መ/ሜዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ክበብ

መ/ሜዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ክበብ This is my website.

05/11/2022

ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ክበብ በቅርቡ ስራውን ለመጀመር አባላቶቹን በመመዝገብ ላይ ሲሆን እርሶዎም የክበቡ አባል በመሆን በሃገራችን ያሉ የቱሪስት መስህቦችን፣ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ቦታዎችን ይወቁ።

25/09/2022
09/06/2022

የገዳም ሚካኤል አመሰራረት
በአማራ ክልል በሰ/ሸዋ ዞን በመ/ቀ/ገ/ወ/ ከወረዳዉ ርዕሰ ከተማ ዘመሮ በ32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በ06 ቀበሌ ወይም ቋች ይገኛል፡፡ይህ ገዳም የተመሰረተበት ዘመን በትክክል ባይታወቅም ከአፄናኦድ ዘመነ መንግስት በፊት ማለትም ከ1414 ዓ.ም በፊት እንደሆነ ቀደምት አባቶች ይናገራሉ፡፡የገዳሙ መስራች የነበሩት አባት ኮካ ሃይማኖት የተባሉት አቡነ ተክለሃይማኖትንና የቅዱስ ሚካኤልን ፅላት ከጎንደር ይዘዉ መጥተዉ በዚሁ ገዳም ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታማረፊያ ቦታ እየፈለጉና እያሰሱ ባሉበት ወቅት በአንድ መደዳ ሶስት ዋሻ ያለ ሲሆን ከታች አንድኛዉ ዋሻ አባ ሳፎ ተብሎ የሚጠራዉ ለአገልግሎት ብቁ ያልሆነ ሲሆንባቸዉ 3ኛዉ ዋሻ ላይ ሲወጡ ከመሃል ወገቡ ሲያልፉ መቋሚያቸዉ ከእጃቸዉ አምልጣ ገደል ገባች እንደገና ወደ ኋላ ተመልሰዉ መቋሚያቸዉን ፈለጉ ፡፡ ሲፈልጉም በዘለኮ ሃረግ የተሸፈነ ዋሻ አግኝተዉ ወደ ዋሻዉ ሲገቡ ሶስት ጃርት አገኙ፡፡እንግዲህ እግዚአብሔር የፈቀደልኝን ቦታየን አገኘሁ አዚህ ማደሪያየን አዘጋጀልን ከድካሜ አረፍሁ ባዕቴን ለእኔም አገኘሁ ከዚሁ አርፋለሁ ብለዉ የቃል ኪዳኑን ታቦት በዚሁ ዋሻ ዉስጥ አስገብተዉ ፀሎታቸዉንና አገልግሎታቸዉን ቀጠሉ፡፡እኝህ አባት የተሰጣቸዉ ፀጋ ከዚሁ ከመ/ቀ/ገ/ወ/በ05ና በ06 ቀበሌ መካከል ከሚገኘዉ ወንዝ ዋሻ ገዳም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እያሉ ለሰርክ ቅዳሴ ግዜ በ6 ሰዓት በቀስተ ዳመና ተጭኖ ደብረሊባኖስ ገዳም ለአቡነ ተክለሃይማኖት ቅዳሴ ይደርሳሉ፡፡የቅዳሴዉ ስረዓት ከተፈፀመ በኋላ ስረዎተ ህዝብ እንደተደረገ ተመልሰዉ እዚያዉ እባእታቸዉ እተቀመጡበት ገዳም ቅዱስ ሚካኤል ይገኛሉ፡፡እኝህ ፍፁም አባት እዚህ ቦታ ላይ የአቡነ ተክለሃይማኖትን ገድልና እንደዚሁም የቅዱስ ሚካኤልን ድርሳን በብራና ፅፈዉ አኑረዋል፡፡በዚሁ በፃፉት መፀሀፍ ላይ የራሳቸዉን ፎቶ ወይም ምስል በእጃቸዉ ስለዉ አስቀምጠዋል፡፡እረፍታቸዉም በዚሁ ቦታ ነዉ፡፡የሳሉት ስዕል ገድልና ድርሳናቸዉ እንደዚሁም በገዳሙ ያለዉ ፀበል ህሙማኖችን እየፈወሰ ይገኛል፡፡
ዋሻው ውስጡ ተፈልፍሎ የተሰራ ሲሆን ለገዳሙ ልዩ ግርማ ሞገስና ውበት ያለበሰው ምንጭ ከዋሻው አናት ላይ ወደ ዋሻው አፍ በመፍሰስ ፏፏቴ ስለሚፈጥር የተመልካችን ቀልብ ከመግዛቱም በተጨማሪ አከባቢው አረንጓዴ እንዲለብስ አስችሎታል፡፡ በተጨማሪ ጥር 12 እና ሰኔ 12 ከተለያዩ አካባቢዎች በሚመጡ ማህበረሰቦች በአካባቢዉ ማህበረሰብበዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡

