Gamo Tour & Travel, Ethiopia

Gamo Tour & Travel, Ethiopia Let's tour,
Let's travel, &
Let's take a memory!
(2)

25/09/2023
አይኖች ሁሉ ወደ ጋሞ ዞን!በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ የዮ ማስቃላ የዶርዜ እርድ ሥነ ስርዓት በርካታ ቱሪስቶች ታድሟል፡፡የበዓሉ ታዳሚ ቱሪስቶች ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡መስከረ...
25/09/2023

አይኖች ሁሉ ወደ ጋሞ ዞን!

በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ የዮ ማስቃላ የዶርዜ እርድ ሥነ ስርዓት በርካታ ቱሪስቶች ታድሟል፡፡
የበዓሉ ታዳሚ ቱሪስቶች ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

መስከረም 14/2016 ዓ.ም!

በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ የዮ ማስቃላ የእርድ ሥነ ስርዓት በ"ዶርዜ ቦዶ" ገበያ እየተካሄደ ነው።በወረዳው ዶርዜ ቀበሌ በተካሄደ ሥነ የእርድ ስርዓት በሺህዎች የሚቆጠር ሰንጋ በሬ በየዓመ...
25/09/2023

በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ የዮ ማስቃላ የእርድ ሥነ ስርዓት በ"ዶርዜ ቦዶ" ገበያ እየተካሄደ ነው።

በወረዳው ዶርዜ ቀበሌ በተካሄደ ሥነ የእርድ ስርዓት በሺህዎች የሚቆጠር ሰንጋ በሬ በየዓመቱ ይታረዳል።
ዮ ዮ ዶርዜ ማስቃላ!

በጋሞ ዞን በደጋ ኦቾሎ ጥንታዊዉ በከሮ ዱቡሻ በዉስጡ ይገኛል!
24/09/2023

በጋሞ ዞን በደጋ ኦቾሎ ጥንታዊዉ በከሮ ዱቡሻ በዉስጡ ይገኛል!

የተፈጥሮ ማር ምርት በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ!
18/09/2023

የተፈጥሮ ማር ምርት በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ!

ባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዘገበ!  የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድር...
18/09/2023

ባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዘገበ!

የዓለም ቅርስ ኮሚቴ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ አሳልፏል።

 !********************************************* ካጫ ጉርዶ  ሸንዴራ ውብ ባህላችንን አሰቀምጣቹ  የምዕራባዊያንን መጤ ባህል ለምትቀላውጡ ( ቤቢ ሻውር ለምትሉ ❌)...
18/09/2023

!
*********************************************
ካጫ ጉርዶ ሸንዴራ ውብ ባህላችንን አሰቀምጣቹ የምዕራባዊያንን መጤ ባህል ለምትቀላውጡ ( ቤቢ ሻውር ለምትሉ ❌)
በጋሞ ብሔረሰብ ባሕል መሰረት ሴት ልጅ የመዉለጃ ጊዜዋ ሲደርስ አስፈላጊዉ ዝግጂት የሚከናወንበት ስርአት ነዉ፡፡
ካጫ ጉርዶ ሸንዴራ ቅቤ አናቷ ላይ በመቀባት ተጀምሮ የገንፎ ስርዓት ይካሔድላታል፡:
Via: Mintamir Ayele Kecho!

ዮ ሎላሼ ፣ ዮ ማስቃላ!እንኳን ለጋሞ ህዝብ የዘመን መለወጫ ዮ ሎላሼ በሰላም እና በጤና አደረሰን/አደረሳችሁ!
18/09/2023

ዮ ሎላሼ ፣ ዮ ማስቃላ!
እንኳን ለጋሞ ህዝብ የዘመን መለወጫ ዮ ሎላሼ በሰላም እና በጤና አደረሰን/አደረሳችሁ!

