም የመፍጠር ሀሳብ አላት እንጂ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አይዲዮሎጂ ገረድ አይደለችም ። አትሆንም ።

ሠላም ለሀገራችን

ፀሃፊ:- Natnael Kebede
Jara Travelers

   Kena Saketa  Team Jara Travelers ❤
07/11/2023


Kena Saketa



Team Jara Travelers ❤

   Jara Travelers
06/11/2023





Jara Travelers

   Jara Travelers ❤
04/11/2023





Jara Travelers ❤

ኦሮሞ ለልጁ ስም ሲያወጣንኳ «ሌንሳ» ብሎ ነው። እርጥብ ሳር እንደማለት ነው። ባህሉ፣ አኗኗሩ ትውፊቱ በሙሉ ከተፈጥሮ ጋር የተሰናሰለ ነው። ውሃ ፣ ሳር ፣ ዛፍ እነዚህ ሶስት ነገሮች ከኦሮሞ...
04/11/2023

ኦሮሞ ለልጁ ስም ሲያወጣንኳ «ሌንሳ» ብሎ ነው። እርጥብ ሳር እንደማለት ነው። ባህሉ፣ አኗኗሩ ትውፊቱ በሙሉ ከተፈጥሮ ጋር የተሰናሰለ ነው። ውሃ ፣ ሳር ፣ ዛፍ እነዚህ ሶስት ነገሮች ከኦሮሞ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አላቸው፡፡ ዛፍ (ዋርካ) (ኦዳ) ምኩራቡ ማለት ነው። ከፀሃይ ይጠለልበታል። ለፍርድ ፣ ለእርቅ፣ ለሹመት ፣ ይሰየምበታል። ውሃ አዝእርቱን ያበቅበታል። ይጠጣዋል። ከብቶቹን ያረሰርስለታል። እርጥብ ሳር ዋቃ ጉራቻ ሲባርከው የሚሰጠው ምልክት ነው። የበረከቱ፣ የልምላሜው፣ የተፈጥሮ ፀጋው ምልክት! ልምላሜውን እየቀጠፈ የተባረከው ውሃ ውስጥ ነክሮ ውሃውንም፣ ፀሃዩንም። ልምላሜውንም። ማሩንም። ቅቤውንም። ወተቱንም። ጤናውንም ለሰጠው ፈጣሪ ምስጋና ያቀርባል። ኦሮሞና ምስጋና አይነጣጠሉም። በትንሹ የሚያመሰግን ህዝብ ነው።

ዋቄፈታ እምነት ነው። ሊያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ እምነቶች በሙሉ ቀዳሚው! ክርስቲያን ብሆንም ፍልስፍናው ይደንቀኛል። ዋቃ ጉራቻ ማለት (ጥቁሩ አምላክ ማለት ነው) አለም ጥቁረትን እንደውርደት ተጠይፎ አምላኩንና መላእክቱን ሳይቀር ነጭ አድርጎ ሲስል ኦሮሞ ፈጣሪውን በራሱ መልክ ነው የቀረፀው። መፅሃፉም ሰው በፈጣሪ መልክ ተፈጠረ ይላል። ፈጣሪ እኔን ነው የሚመስለው። ከሚል በራስ ማንነት የመኩራት ፍልስፍና ውጤት ነው!
#ፀሃፊ:- Meti Sorecha





Jara Travelers

Kena Saketa  Jara Travelers
03/11/2023

Kena Saketa




Jara Travelers

የሠላሌ ህዝብ ይለያል! አከባቢውም ድንቅ ነው!!  ፨ባንድ በኩል ከኦሮሞ ጠላት ጋር ከባድ ውጊያ ላይ ይገኛል፤፨በሌላ በኩል ደሞ የኦሮሞ የእምነት በዓላትን ተንከባክቦ ለትውልድ ለማስረከብ በ2...
31/10/2023

የሠላሌ ህዝብ ይለያል! አከባቢውም ድንቅ ነው!!
፨ባንድ በኩል ከኦሮሞ ጠላት ጋር ከባድ ውጊያ ላይ ይገኛል፤
፨በሌላ በኩል ደሞ የኦሮሞ የእምነት በዓላትን ተንከባክቦ ለትውልድ ለማስረከብ በ2,500 ፈረሠኞች እና ከየአከባቢው በመጡ ውብ ህዝብ የደመቀ የበአል ዝግጅት አዘጋጅቶ፤ በባህሉና በእመነቱ መሠረት እምነቱን ከእነ በአላቱ ለትውልድ የሚያስቀጥል በጀግና እና በጠበብት የተሞላ ህዝብ ነው። 🙏🙏🖤🖤

የሠላሌ ህዝብ በኦሮሚያ ጠላቶች በተነሳ ከፍተኛ ችግርና ከባድ ትግል ውስጥ ባለበት ወቅት በመልካ ሲርጢ በመገኘት; የሠላሌ ወገኖቻችንን እኛ አብረናቹ ነን፤ ችግራችን ቢበዙም እንኳን የኦሮሞ የእምነት በአላት አይቀዘቅዙም፤ አለን እኛም ለብቻችሁም አይደላችሁም በሚል ተነሳሽነት..፤
ብዙ ሠወች አሁን መሄድ ስጋት አለው ሲሉ ወደሚሠማበት ውብ ወደሆነው የሠላሌ ምድር መልከ-ሲርጢ ድረስ በመገኘት ከታላቁ ከሸነን-ጂዳ ጎሳዎች ተወላጆ ከሆነው የጂዳ ህዝብ ጋር አንድ ላይ በጋራ የበአሉን ደስታ መካፈል፤ የሠላሌን ህዝብ በአካል ትከሻውን አቅፎ ምን እንደገጠመውና ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ መጠየቅና፤ ወንድማዊነትን በመግለፅ ማበረታታቱ እጅግ በጣም የሚመሠገንና ምሳሌ የሚሆን ተግባር ነው።
Ulfaadha🖤❤🙏🙏My team🥰

Nagaa
Nagaa
Nagaa
🖤🖤🙏🙏🖤
ሠላሌ ምርጥ ህዝብ! ድንቅ ተፈጥሮ 👌

#ፀሃፊ:- Nur JM

Jara TNur JMrsJara Travelers

ሁሉም ክብ ሰርቶ ጫወታዉ ደምቋል። አንዱ ጠላ፣ ሌላዉ አረቄዉን ይዞ እያለ በመሃል ጉዞው ላይ የተዋወኳት ልጅ (ኬና ) በትልቅ ብርጭቆ ወተት ስትጠጣ አየዋት። "ለኔም" አልኩ! ከዛ ባለቤቱ ሰ...
31/10/2023

ሁሉም ክብ ሰርቶ ጫወታዉ ደምቋል። አንዱ ጠላ፣ ሌላዉ አረቄዉን ይዞ እያለ በመሃል ጉዞው ላይ የተዋወኳት ልጅ (ኬና ) በትልቅ ብርጭቆ ወተት ስትጠጣ አየዋት። "ለኔም" አልኩ!
ከዛ ባለቤቱ ሰምቶኝ "ወተት ፈልገሽ ነው?" አለኝ "አዎ ግን የፈላ" አልኩት።

ከዛ ትንሽ ቆይቼ "ደግሞ ስኳር ይኑረው" ብዬ ነገርኩት። እንዳልኩት ሆኖ ወተቱ መጣልኝ! ጠጣዉ! ልረካ አልቻልኩም። ከነ ጆኩ አስቀመጠልኝና እስከ እንጥፍጣፊው ጠጣሁት!

ከዚህ በኋላ ነበር ሂሳብ ስንጠይቅ "ወተት አንሸጥም" አሉን። "እንዴ አይሆም" አልኩ። እኔ ወተቱ ብቻ ሳይሆን አንዴ 'አፍሉት' አንዴ 'ስኳር' ብዬ ሳስቸግር እንደነበረ ትዝ ሲለኝ ደግሞ ካልከፈልን ብዬ ብለምነዉ አሻፈረኝ አለ። ነገሩ እጄን ባፌ አስጫነኝ🤭

ለጀማዉ ሁሉ አወራዉ። ደሱን እረ ምንድነው የሚሉት መክፈል አለብን ስለው እየሳቀ አስረዳኝ። "ይሄኮ የአከባቢው ባህል ነዉ" አለኝ። ለካ ብዙዎቹ ይሄን ባህል ያዉቁታል እኔ አባባሉን ብቻ ነበር የሰማሁት ( ኦሮሞ ዉሃ ከጠየከዉ ወተት ይሰጥሃል )። ስለነገሩ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም!

አቡዬ አባቴ ብዙ ነግሮኛል።ግን አሁን አይኔ አየች!ገረመኝ በቃ! ደግነትና ፍቅር አካል ለብሶ ሰዉ ሆኖ አወራን፣ አጫወተን፣ አበላን፣ አጠጣን አብሮን ዋለ... ohh my kind people 🥺

ለንባብ አይበቃም አዉቃለሁ። ግን የተሰማኝን በትንሹ ላጋራ ብዬ ነው!

#ፀሃፊ:- MiMihret AmsaluVisit_Selale



JaJara Travelers

     Jara Travelers
30/10/2023





Jara Travelers

እንኳን ደስ አለን!!ሌጲስ በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና ሽልማት አገኘ፡፡በኢትዮጵያ ማእከላዊ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውን የሌጲስ መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት በ...
19/10/2023

እንኳን ደስ አለን!!

ሌጲስ በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና ሽልማት አገኘ፡፡

በኢትዮጵያ ማእከላዊ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውን የሌጲስ መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት በተባሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት እውቅና ሽልማት ተሰጥቶታል፡፡

በአስደናቂ እይታዎች፣ ፏፏቴ፣ አእዋፍት እና የዱር እንስሳት በውስጡ የያዘው የሌጲስ መንደር ከቀርከሃ በሚሰሩ የእደ-ጥበብ ውጤቶች በስፋት ይታወቃል፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዓለም ድንቅ መንደርነት የጮቄ ተራራ እና ከወንጪ የኢኮቱሪዝም መንደርን ያስመዘገበት ሲሆን የሌጲስ መንደር ሶስተኛ ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት ሆኖ በመመዝገቡ እንኳን ደስ ያለን!!

