03/01/2025
"በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም መፈጠሩ ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል" የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋየ
*****
በላሊበላ የዘንድሮውን የልደት በዓል በድምቀት ለማክበር ከክልል እስከ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል።
በዓሉን እንደወትሮው ሁሉ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር የአብክመ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከሰሜን ወሎ ዞን እና ከላሊበላ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወኑን የቢሮው ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋየ ገልፀዋል።
አቶ መልካሙ ለአሚኮ እንደገለጹት ቀደም ሲል ለሆቴሎች ክትትልና ድጋፍ ሲደረግላቸው ቆይቷል፤ ለአስጎብኝዎችና ለሆቴል ሰራተኞችም ሙያዊ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል ብለዋል።
በተጨማሪም ከሀይማኖት አባቶች፣ ከጸጥታ አካላት፣ ከአስጎብኝ ድርጅቶች እና ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይቶች የተደረጉ መሆናቸውንም አብራርተዋል።
ሆቴሎችና አስጎብኝ ድርጅቶች ለቱሪስቶች ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት መጨረሳቸውንም ገልፀዋል።
አሁን ላይ ቱሪስቶች ወደ ላሊበላ መግባት መጀመራቸውን የተናገሩት አቶ መልካሙ በላሊበላ እና አካባቢዋ አንጻራዊ ሰላም መኖሩ ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል ብለዋል።
ቱሪስት ለጉዞ የሚዘጋጀውና የሚያቅደው በመዳረሻው ያለውን የሰላም ሁኔታ መሠረት በማድረግ መሆኑን ጠቅሰው ሰላምን ማስፈን ለቱሪስት እንቅስቃሴ ዋናው ቅድመ ሁኔታ መሆኑን አመልክተዋል።
አሁን ላይ ወደ ላሊበላ ከአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ከፍተኛ ቀጥር ያላቸው ቱሪስቶች እየገቡ መሆናቸውንም አቶ መልካሙ አስታውቀዋል።
ኑ! ገናን በላሊበላ አብረን እናክብር
#ቤዛኩሉ #ገና #ላሊበላ