የጋሞ ጨንቻ ዶርሶ ፏፏቴ!Gamo Tour & Travel, Ethiopia
16/09/2023

የጋሞ ጨንቻ ዶርሶ ፏፏቴ!
Gamo Tour & Travel, Ethiopia

"ሶፌ" የሙሽራዎች የቁንጅና ውድድር!"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""የጋሞ ብሔረሰብ የተለያዩ ያልተከለሱ...
16/09/2023

"ሶፌ" የሙሽራዎች የቁንጅና ውድድር!
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

የጋሞ ብሔረሰብ የተለያዩ ያልተከለሱና ያልተበረዙ የቱባ ባህሎች ባለቤት ነው፡፡

ከእነዚህ ባህልና ዕሴቶች መካከል ለየት የሚለውን ባህላዊ የሙሽራዎች የቁንጅና ውድድር/ሶፌ እናስቃኛችሁ።

ሶፌ በዓመቱ ያገቡ ሙሽሮች የአከባቢው ህዝብ በብዛት በሚሰበሰቡበት ገበያ በመውጣት ዕውቅና ተሰጥቷቸው ከህብረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበት ሥርዓት ነዉ።

በሶፌ ስርዓት ውስጥ ባል ፣ የባል ቤተሰብም ይገመገማሉ። የማን ቤተሰብ በደንብ ተንከባከበ ፣ የማን ሚስት አማረባት የሚለውን ህብረተሰቡ ይዳኛል።

የሶፌ ሥነ ስርዓት በጋሞ አካባቢዎች ሁሉ የሚከበር ሲሆን ከቦታ ቦታ የተወሰነ ለውጥ አለ። አንዳንድ አካባቢ በፈረስ፣ አንዳንድ አካባቢ ደግሞ በእግር ፣ አንዳንድ አካባቢ በርካታ ጨሌ በሙሽራዋ አንገት ላይ ይደረጋል። አንዳንድ አካባቢ ቅቤው በቅርጽ ተከምሮ ሲታይ በሌላ አካባቢ የሙሽራዋ ፀጉር በቅቤ ርሶ /ፑንጽሮ/ ይበጠራል፣ በአንዳንድ አካባቢ ካባ ይደረባ በአንዳንዱ አይደረግም።

ሶፌ በጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ የጋብቻ ደረጃዎችን አልፎ መጨረሻ ላይ ሙሽራዎች በባህላዊ መንገድ እንደተጋቡ ማሳወቂያ የባህል ስርዓት ነዉ፡፡

በጋሞ ባህል ያገባች ሙሽራ ከ1 እስከ 4 ወር ከቤት ሳትወጣ የተለያዩ ሰውነት ገንቢ የሆኑ ምግቦችን ለአብነት ገንፎ ፣ ቅንጬ ፣ ጩኮ ፣ ቡላ ፣ በማር የታሸ ቆሎ ወዘተ . . . እየተመገበች ትቆያለች።

በሙሽራውና ሙሽራዋ አብሮ አደጎች ፣ ጎረቤት የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃ በክራር ፣ ከበሮ ፣ ዋሽንት…ወዘተ ታግዘው ባህላዊ ዜማዎችን እያዜሙም ይጨፍራሉ።

በሶፌ ዕለት በአከባቢው ሁሉም ያገቡ ሙሽሮች በወዳጅ ዘመድ ታጅበው ፣ በቅቤ የራሰውን ጸጉራቸውን ፑንጽሮ አበጥረው ፣ በከበረ ጨሌ ፣ በጋሞዎች የጥበብ ቀሚስ አጊጠው ፣ በጋቢ ተሸፋፍነው ፣ በላዩ ሱፋሌ(ካባ) ደርበው ፣ እንስራ ሙሉ ጠላ አስይዘው ወደ ገበያ ይወጡና ሴት ሙሽራዎች ገበያውን አራት ጊዜ ይዞራሉ፡፡ወንድ ሙሽራዎች በተራቸዉ ሶስት ጊዜ ገበያውን ይዞራሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ጠላው እየተጠጣ ገበያተኛ ሁሉ ትዳራቹ ሙሉ ይሁን ፣ ያማረ ትዳር ይሁን፣ ውለዱ ክበዱ ፣ወንድ ውለዱ ፣ሴት ውለዱ፣እያሉ ይመርቃሉ፡፡ እግረ መንገዳቸውን የማን ቤተሰብ ጥሩ ቀልቦ ሙሽራዋ እንዳማረባት ፣ የማን ቤተሰብ እንዳጎሳቆለ ፣ አለባበሷ ፣ መዋቢያዋ ታይቶ ፣ የእከሌ ቤተሰብ ጥሩ ይዟል። ሙሽራዋ አምሮባታል። እያሉ ለቤተሰቡም ለባሏም ዕውቅና ይሰጣሉ።

