13/11/2022
ሕይወት አጭር ናት--ሳትቀድማችሁ ቅደሟት
በ40 አመቷ ይህቺን የማትሞላ ዓለምና የመከራ ምድርን የለቀቀችው ታዋቂዋ የዓለማችን ቱጃር ሴት የነበረችው ዲዛይነርና ፀሀፊ 《ክሪስዳ-ሮዲሪጌዝ》 በካንሰር በሽታ ከመሞቷ በፊት ማስታወሻዋ ላይ እንዲህ ብላ ፅፋ ነበር።
🔴✍✍✍…-በአለም ላይ አሉ ከሚባሉ ውድ መኪናዎች ውስጥ አንዱ በእኔ ጋራጅ የተቀመጠው ነው፤ አሁን ግን በዊልቼር ነው የምንቀሳቀሰው።
🔴✍✍✍…-ቤቴ ውስጥ በምርጥ ዲዛይነሮች የተሰሩ ውድ የሆኑ የሚያማምሩ ልብሶችና ጫማዎች አሉኝ፤ ግን አሁን በሆስፒታል በተሰጠኝ ስስ ጨርቅ ነው ገላዬን የሸፈንኩት።
አንብቡት!!!! 🔴✍✍✍…-ባንክ አካውንቴ ላይ እጅግ ከበቂ በላይ ገንዘብ አለኝ፤ ግን እሱን አሁን ልጠቀምበት አልችልም።
🔴✍✍✍…-ቤቴ ፓላስ የሚባል ዓይነት ነው፤ ግን እኔ አሁን ሆስፒታል ውስጥ በምትገኝ ትንሽዬ አልጋ ላይ ነው የተኛሁት።
🔴✍✍✍…-ከአንዱ ባለ-አምስት ኮከብ ሆቴል እንዳሻኝ ወደ አንዱ ባለ-አምስት ኮከብ ሆቴል ስንሸራሸር የነበርኩ ሴትዮ፤ አሁን እዚያው ሆስፒታል ውስጥ ካንዱ የላቦራቶሪ ክፍል ወደ ሌላኛው ላቦራቶሪ ክፍል መመላለስ ግዴታዬ ሆኗል።
🔴✍✍✍…-በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፈሪምልን ብለው እንዳላስጨነቁኝ፤ አሁን ግን የሚያክመኝ ዶክተር እንኳ አንድም ቀን ፊርማዬን ጠይቆኝ አያውቅም።
🔴✍✍✍…-ፀጉሬን የማስውብበት ውድ የተባሉ ሰባት አይነት አልማዞች እና ወርቆች ነበሩኝ፤ አሁን ግን ይኽን ማድረግ አልችልም ምክንያቱም ፀጉር የለኝም።
🔴✍✍✍…-በግል አውሮፕላኔ ዓለም ላይ የፈለኩበት ቦታ ብቻዬን መሄድ እችል ነበር፤ አሁን ግን ለመናፈስ ስፈልግ እንኳ የግድ የሁለት የሰዎች እርዳታ ያስፈልገኛል።
🔴✍✍✍…-በቀን በቀን ብፌ በሚባል ዓይነት የተመረጡ ምግቦችን እመገብ ነበር፤ አሁን ግን በቀን ሁለት ፍሬ ታብሌትና ትንሽ ጠብታ ጨው ማታ ላይ የምወስደው ነው ምግቤ።
🔴✍✍✍…………ይኼ ሁሉ ሀብት እና ድሎት ግን እኔን ከበሽታዬ ሊያድነኝ አልቻለም፤………እውነተኛ ሕይወት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ፣ ለትዕዛዛቱም መገዛት ነው።
ህይወት አጭር ናት፤ ሳትቀድማችሁ ቅደሟት።
═════════❁✿❁ ═════════