Visit Lalibela

Visit Lalibela Lalibela is one of the highest tourist destination in Ethiopia 0921264565

26/01/2024

well come

ላስታ ቅዱስ ላሊበላ የምድራችን ዕንቁ ስፍራsaint Lalibela monasteries the center of holy place
09/01/2024

ላስታ ቅዱስ ላሊበላ የምድራችን ዕንቁ ስፍራ
saint Lalibela monasteries the center of holy place

ሙሽራዋ ባህር ዳር ባህር  ጥምቀትን በአዲስ ቦታ በሀይማኖታዊ  አስተምህሮ መስረት ***ታላቅ የምሥራች ነው።  የባህርዳር የጥምቀተ ባሕር ቦታ ከመስቀል አደባባይ ወደ ወደጣና ሐይቅ ተዛውሯል።...
16/01/2023

ሙሽራዋ ባህር ዳር ባህር ጥምቀትን በአዲስ ቦታ በሀይማኖታዊ አስተምህሮ መስረት
***
ታላቅ የምሥራች ነው። የባህርዳር የጥምቀተ ባሕር ቦታ ከመስቀል አደባባይ ወደ ወደጣና ሐይቅ ተዛውሯል።

ልዩ ቦታው ከዲፖ ወደ ቅዱስ ሚካኤል በሚወስደው አስፓልት ላይ ከሽምብጥ ቅዱስ ሚካኤልና ከአቫንቲ ሆቴል መካከል በሚገኘው ጣና ዳር ሆኗል።

ለዘንድሮው ጥምቀት ማክበሪያ የሚሆን ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል፣ ጥምቀተ ባሕሩም ተዘጋጅቷል። አዲሱ ባሕረ ጥምቀት ወደፊት ያለው ዲዛይን ሲያልቅ በፎቶ የምትመለከቱት ገፅታ ይኖረዋል። በውስጡ በጣም በርካታ አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።

ልደትን በላስታ በላልዬ ምድርቅኔ ማህሌቱን  ቤዛ  ኩሉ ሳከበርደግሞ ለጥሞቀቱ እንገናኝ  ጎንደር በአርባ አራቱ ደብር በቅዱሳን ሀገር
14/01/2023

ልደትን በላስታ በላልዬ ምድር
ቅኔ ማህሌቱን ቤዛ ኩሉ ሳከበር
ደግሞ ለጥሞቀቱ እንገናኝ ጎንደር
በአርባ አራቱ ደብር በቅዱሳን ሀገር

13/01/2023

ገና ልደት ላሊበላ
2015 ዓ.ም

ላስታ ቅዱስ ላሊበላ የገና ልደት በዓል አከባበር የ2015 ዓ.ም
12/01/2023

ላስታ ቅዱስ ላሊበላ
የገና ልደት በዓል አከባበር
የ2015 ዓ.ም

ላስታ ሆይ ከሀገራት ሁሉ አንች በለጥሽ በውስጥሽም ጥበብን ወልድሽ ዕምነት ጥበብ ቅርስ ++++++++++++++++++ሀገሬ ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም ታሪክና ዝናሽ ይነገር ለዓለም በግርማ ሞገስ...
09/01/2023

ላስታ ሆይ ከሀገራት ሁሉ አንች በለጥሽ
በውስጥሽም ጥበብን ወልድሽ
ዕምነት ጥበብ ቅርስ
++++++++++++++++++
ሀገሬ ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም
ታሪክና ዝናሽ ይነገር ለዓለም
በግርማ ሞገስሽ ኑሪ ለዘላለም
በብራና ይፃፍ ስምሽ በቅዱሳን
ድንቅ ልጆች አሉሽ የዓለም ጠቢባን
ቅዱስ ላሊበላ ካህን ወንጉስ
ደግሞም ጥብበኛ ሃናፄ መቅደስ
ያውና ይታያል ቤተ ጊዮርጊስ
የአለም ድንቅ ታሪክ የኢትዮጵያ ቅርስ
ቤተ ማርያም ብየ ገባሁ መድሃኒዓለም
ጥበብህ ዕፁብ ነው ልመሰክር ለዓለም
የምስጢራት ሀገር ላስታ ደበረ ሮሃ
በአሸተኗ ማርያም
ደግሞም በይምርሃ
አሽተን ናአኩቶላአብ ብልባላ ጊዮርጊስ
አስደናቂ ቦታ ይምርሃ ክርስቶስ
የጥበብ ሀመልማል የጥበብ ውቅያኖስ
ዛሬም ምስክር ነው ታምረኛው መቅደስ
ድብር ገዳማቱ በጥበብ ተከቦ
እንደ ግምጃ ካባ እንደ ወርቀ ዞቦ
ዘወትር ቅዳሴው ዘወትር ማዕጠንቱ
ምድራዊ ገንት ነው ሮሃ መሬቱ

