
23/08/2022
የከተማው_ወጣት_ልጃገረዶች_በቤተክርስቲያን_እመቤታችንን_እያመሰገኑ_አክብረውት_ውለዋል_በአማረ_ዜማቸው። it is the day of girl Ethiopia is the country that who gives recognition for the girl as the world celebrates women's day we where the first from the other world
ላይ ሊቃውንተ ካህናት ያሬዳዊ ዝማሬ ካሰሙ ቡሃላ የቅዱስ ላሊበላ የሰንበት ተማሪዎች የአሸንድየ ጨዋታን በዝማሬ አብስረዋል ከአባቶች ቡራኬያቸውን ምርቃት ተቀብለው ቤተማረያም ካመሰገኑ ቡሃላ ወደ ቤተጊወርጊስ በማቅናት እንደምታዩት ደምቀው ውለዋል።
👉 #በየአመቱ የማይጠፉት ብአሉን የሚያደምቁት የከተማው የአሸኝድየ ቡድንም እመቤታችንን በቤተ ማርያም በማመስገን ከዛ ቤተ መድኀኔዓለም፣ቤተ ጊዮርጊስ፣ቤተ አማኑኤል እየሄዱ በሚያምር ዝማሬ አመስግነዋል።
።
👉ባህል የአንድማህበረሰብ አኗኗር፣አመጋገብ፣አለባበስ፣ማህበራዊ ትስስርና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መስታውት ነው፡፡በማህበራዊ ግንኙነት ወቅት በሚኖሩ መስተጋብሮች ባህል የአንድን ማህበረሰብ የአኗኗርና የአጊያጊያጥ ዘይቤ አጉልቶ በማሳየት ረገድ ወደር የሌለው ሚና ይጫወታል፡፡ ሃገራችን ኢትዮጵያም ህብረ ብሄራዊነት የሚንፀባረቅባት የበርካታ ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ ደሴት እንደመሆኗ መጠን በውስጧ በርካታ ባህሎችን አቅፋ የያዘች ሃገር ናት፡፡
ወረዳችንም የበርካታ ባህሎች ባለቤት ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የወረዳችን የአሸንድየናሆያሆየ ባህላዊ ጨዋታን በወረዳችን ከየት የት እንደደረሰ ከቡዙ በጥቂቱ ጀባ እንበላችሁ፡-ከእነዚህም መካከል በየአመቱ ነሐሴ 16 ቀን የሚከበረው ሻደይ፣አሸንዳ፣ አሸንድየና ሆያሆየ በዓል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ሲሆን ይኸውም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የእመቤታችን የቅድስት ማርያምን ዳግም ትንሳኤናእርገቷን ለማስታወስ ሲሉ እንደሚያከብሩት የሃይማኖቱ ተከታዮች ይናገራሉ፡፡
👉የእመቤታችን የቅድስት ማርያም ስጋ ለበርካታ ቀናት ተሰውሮ ከነሐሴ1-15 ከተጾመና ከተፀለየ በኋላ በ16ኛው ቀን ተገኝቶ ከመቃብር በመፍለስ እንደ ልጇ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ ወደሰማይ አርጓል፡፡በዚህ ወቅት መላዕክት ክንፍ ለክንፍ ተያይዘው በልዩ ምስጋና ና ዝማሬ ሸኝተውታል፡፡ ይህን ለማስታወስና በረከት ለማግኘት ሲሉም ልጃገረዶችናወጣቶች ልዩ የሆነውን የአሸንድየ ቅጠል በሴቶቹ በወገባቸው በመታጠቅ አሸንድየ በሚል ርዕስ ስር በርካታ ዜማወችን እያንቆረቆሩ ጨዋታውን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደሚጀምሩት የእምነቱ ተከታዮች ይናገራሉ፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቡሄ በዓል እንዴት እንደተጀመረ ማብራሪያ መስጠት ግድ ብሎናል፡፡የአሸንድየ በዓል ከእመቤታችን እርገት ጋር ተያይዞ የሚከበር ሲሆን የቡሄ በዓል ደግሞ ጌታ በድብረ ታቦር ተራራ ለሃዋርያትና ለነቢያት መገለጡን የሚያጠይቅ ነዉ፡፡ጌታ በድብረ ታቦር ተራራ በተገለፀበት ወቅት ሁለቱን ነቢያት ሙሴንና ኤልያስን እንዲሁም ከሃዋርያት ዮሃንስንና ጴጥሮስን ከጌታ ጋር በደብር ታቦር ተራራ በነበሩበት ጊዜ ብርሃነ መለኮት ተገልጾላቸዋል፡፡በወቅቱም ብርሃን፣ጭጋግና ነጎድጓድ ተግልጾ ስለነበር በዚያን ወቅት እረኞቹ አልመሽም እያሉ በዱር ዉለዉ አድረዋል፡፡ስለሆነም ወላጆቻቸዉ/ቤተሰቦቻቸዉ ልጆቻቸዉ ሲቀሩባቸዉ ሙል ሙል/ቡቼ/ ዳቦ የሚባል ስንቅ ጋግረዉ ፍለጋ ወጥተዋል፡፡የቡሄ በዓል በየአመቱ መከበር የጀመረዉ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መሆኑን የአበዉ ድርሳናትና የሃይማኖቱ ተከታዮች ያስረዳሉ፡፡ጌታ በደበረ ታቦር ተራራ ተገልጾ ሳለ የነበረዉን የነጎድጓድ ድምጽ ለማስታዎስ ወንዶቹ ከግራር ልጥ፣ከጭረት ሶስት ጣታ ቀጭን ፍትል ገመድ በመጠቅለል የሚሰሩት ጀራፍ ይባላል፡፡ ጅራፉ ሶስት ጣታ የመሆኑ ምሳሌ ጌታ በአብ፣በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ለሃዋርያት የመገለጡ ምሳሌ ነዉ፡፡በአንድ የመጠቅለሉ ምሳሌ ደግሞ አንድነቱንና ሦስትነቱን የሚያሳይ ነዉ፡፡ታዲያ ይህንን ታሪክ ለማመልከት ሲሉ ወንዶች ተሰባስበዉ ጅራፉ ያኖጋሉ፡
ይህ ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው በዓል በላስታ ላሊበላ አካባቢ አሽንድየ፣ በትግራይ ክልል አሸንዳ፣ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደግሞ ሻደይ በሚሉ መጠሪያዎች ይታወቃል፡፡እኛም በላስታ ላሊበላ አካባቢ ቡግና ወረዳ ውስጥ በአሸንድየ ወቅት የሚዜሙ ግጥሞችን በጥቂቱ ልናስቃኛችሁ ወደድን፡፡ልጃገረዶች ከየሰፈሩ ከተሰባሰቡ በኋላ የአሸንድ ቅጠል ከወገባቸው አስረው ወደየሰፈሩ ጎራ ይላሉ፡፡ በመቀጠልም፡-
አስገባኝ በረኛ--------የጌታው ዘበኛ
አስገባኝ ከልካይ-----እመቤቴን ላይ
ጌታው አሉ ወይ-----------አሉ ወይ
አዎ አሉ እንጂ ---------ግቡ ይላሉ እንጂ
አዎ አሉ እንጂ---------ተዘንብሏል ጠጅ በማለት በሚመስጥ ዜማ ወደ ግቢው ጎራ ይላሉ፡፡ ቀጥለውም፡-አሸንድየ አሸንድየ ሆይ---በማለት ከአባለቱ አንዷ ዜማን ስታንቆረቁረው አባላቱ ‹‹እርግፍ አትይም ወይ---››እያሉ ይቀበሏታል፡፡ቀጥላም፡-
አሸንድየ እኮ አሸነደየ ሙሴ---እያለች ስታዜም‹‹ፈሰስ በይ በቀሚሴ›› እያሉ ይቀበሏታል፡፡ ከዚህ በኋላ፡-እቴ አደይ አበባ-----እቴ አደይ
እቴ አደይ ወይኒቱ----ከራሴ ላይ ንቢቱ
ሎሚ ወድቃ በስተኋላየ---እስቲ አንሻት ባልንጀራየ
ሎሚ ወድቃ ከቤቴ ደጅ---አንቺ አንሻት የጌቴው ልጅ
የሚሉና ሌሎች ዜማዎችን በደማቅ ሁኔታ በማዜም የባህል ጭፈራቸውን ያካሂዳሉ፤ ልዩ ልዩ የምስጋናና የውዳሴ ዜማዎችንም ማውረድ ይጀምራሉ፡፡ ለምሳሌ፡-
አሽከር ይሙት ይሙት--ይላሉ የኔታ
አሽከር አይደለም ወይ---የሚሆነው ጌታ በማለት ከበሩ ያስገባቸውን ዘበኛ ያሞግሳሉ፡፡ ወገባቸውን እያሽከረከሩ ‹‹እየው ሲዞር ወገቤ ---ነጭ ጤፍ ነው ቀለቤ›› በማለት ገና ቀንበጥ ወገብ ያለቸው መሆኑን ከጠቆሙ በኋላ ከመከላከላቸው አንዷ ወጋቧን ማሻከርከር አለመቻሏን ለመግለፅ ደግሞ
