Trekking in ethiopia

Trekking  in ethiopia Welcome To Trekking Ethiopia
trekking Ethiopia We allow your chapter of the human story to develop as you travel.

For all our partners and friends We wish you a Happy Ethiopian New year with good health September 11/2024
10/09/2024

For all our partners and friends We wish you a Happy Ethiopian New year with good health
September 11/2024

ዮኔስኮ ታድሏል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በዓለም ቅርስነት መዘገበ።አንዱ ፓርክ ብዙው ዓለም፤ የዓለም ቅርስ ኾኗል።
18/09/2023

ዮኔስኮ ታድሏል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በዓለም ቅርስነት መዘገበ።
አንዱ ፓርክ ብዙው ዓለም፤
የዓለም ቅርስ ኾኗል።

01/05/2023
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!የኢሬቻ በዓልን ለምታከብሩ የኦሮሞ እህት ወንድሞቻችን በሙሉ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።Visit oromyaሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን!
01/10/2022

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የኢሬቻ በዓልን ለምታከብሩ የኦሮሞ እህት ወንድሞቻችን በሙሉ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።

Visit oromya

ሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን!

28/05/2022
የሀገር ዉስጥ ጉብኝት /የዘመድ ጥየቃ መርሀ ግብር የጉዞ አይነት ፡ የዘመድ ጥየቃ፡-የሚጎበኟቸዉ ቦታዎች፡  ደ/ብርሃን ፤ አልዩ አምባ ፤ ቁንዲና ሰሪቲ ፤ እንቁላል ኮሶ  መንደርየቆይታ ጊዜ ...
28/08/2021

የሀገር ዉስጥ ጉብኝት /የዘመድ ጥየቃ መርሀ ግብር
የጉዞ አይነት ፡ የዘመድ ጥየቃ፡-
የሚጎበኟቸዉ ቦታዎች፡ ደ/ብርሃን ፤ አልዩ አምባ ፤ ቁንዲና ሰሪቲ ፤ እንቁላል ኮሶ መንደር
የቆይታ ጊዜ ፡ 2 ቀን/ 1 ምሽት
የሚጠቀሙት የትራንስፖርት አይነት ፡ 4 እግር ተሸከርካሪ / ላንድ ክሩዘር/
የተጓዦች ብዛት ፡-_____________