በ #አበበ አበራ

ቅዱስ ላሊበላ ዳግማዊት ኢየሩሳሌም          +++++++የምስጢራት ሀገር ላስታ ደበረ ሮሃበአሸተኗ ማርያም ደግሞም በይምርሃአሽተን ናአኩቶላአብ ብልባላ ጊዮርጊስ አስደናቂ ቦታ ይምርሃ ክር...
05/01/2023

ቅዱስ ላሊበላ ዳግማዊት ኢየሩሳሌም
+++++++
የምስጢራት ሀገር ላስታ ደበረ ሮሃ
በአሸተኗ ማርያም
ደግሞም በይምርሃ
አሽተን ናአኩቶላአብ ብልባላ ጊዮርጊስ
አስደናቂ ቦታ ይምርሃ ክርስቶስ
የጥበብ ሀመልማል የጥበብ ውቅያኖስ
ዛሬም ምስክር ነው ታምረኛው መቅደስ
ድብር ገዳማቱ በጥበብ ተከቦ
እንደ ግምጃ ካባ እንደ ወርቀ ዞቦ
ዘወትር ቅዳሴው ዘወትር ማዕጠንቱ
ምድራዊ ገንት ነው ሮሃ መሬቱ
ዕውቀትና ጥበብ ታሪክ ምስክሩ

30/11/2022
ላስታ ላሊበላ ሮሃ ሰፈር/ ገጠርጌፎቶ በምንሊክ ፋንታሁን2015ዓ.ም
21/11/2022

ላስታ ላሊበላ ሮሃ ሰፈር/ ገጠርጌ
ፎቶ በምንሊክ ፋንታሁን
2015ዓ.ም

21/11/2022

የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ብዓል በቅዱስ ላሊበላ በደብረ ሮሐ ሊቃውንተ ካህናት ህዳር 12/2015

17/11/2022
ኢትዮጵያን ከመሩ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ማዕረግ ቅዱስ ተብለው ከሚጠሩት አራቱ የዛግዌ ነገሥታት አንዱ የሆነው የቅዱስ ነአኩቶለአብ  ዓመታዊ ክብረ በዓል ...
12/11/2022

ኢትዮጵያን ከመሩ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በቅድስና ማዕረግ ቅዱስ ተብለው ከሚጠሩት አራቱ የዛግዌ ነገሥታት አንዱ የሆነው የቅዱስ ነአኩቶለአብ ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሯል በየ አመቱ ህዳር 3 ቀን የሚከበረው በዓል ቅዱስ ናአኩቶ ለአብ በዚህ ቀን እራሱ ባነፀው የዋሻ ውስጥ ጥንታዊ ቤተመቅደስ የተሰወረበትን ቀን ምክኒያት በማረግ በየ አመቱ ህዳር 3 ቀን እንደ ገና እንደ ጥቅምት 19 ቀን ይምርሃ ገብርኤል አመታዊ ክበረ በዓል ሁሉ ይህች ቀንም በ ቅዱስ ናአኩቶ ለአብ ጥንታዊ ገዳም በድምቀት ተከበራለች።
የቅዱስ ነአኩቶለአብ ገዳም ላሊበላ ከተማ ለመድረስ 6 ኪ.ሜ ሲቀር የሚገኝ ከግዙፍ ተራራ ስር የተመሰረተ የዋሻ ውስጥ ገዳም ነው።
የቀዱስ ናአኩቶለአብ ረዴት በረከት ቃልኪዳን ከሁላችንም ጋር ይሁንልን።
በረከቱ ይደረሰን።
2015 ዓ.ም ላሊበላ ኢትዮጵያ

02/11/2022
አዲስ አመት አሁድ ገበያው ቅዳሜ     ላስታ ላሊበላ የ 2015ዓ.ም አዲስ አመት ዋዜማ     ቅዳሜ  ገበያ  ላሊበላ ድምቅምቅ ያለ የገበያ ቀን በያላችሁበት ሸጋ ቅዳሜ ይሁንላችሁ ጳጉሜን 5...
10/09/2022

