Sheka Zone Tourist Attraction & Information Center

Sheka Zone Tourist Attraction & Information Center Come and visit the Green land of Sheka, south west Ethiopia 🇪🇹🌲

Come and visit the hidden treasures of Sheka!🌴
10/01/2025

Come and visit the hidden treasures of Sheka!🌴


31/12/2024
29/12/2024

የ2017 ዓ.ም የባህል ፌስቲቫል
ሸካ ዞን
ማሻ
የሸካቾ ብሄር ባህላዊ ሙዝቃና ዉዝዋዜ📸

29/12/2024
''ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለአንድነታችንና ለሰላማችን'' በሚል መርህ ቃል በሸካ ዞን በሚገኙ ሶስት ወረዳዎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች መካከል የባህል ስፖርተኞችና የባህል ፌስቲቫል ውድድር በማ...
28/12/2024

''ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለአንድነታችንና ለሰላማችን'' በሚል መርህ ቃል በሸካ ዞን በሚገኙ ሶስት ወረዳዎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች መካከል የባህል ስፖርተኞችና የባህል ፌስቲቫል ውድድር በማሻ ከተማ መካሄድ ጀምረዋል ።

ውድድሩ እየተካሄደ የሚገኘው የሸካ ዞን ስፖርት ምክር ቤት ከዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ጋር በመሆን ነዉ ።
*********
የዘንድሮው የ2017 የሸካ ዞን የባህል ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ባህላዊ ስፖርቶቻችን ለአንድነታችንና ለሰላማችን በሚል መርህ ቃል እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል ።

በዚህም በዞኑ የሚገኙ ሶስት ወረዳዎችና ሁለት ሁለት ከተማ አስተዳደሮች መካከል በአስራ ሶስት የስፖርት አይነቶች በማሻ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም ውድድር መካሄድ ጀምረዋል ።

በውድድር መረሃ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት
የሸካ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊና የዞኑ ስፖርት ምክር ቤት ተወካይ አቶ ዳንኤል አድራሮ ክልላችን እንደ አዲስ ከተቋቋመ ወድህ ለተከታታይ ሶስት ዓመት በባህል ስፖርት ውጤታማ እንደሆነ በመግለጽ ለቀጣይነቱ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጾኦ እንድያበረክት ኃላፊው ጥሪያቸውን አስተላልፏል።

የማሻ ከተማ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መልካም እንደሻው ስፖርት የሠላም ችቦ የሚለኮስበት የአንድነትና የወዳጅነት ስሜት የሚንፀባረቅበት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚጠናከርበት ነው ብለዋል።

የሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምርያ ተወካይ አቶ ብርሀኑ አያሾ በዞናችን ባህላዊ ስፖርቶች ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ሆኖ ለትውልድ እንድተላለፍ ለማድረግ የባህል ስፖርቶች ውድድርና ፌስቲቫል ውድድር ማካሄድ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

በውድድሩ እያንዳንዱ ሰዉ ባህሉንና ወጉን እንድሁም ትውፊቱን እንዲያውቅና እንዲያስተዋውቅ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑም ባለፈ የወንድማማችነትና እህታማማችነትን ስሜት የሚያሳድግ መሆኑንም ገልፀዋል ።

የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴዎች በበኩላቸው በቀጣይ በክልል ደረጃ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በሚካሄደው የ2017 ዓ.ም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር ላይ ዞኑን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎችን ለመመልመል ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።

ውድድሩ ለተከታታይ አምሰት ቀናት በማሸ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም እንደምካሄድም ተገልጾዋል።

የመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የዞን፣ የወረዳ ፣የከተማ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ስሆን የዘንድሮ የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር በ218 ተወዳዳሪዎች መካከል በአስራ አንድ ስፖርት አይቶች እንደሚደረግም ተጠቁሟል ።

FM

የሸካ ዞን የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር ከታህሣሥ 19_25/2017 ዓ.ም ድረስ  በማሻ  ከተማ ሁለገብ  ስታዲየም እንደሚካሄድ የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታውቋል...
27/12/2024

የሸካ ዞን የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር ከታህሣሥ 19_25/2017 ዓ.ም ድረስ በማሻ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም እንደሚካሄድ የዞኑ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታውቋል።
***********
ፌስቲቫሉ በዞኑ ውስጥ በሚገኙ በሶስት ወረዳና ሁለት ከተማ አስተዳደር የባህል ልዑካን ቡድኖች በተገኙበት ይደረጋል።

የባህል ፌስቲቫልና የባህል ስፖርት የማኅበረሰቡን ባህልና ማኅበራዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅና ትስስር በማጠናከር ፣ የሀገር በቀል ዕውቀትን ለማልማት እንዲሁም ለዕደጥበብ ውጤቶች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና አለዉ፡፡