የቱሪዝም ሚኒስቴር

Team Jara Travelers ❤
11/10/2023

Team Jara Travelers ❤



Team Jara Travelers
10/10/2023

Team Jara Travelers



Team Jara Travelers ❤
09/10/2023

Team Jara Travelers ❤


እኛ ጃራዎች ነን። በ Natnael Kebede ገና ሶስተኛ ወራችንኮ ነው። ጥቂት ጓደኛሞች ውረድ እንውረድ ተባብለው ፣  አገጫጭተው እና አገጫጭተን ወደ ፖርቱጋል ድልድይ (ሠላሌ)  ሄድን። አ...
03/10/2023

እኛ ጃራዎች ነን።

በ Natnael Kebede

ገና ሶስተኛ ወራችንኮ ነው።

ጥቂት ጓደኛሞች ውረድ እንውረድ ተባብለው ፣ አገጫጭተው እና አገጫጭተን ወደ ፖርቱጋል ድልድይ (ሠላሌ) ሄድን። አስደናቂ ቆይታ ነበረን። ሁሉም አባላት (15ቱ ) ይድገም ፣ ይደገም ፣ ይደገም ተባባልን። የመጀመሪያው ጉዞ
ያደረገነው መልክዕ ምድርን መሠረት አድርገን ነበር።

ስቶሪ ይጨመርበት ተባባልን ፤ መፅሀፍ ጣል አደረግንበት፤ The Shepherd Surgeon የሚለውን የፕ/ር ምትኩ በላቸው ታሪክ አክለን የትውልድ ቦታቸው ወንጪ ፈሰስን።

Our travel should discover and rediscover stories including places ብለን ሁሉም በየተሰጥኦ ተሰማራ።

ሸገርን ረስተን ነሆለልን። በወሊሶ ሄደን በአምቦ እስከንመለስ ብዙ ተጋን ። የገበሬ ማዕድ ተቋደስን ፤ ፈረስ ጋለብን ፤ ምርቃት ተቐበልን ፤ ያየነውን ማስታወሻ ያዝን፤ ታዋቂው የህክምና ባለሙያ የፕ/ር ምትኩ በላቸው ልህቀት ተወያየን ።

ስንመለስ የያዝነውን ዘረገፍን ፤ ፎቶ ሼር ተደረገ ፤ ማስታወሻ የያዙ በፍጥነት ለጠፉ ፤ ልጥፉ ያለስስት ሁሉም አባላት ሼር አሉት። ወንጪ እንደ ዕጣ ተጣጣልንባት ፤ ሶሻል ሚድያው እሁድ ኢንሴኔ የሚባል የአካባቢው ምግብ ስንጎራረስ ፣ ኮባ ተደግፈን ፣ ጀልባ ላይ ሰንንሳፈፍ ፣ እንደ ሲውዘርላንድ ገጠሮች ምስላችን ብቻ የቀረ መስሎት ነበር፤ ሰኞ ግን ሌላ ነበር፤

Finfinne Times ፣ Mubarek Sultan ፣ Nardos Bogale ፣Hasenet Sani ስለ ወንጪ በግሩም ሁኔታ ፃፉ ፤ Robera Amsalu በራዲዮ ስለ ወንጪ ዝም አላለም ፤ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የወንጪን ውበት መጠጠላት። መፃፉ ፣ መሄዱ እና ፎቶ ከመፖስቱ ላይ ጃራ ተናገረች ፤ ልጆቼ የምትለጥፉትን ሼር አድርጉ አትሰስቱ አለች። ሁሉም ጃራ ያለውን ወይ ይለጥፋል ወይ ሼር ያደርጋል ። ከዛስ ከወንጪ መልስ የጃራ አባላት ተነጋገሩ ። እሺ ጃራ ላይ ምን ሀሳብ እንጨምርበት ተባባሉ ፤

Exposing the untold story

ለጥቆ ወደ ቢሾፍቱ ሄድን ፤ Expositionም አይደል ? ከአባታችን የመጫ እና ቱለማ መሪ ታዋቂው ፈላስፋ እና ሠ0ሊ ለማ ጉያ ጀርባ የተሸሸገ ሀሳብ ላይ አደፈጥን። Lemmism ላይ ጥቂት ቆየን። ስዕል ጎበኘን ፤ ለለማ ሙዚየም ገቢ ይሆን ዘንድ የአፍሪካ ኵራት የሆኑትን የህይወት ታሪክ መፅሀፍ ገዛን ፤ ከልጃቸው ነጻነት ለማ ጋር ስለ ለሚዝም ፍልስፍና አውርተን ወደ መገሪሳ (አረንጓዴ) ሀይቅ ሄድን ። ጥቂት ዘና ብለን ወደ ሸገር ተመለስን ፤

ስንመለስ

የሀሳብ ሽርሽር በፌስ ቡክ አደረግን ፤ ከመፅሀፉ ያገኘነውን እዉነት ገለጥን ፣ With different perspective ማዕድ አጋራን ፤ ማዕዳችን የሁላችሁ እንዲሆን ጃራዎች የተፃፉትን ሁሉ ሼር አሉ። ከዛ ነው ብዙዎች