መርሀ ግብር 1
የመጀመያ ቀን ፡መነሻ አዲስ አበባ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዐት ሲሆን ከ 2፡00 ጉዞ በኋላ ደ/ብርሀን ቁርስ በልተን ጉዞ ወደ አልዩ አምባ እናደርጋለን ፡፡
አልዩ አምባ ታዳጊ ከተማ የምትገኘው የሰ/ሸዋ/ዞን በአንኮበር ወረዳ ውስጥ ነው፡፡ ይች በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የምትገኘው የታሪክ መሠረት የጉምሩክ መስራች የሆነችው ሞቃታማ የወረዳችን ፈርጥ ከተማ በአገራችን የጉሙሩክ ታሪክ ሲነሣ በግንባር ቀደምትነት ትነሣለች፡፡
አልዩ አምባ የሚለውን ስያሜ ያገኘችው አለዩ ከሚባል እንድ የሐደፊሠው ከሆነ እና በንግድ ስራ የተሠማራ የግለሠብ ስም ሲሆን ግለሠቡም አሁን ታዳጊ ከተማዋ ባለችበት አምባ ላይ የሚኖር በመሆኑ የአልዩ አምባ ከሚለው አልዩ አምባ የሚለውን ስያሜ እንዳገኘች አንዳንድ አባቶች ይናገራሉ፡፡
አልዩ አምባ 2 ብሔረሰቦች አማራና አርጎባ በፍቅር ተሳስበውና ተደጋግፈው የሚኖሩበት እንደሁም አልፎ አልፎ ከአጎራባች ወረዳ ከአፋር ክልል የአፋር ብሄር መጥተው ከእነርሱ ጋር አብረው የሚኖሩበት ስትሆን ከተማው በተለያዩ አቅጣጫዎች በ19ኛው ክ/ዘመን በስራና ንግድ /long distance trade/የነበረበት ወቅት 4 በሮች እንደ ነበራት አንዳንድ ታላላቅ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ከተማዋ በአገራችን ታላላቅና የመጀመሪያ የንግድ እና የጉምሩክ ማእከል የነበሩበት ከተማዎች በግንባረ ቀደምነት የምትጠቀሰ ነች፡፡ ለዚህም ምክንያት ከ1912—192ዐ ዓ/ም በቅርቡ በአገራችን የባሪያ ንግድ በተባበሩት መንግስታት/league of nation/ እስከ ቆመበት ድረስ ያለው ትኬት በግለሰቦች አጅ ዋናው ቅጅ መገኘቱ መስክር ነው፡፡ከላይእንደተጠቀሰው 4 በሮች የነበረ ሲሆን 2 መግቢያ 2 መውጫ ከነዚህ ውስጥ አዋሽና ጨኖ በር መግቢያ እነዚህ የተለያዩ እንደ ጨው፣ሻይ የተለያዩ ሸቀጣሸቀጦች በእነዚህ በሮች በሀይል ወደብ በኩል የሚገባበት 2 መውጫዎች አንኮበር እና ምንጀር በር የሚባሉት ሲሆኑ ከመሐል አገር እሰከ የአገራችን የሰሜኑ ክፍለ የሚለከው በአንኮበር በር ሲሆን ምንጃር በር ወደ የአገራችን ክፍል ደቡቡ አካባቢ የተለያዩ ምርቶች የሚወጡበት ከተማዋ በአገራችን የመጀመሪያዋ የጉምሩክ ከተማ ከመሆነዋ አንፃር በወቅቱ የነበረው የባሪያ ንግድም ቁርጥ መቁረጫ ነበረች፡፡ የባሪያው በአብዱልረሱል ከተገባያዩ በኋላ ወደ አልዩ አምባ በመውሰድ ባሪያው የተከለሰው 12ዐ ብር ያልተኮለሰው በ6ዐ ብር እንደሚሸጥና ቀረጥም 1 ብር በመክፈል በጨኖበት ወደ ተለያዩ የአረብ አገሮች እየወሰዱ ይሸጡ ነበር ባርያው ስቀረጥ መልሱ ቀመነው የማንም አገልጋይ እንዲሆነ በአሁኑ ወቅት በአንድ ግለሰብ እጅ ያለ የባሪያና የግብር መቅረጫው ይገኛል፡፡ ጉብኝት ከጨረስን በኋላ ምሳ በ አገልግል ይዘን አንኮበር እንበላለን በዚያዉም የ አንኮበር ቤተ መንግስት እንጎበኛለን፡፡ ከስኣት ወደ ቁንዲ በመንዳት የግማሽ ሰአት የእግር ጉዞ አድርገን በመቀጠል ወደ ደብረብርሀን በመሄድ አዳራችንን ደ/ብርሀን ይሆናል ፡፡
ሁለተኛ ቀን ፡ በጠዋት በመነሳት ከ ቁርስ በኋላ ከደ/ብርሀን ወደ እንቁላል ኮሶ ጉዞ እናደርጋለን፡፡ እንቁላል ኮሶ በአለም ላይ የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአፍሪካ የድል አባት የሆኑት የንጉሰ ነገስት እምየ ምኒሊክ ዘኢትዮጵያ የተወለዱበት ቦታ ነዉ ፡፡ ይህን ከጎበኘን በኋላ ጉዟችንን በመቀጠል የጦር ሜዳው ጀግናው ፊትአውራሪ ገበየሁ ታሪክና ጀግንነት እንዲሁም አጽማቸዉን የተቀመጠበትን እንጎበኛለን፡
ጀግንነት ሲባል ፈጥኖ ወደ አምሮአችን የሚመጣው ጦር ሜዳ ነው፡፡ ጀግና ማለትም ውጊያ ወረዳ ውስጥ ዘልቆ ጠላትን ድል በመንሳት ግዳጁን በብቃትና በቁርጠኝነት የተወጣ ማለታችን ነው፡፡ ታዲያ ዛሬ የወረዳችን ተወላጅ ስለሆኑት ስለ ጀግናው ፊታውራሪ ገበየሁ /ጐራው ገበየሁ/ ታሪክ እናስታዋውቃችኋለን፡፡
ፊታውራሪ ገበየሁ በባሶና ወራና ወረዳ በአንጐለላ ቀበሌ አስተዳደር ገጠር በምትባል ጐጥ ውስጥ እንደተወለዱ ይነገራል፡፡ ኢጣሊያ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ለመግዛት የነበረው ህልም እንዲሳካ በማሰብ በተለያዩ ወቅቶች ሃገራችንን የማዳከም ስራ አካሂዷል፡፡ በዚህም ጊዜ በወቅቱ ሃገሪቱን ያስተዳድሯት የነበሩት አፄ ምኒልክ እና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ እንዲሁም መኳንንቶቹ ኢትዮጵያ ሉአላዊነቷን ጠብቃ እንዳትኖር በአካባቢው የሚነቀሳቀሱ ቅኝ ገዥዎች የነበራቸውን ህልም በንቃት የሚጠባበቁበት ወቅት ነበር፡፡
በዚህ ወቅት አፄ ምኒልክ ለመጀመሪያው ግንባር ቀደም ወታደር ስማቸው በጀግንነት የተጠራውን ፊታውራሪ ገበየሁን የጠቅላይ የጦር አዛዥ አድርገው በ1888 ዓ.ም እሁድ ቀን ጦርነቱ እንደተጀመረ ወዲያው የኢጣሊያ ጦር አዛዥ ያገር ተወላጁን /ባንዳውን/ ጦር እፊት አስቀድመው ሲዋጉ የራስ መንገሻና የራስ ሚካኤል እንዲሁም የዋና ስዮም ጓንጉል ወታደሮች በጥይት ስለቆሏቸው አብዛኞቹ አለቁ፡፡ የተወሰኑት እጃቸውን ሲሰጡ ጥቂቶቹ ደግሞ ያልተነካውን የጄኔራል አርምንዴን ሰራዊት እየሄዱ ተቀላቀሉ፡፡
የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊትም በነፊታውራሪ ገበየሁ /በጐራው ገበየሁ/ እየተመራ እየፎከረና እያቅራራ ወደ ፊት አልፎ ጐስሶ ከሚባለው ጉብታ ላይ በመድረስ እንደገና ገጠማቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ባንደኛው ወገን ለመሸሽ እንኳን የማይመች ሆኖ በሌላው ወገን ደገመ ስለተከበቡ የሚሄዱበት አጥተው ተስፋ በቆረጡ ጊዜ እንደገና ውጊያው ተጀምሮ በርካታ ወታደሮች እንደሞቱም ይነገራል፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ጀግናው ፊታውራሪ ገበየሁ ከሰራዊታቸው ተለይተው እጠላት መሃል ገብተው ከቀኝ አዝማች ታፈስ ጋር እየፎከሩ የጠላትን አንገት በጐራዴ እየቆረጡ በጥይት እየተመተሙ ወደቁ፡፡ በወቅቱ የፊታውራሪ ገበየሁን ጀግንነት የሚገልፅ ግጥም እንደሚከተለው ተገጥሞ ነበር፡፡
“ የአደዋ ስለሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው” ተብሎላቸዋል ፡፡