ይህ ሥነ-ስርዓት ከተፈፀመ በኋላ ሙሽራዋ ከህብረተሰቡ ጋር በይፋ ትቀላቀላለች፡፡ የተለያዩ ማህበራዊ ክዋኔዎችን ለመስራት ወደ አዲስ ምዕራፍ ትሸጋገራለች።

Gamo Tour & Travel, Ethiopia

Bilbo Hot Spring at Maze National parkBilbo is a form of geyser that is located inside Maze national park. It is 21km fa...
15/09/2023

Bilbo Hot Spring at Maze National park

Bilbo is a form of geyser that is located inside Maze national park. It is 21km far from Daramalo woreda’s capital, Wacha.

To get Bilbo, you should travel an hour by car or by motor bike. The general looking of the geyser is quite unique and exceptional. One among others that makes it special is the evaporation of water without any normally observable heat.

Bilbo Hot Spring is very different since it has both liquid and gaseous state of water at once without seasonal fluctuation of its volume. When the liquid state of the water springs up from ground, it releases the smoke in to the air.

The released cloud of smoke covers some part of the area that can be seen from a far distance. Some people use it as holy water while for others it serves as traditional medicine. To have the everlasting satisfaction, visit the place.
Via: Loolashe Tube

"ዮ ..ዮ ..ጋሞ ማስቃላ/ዮ ዮ ሎላሼ""ዮ ጋሞ ማስቃላ " በዓል ከቅድመ ዝግጅት እስከ ሽኝት የሚከወኑ ተግባራት ፦በወረሃ መስከረም የሚከበረው የ' ዮ' ጋሞ ማስቃላ ዘመን መለወጫ በዓል በጉ...
15/09/2023

"ዮ ..ዮ ..ጋሞ ማስቃላ/ዮ ዮ ሎላሼ"
"ዮ ጋሞ ማስቃላ " በዓል ከቅድመ ዝግጅት እስከ ሽኝት የሚከወኑ ተግባራት ፦

በወረሃ መስከረም የሚከበረው የ' ዮ' ጋሞ ማስቃላ ዘመን መለወጫ በዓል በጉጉት ተጠባቂና በሀገራችን ልዩ ድባብ ከሚስተዋልባቸው በዓላት አንዱ ነው፡፡ በጋሞዎች ‹ዮ '' ማስቃላ› ማለት ‹መስቀል እንኳን ደህና መጣልን› ማለት ነው፡፡ የሕዝቡ የዘመን መለወጫ በመሆኑ በልዩ ድምቀትም ይከበራል፡፡

ለዮ ማስቃላ በዓል ሲባል እናቶችና አባቶች እቁብ በመጣል ዝግጅቱን ይጀምራሉ፡፡ እናቶች ለማስቃላ ቡላ፣ ወተት፣ ቅንጬ ለመሥራት የሚያገለግለውን ገብስ፣ በቆሎ ፣ ቅቤና ቅመማ ቅመም ለማዘጋጀት ዓመቱን ሙሉ እቁብ ሲጥሉ ይከርማሉ፡፡ አባቶች ደግሞ የሚጥሉት እቁብ ለሰንጋ መግዣነት የሚውል ነው፡፡

