Visit aregoba

Visit aregoba Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Visit aregoba, Travel Company, adis Ababa, Awash.

ባህላችን ውበታችን ነው
05/05/2024

ባህላችን ውበታችን ነው

26/04/2024

Thanks for being a top engager and making it on to my weekly engagement list! Hayati Mohammed, Selam Selam

 #ቅኝት | "ኮረሚ" - የጥንታዊት አርጎባዎች መንደርን ታሪክን በአግባቡ በመሰነድ ለአለም ባለማስተዋወቃችን ኢትዮጵያ ከኢስላሚክ ቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን ገቢ አሳጥቷታል"። ጋዜጠኛና የኢስ...
24/04/2024

#ቅኝት | "ኮረሚ" - የጥንታዊት አርጎባዎች መንደርን ታሪክን በአግባቡ በመሰነድ ለአለም ባለማስተዋወቃችን ኢትዮጵያ ከኢስላሚክ ቱሪዝም ማግኘት የሚገባትን ገቢ አሳጥቷታል"።

ጋዜጠኛና የኢስላሚክ ታሪክ ፀሃፊ ተሾመ ብረሃኑ
****************************************

ከሀረር ከተማ በስተ ደቡብ 8 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው "ኮረሚ" ተብላ በምትጠራው የጥንታዊ የአርጎባዎች መንደር የሸዋል ኢድ በዓል በድምቀት የተከበረ ሲሆን በቦታው የሚገኙ ዘመናትን ያስቆጠሩ ታሪካዊ ቦታዎች ተጎብኝተዋል።

የክልሉ የባህል፣ የቅርስና የቱሪዝም ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተወልዳ አብዶሽ ጥንታዊዎቹ የአውሶፊ አውቡርቃ መስጊዶችና አካባቢዎቹ ለአርጎባ ማህበረስብ የስልጣኔ ቀዳሚ ህዝቦች መሆናቸውን የሚያሳይ ታሪካዊ አሻራዎች ናቸው ይላሉ።

በሀረር - ኮረሚ መንደር ከ13ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የሀረር መዲና የነበረችው "ደከር" የምትገኝ መሆኗን ገልፀው የጥንታዊ ኢስላማዊ የግብርናና የስነ ህንጻ ጥበብ ህያው መገኛ እንደነበረች ያስረዳሉ።

ጋዜጠኛና የኢስላሚክ ታሪክ ፀሃፊ አቶ ተሾመ ብረሃኑ እንደሚሉት አርጎቦች በሀረር ታሪክ በሥነ ህንጻ ፣ በልስና ሥራና በሌሎችም ዕደጥበብ ሥራዎች የታወቁ ሲሆኑ ሥራቸው አዲስ አበበ እስከሚገኘው የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ቤተመንግሥት እንደሚዘልቅ ይናገራል።

"ጎዜ" እራስን ከጠላት የመከላከያ እና የትምህርት ከተማቸው ፣ "አብዱልረሱል" የባሪያ ንግድ ከተማ ፣ "አልዩ አምባ" የቀረጥ ከተማ ፣ "ኬላ-ኦሲስ ኖራ" አስተዳደራዊ ከተማ ፣ "ጨኖ" የደረቅ ወደብ ከተማቸው ፣ "ጀበርት" አስተዳደራዊ ከተማ ፣ "ኩሊባስ" የመኖሪያ ከተማን ጨምሮ "አህዋጅ" የሸሪፎች/አሽረፎች የመቃብር ቦታዎች እና የትምህርት ማዕከልቻውን በሚገባው ልክ ለአለም ባለማስተዋወቃችን ኢትዮጵያ ከኢስላሚክ ቱሪዝም ታገኝ የነበረውን ገቢ እንድታጣ አድርጓታል ሲሉ ይገልጻሉ።

በቀጣይ እነዚህን ታሪካዊ ቦታዎች ማስተዋወቅ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ትልቅ መነቃቃት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለዋል።

ስንታየሁ አበራ - ከኮረሚ (የጥንታዊ አርጎባዎች መንደር)

23/04/2024

ባህላችን ውበታችን ነው

20/04/2024

_ባህላዊ _ልብሶች _ጌጣጌጦች(በከፊል እይታ )

የ1445ኛው  የሸዋል ዒድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል ሁለተኛ ቀን ውሎ በሀረሪ ክልል የአርጎቦች መንደር ጉብኝት ተካሔደ። በጉብኝቱ ላይ  የፌደራል እ...
17/04/2024

የ1445ኛው የሸዋል ዒድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል ሁለተኛ ቀን ውሎ በሀረሪ ክልል የአርጎቦች መንደር ጉብኝት ተካሔደ።
በጉብኝቱ ላይ የፌደራል እና የሀረሪ ክልል የስራ ሀላፊዎች የታሪክ ተመራማሪዎች የአርጎባ ጀበርት ይፋት ሱልጣኔት ሱልጣን መሀመድ አሽራዬ ፣ የአርጎባ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ሙሳ የአርጎባ ልማት ማህበር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙስጠፋ ሸሁ ፣ የአርጎባ ልዩ ወረዳ አሰሰተዳዳሪ አቶ ባባ አቦ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