03/05/2022
ለገና /ልደት/ እንኳን አደረሳችሁ /አደርሰንበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በክርስትና እምነት ተከታዮች ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት መካከል ነው፤ የልደት ወይም የገና በዓ...
06/01/2022

ለገና /ልደት/ እንኳን አደረሳችሁ /አደርሰን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በክርስትና እምነት ተከታዮች ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት መካከል ነው፤ የልደት ወይም የገና በዓል ነው።
የገና (ልደት) በዓል በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ ዐብይ በአላት ውስጥ አንዱ በአል ነው። እለቱ በትንቢተ ነቢያት የተነገረለት የሰውን ልጆች በጥንተ ተፈጥሮ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ አሁን ደግሞ በሐዳስ ተፈጥሮ ለመፍጠር ማለት ሰውን ለማዳን ሰው ሆኖ የተወለደበት እለት ነው።
ገና የሚለው ቃል ከጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ የተወረሰ ቃል እንደሆነ እና ትርጉሙም ልደት ማለት እንደሆነ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት መምህራን ይገልጻሉ።
መጽሐፍት ላይ ስለ ልደት በዓል ከተጻፉት መካከል በጥቂቱ እናካፍላችሁ።
እንዲህ ይላል፥ በትንቢተ ነቢያት የተነገረለት የሰውን ልጆች በጥንተ ተፈጥሮ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ ሰውን ለማዳን ሰው ሆኖ የተወለደበት ዕለት ነው። በዓለ ልደት በየዓመቱ የሚከበረው ታህሳስ 29 ቀን ነው። በዘመነ ዮሐንስ ግን የሉቃስ ጷጉሜን ስድስት ቀን ስለምትሆን ልደት ታኅሳስ 28 ቀን ይውላል።
ይህም የተጀመረው በአፄ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት ነው ይባላል። የልደት በዓልከጾም ዘመን ጋር የተያያዘ ስለሆነ ገሃድ የለውም፤ የማይፆሙ ሰዎች ግን ዋዜማውን ብቻ ገሃድ ብለው ይፆሙታል።
በዚህ ዕለት ልደትን የምታከብር ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም፤ የእስክንድሪያ ቤተክርስቲያንም በዓሉን በዚሁ ዕለት ታከብራለች። ከኢትዮጵያ ጋር በዓለ ልደትን የሚያከብሩ አገራትም ግብፅ፣ ሶሪያ፣ ህንድ እና አርመን ናቸው። ከሩቅ ምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ ግሪክና ሩሲያ ይገኛሉ።
ታዲያ ሄሮድስ በነገሠበት ዘመን የይሁዳ ክፍል በምትሆን በቤተልሔም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ጥበበኞች ሰዎች ከምሥራቅ መጡ። ወደቤት ገብተው የተወለደውን ህጻን ከእናቱ ጋር አይተው ከፈረስ ከሰረገላ ወርደው ሰገዱለት፤ ሳጥናቸውን ከፍተው ኮሮጇቸውን ፈትተው ወርቁን፣ ዕጣኑን እና ከርቤውን ገበሩለት። ከእነዚህም በቤተልሔም ተወልዶ ሳለ ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤን ከገበሩለት ነገሥታት አንዱ የኢትዮጵያ ንጉሥ ባዜን እንደነበር ይተረካል።
የገናን በዓል ስናነሳ ታዲያ የገና ባህላዊ ጨዋታም አብሮ ይነሳል