አዲስ አመት አሁድ
ገበያው ቅዳሜ
ላስታ ላሊበላ
የ 2015ዓ.ም አዲስ አመት ዋዜማ
ቅዳሜ ገበያ ላሊበላ
ድምቅምቅ ያለ የገበያ ቀን
በያላችሁበት ሸጋ ቅዳሜ ይሁንላችሁ
ጳጉሜን 5/2014 ዓ.ም

ጉብኝት ንሀሴ 18/2014 ዓ.ም ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ ከባህር ላይ የታነፀው ዕፁብ ድንቅ ቤተ መቅደስ
24/08/2022

ጉብኝት
ንሀሴ 18/2014 ዓ.ም
ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስ
ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ
በተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ ከባህር ላይ የታነፀው ዕፁብ ድንቅ ቤተ መቅደስ

አቤቱ ፈጣሪ ቀዱስ ሀያል አግዚአብሔር ሆይክብርና ምሰጋና አምልኮና ውዳሴ ከምድር እሰከ አርያም ላንተ ይሁንአይኔ ዓለም አየ እግሬ ደረሶ የ ድንጋ ውጋግራ የ ድንጋይ መሰሶ እንኳን ለእመቤታችን...
22/08/2022

አቤቱ ፈጣሪ ቀዱስ ሀያል አግዚአብሔር ሆይ
ክብርና ምሰጋና አምልኮና ውዳሴ ከምድር እሰከ አርያም ላንተ ይሁን
አይኔ ዓለም አየ እግሬ ደረሶ
የ ድንጋ ውጋግራ የ ድንጋይ መሰሶ
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
የትንሳኤ ዕረገት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
ላሊበላ
ንሀሴ 2014 ዓ.ም

አዲስ ዜናበቅዲስ ላሊበላ ከተማ መብራት ከተቋረጠ አንድ አመት ከ አንድ ወር በላይ ያለፈ ሲሆን 2013 ዓ.ም ሀምሌ ወር  የተቋረጠው ማለት ነውዛሬ በ ጄኔረተር የመብራት አግልግሎት ማግኘት ጀ...
19/08/2022

አዲስ ዜና

በቅዲስ ላሊበላ ከተማ መብራት ከተቋረጠ አንድ አመት ከ አንድ ወር በላይ ያለፈ ሲሆን 2013 ዓ.ም ሀምሌ ወር የተቋረጠው ማለት ነው
ዛሬ በ ጄኔረተር የመብራት አግልግሎት ማግኘት ጀመረች የ አሽንድዬ በዓልን ምክኒያት በማደረግ
አሁን ከምሽቱ 2:00 ስዓት ገደማ በመሀል ከተማዋና በተወሰኑ መንደሮች በፈረቃ በጀኔረተር የ ኤሌክትሪክ መብራት ማግኘት ችለዋል
እንዲሁ በታህሳስ 30/2014 ዓ.ም የ ገና ልደት በዓልን ምክኒያት በማደረግ መብራት በተቋረጠ በ6ኛው ወር ከጄኔረተር የተገኝ የ ሀይል አገልግሎት ለተወሰነ ጊዜ እነደነበረ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ከታህሳስ እሰከ ንሀሴ በ6ኛው ወር ላይ መብራት ማየት ቸለናል
እንግዲሂ የቅዱስ ላሊበላ ከተማ በ አንድ አመት ውስጥ ለሁለት በተለያዩ ጊዚያት ለ አጭር ጊዜና አመታዊ ክበረ በዓልን ምክኒያት በማደረግ ብቻ የመብራት ተጠቃሚ የሆነች ብቸኛዋ ሀገር ላስታ ላሊበላ
ይህን ሁኔታ ስዎች ሁሉ ተገንዘበውት በያሉበት ቦታ ሁሉ ሆነው እንዴት ? ለምን ? የሚሉ ሀሳቦችን እያነሱ ቢነጋገሩባቸው መልካም
ንሀሴ 13/2014 ዓ.ም