ጃራነት ማለት
ልብ ያልተባለውን ልብ ማለት ፣
ያልተሄደበት መንገድ መመርመር
ያልቀናበረ ሙዚቃ ወደ ህዝብ ጆሮ ማድረስ ነው ያሉት።

ጃራ ጥቂት ጓደኛሞች የጀመሩት የጉዞ ግሩኘ ነው። በፅሁፍ ፣ በባህል ፣ በጉዞ ፍቅር ናላቸው የዞረ ሠዎች ጥቂት ገንዘብ እያዋጡ የሚሄዱበት ግሩኘ ነው። ምንም አይነት ስፖንሠርም ይሁን የመንግስት አካል ከጀርባው ደጋፊ አካል የለውም። በቀላሉ እዚሁ አዲስ ውስጥ ድራፍት መጠጣት ፣ ትልልቅ ካፌዎች መግባት ፣ Night club በመጨፈር ፣ መስፍን ቁርጥ ስጋ መብላት ፣ ፑልና ከረንቡላ መጫወት ወይም ኳስ ማየት ብቻ ተዝናኖት አይደለም ብለን ያመንን ነን።

መዳረሻችን

የኦሮሞ ገበሬ ቤት ነው ፤ ማደሪያችን የኦሮሞ ትውፊት እና እሴት ፣ ጌጣችን የኢትዮጵያ ብሄሮች ታሪክ ነው ብለን ነው የምናስበው ። ጆሮዎቻችን ቅድሚያ የሚሰጡት አልተሸጥንም እና አልሽጣችሁንም ለሚሉ የኢትዮጵያ ህዝብ Anthropology ነው። ለእኛ ለጃራዎች ከአንዷ ኢትዮጵያዊ እናት ሌላኛዋ አትበልጥም ፤ እኛ ጃራዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ እናቶች እኩል ሠዐት አምጠው የወለዱን ልጆቻችን ናቸው። አብዛኛው ጃራ ሠራተኛ ነው ፤ ቅዳሜና እሁድ ካልሆነ ጉዞ ይቸግረዋል ፤ ለዛ ነው ሸዋን የመረጥነው እንጂ የሸዋ ገበሬ ባህል ከቀሪው ኢትዮጵያ ባህል በልጦ አይደለም ። እንዲ እንድናስብ ጃራ አትፈቅድም። ራቅ ወዳለ አከባቢ ለመሄድ በጀት እና ጊዜ ይፈልጋል። ሀመርም ይሁን ባሌ ፣ ባሌም ይሁን ሶማሌ ፣ አውራ አምባም ይሁን ሰለኽለኻ ለመሄድ ያነስን አቅም እንጂ ልብ እና Cultural excellence አላጣንም ። አንዳንድ Content የላችሁም፣ አትፅፉም ፣ ቪድዮ የላችሁም እያሉ የሚተቹ ዙምቢዎች አሉ። የሌሎቹን ትተን ስለ ሄድንበት አካባቢ እኔ እንኳ 13ኛ ፅሁፍ አለኝ ፤ ፊንፊኔ ታይምስ 5ኛ ፅሁፍ አለው። አንዳንዱ ደግሞ የእንትን ብሄር ይበዛል እያለ መንደሩ መዘለሉን ይለፍፋል። ጭራሽ ወዳጆች ተሰብስበን የምንጓዘውን ጉዞ እንደ ሹመት የእገሌ ግሩኘ ፣ ጉጂ የለም ፣ ወለኔ የለበትም ፤ ኮንታ የለም ይልልኛል።

Anyways እኛ ጃራዎች ገና ብዙ እንጓዛለን ፤ ብዙ አንብበን ብዙ እንፅፋለን፤ ብዙ እንጠይቃለን ፤ ብዙ እንፈካለን ፤ በመላው ኦሮሚያ እና ኢትዮጵያ እየዞርን ህዝባችንን እንሸጣለን ፤ በህዝቦች መሀል ድልድይ እንሰራለን። ምክንያቱም እኛ ጃራዎች ነን።

በመስቀል ቀን በሰላሌ ቱባውን ባህል አየን፤ ደስም አለን!!I know ስለ ሰላሌ ለመፃፍ ቆይቻለው ግን better late than never አይደል የሚባለው?ሰላሌን የማውቀው በነፃነት ነበር።...
03/10/2023

በመስቀል ቀን በሰላሌ ቱባውን ባህል አየን፤ ደስም አለን!!

I know ስለ ሰላሌ ለመፃፍ ቆይቻለው ግን better late than never አይደል የሚባለው?