የዘንድሮ የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር በሻህ ፣በቡብ፣ በኮርቦ፣ በገበጣ፣ በትግል ፣በቀስት ፣ በፈረስ ሽርጥ፣ በፈረስ ጉጊስ ፣ በባህላዊ ጭፈራዎች እንድሁም በባህላዊ ምግብ ዝግጅትና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ጋር በደማቅ ሁኔታ ይደረጋል።

በክልል ደረጃ በኮንታ ዞን በአመያ ከተማ በሚካሄደው የ2017 ዓ.ም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ዉድድር ላይ ዞናችንን ወክሎ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎችም ይመለመላሉ።

የባህል ስፓርቶች እና የባህል ፌስታቫል ውድድር እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በማሻ ሁለገብ ስቴድየም ለሕዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚካሄድ መምሪያዉ አስታውቋል፡፡

ከካፋ እና ሸካ ጥቅጥቅ ደኖች እስከ ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክኢትዮጵያ ለምለም ምድር ናት ለሚለው አባባል ሁነኛ ማሳያው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ነው፡፡ ክልሉ በሁሉም አቅጣጫ...
16/12/2024

ከካፋ እና ሸካ ጥቅጥቅ ደኖች እስከ ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ

ኢትዮጵያ ለምለም ምድር ናት ለሚለው አባባል ሁነኛ ማሳያው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ነው፡፡ ክልሉ በሁሉም አቅጣጫ ውብ የተፈጥሮ ፀጋን የተላበሰ ስለመሆኑ በሚያሳብቁ አረንጓዴ እጽዋት የተሞላ ነው፡፡

በክልሉ የሚገኙት ካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ኮንታ ዞኖች አረንጓዴ የለበሱ ድንቅ የተፈጥሮ ባለቤቶች ናቸው፡፡ ይህም ክልሉን ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ አድርጎታል፡፡

በአጠቃላይ በክልሉ ከ5 ሺህ በላይ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች እንዳሉና ከእነዚህም ውስጥ እንደ ክልል እስካሁን 1 ሺህ 100 የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች በጥናት የተለዩ፣ እንዲሁም ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ ስለመሆናቸው የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከፍተኛ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራ እንዲሆን ያስቻለው አረንጓዴነቱ (በእጽዋት መከበቡ) ስለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ አረንጓዴ ያስባለው ደግሞ ዓይንን የሚማርኩ እና መንፈስን የሚያድሱ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች በብዛት መኖራቸው ነው፡፡

ለዚህም አብነት ሆኖ የሚነሳው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣ የትምህርትና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው የሸካ ጥብቅና ጥቅጥቅ ደን ነው፡፡ የሸካ ጥብቅና ጥቅጥቅ ደን (Biosphere) በውስጡ ጫካ፣ የቀርከሃ ዛፎች፣ በውሃ ዙሪያ የሚገኝ ርጥብ መሬት፣ የእርሻ መሬት፣ እንዲሁም የገጠር እና የከተማ ሰፈራ አካባቢዎችን የያዘ ነው፡፡

ከቀዝቃዛ ጀምሮ እጅግ እርጥበታማ የደጋ ስፍራዎች እስከ ሞቃታማ ቆላ ድረስ የአየር ጠባይ የሚስተናገድበትም ነው፡፡ የዩኔስኮ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የሸካ ጥብቅ እና ጥቅጥቅ ደን አጠቃላይ 238 ሺህ 750 ሄክታር መሬት ይሸፍናል። የበርካታ እንስሳት እና እጽዋት ዝርያዎች መኖሪያም ነው፡፡

ከ300 በላይ ትላልቅ እጽዋቶች፣ 50 አጥቢ እንስሳት፣ 200 አዕዋፋት እና 20 የእንቁራሪት አስተኔ ዝርያዎች መገኛም ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ብርቅዬና ሀገር በቀል የሆኑ 55 የእጽዋት፣ 10 አዕዋፋት እና 38 የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው እንስሳትና እጽዋት ዝርያዎች እንደሚገኙም ዩኔስኮ በድረገጹ አስፍሯል፡፡ አረቢካ ቡና፣ ቁጥቋጦ እና ሌሎች የእጽዋት ዝርያዎችም በደኑ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

በእንስሳት በኩል በውሃ ውስጥም በየብስም የሚኖሩ፣ ትላልቅና ትናንሽ አጥቢዎች፣ ተሳቢዎች እና የአዕዋፋት ዝርያዎች መኖሪያቸውን በደኑ አድርገዋል፡፡