አሸንድዬ ማለት ምን ማለት ነው ?አሸንድዬ ማለት አሸንድዬ ነስ መልኩ አረንጓዴ አሽን ክታብ መጠኑ ከ ዶግ የማያነስ ቀጠሉ እንደ ሽንኩርት ቀጠል የሆነ ከስር ወደላይ በቅሎ ከፍ ካለ በኋላ ዘን...
13/08/2022

አሸንድዬ ማለት ምን ማለት ነው ?
አሸንድዬ ማለት አሸንድዬ ነስ መልኩ አረንጓዴ አሽን ክታብ መጠኑ ከ ዶግ የማያነስ ቀጠሉ እንደ ሽንኩርት ቀጠል የሆነ ከስር ወደላይ በቅሎ ከፍ ካለ በኋላ ዘንፍልፍል ብሎ የሚሄድና ፍሬ የሚያፈራ አበባው እንደ ፍኽሶ ነው ሴቶች በመቀነታቸው እየሰኩ ይታጠቁታል የ ቡሄ ጊዮርጊስ ጀምሮ እሰከ መሰቀል ድረስ የበጌ ምድር ፤ የላስታ ፤ የዬጁ ሴቶች አሸንድ እኽ አሸንዳ አበባ እርግፍ እንደ ወለባ እያሉ ይዘፍኑበታል።

ምንጭ አምሓረነት መፅሐፍ
ከሳቴ ብርሃን ተሰማ 1951 ዓ.ም
ንሀሴ 7/2014 ዓ.ም

ውድ የ ሀገሬ ልጆች እንኳን ለ 2014 ዓ.ም የ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የ ፍለስታ ፆም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።ያለፈው አመት በላስታና በዙሪያው የሚገኙ አካባቢዎች የፍልሰታን...
07/08/2022

ውድ የ ሀገሬ ልጆች እንኳን ለ 2014 ዓ.ም የ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የ ፍለስታ ፆም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ያለፈው አመት በላስታና በዙሪያው የሚገኙ አካባቢዎች የፍልሰታን ፆምና ሱባኤ በተረጋጋ ሁኔታ ለማሳልፍ አሰቸጋሪ ወቅት መሆኑ የሚታወስ ነው ነገር ግን በዚያን ወቅት በተለይ የቅዱስ ላሊበላና የ አካባቢው ኗሪዎች ከወትሮ በበለጠ ሁኔታ በቅዱስ ላሊበላ በ አስራ አንዱም ቤተመቅደሶች በመገኘት የነበረውን አስቸጋሪ ጊዜ በፆም በፀሎት በማስቀደስ ያን መጥፎ ጊዜ በሰላም ለማሳልፍ ችለናል በወቅቱ በየ ቤተክርስቲያናቱ የሚገኘው የስው ብዛት አጀብ ነበር በወቅቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመሂድ ወጭ ሌላ ዕድል ስላልነበረ ሁሉም ሰው ከህፃን እሰከ አዋቂ ቤተክርስቲያን በማዘውተር ወቅቱን በዚህ ሁኔታ ማሳለፍ ተችሏል። ነገር ግን ሀይማኖታዊና ባህላዊ አሽንድዬ በዓላችን ማክብር አልቻልንም ።
በዚህ አመት ደግሞ ያለ ሰቀቀን በነፃነት እንደተለመደው ሱባዔያችን በሰላም ጀምረናል።

ታዲያ ግን በዚህ አመት የመ
ማይቀርበት አሽንድዬ ላስታ ላሊበላ በድምቀት ይከበራል።
በ 2013 ዓ.ም ይህ ውብና ተናፋቂ ሀይማኖትዊ የ አሸንድዬ በዓል ማክበር ያልተቻለበት ወቅት አንደነበር የሚታወስ ነው በዚህ አመት ግን የባለፈውን አመትም ጭምር ድርብ አሸንድዬ ላስታ ላሊበላ በጉጉትና በናፍቆት የሚጠበቀው ውብ ድንቅ በዓል በድምቀት ይከበራል። የሻደይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓል ከነሐሴ 16 ጀምሮ ሻደይ በሰቆጣ ሶለል በቆቦ አሸንድዬ በላስታ ላሊበላ ይከበራል እንዳት ቀሩ
በ አንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው ብሂሉ ።
ንሀሴ 16 ቀን የ እመቤታችን ትንሳኤ በዓል ቅዳሴው በቤተ ማርያም ይከናወናል ቀጥሎ የ ቅዱስ ላሊበላ ሊቃውንት መንፈስን የሚያድሰው ማህሌት በቤተ መድሃኔ ዓለም አውደምህረት ይከናወናል ቀጥሎ እዛው ላይ አሸንድዬ ሀይማኖታዊ በዓል በቅዱስ ላሊበላን ደብረ ሮሃ ማህብረ ቅዱሳን እሴት እህቶቻችን ይቀርባል
።ከዚያ ቡሃ የላስታ ውብ እህቶቻችን እንደ እድሜ እኩዮቻቸው በ አንድ ላይ እየሆኑ የ አሸንድዬ ድንቅ ባህላዊ ትውፊታችን በተከታታይ ቀናት ከ ጣዕመ ዜማና ስንኝ ሰነ ግጥም ጋር እያዋህዱ በነፃነት ይቧርቃሉ ይጫወታሉ።
እኔ ይህን አጋራዋችሁ ነገር ግን በ አካል በቦታው
ሆኖ ማየት ከ ቃላት በላይ ነው።
ላስታ ቅዱስ ላሊበላ
ንሀሴ 1/2014 ዓ.ም