የገና ጨዋታ
የገናን ባህላዊ ጨዋታን ስንመለከት አስቀድሞ የቡድን አባላት የሚሆኑ ሁለት ሰዎች ይመረጣሉ፡፡ ሁለት ሁለት ተጫዋቾች ወደ አባቶች ይቀርቡና በምርጫው ወደ ቡድን ውስጥ ይገባሉ፡፡ የሚያስፈልገው የተጫዋች ቁጥር ሲሞላ ወገን ወገናቸውን ይዘው በዱላ ቀልጣፋ የሆኑ ተጫዋቾች ጥንጓን( መጫወቻ ኳሱ) ወደፊት እንድትቀጥል ይመቷታል ወይም ይመልሷታል፡፡ ተጫዋቾች ብዙ ጊዜ በጨዋታው ስለሚሰጡ ጥንጓን ከእግር መካከል በገባች ጊዜ ከሰው እግር ጋር ደርበው ስለሚመቱ የእግር መሰበር በዚህም ሳቢያ ወገን ለይተው እስከመፈናከት ይደርሳሉ፡፡ በንጉሳውያን ዘመን የመኳንንቱም አሽከሮች፣ የንጉሡና የንግሥቲቷ አሽከሮች የጌቶቻቸውን ስም በጉብዝና የሚያስጠሩት በባህላዊው የገና ጨዋታ ነው፡፡
ጨዋታው በመንደር ልዩነት ከሆነ የታች አምባ ቡድን ሀምሳ ተጫዋቾች ቢሆኑ የላይ አምባ ቡድን ሰባ ሆነው ቢጫወቱ የሚከለክል ደንብ አልነበረም፡፡ ጨዋታው በመጨረሻ ፀብ ስለሚያነሳ ብዙ ጊዜ ጉዳት ያጋጥማል፡፡ ጥንጓም ኃይለኛ ለጊ በመታት ጊዜ ዐይን እስከ ማጥፋት ትደርሳለች፡፡ ተጫዋቾች “በሚና” ብለው በሚጫወቱበት በቆልማማ ዱላ ቢደባደቡም የሚገላግል ዳኛ አልነበረም፤ ጨዋታውን በሚመለከቱ አባቶችም በድብድብ ከመሳቅ በስተቀር ሽምግልናቸው ለገና ጨዋታ አልተለመደም፡፡ “እግር ይብሳል፣ ያንከላውሳል፡፡” እያለ ማስፈራራት፣ ራስን መቀወር ወይም እንቆራቆስ ብሎ እጅና እግርን በዱላው መምታት በገና ጨዋታ የተለመደ ነበር፡፡
የገና ጨዋታ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎች አገሮች የታወቀውና በኦሊምፒክ የስፖርት በዓል ከሚደረጉ ውድድሮች አንዱ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህም ጨዋታ ሆኪ በሚል ስም ይጠራል፡፡ ፈረንጆች የፊት አደጋን መከላከያ ዘዴ ይጠቀማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያገር ባህል ገና ጨዋታ በሚደርስ አደጋ ማንም ተጫዋች አይጠይቅም፡፡
በገና ጨዋታ አሸናፊ ለሆኑት ቡድኖች ፊሪዳና ጠጅ ተሰጥቷቸው እየበሉና እየጠጡ፣ እየዘፈኑ ሲሸልሉና ሲያቅራሩ ሜዳውን የጦርነት ድል ያገኙበት ያስመስሉት ነበር፡፡ ከሚዘፍኑትና ግጥሞች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
“ማታ ነው ድሌ፣
ይሄ ነው አመሌ፡፡
አሲና በል አሲና ገናዬ፡፡
ኦ! ጉ! አሲና በል አሲና ገናዬ፡፡
ግፋው ግፋው አለኝ እኔ እንደምን ልግፋው፣
የአንድ በሬ ጨጓራ እንደ ቅል የነፋው፡፡
የብብቱ ሽታ፣ የመንፈቅ በሽታ፡፡
የጀርባው መርሬ፣ ያውላል ጥድ በሬ፡፡
ካስር ጋን አተላ፣
አይተርፈው በአንኮላ፡፡
እግርህ የሸረሪት ሆድህ የእንቁራሪት፣
ቀን እንደጠላሁ ና እንዳትመጣ ሌሊት፡፡”
ስድብ ለተራው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በመኳንንቱና በነገሥታቱም ላይ ሊሰነዘር ይችላል፡፡ በሚደርስባቸው ስድብ ግን ምንም ዓይነት ቁጣና ቅጣት አያደርጉም፡፡
“በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ
በገና ጨዋታ የለም ሎሌ ጌታ፡፡” የሚለው የዘፈን ግጥም ይህን ባህል ይገልፃል፡፡
የገና ጨዋታ ከክርስትና ሃይማኖት በፊት ይዘወተር እንደነበርና በኢትዮጵያ ከታኅሣሥ የመኸር ወቅት ጋር የተያያዘ ባህል ነበረ፡፡ ከበዓሉ ጋር የተያያዘ ብዙ የስነቃል ግጥሞችን ይገኛሉ፡፡
“ታኅሣሥ ገሠገሠ ከተፍ አለ ገና፣
እጠብቅሀለሁ አንተ ልጅ ቶሎ ና፡፡
ይወዘውዘኛል አልጠላኝም ገና፣
ፍቅር ሞገደኛው እየነሳኝ ጤና፡፡
ምግብ አያስበላ አያስለብስ ልብስ፣
ሞገደኛው ፍቅሩ ይዞኝ በታኅሣሥ፡፡
በማለዳ ጀንበር በገና ጨረቃ፣
እኔን እኔን ብላ መጣች ተደብቃ፡፡”
መልካም የገና በዓል!
መ/ሜዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ክበብ