ጃርት፣ የተለያዩ የዝንጀሮ ዝርያዎች፣ የአፍሪካ ጎሽ፣ አንበሳ፣ ነብር፣ የአፍሪካ ጥርኝ፣ የኢትዮጵያ ጥንቸል፣ የአቢሲኒያ ባለጥቁርና ቢጫ ቀለም ወፍ እና ግንደ-ቆርቁር ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ዩኔስኮ የሸካ ጥብቅና ጥቅጥቅ ደንን የመዘገበው በአውሮፓዊያኑ 2012 ነው፡፡

ከሸካ በተጓዳኝ የካፋ ጥብቅና ጥቅጥቅ ደን (Biosphere) በዩኔስኮ የተመዘገበ ሌላኛው በክልሉ የሚገኝ የቱሪዝም መዳረሻ ነው፡፡ በካፋ ዞን የሚገኘው ደኑ፣ በዓለማችን ተወዳጅ የሆነውና ው የአረቢካ ቡና መገናኝ ቦታን ያካልላል፡፡

የብዝሃ- ሕይወት መገኛ የሆነው ደኑ፣ ዩኔስኮ እንደመዘገበው 760 ሺህ 144 ሄክታር መሬት ይሸፍናል። 5 ሺህ የተለያዩ ዓይነት እጽዋቶች መገኛም ነው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የተለያዩ ዛፎች፣ ቁጥቋጦዎች እና የጫካ ቡና በስፋት ይገኝበታል፡፡
ከእጽዋት ዝርያዎች መካከል 110 የሚሆኑት ሀገር በቀል ናቸው፡፡ አረቢካ ቡና፣ ኮረሪማ፣ የቀርከሃ ዛፎች እና ሌሎችም የእጽዋት ዝርያዎች በስፋት በደኑ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም 300 የሚጠጉ የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች እንዳሉ ይነገራል፡፡

የለሊት ወፍ፣ አይጠ-ሞጎጥ፣ የተለያዩ የዝንጀሮ ዝርያዎች፣ ጉማሬ፣ ጎሽ፣ አጋዘን፣ ጃርት፣ ከርከሮ፣ ጅብ፣ የጫካ አሳማ፣ አንበሳ፣ ነብር፣ ፍልፈል፣ ጥርኝ፣ ቀበሮ እና ጉሬዛ ከእንስሳቱ መካከል ይገኙበታል፡፡

የካፋ ጥብቅ እና ጥቅጥቅ ደን በፈረንጆቹ ሰኔ ወር 2010 ነበር በዩኔስኮ የተመዘገበው፡፡

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከታደላቸው ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች መካከል የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ አንዱ ነው፡፡ ፓርኩ በዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች መካከል የሚገኝ ነው፡፡ በአጠቃላይ 1 ሺህ 410 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ይሸፍናል፡፡

ከ1 ሺህ 200 እስከ 2 ሺህ 300 ሚሊ ሜትር ዓመታዊ የዝናብ መጠን ይመዘገብበታል፡፡ ሙቀት ደግሞ ከ10 ድግሪ ሴልሺየስ እስከ 29 ድግሪ ሴልሺየስ። ከመጋቢት እስከ መስከረም ወራት ድረስ እርጥበታማ ወቅቶች ሲሆኑ፣ ከታህሳስ እስከ የካቲት ደግሞ ፓርኩ ደረቅ ወቅቶችን ያስተናግዳል፡፡

ፓርኩ ትናንሽ ሃይቆች በውስጡ ሲይዝ፣ ቡሎ፣ ከበሪላ፣ ሽታ እና ጮፎሬ ሃይቆች አብነት ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ በርካታ ወንዞችንም እንዲሁ በውስጡ ይዟል፡፡ ወደ 49 የሚጠጉ ወንዞች ከፓርኩ በመነሳት ወደ ኦሞ ወንዝ ይገባሉ፡፡ የአሳ ዝርያዎች፣ ፍል ውሃዎች፣ ፏፏቴዎች እና ዋሻዎችን የተቸረ ውብ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 37 ዓይነት ትላልቅ አጥቢ እንስሳት እና 237 የአዕዋፋት ዝርያዎች መገኛም ነው። ከአጥቢ እንስሳት መካከል የአፍሪካ ዝሆኖች፣ ጉማሬ፣ ጎሽ፣ አንበሳ፣ ነብር፣ አምባራይሌ፣ የተለያዩ የዝንጀሮ ዝርያዎች እና ከርከሮ ይገኙበታል፡፡

ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ በ1997 ዓ.ም በብሄራዊ ፓርክነት እንደ ተቋቋመ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ፓርኩ የብዝሃ-ሕይወት እና የአስደማሚ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት በመሆኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ዋነኛው ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡
west communications