ፎቶ ህዳር 22/2014       የቅዱስ ላሊበላ ከተማ ነፃ በወጣች ጊዜና       ወራሪው ሀይል በከተማዋ በነረበት ጊዜ        መህልከተማዋ አደባባይ የተወሰደ ሀምሌ 29/2013 ያች ቀ...
05/08/2022

ፎቶ ህዳር 22/2014
የቅዱስ ላሊበላ ከተማ ነፃ በወጣች ጊዜና
ወራሪው ሀይል በከተማዋ በነረበት ጊዜ
መህልከተማዋ አደባባይ የተወሰደ

ሀምሌ 29/2013 ያች ቀን ለ ቅዱስ ላሊበላና ለአካባቢው ህዝብ እንዲሁም ለመላው የ ኢትዮጵያ ህዝብ ከባድ ድንጋጤ ጭንቀት እንዲሁም ቁጭትና ንዴት ውስጥ እድንገባ የዳረገችን መራራ ቀን ነበረች ።
ምክኒያቱ ደግሞ አሸባሪው የህወሓት ታጣቂና የትግራይ ወራሪ ሀይል ቡድን የ ቅዱስ ላሊበላ ከተማንና አካባቢውን በመወረሩና በመቆጣጠሩ ነበር።
በወቅቱ በ ላሊበላና ከተማና በዙሪያው ባሉ የጦር ግንባሮች የነበረው ልዩ ልዩ የጦር አደረጃጃት ወደ ኋላ ማፈግፈጉንና አካባቢውን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ከተማዋ ሀምሌ 28 ቀን ሌሊት 2013 ዓ.ም በሽብር ተናጠች ሁሉም ነገር ከቁጥጥር ውጭ ሆነ የከተማው ህዝብ በከባድ በድንጋጤና ውዥንብር ወስጥ ወደቀ በ ስዓቱ ሌሊቱ የሚያስፈራ እጅግ ቀዝቃዛና ከባድ ዝናብ እየዘነበ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ፍፅም ሰላማዊና ያልታጠቁ ሰዎች ማለትም ህፃናቶች ነፍሰ ጡር እናቶች አራስ የወለዱ እናቶች ለጋ ወጣቶች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በዚያ ከባድ ጨለማና ዝናባም ሌሊት ከተኛበት ቤቱ ወጥቶ በዱር በገድል በውሃ ሙላት በወንዝ በጭቃ እንዲከራተትና በዝናብ ቤታቸውን ለቀው በረሃ ላይ እንዲያደር ተገደዱ ምክንያቱ ደግሞ ቀኑ በሰላም ወሎ በመሸም ጊዚ ሌሊቱም ሰላም ነው ተብሎ ነበር ነገር ግን ሰላምን የማያውቀው አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ታጣቂ ሀይል ቡድን የከተማዋንና የህዝቦችን ሰላም በመንሳት በሀምሌ በክረምቱ ሌሊት ታሪክ ይቅር የማይለው ሽብር በመፈፀም ያልታጠቁ ፍፁም ሰላማዊ ሰዎች ከ ሞቀ ቤታቸው ወጥተው በ ዱር በገደል በወንዝ በተራራ በሸሎቆና በጭቃማ ስፍራ ስደትና ሰቃይ እንዲደርስባቸው አደርጓል ። በዚያ ቀን ከሁሉም በላይ ሰቃዩና እንግልቱ በርትቶ የነበረው አራስና ጨቅላ ህፃናት ታቅፈው በነበሩ እናቶች በነፍሰ ጡርና በህፃናቶች ላይ የደረሰው እንግልት እጅግ ያማል እጅግ ያበሳጭ ነበር እንግዲህ የ ከተማዋ ህዝብ ከ ህዋህት ወራሪ ሀይል ጥቃት ለመዳን በሌሊት ሸሸቶ በጫካ አድሮ በነጋ ጊዜም ሀምሌ 29/2013 ዓ.