ሰላሌን የማውቀው በነፃነት ነበር። ነፂ የ8 አመት ልጅ ሳለው ለበአል ወደ አምቦ ከወላጆቼ ጋር ለመሄድ አውቶቢስ ተራ ውስጥ ያገኘናት የቤተሰባችን አባል ነች። ባልታሰበ አጋጣሚ ተገናኝተን ቤተሰብ ሆነን ቀርተናል። የነፂን ውበት ለመግለፅ ቃላት ያጥረኛል። ልቅም ተደርጋ የተሰራች የአምላክ ስራ ናት። እኔ ሴቷ እንዲህ ካልኩኝ ወንዶች ሲያይዋት ሀውልት እንደሚሆኑ መገመት አይከብዳችሁም (spoiler alert ባለ ትዳር ነች🙄)።

ጉዞዋችንን ጀምረን ብዙም ሳንዘልቅ የሱሉልታን ሜዳዎች ማየት ጀመርን። ረሃብ አይተው ሚያውቁ ማይመስሉ ከብቶች ለቄንጥ ከሰፊው ሜዳ ሲግጡ፣ ፈረሶች ከነ ውርንጭላቸው ሲቦርቁ፣ ህፃናት በሚያምር ቅላፄ ሲያዜሙ ሳይ ነው ውብ ቆይታ እንደሚኖረኝ የገባኝ። መሬቱ ለጥ ከማለቱ የተነሳ መነሻውን ከመዳረሻው መለየት ይሳናል። በአራቱም አቅጣጫ ስታዩ ሰላማዊና የማይዋዥቅ የሳር ሀይቅ ይመስላል። ምነው ፈረስ መጋለብ ችዬ መዳረሻውን በፈለኩ? ፀጉሬን በትኜ፣ ሀሳብና ጭንቀቴን ጥዬ... ይህ እርጎ የሆነ አየር ፊቴን አለሳልሶ አልፎ፣ ደረቴን በዳሰሰኝ ያስብላል።

ከሱሉልታ፣ ጫንጮ ከዛም ሙከ ጡሪ እያልን ገሰገስን። መዳረሻችን ጅዳ፣ ሲርጢ የምትባል ገጠራማ ከተማ ናት። በጊዜ አልደረስንም። በያገኘንበት ስንወርድ፣ ፎቶ ስንነሳ፣ መንገደኛ ስናናግር፣ የጀግናው ሻለቃ አበበ ቢቂላ የትውልድ መንደር ደረስን። ጋንጎ የምትባል ቦታ የተወለደ ሲሆን ታናሽ ወንድሙ ስሜ ቢቂላ በህይወት እንዳለ ነገሩን። በሩጫ ሀገራችንን አስጠርቶ፣ ድልን ተቀናጅቶ ሲመጣ በጊዜው የሀገሪቱ መሪ የነበሩት ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ምን ባደርግልህ ትሻለህ ብለው ሲጠይቁት በስሜ የትውልድ መንደሬ ላይ ት/ቤት ገንቡልኝ ብሎ የተገነባ ት/ቤት ነው። አበበ በልጅነቱ ያላገኘውን የትምህርት እድል ከሱ በኋላ ለሚመጣ ትውልድ መንገድ የቀየሰ መሃንዲስና አርቆ አሳቢ ጭምር ነው።

ጉዟችን እንደቀጠለ ነው። መንገደኛም አይደለን... መንገድ ሲኬድ ይርባል። በየመንገዱ እየበላን፣ እየጠጣን፣ እየተሳሳቅን፣ እየተቃለድን ነበር የደረስነው። ማረፊያችን የነበረው አንድ የሲርጢ ነዋሪ ቤት ነበር። ዳመራ አብርተን፣ ወጣቶች ጨፍረው፣ በተስረቀረቀ ድምፃቸው ጌረርሳው፣ ሄቤኬው፣ የፍቅር እንጉርጉሮው ቀጠለ። ጨዋታው እየደራ፣ እየተፋፋመ መጣ። በጠላቸው ሊያስቀኑኝ ሲሞክሩ፣ አንጀት የሚያርስ እርጎ ተሰጠኝ። 4 ብርጭቆ እርጎ በመጠጣት ሪከርዴን ሰብሬያለው።

በማግስቱ የመስቀል ቀን ነው። ኦሮሞ ከከብቶቹ ጋር ያለው መስተጋብር እጅጉን የጠነከረ ነው። በአብዛኛው የኦሮሚያ ገጠራማ ቦታዎች አንድ ብሂል አለ። ''Masqalatti kan beela'ee waggaa guutuu beela'aa.'' ትርጓሜውም በመስቀል የተራበ፣ አመቱን ሙሉ ይራባል ነው። ስለዚህም መስቀል የሰው ብቻ ሳይሆን የከብቶችም በአል ነው። ያሻቸውን ሰብል ጤፍ የለ፣ ገብስ የለ፣ ስንዴ የለ ያለ ምንም ከልካይ ይመገባሉ። የመስቀል ቀን ከብቶቹን ከበረታቸው የሚያስወጣው የቤቱ አባወራ ነው። የእረኛው የእረፍት ቀኑ ነው። ሙሽራ የሰርጉ ቀን መአድ ቀድሞ እንደሚያነሳ፣ እረኛም በመስቀል ቀን የመጀመሪያው ተመጋቢ እሱ ነው። በዚህ ልክ ከመከባበር እና መተሳሰብ የበለጠ ምን አለ?

በ GGifty TesfayeTGifty Tesfayeተፃፈ!

