14/02/2024
" በተለያየ ሶሻል ሚዲያ ' አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን ' ከሚሉ ህገወጦች ራሳችሁን ጠብቁ ፤ ... በኦንላይ ምንም አይነት አስቸኳይ ፓስፖርት አይሰጥም " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት ምን ያስፈልጋል / ለምን ምን ጉዳዮች ይሰጣል አለ ?
- የህክምና ማስረጃ
- የትምህርት ዕድል ማስረጃ
- ለመንግስት ስራ ጉዳይ ለስብሰባ፣ ለወርክሾኘ
- ጊዜው ያላለፈ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ለባል/ለሚስት/ለልጅ
- ለአስመጭና ላኪ /ከፍተኛ ግብር ከፋይ/
- ፓስፖርት ላይ ጊዜው ያላለፈ የተመታ ቪዛ ካለ /ለማሳደስ/
ከእነዚህ ሰነዶች በአንዱ ዋናው ቢሮ በአካል በመገኘት ብቻ የተሟላ ማስረጃ በመያዝ በአስቸኳይ መስተናገድ ይቻላል ሲል አሳውቋል።
ክፍያ የሚከፈለው በቢሮ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል።
ዜጎች በተለያየ ሶሻል ሚዲያ " አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን " ከሚሉ ህገወጦች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።
በኦን ላይን ምንም አይነት አስቸኳይ ፓስፖርት የማይሰጥ መሆኑንም ገልጾ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሏል
የኢትዮጲያ ፓስፖርት ቀጠሮ አገልግሎት 🇪🇹 (Ethio Passport Online Servise)