ም የወራሪው ሀይል ታጣቂ አንድም ወደ ከተማዋ አልደረሰም ነበር። ህዝቡም ይህን ባየ ጊዜ በጣም አዘነ ተቆጨ ምክኒያቱም በዚያ ሌሊት በካድ መደናገጥና መሸበር መንፈስ ከተኛበት ቤቱ ወጥቶ ዱር እንዲሸሸ ያደረገው ከ አራት ስዓት አካባቢ ጀምሮ በገነተ ማርያምና በአካባቢው የነበረው የ አማራ ልዩ ሀይል ሚሊሻው አጠቃላይ ግንባር ላይ የነበረው ሀይል ከተማዋን አቋርጦ ሲወጣ በማየቱ ነው ።በስዓቱም ምንም አይነት ጦረነትም ሳይካሀድ ምንም አይነት ተኩስ አልነበረም ለዚያም ነቀር የከተማው ህዝብ በስዓቱ የ ህወሃት ታጣቂ ሀይል ቡድ የት ቦታ እንደደረስ ለማወቅ አልልቻለም ነበር ገነተ ማርያም ይደረስ ናኩቶ ለአብ አካባቢ ይደረስ በትክከል የት ቦታ ላይ እነደነበረ ለ ማወቅ ችግር ነበር
ሌሊት ነው ጨለማ ነበር በከተማዋ መብራት የለም ከባድ ዝናብ እየጣለና አየዘነበ ነበር።ብቻ በቦታው የነበረው የ ጦር ሰራዊት ከአካባቢው ሲወጣ አሸባሪው ሀይልም ወዲያውኑ ከተማዋን የተቆጣጠር ነበር የመስለው ነገር ግን ወራሪው ሀይል ገነተ ማርያም ማዶ ተከዜ ወንዝ ሳይሻገር ነበር ያደረው ነገር ግን ወራሪው ሀይል ሀምሌ 29 ቀን 20 13 ዓ/ም ከገነተ ማርያምና ኩልመስክ አካባቢ ተነስቶ ከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ወደከተማዋ መግባት ጀመረ ከዚያ ሰዓት ጀምሮ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ።
ሆኖሞ ሀምሌ 29/2013 ዓ.ም ያሳለፍንው ቆጭትና ሀዘን እንዲሁም ንዴት ብስጭት በ ህዳር 22/2014 ዓ.ም በነበልባሉ በ አማራ ልዩ ሀይል በጀግናው ፋኖ ሚሊሻው ድንቅ ጀግንነት ወራሪውን ሀይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ከሞት የተረፈው ላስታንና አካባቢውን ለቆ ለመሂድ ተገደደ የ ከተማዋና የ አካባቢው ህዝብም በዚያ ትውልድ ማለትም በዚያን ወቅት በትግል በጦር ሜዳና በግንባር ላይ ተሰልፎ በነበረው ጀግና ትውልድ ያን የሀዘን ቀን በደስታ በ እልልታ በኩራት ደምስሶታል።
ሁለቱም ቀናት ማለትም ሀምሌ 29/2013 ዓ.ም እና ህዳር 22/2014 ዓ.ም ለ ላሊበላ ከተማና ለ አካባቢው ህዝብ የ ቀንና የሌሊት ያህክል ነው ሰሜታቸው ወይም የስርግና የ ሞት ያህል ነበር ሰሜታቸው
ማለትም 29/2013 ዓ.ም የ ሞት የ ሀዘን ሰሜት ነበር
ህዳር 22/2014 ዓ.ም ደግሞ የ ሰርግ የደስታ ቀን ነበር።
በዚያን ጊዜም ሂዋታቸውን መሰዋዕትነት ከፍለው ከ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሀይል ቡድን ነፃ ላወጡን።
ለ አማራ ልዩ ሀይል
ለ አማራ ፋኖ
ለ አማራ ሚሊሻ
ለ ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዋዊት
እሰከ ዘላለሙ ድረስ ክብር ምስጋና ይደረሳችሁ
የፈፀማችሁት የነፃነት ተጋድሎ በታሪክ ህያው ምሰክር ነው