13/07/2023

የአርጎባ ማህበረሰብ የባህላዊ በአለ ሲመት

ተቋርጦ የነበረው የይፋት ወላስማ ሱልጧኔት እነሆ ቀጠለ !!🙏ከ 450 አመታት በፊት ተቋርጦ የነበረው ታላቁ የይፋት ወላስማ ሱልጧኔት በዛሬው እለት በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ ጋቸኒ ከተ...
11/07/2023

ተቋርጦ የነበረው የይፋት ወላስማ ሱልጧኔት እነሆ ቀጠለ !!🙏

ከ 450 አመታት በፊት ተቋርጦ የነበረው ታላቁ የይፋት ወላስማ ሱልጧኔት በዛሬው እለት በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ ጋቸኒ ከተማ ከተለያዩ ክልሎች በመጡ በርካታ የአርጎባ ማህበረሰብ አባላት እና የአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች (መሻኢኾች) በተገኘሁበት ሱልጧኔቱን በይፋ ሰይሟል።

አንጋፋው ሸህ #አባህሙጋ በቁርአን ና በዱዓ መርቀው ፕሮግራሙን የከፈቱት ሲሆን ቀጥሎም የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና ወኪሎች በአለ ሲመቱን አስመልክተው በየተራ የእኳን ደስ አላቹህ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።በተጨማሪም በየመሀሉ ስለ አርጎባ የይፋት ሱልጧኔት ታሪክ ዙሪያ በተለይም ደሞ ስለ ባህል ወግና ስርዓት የሚያንጸባርቁ ታሪካዊ ስነጽሁፎች እንዲሁም ሀይማኖታዊ መልዕክቶችን ያዘሉ የተውሂድ አጀሞችን በማቅረብ በዓለ ሲመቱን አድምቀውታል።

በመቀጠልም ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ለአርጎባ ህዝብ ፖለቲካዊ ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግዚያቸውን ገንዘባቸው ጉልበታቸውን ባጠቃላይ ሁሉ ነገራቸውን ሰውተው ለሰሩ ነገር ግን አሁን ላይ በህይወት የሌሉትን የብሄረሰቡ ታላቅ ባለውታዎችን ሱረቱል ፋቲሃ በመቅራት እንዲታሰቡ የተደረገ ሲሆን ከቡዙ ለጥቂቶቹ በቅርብ ቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የማስታወሻ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በመጨረሻም ስለሱልጧኑ የህይወት ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ በመድረክ መሪዎች ከቀረበ ወዲያ ከአርጎባ ማህበረሰብ ከተወጣጡ አሊሞች መሻአኺች እና የሀገር ሽማግሌዎች ባጠቃላይ የበአለ ሲመቱ አስፈፃሚዎች ለክቡር ሱልጧን ካባ የማልበስ ስነስርዓት ከተካሄደ ቡሃላ የሱልጧኔቱን ማስቀጠል አስፈላጊነት እና ስለሚኖረው ጠቀሜታዊ ፋይዳ ለታዳሚው ገለጻና ማብራሪያ ሰተው በቀጣይም ለሚሰሩት ስራዎች ህዝቡ ከጎናቸው ሆኖ እንዲያግዛቸው የአደራ መልእክት በማስተላለፍ ፕሮግራሙ ፍጻሜውን አግኝቷል።😍

09/07/2023
 _______በአርጎባ ጋቸኔ ከተማ ላይ ከሚገኙ ቅርሶች መካከል የእማ መዲና መስጊድ አንዱ ነዉ፡፡ እማ መዲና አሊም ሴት ነበሩ፡፡ ቱፋህ ኢብኑ ሐጀር የሻፊኢይ ኪታብን በእጃቸው የፃፉ ታላቅ አ...
05/07/2023


_______
በአርጎባ ጋቸኔ ከተማ ላይ ከሚገኙ ቅርሶች መካከል የእማ መዲና መስጊድ አንዱ ነዉ፡፡ እማ መዲና አሊም ሴት ነበሩ፡፡ ቱፋህ ኢብኑ ሐጀር የሻፊኢይ ኪታብን በእጃቸው የፃፉ ታላቅ አሊም ናቸዉ፡፡ በዚህ በፃፉት መፀሐፍ ላይ በአሊሞች ሲያስገመግሙ ካለ አንዲት አናባቢ በስተቀር ስህተት ሳይገኝበት በመቅረቱ አድናቆትን አትርፈው እስከ ዛሬ በአርአያነት ይዘከራሉ፡፡