14/11/2024
የቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ የስራ ዕድል የሚፈጥርና ኢኮኖሚ የሚያመነጭ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ፦ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የዓለም የቱሪዝም ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች...
14/11/2024

የቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ የስራ ዕድል የሚፈጥርና ኢኮኖሚ የሚያመነጭ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ፦ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የዓለም የቱሪዝም ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ3ኛ ጊዜ "ቱሪዝም ለሠላም በሚል መሪ ቃልበተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት መልዕክት ቱሪዝም መድረኩ የቱሪዝም አቅሞችና ሀብቶችን የሚንዳስስበት፣ የሚንመካከርበትና እንደ ክልል የተጀመሩት ስራዎች የሚናጠናክረበት ብለዋል።

ሀገራችን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ያሉ ቢሆንም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ አጥጋቢ ባለመሆኑ በለውጡ ዓመታት በመንግስትና በፓርቲ ትኩረት ከተሰጡት ከኢንዱስትሪ ዘርፎች ውስጥ ተጠቃሽ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም የቱሪዝም መስህቦችንና መደረሻዎችን ለማስፋት የተደረጉት ሙከራዎች በኢንዱስትሪ የተሻለ መነቃቃት እየተፈጠረ እንደሆነ ርዕሰ መስሀዳድሩ ገልጸዋል።

በቱሪዝም ኢንዱስትሪው የሚያጋጥሙት ተግዳሮች ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ አሰራርን በማሳለጥ ከኢኮኖሚ የሚገኘውን ጥቅም አሟጦ ለመጠቀም በትኩረት መስራት ያሻል ሲሉ አስገንዝበዋል ።

ዘርፉ ትልቅ የስራ ዕድል የሚፈጥርና ኢኮኖሚ የሚያመነጭ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በቱሪዝም ዘርፍ የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የመስተንግዶ ስፍራዎችን የመዝናኛ ቦታዎችንና መሠል ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት የተፈጥሮ ሀብት ፣የታሪክ እና የባህል ትውፊቶችን በማስተዋወቅ ኢኮኖሚ ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የዓለም የቱሪዝም ቀንን በሚመለከት መልዕክት ያስተላለፉት የፌዴራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ
የዓለም የቱሪዝም ቀን በየዓመቱ የሚከበረው የቱሪዝም አስፈላጊነትና ጠቀሜታ እንዲሁም ቱሪዝም በሀገር አቀፍ ደረጀ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊና ባህላዊ እሴቶች ላይ የሚኖረው አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመላው የዓለም ማህበረሰብ ለማሳወቅ ታስቦ ነው ብለዋል።

ቱሪዝም ስራና የስራ ዕድሎችን የመፍጠር አቅም ከመፍጠር አኳያ ሁለገብ ድርሻ ያለው ዘርፍ ከመሆኑም ባሸገር ቱሪዝም ዘርፉን ተፈጥሯዊ ታርካዊና ባህላዊ ይዘቶችን በመጠበቅ ፣ በመንከባከብ ና በማስተዋወቅ እንዲሁም የከተማ ፍልሰት በመቀነስ በኩል ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አስገንዝበዋል ።

የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ክልሉ ብዙ የቱሪዝም አለኝታ እና በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ባለቤት መሆኑን ገልፀዋል።

በተለይም ክልሉን በአረንጓዴ ቱሪዝም ልዩ ፀጋ ያለዉ መሆኑን በመግለጽ ይህ መድረኩ እምቅ የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ በማስተዋወቅ እና በማልማት ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ በር ከፋች መሆኑን አቶ ፋንታሁን ተናግረዋል።

ከቱሪዝም ዘርፍ ተገቢው ጥቅም እንዲገኝ ለማስቻል የባለድርሻ አካላት ያላሰለሰ ጥረትን የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል ስል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

የሀዘን መግለጫ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨የሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ባልደረባ የነበረና በባህላዊ ክራር ጨዋታ የሚታወቀው አርቲስት ሻጊቶ ቆጭቶ ባደረበት ህመም ምክንያት በመቱ ሆስፒታል ስ...
18/10/2024

የሀዘን መግለጫ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ባልደረባ የነበረና በባህላዊ ክራር ጨዋታ የሚታወቀው አርቲስት ሻጊቶ ቆጭቶ ባደረበት ህመም ምክንያት በመቱ ሆስፒታል ስረዳ ቆይቶ በቀን 7/02/2017 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

መላዉ የዞናችን ህዝቦች በአርቲስት ሻጊቶ ህልፈተህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን እንመኛለን።

