08/09/2023
የጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የ“ጓንዷ” በዓልን ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀዋል: ''ጓንዷ'' ከጨለማ ወደ በረሃን, የብሩህ ተሰፋ መሸጋገሪያ ነው።
በጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የ"ጓንዷ" በዓል አሮጌውን ዓመት ሸኝተን አዲሱን ዓመት በተስፋ የምንቀበልበት፣ የበሰሉ እሼቶች የሚቀምሱበት, የተጣሉ ሰዎች የሚታረቁበት, አባቶች ትውልድን የሚመርቁበት, ያላገቡ ወንዶች እና ሴቶች የሚታጩበት ወይም የሚጋቡበት እንዲሁም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ባህላዊ ዕሴቶች እና ጨዋታ የሚንፀባረቁበት፣ ከትውለድ ትውልድ ሲሸጋገር የቆየ፣ ለዘመናትም የሚቀጥልና መላው የጉሙዝ ሕዝብ የሚኮራበት ውብ በዓል ነው: ባህሉ ከጳጉሜ 1 ጀመሮ እሰከ ፀዳይ ወራቶች ይላሉ የማሕበረሰቡ የሀገር ሸማግሎች: ባህሉን ከጥንት ሲከበር እንደነበር ይላሉ አባቶች
ይህ በዓል ለዘመናት አብረውት ከኖሩት ሌሎች ወንድምና እህት ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በፍቅር፣ በይቅርታና እንዲሁም በትብብር አብሮነቱን የሚያድስበት ብሎም ነገውን የሚሰራበት በዓል ነው፡፡
በዓሉ ከነገ ጷጉሜ 1 ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች
የኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር አወቀ አይሸሽም፣ የበዓሉን አከባበር በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፣ በዓሉ በጉሙዝ ብሔረሰብ ዘንድ በየዓመቱ በድምቀት ከሚከበሩ እና ልዩ ትርጉም ከሚሰጣቸው በዓላት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።
የዘንድሮውን የ“ጓንዷ” በዓል በክልል ደረጃ በተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡
በዓሉን በድምቀት በማክበር የጉሙዝ ብሔረሰብ ባህል፣ ታሪክና እሴትን ለትውልድ ማስተላለፍና ለዓለም ከማስተዋወቅ ባለፈ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እንደሚከናወኑም ነው የገለጹት፡፡
ጳጎሜ 1 በነገው ዕለት በዓሉን በማስመልከት የአካባቢ ጽዳት ዘመቻ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በዓሉ ጳጉሜ 2 በደም ልገሳ፣ ጳጉሜ 3 ለተቸገሩና ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ፣ ጳጉሜ 4 ደግሞ በኡራ አምባ 5 ቀበሌ በመገኘት ከዚህ ቀደም የተተከሉ የችግኞችን እንክብካቤ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
የበዓሉ ማጠቃለያ በሆነው ጳጉሜ 5 ደግሞ "ጓንዷ ለዘላቂ ሠላምና ልማት" በሚል በፓናል ውይይት፣ በኤግዚቪሽን እና በባህላዊ ትዕይንቶች እንደሚከበር አስታውቀዋል።
የኮሚቴው አባል አቶ ቢንያም መንገሻ በበኩላቸው፣ በዓሉን የብሔረሰቡ ተወላጆች አዲሱን ዓመት በተስፋና በአዲስ መንፈስ ለመቀበል በተለዬ ሁኔታ ያከብሩታል ብለዋል።
በዓሉ የዕርቅ፣ የአንድነት፣ የሚታረቁበት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገሪያ መሆኑንን ነው
በየዓመቱ በባህላዊ ዘፈንና ጭፈራ፣ ያለውን ተካፍሎ በጋራ በመብላትና በመጠጣት በደስታ የሚከበር ነው አስተባባሪ ጥሪ አቅርቧል፡፡