JJara Travelers TJara Travelers

Team Jara Travelers 😍😍Bokku Arts👌
30/09/2023

Team Jara Travelers 😍😍

Bokku Arts👌

We will waiting for you at 8:00 local timeAt Addis Ababa city Administration(municipality) city Hall(mazegaja bet) Bokku...
29/09/2023

We will waiting for you at 8:00 local time
At Addis Ababa city Administration(municipality) city Hall
(mazegaja bet)
Bokku Arts
Mubarek Sultan
See you there!

ሶሻሊስቱ ሠላሌቁጥር ሁለትመስቀል ይለያል ብየሀለሁ ፤ ከብቶቹ መስከረም 16 ከመሆኑ በፊት ከብቶች ይቆለፍባቸዋል ፤ መኖ እና ውሃ እዛው ይቀርብላቸዋል ፤ ወጥተው ግን አይግጡም ፤ የሚግጡት መ...
29/09/2023

ሶሻሊስቱ ሠላሌ
ቁጥር ሁለት

መስቀል ይለያል ብየሀለሁ ፤

ከብቶቹ

መስከረም 16 ከመሆኑ በፊት ከብቶች ይቆለፍባቸዋል ፤ መኖ እና ውሃ እዛው ይቀርብላቸዋል ፤ ወጥተው ግን አይግጡም ፤ የሚግጡት መስከረም 17 ላይ ነው። አንዳንድ መንደር ታጥሮ ለከብቶች የሚቀመጥ ግጦሽ አለ፤ አንዳንዱ ጋር አይታጠርም ፤ ታፍነው የሰነበቱት ከብቶች የመስቀል ቀን ከሌሊቱ ዘጠኝ ሠዐት ይለቀቃሉ ፤ በጦርነት ጊዜ እስር ቤት የተፈታለት ወንጀለኛ ይመስል ነፃ ሆነው ይሮጣሉ ፤ ያገኙትን ይበላሉ፤ ያገኙትን ይረግጣሉ ፤ ያገኙትን ያበላሻሉ ፤

ያ ቀን እዚህ ገባህ፣ እዚህ ወጣህ አይባሉም ፤ አይታገዱም ፤ አበላሽህ አይባሉም ፤ ዝምብለው ደመነፍሳቸው ያላቸውን ይፈፅማሉ ፤ ወደ ሌላ ገበሬ ማሣ ገብተው ቢያበላሹ ጠያቂ የለባቸውም ፤ መስቀል ነውና ገበሬው ያውቃል እርስ በእርስ አይጣላም ፤

ከብቶች መሬቱ ላይ ሲንደባለሉ እና ሲሮጡ ማየት እንዴት ደስ ይላል ፤ እስኪጠግቡ ግጠው እና ጠጥተው ወደ በረታቸው ሲገቡ የእረኛው ደስታ ይጀምራል።

እረኝነት

በብዙ ሀገራት የትንሽ ልጅ ፣ ድምፁ የማይሰማ ፣ ክብሩ ዝቅ ያለና የተናቀ ነው ። እረኝነት በሀገራችን ኢትዮጵያም ቢሆን ኩራዝ ይዞ ጌቶቹን የሚያበላ ፣ ጌቶቹ ሲበሉ የሚበሉትን እህል በአይኑ እንዲያይ የማይፈቅድለት እና እህል ሲሰጡት ጎንበስ ብሎ መሬት ስሞ የሚቀበል ነው ፤ ይህ ግን የመስቀል ቀን በሠላሌ የለም ። Classless ማህበረሰብ የሚመኘው Socialism ይህን ቢያይ ፣ ማርክስ እና ማኦ ይህን ባህል ቢያዩት እላለሁ ፤ በዚህ ቀን በሠላሌ የሠው ልጅ ሁሉ እኩል ነው፤ አረ በመስቀል ከዛም በላይ ነው ሠላሌ።

* በእስራኤል በጎች የእረኛውን ድምፅ ሰምተው ይከተሉታል። ነገር ግን በሲርጢ ፣ በጂዳ ፣ በሰላሌ እረኛ ንጉስ ነው። የመስቀል እለት ጧት መርቃ ( ገንፎ ) ይበላል።

ገንፎው ጣባ ላይ ከቀረበ በኋላ የመጀመሪያ ቅምሻ የአባወራው ወይም የሽማግሌ ወይም የአባገዳ አይደለም ። የመጀመሪያዋ ቅምሻ የእረኛው ብቻ ነው ፤ እረኛው ሳይቀምስ የሚበላ ቁርስ የለም። እረኛ ለከፈው ሲባል የነበረ ማዕድ የመስቀል ቀን እረኛ የባረከው ማለት የሰላሌ ባህል ነው።

ሶሻሊስቱ ሠላሌ

ፀሃፊ:- Natnael Kebede

Jara Travelers

28/09/2023
ሰላሌ ተጋቢዘ ኸይደ❤ ደስ ክብል ባህሊ። ለካ ብዙሕ ዘይፈልጦ ዓዲ ኣሎ ወጣት ጂዳ ስርጢ እትበሃል ንእሽተይ ከተማ ናይ መስቀል ኣከባብራ ኣርእዮምና።ኣቀማምጣ መሬታሞ ታይሞ ተዓዲሎም ጥራሕዩ ዘ...
28/09/2023