ወጣቶች ለደመራ እንጨት በመሰብሰብና በማሰናዳት፣ ለከብቶች ሳር አጭዶ በመከመርና ጉልበት የሚጠይቁ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ያግዛሉ፡፡ "ዮ "ማስቃላ በጋሞ ብሔረሰብ በኩል ሁሉም ቂሙን ረስቶ በእርቅ፣ በይቅርታ ፣ በሠላምና በአብሮነት ከክፉ ተግባርና ሐሳብ ወጥቶ በአዲስ መንፈስ የሚታደስበት ጊዜ ነው፡፡
የ"ዮ "ማስቃላ በዓል በጋሞዎች ምድር ረዘም ላለ ጊዜ ይዘልቃል፡፡

“ኡሻቻ” (ቀኝ) ይሉታል በሀገሬው ቋንቋ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ነጮች ጭምር የጋሞን ማስቃላ ለመታደም ወደ ጋሞ ምድር ይመጣሉ አብረው ያከብራሉ። ዝግጅቱ ለሰዎች ብቻ ሳይሆን እንስሳትንም በማሰብ የሚከናወን ነው፡፡ በበዓሉ ወቅት ሁሉም ወደ በዓሉ የሚሄዱ በመሆኑ ከብቶች የሚመገቡት ድርቆሽ ቀደም ብሎ ይዘጋጃል፡፡

ከዚህ ውጭ በበዓሉ ወቅት የሚግጡት ሰፊ ቦታ/ ካሎ/ ለግጦሽ ተካልሎ ይቀመጣል።
ሕጻናት ከብቶቹን ወደ ግጦሽ መስክ ካሰማሩ በኋላ ‹‹ለአዲሱ ዓመት እንኳን አደረሰን ፤ እንኳን መስቀል በሰላም መጣልን፤… … በደስታ አደረሰን ፤ ለዚህ ቀን እንኳን አበቃን እያሉ›› ይጨፍራሉ፡፡ ዮ ዮ ማስቃላ ዮ

ዘገባው የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው!
መስከረም 4/2015 ዓ.ም
Gamo Tour & Travel, Ethiopia

በደቡብ ኢትዮጵያ ጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶርዜ ባህላዊ መንደር ላይ ዮ-ማስቃላን ምክንያት በማድረግ በአንድ ቦታ ከ1000 በላይ በሬዎች እንደሚታረደ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዓለማችን በአን...
14/09/2023

በደቡብ ኢትዮጵያ ጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶርዜ ባህላዊ መንደር ላይ ዮ-ማስቃላን ምክንያት በማድረግ በአንድ ቦታ ከ1000 በላይ በሬዎች እንደሚታረደ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዓለማችን በአንድ ቦታ ወይም ሜዳ ከ1000 ሺህ በሬ በላይ የሚታረድበት ከዶርዜ ውጪ የለም ተብሎ ይታመናል።

ማህበረሰቡ በገበያ አደባባይ ከብቶችን በማረድ ጥሬ ስጋ እየበላ፣ ቦርዴ(Madha)፣ ጠጁ፣ አርቀው ፣ የተለያዩ ባህላዊ መጠጦችን እየጠጣ እና ባህላዊ ጭፌራዎችን እየተጫወተ በዓሉን በደስታ ያሳልፋል፡፡

ይህን ታሪካዊ ባህል፣ ትልቅ ደስታና ፈሽታ የሚስተዋልበትን መስህብ ሊንከባከበውና ልናበለፅገው ይገባል። የዘንድሮው ዮ ማስቃላ ወይም እርድ ስነስርዓት በመስከረም 14 ይፈፀማል፡፡ ይህን በዓል ለመታደም ከሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ወጪ የተለያዩ እንግዶች ወደ ቦታው ይመጣሉ፡፡
ዞናችን ሠላማዊ በመሆኑ ለእንግዶች ምቹ ነው!