Visit aregoba
29/05/2023

Visit aregoba

visit aregoba
24/05/2023

visit aregoba

visit argoba
04/05/2023

visit argoba

ውበት ስለካ አርጎባ ነው ለካ
03/05/2023

ውበት ስለካ አርጎባ ነው ለካ

❤ አርጎባ❤
04/03/2023

❤ አርጎባ❤

08/12/2022
27/09/2022

❤argoba ❤
27/09/2022

❤argoba ❤

♥ ♥አርጎባ የሚለው ቃል የአርጎባ ብሔረሰብ መጠሪያ ሲሆንትርጉሙም አረብ ገባ ማለት እንደሆነ የዕድሜ ባለፀጎችያስረዳሉ፡፡የከሳቴ ብርሃን ተሰማ መዝገበ ቃላት ደግሞ አርጎባማለት በይፋት /ሰሜን...
25/09/2022

♥ ♥

አርጎባ የሚለው ቃል የአርጎባ ብሔረሰብ መጠሪያ ሲሆን
ትርጉሙም አረብ ገባ ማለት እንደሆነ የዕድሜ ባለፀጎች
ያስረዳሉ፡፡
የከሳቴ ብርሃን ተሰማ መዝገበ ቃላት ደግሞ አርጎባ
ማለት በይፋት /ሰሜን ሸዋ/ የሰፈረ የእስልምና
ሃይማኖት ተከታዮች መጠሪያ እንደሆኑ ይገልጻሉ፡፡
የብሔረሰቡ አባላት ቀደም ባለው ጊዜ ነጋዴ፣ ወላስማ፣
ጀበርት፣ ይፋት ወዘተ በሚሉ መጠሪያ ስሞች ሲጠሩ
ነበር፡፡
የአርጎባ ብሔረሰብ ቋንቋ አርጐብኛ ሲሆን አማርኛ፣
ኦሮምኛ በተወሰነ ደረጃም አረብኛ በአካባቢው ይነገራሉ፡፡
አንዳንድ የታሪክ ምሁራን እና የአርጎባ ብሔረሰብ አባላት
አርጎባዎች በ7ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ
ከገቡት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር የዘር ሀረግ
ትስስር እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡
ከአርጎባ ብሔረሰብ መኖሪያ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ሾንኬ
በመባል ይታወቃል፡፡
ሾንኬ ከከሚሴ ከተማ በስተምስራቅ 25 ኪ/ሜ ርቀት
ላይ በዳዋ ጨፋ ወረዳ በጅሮታ ቀበሌ ይገኛል፡፡
የሾንኬ መንደር ከፍተኛ ቦታ ላይ ውብ በሆነ ጥበብ
ከእንጨት፣ ድንጋይ፣ አፈርና ጭቃ የተሰሩ ቤቶችን የያዘ
መንደር ነው፡፡
መንደሩን ከርቀት እንዲሁም ተራራው ጫፍ ላይ
ወጥተው ሲያዩት እጅግ ማራኪ ነው፡፡
የሾንኬ ውበት የሚጀምረው ወደ መንደሩ ከሚወስደው
ጎዳና ነው፡፡
ጎዳናው ወጣ ገባ የበዛበትና ዙሪያ ገባውን በደን የተሸፈነ
በመሆኑ ተፈጥሯዊ ውበቱ መንፈስን ያረካል፡፡
አብዛኛዎቹ የአርጎባ መንደሮችና መስጅዶችም
የተመሠረቱት ገለል ባለና በከፍተኛ ቦታዎች/ተራራዎች
ላይ በመሆኑ አቀማመጣቸው ዓይንን ይስባል፤ መንፈስን
ይማርካል፡፡
የአርጎባ ብሔረሰብ የራሱን ወግና ባህል
የሚጠብቅባቸው ጥንታዊ መስጅዶች አሉት፡፡
ከእነዚህ መካከል የሾንኬ መስጅድ አንዱ ነው፡፡
የሾንኬ መስጅድ በአራት ማእዘን ቅርጽ የተሰራ ነው፡፡
ጣራው በረጃጅም የዛፍ ግንዶች ተከድኗል፡፡
በግንዶቹ ላይ አፈርና ጭቃ ሰለሚሞሉ ጣሪያው ለእህል
ማስጫና ለመናፈሻነትና ያገለግላል፡፡
ግድግዳው ባልተጠረቡና እርስ በርሳቸው በተያያዙ
ድንጋዮች ተገንብቷል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች መስጅዱን
ከበው ይገኛሉ፡፡
ለእምነቱ ተከታዮች ግልጋሎት የሚሰጡ በርካታ
ቁሳቁሶችም በታሪካዊ መስጅዶችና ቅዱስ ስፍራዎች
ይገኛሉ፡፡
ተፈጥሮ፣ ባህልና ታሪክን አጣምሮ የያዘውን የሾንኬ
መንደር ይጎብኙ!!

Address

Adis Ababa
Awash
115599

Telephone

+251989901010

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit aregoba posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Visit aregoba:

Videos

Share

Category