ፈጣሪ ነፍሱን በሰላም ያሳርፍ !
ሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ

07/10/2024

የሸካ ጥብቅ ደን - የብዝሃ ህይወት ስብጥር ተምሳሌት
#ሀገሬ

የሸካ ተፈጥሮ ደን ህብረተሰቡ በሀገር በቀል ዕውቀቱ በባህላዊ መንገድ ጠብቆ ያቆየው የማህበረሰቡ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እሴት ውጤት ነው። ደኑ እስከ አሁን የብዝሃ ህይወት ስብጥሩን ሳይለቅ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ መምጣቱ ህብረተሰቡ ለተፈጥሮ ሀብት ያለውን ተቆርቋሪነት የሚያመላክት ነው። ሸካዎች የተፈጥሮ ደኑ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የመጠለያና የመዝናኛ ምንጭ እና መሠረትም ነው ብለው ያምናሉ።

በተለያዩ የተፈጥሮ ፀጋዎች የታደለው የሸካ ምድር ካለው 238 ሺሕ 750 ሄክታር የቆዳ ስፋት ከ131 ሺሕ 639 ሄክታር በላይ የተሸፈነው በጥብቅ የተፈጥሮ ደን መሆኑን መረጃዎች ያመላክታል። ከአጠቃላይ ቆዳ ስፋቱ 55 በመቶው በጥብቅ የተፈጥሮ ደን እንደተሸፈነ የሚነገርለት የሸካ ደን ወደ 28 ሺሕ ሄክታር የሚጠጋ የቀርቀሃ ደን ክምችት ያለበትም ነው፡፡

ደኑ በውስጡ ዝግባን ጨምሮ ቀረሮ፣ ዋርካ፣ ጎንጂ፣ ጥቁር እንጨት እና ሌሎች ግዙፍ ሀገር በቀል የዛፍ ዝሪያዎች የሚገኙበት ሲሆን ከ650 በላይ የብዝሃ ህይወት ስብጥር ይገኝበታል፡፡

በአረንጓዴ ውበቱ ቀልብን የሚማርከው ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደኑ በውስጡ ከ300 በላይ የዛፍ ዝሪያዎች፣ 50 አጥቢ የዱር እንስሳት፣ 2 መቶ የሚሆኑ የወፍ እንዲሁም 20 የተሳቢ እንስሳት ዝርያዎችንም አቅፎ ይዟል።

አከባቢው ዓመቱን በሙሉ ዝናብ የማይታጣና በገፀ ምድርና በከርሰ ምድር ውሃ ክምችት የታደለም ነው። የባሮ፣ በቆ፣ ጋሃማዎ፣ ገማድሮ፣ መነሺ ወንዝ እና ሌሎችን ጨምሮ ከ32 በላይ የሚሆኑ ዓመቱን በሙሉ የሚፈሱ ትልልቅ ወንዞች ምንጫቸውና መነሻቸው ከዚሁ ከጥብቁ የሸካ የተፈጥሮ ደን ነው።

የሸካ ዞን የተፈጥሮ እና የሰው ሠራሽ የመስህብ ሥፍራዎች የሚገኙበት ድንቅ የቱርዝም መዳረሻዎች ያሉበት ነው። ከ46 በላይ ፏፏቴዎች፣ ከ20 በላይ ዋሻዎች እንዲሁም በልዩ አፈጣጠሩ በደጋው ተራራ ላይ በቀርቀሃ ደን የተከበበውን የጋንዲዎችን ሀይቅ ጨምሮ ሦስት ሀይቆች በዞኑ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ወደ 51 የሚጠጉ ሆራዎች በደኑ ውስጥ እንደሚገኙም መረጃዎች ያሳያሉ።

በሀገር በቀልና ዕድሜ ጠገብ የዛፍ ዝሪያዎች የተሸፈነው ይህ አረንጓዴው ምድር የጫካ ቡናን ጨምሮ፣ ማር፣ ኮረሪማ፣ ጥምዝ፣ ሔል፣ ቁንዶበርበሬ፣ ዝንጅብል፣ እርድ እንዲሁም እንሰትና የተለያዩ ፍራፍሬዎች የተፈጥሮ ደኑን ሳይረብሹ ይመረታሉ፡፡

የተፈጥሮ ደኑ በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ ትምህርትና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ እ.ኤ.አ ሐምሌ 2012 መመዝገቡ ይታወሳል። ሸካ ዞንን ይጎበኙ ሀገሪዎን ይወቁ!!
ቸር እንሰንብት!!

