Visit Sheka

Visit Sheka ጥረታችን የሸካን ህዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሮን ማስተዋወቅ ነው! https://www.youtube.com/

 በሸካ ብሔረሰብ ማሽቃሬ ባሮ የታወጁ ትሞና ሼሮ/አዋጅ  ✍️የሀገራችን ህገመንግስት እና ለሎች ህጎችን የማይቃረኑ ከአያቶቻችን  እና ከቅድሜ አያቶቻችን ስወርድና ስወራረስ የመጡ በህዝባችን ው...
02/10/2024


በሸካ ብሔረሰብ ማሽቃሬ ባሮ የታወጁ ትሞና ሼሮ/አዋጅ

✍️የሀገራችን ህገመንግስት እና ለሎች ህጎችን የማይቃረኑ ከአያቶቻችን እና ከቅድሜ አያቶቻችን ስወርድና ስወራረስ የመጡ በህዝባችን ውስጥ ሰርፆ ተግባር ውስጥ ያለ ልማዳዊ አሰራሮች የባህል ክንዋኔዎች የባህል አስተዳደር/ ሚክራቾዎች የባህል ምክርቤት ውሳኔዎች በሙሉ የሚቀጥሉ እና የፀኑ ይሆናሉ

✍️በሀገራችን የተደነገጉ እና ሀገራችን የተቀበለችው ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ድንጋጌዎች የኢፌዴሪ ህገመንግስት እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህገመንግስት የፍታብሔር እና የወንጀል ህጎች በዝህ ቲሞ እና ሼሮ /"አዋጅ የተከበሩ ናየው።

✍️ጋብቻን በተመለከተ

1.የስጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል ጋብቻ እንዳይፈጸም በባህላችን ክልከላ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ተመሳሳይ የዘር ግንድ ያላቸው እና አመጣጣቸው አንድ የሆኑ ጎሳዎች መካከል ጋብቻ መፈፀም የተወገዘ ነው።

2.ሴት ልጅ ከማታገባው ወንድ ገንዘብ እና ንብረት መውሰድ የተከለከለ ነው።በዝህ ህደት ውስጥ የቤተሰብ ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ የተወገዘ ነው

3.ከጋብቻ በፊት በወላጆች ቤት ሳታገባ መውለድ በባህላችን የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።

4.ከአቅም በላይ የሆነ የእርቅ ገንዘብ ወይም ዋጋ ያለውን ቁሳቁስ መቀበል እርቅ በሚፈፀምበት ወቅት ከሙሽሪት ቤተሰብ እናት እና አባት ውጭ ለሌላ ቤተሰብ አባል የስጦታ ዕቃ ማምጣት መስጠት የተከለከለ ነው
-ለመልስ/ምላሽ ከበግ ውጭ የቀንድ ከብት ማምጣት ከዛሬ ጀምሮ የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።

5.የሙሽሪት ቤተሰብ በመልስ ግዜ በባህላችን ከተፈቀደ እንደ ጊደር ላም የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ቅቤ ቅመማቅመም ሳጥን በስተቀር ለታይታ እና ከሌላ ሰው ጋር ውድድር በምመስል ሁኔታ ከባህላችን ውጭ ተጨማሪ ስጦታ መስጠት የተወገዘ ነው።

6.ተጋቢዎች የመከባበር የመረዳዳት የጋራ ንብረት በጋራ የመጠቀም የማስተዳደር መብት አላቸው።
ይን በባህላችን እና በህግ የተቀመጠ ግዴታ መጣስ የጋራ ንብረት መሰወር እና መደበቅ በማንኛውም አኳን አንዱ የአንዱን መብት መጋፋት በባህላችን የተከለከለ ነው።

7.በትዳር አጋሩ በደል የደረሰበት ወገን ወንዱም ይሁን ሴቷ ወደ ፍርድቤት ጉዳያቸውን ከመውሰዳቸው በፊት በባህል መሰረት አለመግባባታቸውን ለመፍታት ተገቢውን ጥረት ማድረግ አለባቸው።

በጋብቻ ውስጥ የሚፈጠር አለመግባባት ቅድሚያ በተጋቢዎች እና በቅርብ ሰዎች/ቤተሰቦች እንድፈታ ይመከራል በዝው አግባብ ካልተፈታ በባህል መሪዎች በጎሳ መሪዎች በተመረጡ ሽማግሌዎች ይፈታል ይመከራል ተበዳይ ይካሳል በዳይ ደሞ እንድክስ ይደረጋል ።
በዝህ ጥፋት ያልተመለሰ እና ተደጋጋሚ በደል ያደረሰ ወገን በአካባቢው ወራፎ ይከለከላል ።