12/09/2023

Happy New Ethiopian Year,
2016 E.C!
መልካም አዲስ አመት 2016 ዓ.ም!

እንኳን ደህና መጣችሁ!ድምጻዊ አብነት አጎናፍርና ቤተሰቡ  በጋሞ ዞን ጨንቻ ዶርዜ ባህላዊ መንደር!
10/09/2023

እንኳን ደህና መጣችሁ!
ድምጻዊ አብነት አጎናፍርና ቤተሰቡ በጋሞ ዞን ጨንቻ ዶርዜ ባህላዊ መንደር!

At Dorze, Gamo Ethiopia!
10/09/2023

At Dorze, Gamo Ethiopia!

Gamo Cultural Foods!
09/09/2023

Gamo Cultural Foods!

በጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ የሚገኝ ድንቅ ተፈጥሮ ነው!"Sutha Pulto"/የደም ምንጭ!!
09/09/2023

በጋሞ ዞን በቁጫ ወረዳ የሚገኝ ድንቅ ተፈጥሮ ነው!
"Sutha Pulto"/የደም ምንጭ!!

Bodo Market in Dorze Village at Gamo Zone, Southern Ethiopia!
08/09/2023

Bodo Market in Dorze Village at Gamo Zone, Southern Ethiopia!

Gugge Zuma!ጉጌ ተራራ!Guge Mountain!
08/09/2023

Gugge Zuma!
ጉጌ ተራራ!
Guge Mountain!

Gamo Cultural House!
07/09/2023

Gamo Cultural House!

በእግር ተለክቶ የሚሰራው የጋሞ ዘመን ተሻጋሪ ባሕላዊ  ቤት !
06/09/2023

በእግር ተለክቶ የሚሰራው የጋሞ ዘመን ተሻጋሪ ባሕላዊ ቤት

!

365 ቀናት በሙሉ ልምላሜው የማይለያቸው❤***********************************‼ኤሊ ዶዜ/ኮዶ ቀበሌያት 'ፆሳ ደሬታ'/Gammo highland areas of Guge Mount...
04/09/2023

365 ቀናት በሙሉ ልምላሜው የማይለያቸው❤
***********************************‼
ኤሊ ዶዜ/ኮዶ ቀበሌያት 'ፆሳ ደሬታ'/
Gammo highland areas of Guge Mountain chain❤💪❤‼

 በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ ይገኛል። እናንተም ጊዜ ስታገኙ ይህንን ድንቅ ተፈጥሯዊ ስፍራ እንዲጎበኙ ግብዣዬ ነው፡፡ Via: Dubusha Media Network DMN
04/09/2023


በጋሞ ዞን ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ዶኮ ሎሻ ይገኛል።
እናንተም ጊዜ ስታገኙ ይህንን ድንቅ ተፈጥሯዊ ስፍራ እንዲጎበኙ ግብዣዬ ነው፡፡
Via: Dubusha Media Network DMN

 #𝚅𝚒𝚜𝚒𝚝 𝙶ammo𝙑𝙄𝙎𝙄𝙏 𝙀𝙏𝙃𝙄𝙊𝙋𝙄𝘼 𝙳𝚒𝚜𝚌𝚘𝚟𝚎𝚛 𝚃𝚑𝚎 𝙱𝚎𝚊𝚞𝚝𝚒𝚏𝚞𝚕 𝚗𝚊𝚝𝚞𝚛𝚎 𝚊𝚗𝚍 𝚌𝚞𝚕𝚝𝚞𝚛𝚎.𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 𝙪𝙣𝙛𝙤𝙧𝙜𝙚𝙩𝙩𝙖𝙗𝙡𝙚 𝙢𝙤𝙢𝙚𝙣𝙩𝙨.. 𝙬𝙞𝙩𝙝 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙛𝙧𝙞𝙚𝙣𝙙𝙨.𝕐𝕠...
03/09/2023