31/12/2021
የአለም ቱሪዝም ቀን በመንዝ ጌራ ም/ወረዳ በ መሰሓለማርያም ቀበሌ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
05/10/2021

የአለም ቱሪዝም ቀን በመንዝ ጌራ ም/ወረዳ በ መሰሓለማርያም ቀበሌ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

05/10/2021

Send a message to learn more.

01/10/2021
01/10/2021
ደመራ በቀይት ኪዳነ ምህረት
26/09/2021

ደመራ በቀይት ኪዳነ ምህረት

እንኳን ለደመራ/መስቀል/በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን              መልካም በዓል
24/09/2021

እንኳን ለደመራ/መስቀል/በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
መልካም በዓል

08/09/2021
06/09/2021
ጳጉሜ ፫      ልዩ  የ 13 ወር ፀጋ ይምጡ ሀይማኖታ፣ታሪካዊና ባህላዊ በሆነው ልዩ ቀን ጳጉሜ ፫ መንዝ ቅዱስ ሩፋዔል ይዋሉ፡፡               ጳጉሜ ፫         መንዝ ቅዱስ ሩ...
03/09/2021

ጳጉሜ ፫
ልዩ የ 13 ወር ፀጋ

ይምጡ ሀይማኖታ፣ታሪካዊና ባህላዊ በሆነው ልዩ ቀን ጳጉሜ ፫ መንዝ ቅዱስ ሩፋዔል ይዋሉ፡፡

ጳጉሜ ፫
መንዝ ቅዱስ ሩፋዔል

ይምጡ ጳጉሜ 3 መንዝ ሩፋኤል ይዋሉ!  መንዝ የታሪክ ሀገር ፣ የነገስታት መነሻ ፣የኩሩ ህዝብ መኖሪያ ፣የሀይማኖት የባህል ሀገር…  ይጓዙ ይጎብኙ ታሪክ ይወቁ መንፈስዎን ያደሱ
28/08/2021

ይምጡ ጳጉሜ 3 መንዝ ሩፋኤል ይዋሉ!

መንዝ የታሪክ ሀገር ፣ የነገስታት መነሻ ፣የኩሩ ህዝብ መኖሪያ ፣የሀይማኖት የባህል ሀገር…

ይጓዙ ይጎብኙ ታሪክ ይወቁ መንፈስዎን ያደሱ

19/08/2021
25/06/2021
menz guassa community conservation areaመንዝ ጓሳ ማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ
25/06/2021

menz guassa community conservation area
መንዝ ጓሳ ማህበረሰብ ጥብቅ ስፍራ

ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ጉዞ ትውስታዎች
24/06/2021

ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ጉዞ ትውስታዎች

Address

Mehalmeda
Mehal Meda
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መ/ሜዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ክበብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to መ/ሜዳ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ጦቢያ ሀገርክን እወቅ ክበብ:

Share