አፄ ምኒልክ እና የጦር አበጋዙ ፊታውራራ ገበየሁ ጦርነት ከመሄዳቸው በፊት ግንባሬን ከተመታሁ አገሬ ወስዳችሁ እንድትቀብሩኝ ጀርባዬን ከተመታሁ ግን የሃገሬ አሞራ ይብላኝ ብለው በተናገሩት መሰረት ጦርነቱ ካበቃ በኋላ ከ7 ዓመት በኋላ ከአደዋ ስላሴ ቤተክርስቲያን አስወጥተው ወደ ትውልድ ሃገራቸው ባሶና ወራና ወረዳ በአንጐለላ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን እንዲያርፍ አድርገዋል፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ አቶ አብርሃም ደምሴ የተባሉ ሃገር ወዳድ አፅሙን አስወጥተው በክብር በመስተዋት ፍሬም አሰርተው አስቀምጠውታል፡፡ እኚህ ጀግና በአድዋ ጦርነት በሰሩት የጀግንነት ስራም ስማቸው በክብር ሲዘከር ይኖራል፡፡
በመቀጠል የዘመድ ጥየቃ ጉብኝት የምናድርግበትን የ ሰርቲ መንደርን እንጎበኛለን ፡፡ ሰርቲ የአርሶ አደር መንደር ሲሆን የገጠሩን ህይወት ምን እንደሚመስል ከመማር አልፎ ገብኝዎች ሊያከናዉኑት የሚችሉት ስራዎች ና እንቅስቃሴዎች ማለትም ፈረስ መጋለበ፤ እርሻ ማረስ፤ ማጨድና መዉቃት ፤ አንጀራ መጋገር ፤ እህል መዉቃጥ ፤
የዘመድ ጥየቃ ጉብኝት ከጨረስን በኋላ ጉዟችንን ወደ አዲስ አበባ በማድረግ የመርሀ ግብራችን መጨረሻ ይሆናል ፡፡
www.balehagerutoursethiopia.com
[email protected]
Mob:0987868686/0911434066