#𝚅𝚒𝚜𝚒𝚝 𝙶ammo
𝙑𝙄𝙎𝙄𝙏 𝙀𝙏𝙃𝙄𝙊𝙋𝙄𝘼
𝙳𝚒𝚜𝚌𝚘𝚟𝚎𝚛 𝚃𝚑𝚎 𝙱𝚎𝚊𝚞𝚝𝚒𝚏𝚞𝚕 𝚗𝚊𝚝𝚞𝚛𝚎 𝚊𝚗𝚍 𝚌𝚞𝚕𝚝𝚞𝚛𝚎.
𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 𝙪𝙣𝙛𝙤𝙧𝙜𝙚𝙩𝙩𝙖𝙗𝙡𝙚 𝙢𝙤𝙢𝙚𝙣𝙩𝙨.. 𝙬𝙞𝙩𝙝 𝙮𝙤𝙪𝙧 𝙛𝙧𝙞𝙚𝙣𝙙𝙨.
𝕐𝕠𝕦 𝕨𝕚𝕝𝕝 𝕖𝕟𝕛𝕠𝕪 𝕥𝕙𝕖 𝕨𝕒𝕣𝕞 𝕨𝕖𝕝𝕔𝕠𝕞𝕚𝕟𝕘 𝕠𝕗 𝔾ammo 𝕤𝕠𝕔𝕚𝕖𝕥𝕪 Yoo Yoo Masqala/Loolashe

 ❗የሶምቦ ዋሻ መገኛ፣ ጎርቃ አባሳ ሀይቅ፣የጎዛ ተክል ድንጋይ መናገሻ፣የዳዳቆ ዋሻ የኡሄ ፏፏቴ መገኛ፣የሻዮደን፣ የጥንታዊ አብያተክርስቲያናት መናገሻ እንድሁም በእምቅ የተፈጥሮ ፀጋ የታደለች...
02/09/2023


የሶምቦ ዋሻ መገኛ፣ ጎርቃ አባሳ ሀይቅ፣የጎዛ ተክል ድንጋይ መናገሻ፣የዳዳቆ ዋሻ የኡሄ ፏፏቴ መገኛ፣የሻዮደን፣ የጥንታዊ አብያተክርስቲያናት መናገሻ እንድሁም በእምቅ የተፈጥሮ ፀጋ የታደለች ለምለም ምድር ዲታ ባንጋ ዴሬ ።

በመንገድ፣በጤናና በትምህርት መላውን የወረዳውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን በማከናወን በፍጥነት እየለማች የምትገኝ ወረዳ ናት።

በንፁህ የመጠጥ ውሀ ሽፋን 48.2 በመቶ ከነበረበት በአምስት አመቱ የልማቱ እቅድም የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን 80 % ለማድረስ ከአጋር ተቋማት ጋርም በህብረት እየሰራ ይገኛል።

ታዲያ ወረዳን ከቀበሌ፣ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኙ መንገዶች በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ በማከናወን አመርቂ ውጤቶች የመጡ ሲሆን የመብራት አገልግሎት በወረዳው በሚገኙ በ25ቱ ቀበሌያትም የ24 ሰዓት የመብራት ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራው ስራም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል።

ለኑሮና ለኢንቬስትመንት ምቹ በሆነቺው ወረዳችን በመምጣት ትርፋማ ለመሆን ፍላጎት ላላቸው ባለሀብቶች ወረዳችን ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እናንተን እየጠበቀች ትገኛለች።

❗❗

Ethio Gamo Dance Groups at Konso!
01/09/2023

Ethio Gamo Dance Groups at Konso!