በሠራዊት ሸሎ

     𝐀𝐧𝐨𝐭𝐡𝐞𝐫 𝐁𝐫𝐞𝐚𝐭𝐡𝐭𝐚𝐤𝐢𝐧𝐠  𝐖𝐚𝐭𝐞𝐫𝐟𝐚𝐥𝐥 𝐅𝐫𝐨𝐦 𝐓𝐡𝐞  𝐒𝐡𝐞𝐤𝐚 𝐙𝐨𝐧𝐞 🌱🌱 🇪🇹 #𝐕𝐈𝐒𝐈𝐓𝐒𝐇𝐄𝐊𝐀      #𝐍𝐚𝐭𝐮𝐫𝐞  #𝐄𝐜𝐨𝐭𝐨𝐮𝐫𝐢𝐬𝐦  #𝐁𝐞𝐚𝐮𝐭𝐢𝐟𝐮𝐥𝐥𝐚𝐧𝐝𝐬𝐜𝐚...
06/10/2024



𝐀𝐧𝐨𝐭𝐡𝐞𝐫 𝐁𝐫𝐞𝐚𝐭𝐡𝐭𝐚𝐤𝐢𝐧𝐠 𝐖𝐚𝐭𝐞𝐫𝐟𝐚𝐥𝐥 𝐅𝐫𝐨𝐦 𝐓𝐡𝐞 𝐒𝐡𝐞𝐤𝐚 𝐙𝐨𝐧𝐞 🌱🌱 🇪🇹

#𝐕𝐈𝐒𝐈𝐓𝐒𝐇𝐄𝐊𝐀 #𝐍𝐚𝐭𝐮𝐫𝐞 #𝐄𝐜𝐨𝐭𝐨𝐮𝐫𝐢𝐬𝐦 #𝐁𝐞𝐚𝐮𝐭𝐢𝐟𝐮𝐥𝐥𝐚𝐧𝐝𝐬𝐜𝐚𝐩𝐞
#𝐖𝐚𝐭𝐞𝐫𝐟𝐚𝐥𝐥 #𝐂𝐚𝐯𝐞 #𝐅𝐨𝐫𝐞𝐬𝐭

come and Discover the hidden treasures of sheka!

የተከበራችሁ የኦሮሞ ህዝቦች እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!!Baga ayyaana Irreechaan isin gahe!
05/10/2024

የተከበራችሁ የኦሮሞ ህዝቦች እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!!
Baga ayyaana Irreechaan isin gahe!

በሸካቾ ብሔረ ማሽቃሬ ባሮ የታወጁ አዋጆች (ትሞና/ ሼሮ)✍️የሀገራችን ህገመንግስት እና ለሎች ህጎችን የማይቃረኑ ከአያቶቻችን  እና ከቅድሜ አያቶቻችን ስወርድና ስወራረስ የመጡ በህዝባችን ው...
02/10/2024

በሸካቾ ብሔረ ማሽቃሬ ባሮ የታወጁ አዋጆች (ትሞና/ ሼሮ)

✍️የሀገራችን ህገመንግስት እና ለሎች ህጎችን የማይቃረኑ ከአያቶቻችን እና ከቅድሜ አያቶቻችን ስወርድና ስወራረስ የመጡ በህዝባችን ውስጥ ሰርፆ ተግባር ውስጥ ያለ ልማዳዊ አሰራሮች የባህል ክንዋኔዎች የባህል አስተዳደር/ ሚክራቾዎች የባህል ምክርቤት ውሳኔዎች በሙሉ የሚቀጥሉ እና የፀኑ ይሆናሉ

✍️በሀገራችን የተደነገጉ እና ሀገራችን የተቀበለችው ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ድንጋጌዎች የኢፌዴሪ ህገመንግስት እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህገመንግስት የፍታብሔር እና የወንጀል ህጎች በዝህ ቲሞ እና ሼሮ /"አዋጅ የተከበሩ ናየው።

✍️ጋብቻን በተመለከተ

1.የስጋ ዝምድና ባላቸው ሰዎች መካከል ጋብቻ እንዳይፈጸም በባህላችን ክልከላ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ተመሳሳይ የዘር ግንድ ያላቸው እና አመጣጣቸው አንድ የሆኑ ጎሳዎች መካከል ጋብቻ መፈፀም የተወገዘ ነው።

2.ሴት ልጅ ከማታገባው ወንድ ገንዘብ እና ንብረት መውሰድ የተከለከለ ነው።በዝህ ህደት ውስጥ የቤተሰብ ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ የተወገዘ ነው

3.ከጋብቻ በፊት በወላጆች ቤት ሳታገባ መውለድ በባህላችን የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።

4.ከአቅም በላይ የሆነ የእርቅ ገንዘብ ወይም ዋጋ ያለውን ቁሳቁስ መቀበል እርቅ በሚፈፀምበት ወቅት ከሙሽሪት ቤተሰብ እናት እና አባት ውጭ ለሌላ ቤተሰብ አባል የስጦታ ዕቃ ማምጣት መስጠት የተከለከለ ነው
-ለመልስ/ምላሽ ከበግ ውጭ የቀንድ ከብት ማምጣት ከዛሬ ጀምሮ የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።