BALEHAGERU TOURS ETHIOPIADestinations: Menz Guassa plateau and semen Shewa Highlands Tour Name: Natural Tour and Trekkin...
19/08/2021

BALEHAGERU TOURS ETHIOPIA
Destinations: Menz Guassa plateau and semen Shewa Highlands
Tour Name: Natural Tour and Trekking
Mode of Transportation: Land
Duration: 4 Days / 3 Nights
Group size: _____________
Arrival date: _____________
Departure Date: __________
Special interest: ___________

Detailed program
Day 01: Addis – Menz Guassa Community Conservation Area.
This day in the morning you will drive about 250kms to Menz guassa and will have short trek nearby the mountain top to view the stunning Guassa plateau and have a chance of sighting the endemic Ethiopian wolf. The Ethiopian wolf is the only true wolf species in Africa, and is legally protected. With a total world population of less than 500 individuals surviving in relict mountain tops, it is one of the most endangered mammal species in the world. Overnight stay at Guassa Community Lodge

Day 02: Guassa Community Lodge – Atse Wuha.
It is a 6 hour trek through a spectacular landscape of moorland where one can experience the highland flora and an impressive array of bird species and wildlife, including the endemic Gelada baboon and the Ethiopian wolf.
Overnight Camping at Atse Wuha


Day 03: Atse Wuha – Cheguarit Meda.
Today’s trek will take about 5 hours through untouched juniper forest of yegana; a visit to a Menz village called Tebab will give a chance to learn about the Menz People’s ways of constructing two-storey stone huts with thatched roofs and their woven wool rugs and traditional blankets which are considered to be some of Ethiopian finest weavers. Overnight: Camping at Cheguarit.


Day 04: Cheguarit –Debre Berehan-Addis Ababa
Have a short trek to the main road to meet the vehicle and drive to Debrebirhan, you drive through the ancient capital of the Kingdom of Shewa to have a pleasant rest on the mountain top that overlooks the Great Ethiopian Rift Valley and its extensive escarpments and then proceed to Debrebirhan and then after lunch you will drive to Addis Ababa.
Overnight stay at the hotel of your choice Hotel or departure.


................................................End of Tour.......................................................

www.balehagerutoursethiopia.com
Mob: +251987868686/+251911434066
Email: [email protected]

You’re Travel Partner in Ethiopia !!!

16/07/2021
ባለሐገሩ አስጎብኚ የዘመድ ጥየቃ ፕሮግራም የሀገር ዉስጥ ጉብኝት   /የዘመድ ጥየቃ / መርሀ ግብርየጉዞ አይነት ፡ የዘመድ ጥየቃየሚጎበኟቸዉ ቦታዎች፡  ደ/ብርሃን ፤ አንኮበር ፤ ቁንዲና ሰሪ...
07/07/2021

ባለሐገሩ አስጎብኚ የዘመድ ጥየቃ ፕሮግራም
የሀገር ዉስጥ ጉብኝት /የዘመድ ጥየቃ / መርሀ ግብር
የጉዞ አይነት ፡ የዘመድ ጥየቃ
የሚጎበኟቸዉ ቦታዎች፡ ደ/ብርሃን ፤ አንኮበር ፤ ቁንዲና ሰሪቲ መንደር
የቆይታ ጊዜ ፡ 3 ቀን/ 2 ምሽት
የሚጠቀሙት የትራንስፖርት አይነት ፡ 4 እግር ተሸከርካሪ / ላንድ ክሩዘር/ወይም ኮስተር ባስ
የተጓዦች ብዛት ፡

ዝርዝር መረጃ /Detailed Tour Package
የመጀመሪያ ቀን/First Day / ፡ መነሻ አዲስ አበባ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል እና እንግዶች የሚያመቻቸዉ ቦታ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዐት ሲሆን ከ 2፡00 ጉዞ በኋላ ደ/ብርሀን ደርሰን ከ 2፡00 -3፡00 ቁርስ ጌትቫ ሆቴል ወይንም ሎካል ሬስቶራንት በልተን ጉዞ ወደ እንቁላል ኮሶ እናደርጋለን ፡፡ እንቁላል ኮሶ በአለም ላይ የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአፍሪካ የድል አባት የሆኑት የንጉሰ ነገስት እምየ ምኒሊክ ዘኢትዮጵያ የተወለዱበት ቦታ ነዉ ፡፡ ከስዐት ወደ ቁንዲ በመንዳት በጣም በሚያምርና ደስ በሚል የመልከአምድር ቦታ የግማሽ ሰአት የእግር ጉዞ አድርገን አዳራችን ቁንዲ ይሆናል ፡፡
ምሽት ቀንዲ ካምፒንግ / overnight camping at Kundi village /