ሰላሌ ተጋቢዘ ኸይደ❤ ደስ ክብል ባህሊ። ለካ ብዙሕ ዘይፈልጦ ዓዲ ኣሎ ወጣት ጂዳ ስርጢ እትበሃል ንእሽተይ ከተማ ናይ መስቀል ኣከባብራ ኣርእዮምና።ኣቀማምጣ መሬታሞ ታይሞ ተዓዲሎም ጥራሕዩ ዘብለካ። መናእሰይ ጂዳ ድምፆም ልገርምዩ ታይሞ ቋንቋኦምንዶ ዘይሰምዖም ኾይነ😞
ጌረርሳ ወይ ድማ ቱታ እንብሎ ንሕና ታይ ኣለዎ ኦሮምኛ ተዝፈልጥ ነይረ ኣቢሉኒ ። ኣዶታት ጭኮ ዲኹም ትብሉታ መርቃ፣ ጥረ ስጋ፣ ርግኦሞ ግደፍዎ😞 ኣቀራርበአን በስማም ኦርጋኒክ ምግቢ በቃ ታይሞ ኣብ ከተማ ኣበይ ክርከብ በሊዕኻ ትፀግብ ኣይመስለንን ኣብሊዐናና 😍
ባህልና ዘኽብሩልና ነኽብረሎም ወለዶ ❤



Nigist Niji

Jara Travelers

ሶሻሊስቱ ሰላሌ አሁን በቀደም ብዬ ስለ ሠላሌ መፃፍ ከመጀመሬ በፊት ቡና ቁርስ ላሰይዛችሁ ፈረንጅ First course እንደሚለው መሆኑ ነው። ከፊቼ ከተማ 16 ኪሜ ኢጀሬ ላይ የተፈጠረ ነገር...
28/09/2023

ሶሻሊስቱ ሰላሌ

አሁን በቀደም ብዬ ስለ ሠላሌ መፃፍ ከመጀመሬ በፊት ቡና ቁርስ ላሰይዛችሁ ፈረንጅ First course እንደሚለው መሆኑ ነው።

ከፊቼ ከተማ 16 ኪሜ ኢጀሬ ላይ የተፈጠረ ነገር ነበር። ኢላሙ እና አሌ የሚባሉ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ። መንገዳቸው ላይ በአንድ ቦታ ተመሰጡ ፤ ቦታው ተራራማ እና ጫካማ ነበር
ቦታው ላይ መስፈር ፈለጉ። ሆኖም ግን አንዳች ነገር እንዳይኖር ተጠራጠሩ ። ከዚያም ኢላሙ ወደ ተራራው እንዲወጣ እና ሁኔታውንም ለመቃኘት ወሰነ ፤ ወንድሙ አሌም ሁኔታው ሠላም ከሆነም ጭስ አጪስ አለው፡፡ አጨሰ ። አሌ ከስር ሆኖ የጎላ ድምፅ አሠማ ፤

ሲላሌ፣ ሲላሌ ፣ ሲላሌ አለው ፤ አይቸሀለው ማለቱ ነበር ፤ እነሆ ሰላሌ የተበጀው እንዲህ ባለው መልኩ እና ቃል መሆኑን አፈ ታሪክ ነገረን።

እናንተም ስለ ሰላሌ በምፅፈው ሲላሌ በሉኝ።

በቀደም ጅዳ ነበረን። ከተማዋ ሲርጢ ትባላለች። ከመጫና ቱለማ መስራች ሀይለማርያም ገመዳ ፣ ታደሰ ብሩ መንደር ፣ በአፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አበበ ቢቂላ መንደር ።

ሰላሌ በመስቀል ይለያል ተብለን ሄድን። አካሄዳችን ጥርጣሬ ነበረው ፤ እንደተወራው ይሆን ወይ የሚል ጥርጣሬ ነበረን ፤ መጠበቅ የሚሉት ነገርም ነበር። ቦታው ደርሰን የሆነውን ካየን በኋላ
እንደ አሌ ሲላሌ አልኩኝ። እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የጃራ አባል በልቡ የሰላሌን ልህቀት ሲላሌ ብሎ ገለፀ።

መስቀል ሲልቅ እነሆ ፦

መስቀል በሶሻሊስቱ ሰላሌ ሶስት አካላትን ያከብራል ፤ ጎቤዎችን ፣ ከብቶችን እና እረኞችን ። እነዚህ ሶስቱ በመስቀል ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው ።