 !"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""የዛሬውን አያድርገውና ነጭ ሳር ብሔራዊ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ...
30/08/2023

!
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
የዛሬውን አያድርገውና ነጭ ሳር ብሔራዊ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የሚገኝ ሲሆን ከአርባምንጭ ከተማ በ 32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሲገኝ 514 ስኩዌር ኪ.ሜ ስፋት አለው ፓርኩ የተቋቋመው 1967 ዓ.ም ሲሆን በፓርኩ ከ91በላይ አጥቢ እንስሳት ፣
ከ351 በላይ አእዋፋት ሲገኙ ፓርኩ ከሚታወቅባቸዉ የዱር እንስሳት በዋናነት፦ ሜዳ አሀያ ፣ ድኩላ ፣ አጋዘን እንዲሁም በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው የስዋይነስ ቆርኬ ይገኙበታል በሌላ በኩል ፓርኩ ውሰጥ ከሚጠቃለሉት ተፈጥሮዊ መስህቦች እንደ ሰርመሌ ፍልውሃ ፣ ከርባዎቹ ምንጮች ፣ የተለያዩ የእፁዋትና የአገር በቀል ዛፎችን በውስጡ አጭቆ የያዘው የአርባምንጭ ደን ፣ የአዞ ገበያ ፣ የእግዘ/ር ድልድይ በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ተጠቃሸ የቱሪስት መስህቦች ናቸው።
ይሄንን ፓርክ መጠበቅ የሁላችንም ግዴታ ነው ፣ ትኩረት ለነጭ ሰር ብሔራዊ ፓርክ!
!

_____   ♦   የሄድኩት ነገር.. 😁🤙👇__★ዛሬ በጋሞ ጥለት እና   ሠርግ ታድሜ ነበር,, ሠው በአግራሞት አድናቆቱን ሲገልፅ ውሏል..  #ከሙሽሮቹ በላይ ትኩረት ሳብኩ መሠለኝ!! 🙄??🤔...
28/08/2023

_____ ♦ የሄድኩት ነገር.. 😁🤙👇
__★ዛሬ በጋሞ ጥለት እና ሠርግ ታድሜ ነበር,, ሠው በአግራሞት አድናቆቱን ሲገልፅ ውሏል.. #ከሙሽሮቹ በላይ ትኩረት ሳብኩ መሠለኝ!! 🙄??🤔 😁 👌

_★እኔን አይጨምርም😁 እንጂ ☞አብዛኛው ሠው ጥሪ ሲጠራ,, የሚያሳስበው ነገር,, ልሂድ? ይዤ ልሂድ?? ,, #ፀጉሬን ምን ላርገው??,, እሚሉ ነገሮች ናቸው!!!

★★ በራሱ ውበት ነው!!
በራሱ ውበት ነው!!
በራሱ ውበት ነው!! 👍★★

❀❀እንዲ ላስዋቡኝ ለዲዛይነሮቼ ዶርዜ ምስጋና❀❀
♥ 🙏🙏
#መሳዬ♥🙏🙏

Dorze Village
Dorze VillageiDorze VillageyArbaMinch CityoArbaMinch CitylDorze_eco_village_&_lodgeDorze_eco_village_&_lodgeDorze_eco_village_&_lodgeAMesay ZewdieiMesay ZewdietArba Minch City NetworktArba Minch City NetworkAArba Minch City NetworkiArba Minch City NetworkkArbaminch Market PlaceArbaminch Market PlaceArbaminch Market Place
Via: Ce Na

 #እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያዬ  #ዳርሽን የእሳት ቅጥር  #ውስጡን የምድር ገነት  #ያድርግልን  #ውብ ተፈጥሮ  #ውብ ፀጋ  #ቡልአ እና ቡናን ለአለም ገበያ የምታቀርብ  #የንጉሥ ጎና ምድ...
27/08/2023

#እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያዬ
#ዳርሽን የእሳት ቅጥር
#ውስጡን የምድር ገነት
#ያድርግልን

#ውብ ተፈጥሮ
#ውብ ፀጋ
#ቡልአ እና ቡናን ለአለም ገበያ የምታቀርብ
#የንጉሥ ጎና ምድር
#የታታርው ሕዝብ መገኛ
#ኮሬ ኢትዮጵያ
Via: Promote Koore