✍️ፍትህ የሚሰጡ ወይም የሚወስኑ ሙግት የሚሰሙ የሚያስታርቁ ቅጥር የሚፈፅሙ የሚያስተዳድሩ የሚያዋውሉ የመንግስትም ሆነ የባህል ሰዎች ተገልጋይ ማጉላላት ቀጠሮ ማብዛት የተወገዘ ተግባር ነው።
✍️እጅ መንሻ አይቀበሉ በዝምድና በስልጣን በገንዘብ ወይም በጥቅማጥቅም በማናቸውም መንገድ ፍትህን አያጓድሉ በእውነት እና በማስረጃ ብቻ ተመስሪተው ይወስኑ ሰው የሰራውን የላቡን ብቻ ይውስድ ይጠቀም ያን መጣስ በባህላችን እና በሰማይ አምላካችን ፊት ሀጥያት ነው በህዝባችን ፊት ቆመን ነጋሪት ጎስመን አወግዘናል።
✍️ጊደር ላም በትኛው ሁኔታ የማትወለድ መሆኗን በባለሙያዎች ካልተረጋገጠ በቀር ለእርድ መጠቀም ፈፅሞ የተከለከለ ነው በባህላችን የተወገዘ ነው።
✍️በአካባቢያቸን በሚመረቱ ምርቶች ላይ በአድ ነገር መጨመር ወይም መቀላቀል የምርት ጥራት ማጓደል ጥራት የሌለውን ወይም የተበላሸን ምርት ለግብይት ማቅረብ ያለ በቂ ምክንያት ዋጋ መጨመር በመልካም ስማችን መነገድ ሚዛን መቀነስ እና ማንኛውንም ተገቢ ያልሆነ ነገር መፈፀም በባህላችን መሰረት የተወገዘ ነው።
-በእውነት መንገድ እና የላቡን ትርፍ መብላት የአምላካችን ትዕዛዝ በመሆኑ ልናከብረው ይገባል ።
ይህንን የጣሰ ወራፎ ይከላከላል ከዛሬ ጀምሮ ይህ ድርግት የፀና ይሆናል።

✍️በልማት ላይ የተደነገገ አዋጅ
✍️በንጉሡ አስተዳደር ክልል ውስጥ የማይታረስ ፆም የሚያድር መሬት እንድሁም ከስራ ውጭ የሚሆን ጉልበት አይኑር።
✍️አርሶአደር ለምግብ ዋስትና ቅድሚያ በመስጠት አምርቶ የራሱን ፍጆታ የመሸፈን እንድሁም ትርፍ ምርት አምርቶ ለገበያ ማቅረብ ይጠበቅበታል ።
✍️አርሶአደሩ በየዓመቱ እንሰት ችግኝ አፍልቶ የመትከል ግዴታ አለበት ክትትል ይደረግበታል ካልተገበረ ይመከራል ለወራፎ ይቀርባል ።
✍️በሸካ ባህል መሰረት የአርሶአደር ቤት በእንሰት እና በአትክልት የተከበበ መሆኑ ይታወቃል ፈፅሞ ቤቱ ገላጣ ሜዳ መሆን የለበትም።
✍️ማንም ሰው ከሰንበት እና ከበዓላትጨውጭ በስር ሰዓት ከስራ ውጭ በመሆን አልባለ ቦታ መገኘት በባህላችን የተከለከለ ነው።
✍️የአካባቢውን ንፅህና ደህንነት የማይጠብቅ ቆሻሻን ያለቦታ መጣል የለበትም ።
✍️ማንም የከተማ ሆነ የገጠር ነዋሪ በመንግሥት የልማት እና የሰላም ስራዎች ላይ በንቃት ካልተሳተፈ የተወገዘ ይሁን
✍️በተፈጥሮ ሀብቶች በቅርሶች እና በታሪካዊ ቦታዎች በህግ እና በባህል የተከለከሉ ክልከላዎችን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለበት።
✍️የተከለከለ ጥብቅ ደን መጨፍጨፍ ማቃጠል ወደ ተከለለ ቦታ የእርሻ ይዞታ ማስፋፋት በባህላችን የተወገዘ ነው።
✍️የወንዝ ዳርቻዎችን ሆራዎችን/እዮ
ረግረጋማ ቦታዎችን ዋሻዎቾን እና ታሪካዊ ቦታዎችን ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎችን ማረስ ማራቆት የተወገዘ እና የተከለከለ ተግባር ነው።
✍️ፈቃድ ሳይሰጥ የህዝብ መሬት በጉልበት መያዝ ማስፋፋት በባህላችን የተወገዘ ነው።
✍️መስረቅ ከሰረቀ ጋር መተባበር በማንኛውም መንገድ መርዳት የራሱ ያልሆነውንና ወድቆ የተገኘውን ንብረት አንስቶ መጠቀም በፍጹም የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።ይህንን ያደረገ ከወራፎ ውጭ ይሆናል
✍️ታላላቅ አባቶቻችንን ,እናቶቻችንን ,የመንግስት ባለስልጣናትን,አስተማሪዎችንን,የሀይማኖት አባቶችንን,የባህል መሪዎቻችንን,ተሿሚዎችንን እንድሁም ለሎች ክብር የሚገባቸውን የማክበር ቅድሚያ የመስጠት ተነስቶ የማስቀመጥ የመታዘዝ የባህላችን ምሶሶ በመሆናቸው የማክበር የባህል ግዴታ አለብን ያለማክበር ያስረግማል ለትችት ያቀርባል ወራፎም ቦታ ያሳጣል የተወገዘ ነው።
✍️በሀሰት መክሰስ በሀሰት መመስከር ማስረጃ መደበቅ በውሸት መማል በባህላችን የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።
✍️የራስን ያልሆነ መሻት በባህላችን የተወገዘ በመሆኑ
በመተት ,በጥንቆላ ,በአስማት በባዕድ አምልኮ ማሰራት እሄን መፈጸም የተወገዘ ይሁን ይንን የሚያደርግ የተረገመ ይሁን
✍️ተበድሮ መካድ ወይም ያለመመለስ ተዋውሎ,ሸጦ ቃል መቀየር መካድ ,ማስካድ የተወገዘ ነው።
✍️በሀዘን ለቅሶ ግዜ የተከለከለ ተግባር
-ከቡና እና ቆሎ ውጭ መስተንግዶ ማዘጋጀት እና አስክሬን ማቆየት የተወገዘ ነው።
-ማቅ መልበስ ለድግስ ብሎ የሟች ንብረት መሸጥ የተወገዘ ነው።
✍️የተበደለ ሰው ለበዳይ ዘመድ ለሽማግሌዎች ወይም ለባህል መሪዎች የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