ጎቤ

ከነሀሴ አጋማሽ ጀምሮ ይጨፍራል ፤ በልብሱ ሽክ ይላል ፤ ዱላውን ይዞ ይወጣል ፤ ባህሉን ያወድሳል ፤ የሚፈልጋትን ያጫል ፤ የሚያምር ረጋዳ ያወጣል ፤ ደግሞ በየቤቱ ነው ጭፈራው ፤ ሲጨፍር በቤቱ ባለቤት ይመረቃል። የሚሰጠውን ፍራንክ ይቀረቅር ፣ ይቀረቅርና የመስቀል ቀን ባጠራቀመው ገንዘብ በሬ ይገዛል ፤ የገዛውን በሬ አድባር ስር ያርድና መንደሩን ይመግባል ፤ ጎቤው ከማህበረሰቡ የሠበሰውን ገንዘብ መልሶ ለማህበረሰቡ ይሠጣል ፤ ጎቤነት ሰጥቶ መቀበል እንጂ እንደ አለሙ ያለ ስግብግብነት የለበትም ፤ ተቀብሎ ጭጭ የለም። በሠበሠው ገንዘብ በሬውን ያርዳል ፤ ሀብታም ድሀ ሳይል ፤ አድባሩ ስር ጥሬ ያቀርባል ፣ ጥብስ ይጠብሳል ፤ አረቄ እና ጠላ ይቀላል፤ ጬኮ በሳህን ይሠጣል ፤ ወግ እያወጋ ተመጋቢውን ያስቃል፤ የሚወዳትን ሴት ጆሮዋ ላይ የፍቅር ቃላት ያንሾካሽካል ፤ ከዚያም ይመረቃል ።

ስለ ጎቤ የመጨረሻውን ልጨምርልህ ጎቤ ሲጨፍር በሌላ ቦታ ፣ በሌላ መንደር ፣ በሌላ ሀገር ካለው ስልጣን በላይ አለው በዚህ ሰሞን ።

በሰላሌ ገጠሮች ውስጥ አዲስ አመት ሲጠባ
ብስራቷን የሚያፈኩ ወጣቶች ‹‹ጎቢዮ ጎባንጎብሲ ያዋዳሎ›› የሚል ዜማ እያዜሙ ወደ መንደሩ አባወራ ቤት ይተማሉ፡፡

ጎቤው እየጨፈረ ነፍሰጡር ሴት ካገኘ " የእገሌ እናት " ይላል አባቱንም ካገኘ "የእገሌ አባት " ይላል ፤ በወርሀ መስከረም ፅንስ ውስጥ ላለው ልጅ ስም የማውጣት ፈቃድ ያለው ማነው ? የሰላሌው ጎቤ ነው።

ታዋቂው የሞገደኛው ነውጤ ደራሲ እና የመጀመሪያው ጥቁር ኖርዌይ ደራሲያን ማህበር አባል አበራ ለማ ፣ አበራ የሚለው ስም የወጣለት እንዲህ ባለው መንገድ ነበር ። ደራሲው በመስከረም ወር እናቱ ሆድ ውስጥ ሆኖ ጎቤዎች መጥተው እንዲህ አሉ፦

"ያ አባ አባራ፣ ያ ሃዳ አባራ " አሉ ፤

ይቀጥላል

Jara Travelers

    Jara Travelers
28/09/2023






Jara Travelers

  2023  Jara Travelers
26/09/2023

2023



Jara Travelers

ወደ ኢሬቻ  እሄዳለሁ 🏃🏃በ Natnael Kebede የሆነ ሠው ስለ ኢሬቻ እንዲህ አለ፣ ተሣደበ፣ አጣጣለ ብላችሁ አትበሉ። ተረት ሲወራ የላም በረት የማለት አመል ይኑራችሁ :: ተረቱ ሲያልቅ...
24/09/2023

ወደ ኢሬቻ እሄዳለሁ 🏃🏃
በ Natnael Kebede

የሆነ ሠው ስለ ኢሬቻ እንዲህ አለ፣ ተሣደበ፣ አጣጣለ ብላችሁ አትበሉ።
ተረት ሲወራ የላም በረት የማለት አመል ይኑራችሁ :: ተረቱ ሲያልቅ አይ ተረት በሉት እና እጃችሁ ይያያዝ ፣ ፍቅር ሰበኩ :: ለሚጠሉም ይሁን ለሚወዱህ ደጋሽ ስለሆንክ ና ወደ ኢሬቻ እንሂድ በለው። ♥️♥️♥️

ሱሪዬን ዝቅ አላደርግም ፤ አንገቴ ላይ ሠንሠለት አላንጠለጥልም ፣ የጫማ ክሬን አልፈታም። ምክንያቱም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ።

ወደ ኢሬቻ ግን እሄዳለሁ
* ራሴን ቅቤ እቀባለሁ :: ቡና ቀላዬን
ኣጣጥማለሁ ። ጬምቦ በላለሁ ። አፋኝ እካፈላለሁ::

Strip Dance ላይ ልሳተፍ አልሄድም ። ሀሎዊንን አላከብርም ። ማስክ አላጠልቅም። አስፈሪ ነገር ፊቴን አልቀባም።
ምክንያቱም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ።

ወደ ኢሬቻ ግን እሄዳለሁ ። ሻምባ አለልኝ ፣ ቲሪ እጨፍራለሁ ፤ እናቶች አሾ አሺላ ሲሉ ደስ ይለኛል። ረገዳ ላይ እገኛለሁ :: ጌረርሳውን አደምቃለሁ ::

     Jara Travelers
23/09/2023






Jara Travelers

     Jara Travelers
23/09/2023






Jara Travelers

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jara Travelers posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category