ሁለተኛ ቀን / Second Day / ፡ ቁንዲ - አንኮበር -ደብረብርሀን
ጠዋት ከ ቁንዲ በመነሳት ቁርስ በኋላ የአንኮበር በተመንግስትን እንጎበኛለን ፡፡
አንኮበር በመካከለኛው ኢትዮጵያ የሚገኝ ከተማ ነው ፡፡ በአማራ ክልል አንኮበር ወረዳ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው አንኮበር ወደ 2,465 ሜትር (8,100 ጫማ) ከፍታ ላይ በሚገኘው የኢትዮ ደጋማ ምስራቅ አቋራጭ ላይ ይገኛል ፡፡ ከደብረ ብርሃን በስተ ምስራቅ 42 ኪ.ሜ እና ከአዲስ አበባ ሰሜን ምስራቅ 172 ኪ.ሜ ያህል ነው ፡፡
የአንኮበር ቤተ መንግስት 1830 ዓ.ም በንጉስ ሳህለስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰራ ሲሆን አጼ ምኒሊክ ከ አጼ ቴዎድሮስ አምልጠዉ ወደ አንኮበር ከመጡ በኋላ በተመንግቱን በማደስ ሸዋን ያስተዳደሩ ሲሆን ንጉሱ አዲስ አበባን ከቆረቆሩ በኋላ በ እንጦጦ እና በ አዲስ አለም ካሰሯቸዉ ቤተ መንግስቶች ጋር ተመሳሳይነት የተላበሰ ነዉ ፡፡
የአንኮበር ቤተ መንግስት ማራኪ በሆነ መልከአምድር ላይ የተሰራ ከመሆኑ በላይ የታላቁ ስምጥ ሸለቆ የሚያልፍባቸዉን የ አፋር ዝቅተኛ ስፍራዎችን እስከ አዋሽ ድረስ መመልከት የሚያስችል እና ከባህር ወለል ጠለል በላይ በ 2870 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ግርማ ሞገስን የተላበሰ ስፍራ ነዉ ፡፡ የእምየ ምኒሊክ ቤተመንግስት አንኮበር ከጎበኘንና ምሳ ከበላን በኋላ ወደ ደብረብርሀን በመሄድ አዳራችንን ደብረብርሀን እናደርጋለን ፡፡


ሶስተኛ ቀን/ Third Day/ ፡ ደብረብርሀን-ሰርቲ መንደር- አዲስአበባ ጠዋት ከ ቁርስ በኋላ ወደ የዘመድ ጥየቃ ጉብኝት የምናድርግበትን የ ሰርቲ መንደርን እንጎበኛለን :: ሰርቲ የአርሶ አደር መንደር ሲሆን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አካካባቢ የሚገኝ ነዋሪዎች አማርኛና ኦሮሚኛ አቀላጥፈዉ የሚናገሩ ናቸዉ ፡፡ የገጠሩን ህይወት ምን እንደሚመስል ከስተማር አልፎ ገብኝዎች ሊያከናዉኑት የሚችሉት እንቅስቃሴዎች ማለትም ፈረስ መጋለበ፤ እርሻ ማረስ፤ ማጨድና መዉቃት ፤ አንጀራ መጋገር ፤ ጌሾ መዉቀጥ፡ እበት መጠፍጠፍ እንዲሁም ወተት መናጥ እና ሌሎችም የመሳሰሉትን እንቅስቃሴዎች በማድረግ የዘመድ ጥየቃ ጉብኝት ከጨረስን በኋላ ጉዟችንን ወደ አዲስ አበባ በማድረግ የመርሀ ግብራችን መጨረሻ ይሆናል ፡፡


ለበለመ መረጃ 0987868686

22/06/2021

#የሸዋ ከፍታ kefeta #2021 አስራት ቦሰና እና ብርሃኑ ሞላ በባለሐገሩ ተሾመ የተሠራ ምርጥ # Berhanu Mola and bosena by balehageru...

20/06/2021

#የሸዋ ከፍታ

06/06/2021

Ethiopia

22/10/2020

Address

Piasa
Addis Ababa
2129

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Trekking in ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share