5.የሙሽሪት ቤተሰብ በመልስ ግዜ በባህላችን ከተፈቀደ እንደ ጊደር ላም የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ቅቤ ቅመማቅመም ሳጥን በስተቀር ለታይታ እና ከሌላ ሰው ጋር ውድድር በምመስል ሁኔታ ከባህላችን ውጭ ተጨማሪ ስጦታ መስጠት የተወገዘ ነው።

6.ተጋቢዎች የመከባበር የመረዳዳት የጋራ ንብረት በጋራ የመጠቀም የማስተዳደር መብት አላቸው።
ይን በባህላችን እና በህግ የተቀመጠ ግዴታ መጣስ የጋራ ንብረት መሰወር እና መደበቅ በማንኛውም አኳን አንዱ የአንዱን መብት መጋፋት በባህላችን የተከለከለ ነው።

7.በትዳር አጋሩ በደል የደረሰበት ወገን ወንዱም ይሁን ሴቷ ወደ ፍርድቤት ጉዳያቸውን ከመውሰዳቸው በፊት በባህል መሰረት አለመግባባታቸውን ለመፍታት ተገቢውን ጥረት ማድረግ አለባቸው።

በጋብቻ ውስጥ የሚፈጠር አለመግባባት ቅድሚያ በተጋቢዎች እና በቅርብ ሰዎች/ቤተሰቦች እንድፈታ ይመከራል በዝው አግባብ ካልተፈታ በባህል መሪዎች በጎሳ መሪዎች በተመረጡ ሽማግሌዎች ይፈታል ይመከራል ተበዳይ ይካሳል በዳይ ደሞ እንድክስ ይደረጋል ።
በዝህ ጥፋት ያልተመለሰ እና ተደጋጋሚ በደል ያደረሰ ወገን በአካባቢው ወራፎ ይከለከላል ።

✍️ፍትህ የሚሰጡ ወይም የሚወስኑ ሙግት የሚሰሙ የሚያስታርቁ ቅጥር የሚፈፅሙ የሚያስተዳድሩ የሚያዋውሉ የመንግስትም ሆነ የባህል ሰዎች ተገልጋይ ማጉላላት ቀጠሮ ማብዛት የተወገዘ ተግባር ነው።
✍️እጅ መንሻ አይቀበሉ በዝምድና በስልጣን በገንዘብ ወይም በጥቅማጥቅም በማናቸውም መንገድ ፍትህን አያጓድሉ በእውነት እና በማስረጃ ብቻ ተመስሪተው ይወስኑ ሰው የሰራውን የላቡን ብቻ ይውስድ ይጠቀም ያን መጣስ በባህላችን እና በሰማይ አምላካችን ፊት ሀጥያት ነው በህዝባችን ፊት ቆመን ነጋሪት ጎስመን አወግዘናል።
✍️ጊደር ላም በትኛው ሁኔታ የማትወለድ መሆኗን በባለሙያዎች ካልተረጋገጠ በቀር ለእርድ መጠቀም ፈፅሞ የተከለከለ ነው በባህላችን የተወገዘ ነው።
✍️በአካባቢያቸን በሚመረቱ ምርቶች ላይ በአድ ነገር መጨመር ወይም መቀላቀል የምርት ጥራት ማጓደል ጥራት የሌለውን ወይም የተበላሸን ምርት ለግብይት ማቅረብ ያለ በቂ ምክንያት ዋጋ መጨመር በመልካም ስማችን መነገድ ሚዛን መቀነስ እና ማንኛውንም ተገቢ ያልሆነ ነገር መፈፀም በባህላችን መሰረት የተወገዘ ነው።
-በእውነት መንገድ እና የላቡን ትርፍ መብላት የአምላካችን ትዕዛዝ በመሆኑ ልናከብረው ይገባል ።
ይህንን የጣሰ ወራፎ ይከላከላል ከዛሬ ጀምሮ ይህ ድርግት የፀና ይሆናል።