Maze National Park/ማዜ ብሔራዊ ፓርክ! """""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""በ1997 ዓ.ም የተቋ...
27/08/2023

Maze National Park/ማዜ ብሔራዊ ፓርክ!
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
በ1997 ዓ.ም የተቋቋመውና በደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የሚተዳደረው ማዜ ብሔራዊ ፓርክ ከአዲስ አበባ 460፣ከሐዋሳ 235 እንዲሁም ከአርባምንጭ ከተማ 196 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ።

ይህ ፓርክ አብዛኛው ክፍሉ የሚገኘው በጋሞ ዞን ሲሆን የጎፋ ዞን አንድ ወረዳ ያዋስነዋል። ከጋሞ ዞን 4 ወረዳዎች ማለትም ቁጫ ፣ቁጫ አልፋ ፣ዳራማሎ እና ካምባ ወረዳዎች እንዲሁም ከጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ያዋስኑታል።

የፓርኩ አጠቃላይ ስፋት 220 ስኬዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘው ብርቅዬው የስዋይኔ ቆርኬ፤ አንበሳ፣ የቆላ አጋዘን ፣አቦሸማኔ ፣ አምባራይሌ፣ትልቁ አጋዘንን ጨምሮ 39 የተለያዩ አጥቢ እንስሳት ፣ 196 የአዕዋፍት ዝርያዎችና 80 ዓይነት የዕፅዋት ዝርያዎች ይገኙበታል ።

ፓርኩ መጠሪያውን ያገኘበት ማዜ ወንዝ እና የቢልቦ ፍል ዉሃ በፓርኩ ከመገኘታቸው ባሻገር ማራኪ የሆነ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ያለዉ በመሆኑ የጎብኝዎችን ቀልብ ይገዛል።

የፓርኩ ጽ/ቤት ከሠላም በር ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የፓርኩ ጽ/ቤት በውስጡ ወ=35 ሴ=5 በድምሩ ለ 40 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።

በፓርኩ ውስጥ ብርቅዬውን ስዋይነስ ቆርኬ እና አንበሳን ጨምሮ ሌሎች የዱር እንስሳትን እንደ ልብ ማዬት የሚቻል በመሆኑ ዘላቂ የማስተዋወቅ እና የማልማት ስራ ብሰራለት ብዙ ጎብኚዎችን የሚስብ ፖርክ ነው።
Gamo Tour & Travel, Ethiopia

22/08/2022
Free medical examination based on interest!All of you are invited!
21/08/2022

Free medical examination based on interest!
All of you are invited!

Announcement for COC examinee  health science college!
19/08/2022

Announcement for COC examinee health science college!

To whom it may concern!Hawasa University!
19/08/2022

To whom it may concern!
Hawasa University!

ማስታወቂያ
**********
ለ2015 ዓ.ም የድህረ ምረቃ (ለ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ) ፕሮግራም አመልካቾች በሙሉ

ለ2015 ዓ.ም የድህረ ምረቃ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም (August 29,2022) ሲሆን የመፈተኛ ሰዓትና ቦታ ፕሮግራሙ በሚሰጥበት ካምፓስ በሚገኙ ት/ክፍሎችና ት/ቤቶች የሚገለጽ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰብያ፡-ተፈታኞች ለፈተና በሚቀርቡበት ሰዓት ማንነታቸውን የሚገልጽ የመታወቂያ ደብተር መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሬጅስትራርና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

To whom it may concern!University of Gondar!
19/08/2022

To whom it may concern!
University of Gondar!

Serving community as usual!
18/08/2022

Serving community as usual!

To whom it may concern!Arbaminch University!
17/08/2022

To whom it may concern!
Arbaminch University!

ክፍት የስራ ማስታወቂያ በቦረዳ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት!
10/08/2022

ክፍት የስራ ማስታወቂያ በቦረዳ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት!

To whom it may concern!Jimma University!
09/08/2022

To whom it may concern!
Jimma University!

Address

Academic Orginization
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Tour & Travel, Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category