‹‹አይዞሬ ነው ወገቧ ---ባቄላ ነው ቀለቧ›› በማለት ተጎም አድርገዋት ያልፋሉ፡፡በሌላ በኩል የገቡበትን ቤት አሳዳሪዎች
ያ የማን ነው እንዝርት---ከመከታው ላይ
የእሜቴ ይሆናል ------የቀጭን ፈታይ
ቀጭን ፈትላ ፈትላ----ባሏ መልበስ ያውቃል
እዩት የእኔ ጌታ------- በሩቅ ያስታውቃል፡፡ በማለት
👉የሰንበት ተማሪዎች ደግሞ
ተወረወረች ኮከብ(2)
በጊወርጊስ ክበብ
ተወረወረች ጨረቃ(2)
በመድሃኒአም ጫንቃ እያሉ ይጫወታሉ
ወንዶቹ ደግሞ ቀን በእረኝነትና በተለያየ አጋጣሚ ይገናኙና ዛሬ ሆያሆየ እንድንል ብለዉ ይቀጣተራሉ፡፡ቀን የተቀጣጠሩትን የረሳ እንኳን ቢኖር ልክ አስራ ሁለት ስዓት ገደማ ሲሆን ትዝ ያለዉ ወጣት ጅራፍ ማንጓት/ማጮህ ይጀምራል፡፡በዚህ ጊዜ ቀን የተቀጣጠሩት ሁሉ ይሰባሰባሉ ወይንም ስም ይጠራሩና ይሰባሰባሉ፡፡ከተሰባሰቡ በኋላ የመጀመሪያ ስራቸዉ አለቃ መምረጥ ነዉ፡፡አለቃ ከመረጡ በኋላ አለቃቸዉ ከማን ቤት እንጀምር ብሎ ለቡድኑ ያቀርባል ፡፡ ከቡድኑ አንዱ ብድግ ያደርግና አምና ከጀምርንበት ከነያያ ማሞ ቤት ነዉ ይላል፡፡ከዚያን ቡኋላ ጂራፍቸዉን እያኖጉ ወደ መረጡት ቤት
ያመራሉ፡፡
💚💛❤ # [email protected]
ከአጥሩ ሲደረሱ እንዱ ክፈት በለዉ አጥሩን-የጌታ ወንዱን እያሉ አጥሩን ከፍተዉ ይገባሉ፡፡አጥሩ ተከፍቶ ከገቡ ቡኋላ የቤቱ ባለቤት ለማስነሳት ክፈት በለዉ ተነሳ የአያ ወንዱ ጎረምሳ እያሉ ከተቀባበሉ በኋላ እንድኛዉ እሆ ንሆ ብል ብሎ ሲያወጣ-እሆ እያሉ ይቀባበላሉ፡፡በእርኝነት ሲደክሙ መዋላቸዉን ለመግለጽ እሆ በል እሆ በል እረኛ-በጊዜ እንድንተኛ እንዲህ እንዲህ እያሉ ጨዋታዉን ሞቅ ደመቅ ያደርጉታል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የገቡበትን ቤት አሳደሪዎች/አባወራዎችን በግጥም ድርደራ
እሆ ንሆበል ምድር ምሸምሽ አወጣሁ እጌታ-እሆ
እባባየ ማሞ ድልድሉ ጌታ- እሆ
ምድር ምሽምሽ አወጣሁ ማሰሮ-እሆ
እከሊታ እከሌ ድልድል ወይዘሮ-እሆ በማለት ሞገሳቸዉን አሃዱ ብለዉ ይጀምራሉ፡፡በተመሳሳይ መልኩ እንደለመዱት አመት ግብራቸዉን እንዲሰጧቸዉ የተለያዩ ስነ-ቃሎችን ይደረድራሉ፡፡ከነዚህም መካከል ከትንሹ በጥቂቱ ጀባ እንበላችሁ፡-ሆያ ሆየ-እህ
ሆያሆየ ሆያ ሆየዉ ናና ባየህዉ ጎዳና-እህ
ትሰጠኝ እንደሁ ስጠኝ ልሄድ እንደ አሮየ ጅብ አልጓግርብህ
የተሰጣቸዉን ስጦታ ለማሞገስ የሚከተሉትን ግጥሞች ይደረድራሉ፡፡
የእኔማ ጌታ ጌታነዉ ጌታ ሲቀመጥ ያምር ሲቆም ይረታ
የኔማ ጌታ የሰጠኝ ሙክት አልጫል ብሎ ገደል ለቀኩት
እነዚህንና ሌሎች በርካታ ዜማዎችንና ግጥሞችን ከደረድሩ በኋላ በሺማግሌዎች ተመርቀዉና የሚቀበሉትን ስጦታ ተቀብለዉ ለቀጣዩ ዓመት መልካም ምኞታቸዉን እየተመኙ ወደ አካባቢያቸው ይመለሳሉ።
ላስታ ቅዱስ ላሊበላ አካባቢ ብዙ ጊዜ ለመስቀል ቃል ይሄንም ያገኙትን በማሰባሰብ መስቀልን በመደገስ የለገሷቸውን እናት አባቶች በመጥራት ድግሳቸውን ያበላሉ።
💚💛❤ 💚💛❤
ነው
buna tour and travel
tour and travel
WhatsApp and mobile +251961050707
Ethiopia is waiting you
[email protected]