✍️በልማት ላይ የተደነገገ አዋጅ
✍️በንጉሡ አስተዳደር ክልል ውስጥ የማይታረስ ፆም የሚያድር መሬት እንድሁም ከስራ ውጭ የሚሆን ጉልበት አይኑር።
✍️አርሶአደር ለምግብ ዋስትና ቅድሚያ በመስጠት አምርቶ የራሱን ፍጆታ የመሸፈን እንድሁም ትርፍ ምርት አምርቶ ለገበያ ማቅረብ ይጠበቅበታል ።
✍️አርሶአደሩ በየዓመቱ እንሰት ችግኝ አፍልቶ የመትከል ግዴታ አለበት ክትትል ይደረግበታል ካልተገበረ ይመከራል ለወራፎ ይቀርባል ።
✍️በሸካ ባህል መሰረት የአርሶአደር ቤት በእንሰት እና በአትክልት የተከበበ መሆኑ ይታወቃል ፈፅሞ ቤቱ ገላጣ ሜዳ መሆን የለበትም።
✍️ማንም ሰው ከሰንበት እና ከበዓላትጨውጭ በስር ሰዓት ከስራ ውጭ በመሆን አልባለ ቦታ መገኘት በባህላችን የተከለከለ ነው።
✍️የአካባቢውን ንፅህና ደህንነት የማይጠብቅ ቆሻሻን ያለቦታ መጣል የለበትም ።
✍️ማንም የከተማ ሆነ የገጠር ነዋሪ በመንግሥት የልማት እና የሰላም ስራዎች ላይ በንቃት ካልተሳተፈ የተወገዘ ይሁን
✍️በተፈጥሮ ሀብቶች በቅርሶች እና በታሪካዊ ቦታዎች በህግ እና በባህል የተከለከሉ ክልከላዎችን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለበት።
✍️የተከለከለ ጥብቅ ደን መጨፍጨፍ ማቃጠል ወደ ተከለለ ቦታ የእርሻ ይዞታ ማስፋፋት በባህላችን የተወገዘ ነው።
✍️የወንዝ ዳርቻዎችን ሆራዎችን/እዮ
ረግረጋማ ቦታዎችን ዋሻዎቾን እና ታሪካዊ ቦታዎችን ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎችን ማረስ ማራቆት የተወገዘ እና የተከለከለ ተግባር ነው።
✍️ፈቃድ ሳይሰጥ የህዝብ መሬት በጉልበት መያዝ ማስፋፋት በባህላችን የተወገዘ ነው።
✍️መስረቅ ከሰረቀ ጋር መተባበር በማንኛውም መንገድ መርዳት የራሱ ያልሆነውንና ወድቆ የተገኘውን ንብረት አንስቶ መጠቀም በፍጹም የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።ይህንን ያደረገ ከወራፎ ውጭ ይሆናል
✍️ታላላቅ አባቶቻችንን ,እናቶቻችንን ,የመንግስት ባለስልጣናትን,አስተማሪዎችንን,የሀይማኖት አባቶችንን,የባህል መሪዎቻችንን,ተሿሚዎችንን እንድሁም ለሎች ክብር የሚገባቸውን የማክበር ቅድሚያ የመስጠት ተነስቶ የማስቀመጥ የመታዘዝ የባህላችን ምሶሶ በመሆናቸው የማክበር የባህል ግዴታ አለብን ያለማክበር ያስረግማል ለትችት ያቀርባል ወራፎም ቦታ ያሳጣል የተወገዘ ነው።
✍️በሀሰት መክሰስ በሀሰት መመስከር ማስረጃ መደበቅ በውሸት መማል በባህላችን የተከለከለ እና የተወገዘ ነው።
✍️የራስን ያልሆነ መሻት በባህላችን የተወገዘ በመሆኑ
በመተት ,በጥንቆላ ,በአስማት በባዕድ አምልኮ ማሰራት እሄን መፈጸም የተወገዘ ይሁን ይንን የሚያደርግ የተረገመ ይሁን
✍️ተበድሮ መካድ ወይም ያለመመለስ ተዋውሎ,ሸጦ ቃል መቀየር መካድ ,ማስካድ የተወገዘ ነው።
✍️በሀዘን ለቅሶ ግዜ የተከለከለ ተግባር
-ከቡና እና ቆሎ ውጭ መስተንግዶ ማዘጋጀት እና አስክሬን ማቆየት የተወገዘ ነው።
-ማቅ መልበስ ለድግስ ብሎ የሟች ንብረት መሸጥ የተወገዘ ነው።
✍️የተበደለ ሰው ለበዳይ ዘመድ ለሽማግሌዎች ወይም ለባህል መሪዎች የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

ይህንን ወደ ጎን በመተው በሰው ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ ቡና መቁረጥ ለሎች ንብረቶችን ማውደም ቤት ማቃጠል እንስሳት ላይ በቀል መወጣት ተደራጅቶ ሰው መደብደብ, መግደል, አካል ጉዳት ማድረስ በደልን በበደል መካስ መሰል ተግባር የተከለከለ ነው ።

01/10/2024

Address

Masha
123456

Telephone

+251918954093

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sheka Zone Tourist Attraction & Information Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sheka Zone Tourist Attraction & Information Center:

Videos

Share