ይህንን ወደ ጎን በመተው በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ቡና መቁረጥ ለሎች ንብረቶችን ማውደም ቤት ማቃጠል እንስሳት ላይ በቀል መወጣት ተደራጅቶ ሰው መደብደብ, መግደል, አካል ጉዳት ማድረስ በደልን በበደል መካስ መሰል ተግባር የተከለከለ ነው ።

4ሺህ ተከታይ እናመሠግናለን🙏ጥረታችን የሸካን ህዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሮን ማስተዋወቅ ነው!ይህ   ድረ ገፅ የሸካን ህዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሮን የሚናስተዋውቅበት የሸካ ህዝቦች ገፅ ...
16/09/2024

4ሺህ ተከታይ እናመሠግናለን🙏
ጥረታችን የሸካን ህዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሮን ማስተዋወቅ ነው!

ይህ ድረ ገፅ የሸካን ህዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሮን የሚናስተዋውቅበት የሸካ ህዝቦች ገፅ ነው።

ተቋርጦ የነበረው የሸካቾ ንጉሳዊ አስተዳደር ታሪክ፣ የተለያዩ የብሄሩ ባህላዊ ሙዝቃዎች፣ የተፈጥሮ ደኖችንና ስለ ደኑ ባህላዊ አጠባበቅ ፣ፏፏቴዎችንና ዋሻዎችን እንዲሁም ሰው ሰራሽ ቅርሶችን በራሳችንና ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች እየወሰደን በገፃችን በተከታታይ ሽፋን ስሰጥ ቆይቷል።

ተቋርጦ የነበረው የሸካቾ ንጉሳዊ አስተዳደር 17ኛው ንጉስ ተቺ ቀጆች ተሰይመው ታሪካዊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል። እኛ ደግሞ እነዚህንና ሌሎችን ስራዎች ባለን አቅም እየመዘገብን ለትውልድ እናስቀምጣለን።

በመጨረሻም ይህን ጽሁፍ የሚያነብ ማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የሆነhttps://www.facebook.com/bitewview ተከታይ በመሆንና ለሌሎችም ሼር በማድረግ በአካባቢውም ሆነ ከአካባቢ ውጭ ሰፊ ሽፋን እንድኖረው ለባህላችን ሚናችንን እንወጣ። አመሠግናለሁ🙏

ዋማ ድጎና ማሽቃረ ነቴ ባሮይስ በድቶቴ!
11/09/2024

ዋማ ድጎና ማሽቃረ ነቴ ባሮይስ በድቶቴ!

12/01/2023
  ቻናላችንን subscribe በማድረግ ይቀላቀሉ።https://youtube.com
10/01/2023

ቻናላችንን subscribe በማድረግ ይቀላቀሉ።
https://youtube.com

Address

Masha
Ilubabor

Telephone

+251917345022

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Sheka posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share