ስራውን በይፋ ጀመረ አማራ ባንክ ለአካባቢያችን ትልቅ አብርክቶ ይጠበቅበታል። በተለይም እንደ ቅዱስ ላሊበላ አለም አቀፍ ቅርስ መገኛ   ለቅርሳችን መጠበቅና ለከተማችን ትኩረት መሰጠት ከሚገባ...
01/08/2022

ስራውን በይፋ ጀመረ
አማራ ባንክ ለአካባቢያችን ትልቅ አብርክቶ ይጠበቅበታል።
በተለይም እንደ ቅዱስ ላሊበላ አለም አቀፍ ቅርስ መገኛ ለቅርሳችን መጠበቅና ለከተማችን ትኩረት መሰጠት ከሚገባቸው አካላት ጋር በመሆን በከተማችን ውስጥ ትልቅ አስተዋፆ እንዲሚያበርከት ትልቅ ተስፋ አለኝ።!
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር
ቅዱስ ላሊበላ ቅርንጫፍ
ሀምሌ 25/2014 ዓም

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም በመጻፋቸው ስለ ህጻኑ ተፈሪ እንዲህ ይገልፁታል።🤔የራስ[ራስ መኮንን የተፈሪ አባት] ዘመዶች ተፈሪን ለማየት ፈቃድ ከራስ እየተቀበሉ መግባት ይችላሉ። በ...
23/07/2022

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም በመጻፋቸው ስለ ህጻኑ ተፈሪ እንዲህ ይገልፁታል።🤔
የራስ[ራስ መኮንን የተፈሪ አባት] ዘመዶች ተፈሪን ለማየት ፈቃድ ከራስ እየተቀበሉ መግባት ይችላሉ። በተቀር ከተፈሪ ግቢ የውጪ ሰው አይደርስም:: ተፈሪ በጣም ያምራል ፤ ቆንጆ ነው:: ለሚያየው ሰው ሴት ልጅ ይመስላል ፤ ጠጉሩን አሳድገውለት እንደ ሹርባ ያበጁታል ፤ ሹርባውን በቅቤ ይቀቡለታል አብደላካኒ ጥብቆ ያለብሱታል:: ምንጊዜም ካንገቱ ላይ መስቀል በወፍራም ማተብ ተንጠልጥሎ ይታያል።

ተፈሪን ራስ ያለመጠን ይወዱታል:: ከቶ አባት ልጁን ሲያፈቅር ከሳቸው የበለጠ ለመሆን ይችል አይመስለኝም። የሳቸው ፍቅርም ብቻ የሚበቃው አይመስላቸውም ፤ ሐረር፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ በሙሉ እንድትወደው ያስባሉ።
ተፈሪ በባሕሪው ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ እንደ ዐዋቂ ሰው ነው:: እንደ ልጅ አይደለም። ጭምት፣ አስተዋይና ዝምተኛ ነው። ሁል ጊዜ ከንፈሮቹን ፈልቀቅ ያደርጋል። መንከትከት፣ መቅበጥ፣ መጮህ አይፈቅድም።

አባቱ የልጃቸውን ባሕርይ እየተመራመሩ፣ "ይገርማል ፤ ምን ዐይነት ሰው ይወጣው ይሆን?"🤔 እያሉ ዘወትር ይናገሩ ነበር:: ባንዳች ምክንያት ያኮረፈ እንደሆነ፣ ከሰው ጋራ, ባንዳች ምክንያት ያኮረፈ እንደሆነ፣ ከሰው ጋራ ሳይነጋገር፣ ምሳውን ሳይበላ ጦሙን ይውላል፣ ስለዚህ ተፈሪን ላለማስቀየም ራስ ይጠነቀቁ ነበር።


እንኳን ተወለዱልን አባታችን 🙏🙏🙏

Address

Abebeabera2010@gmail. Com
Lalibela

Telephone

+251921264565

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Lalibela posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Visit Lalibela:

Videos

Share