Visit Yem

Visit Yem Travel and Explore The Land Of Wonders ! Your Next Great Yem Adventure Awaits. Check Out Our Page.

30/10/2023

Guzo Adwa Hiking Events እናመሰግናለን ! ቀጣዩ መዳረሻችሁ የየም ዞን እንደሚሆን አንጠራጠርም !

29/10/2023

ጥበበኛውን የየም ህዝብ አመስግኑልን ! ሳሙ ኤታ ጥቅምት 17 እንዲህ ባማረ መልኩ ተከብሮ ዋለ - ይህን የ3 ደቂቃ ቪድዮ ይመልከቱ _ ሙሉ ቪድዮ በቅርብ ቀን ይጠብቁን .. Visit Yem

የየም ህዝብ እና የየም ዞን አስተዳደር ላደረጋችሁልን መልካም አቀባበል ምስጋናችን የላቀ ነው !

የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን አባል ይሁኑ !

Follow Us On TikTok : https://tiktok.com/
Follow Us On Instagram : https://instagram.com/visit_yem

Visit Yem  The Land Of Healings ! አስደናቂውን የየም መልከአምድር ይጎብኙ !Photo credit : Akotet Zelalem
27/10/2023

Visit Yem The Land Of Healings ! አስደናቂውን የየም መልከአምድር ይጎብኙ !

Photo credit : Akotet Zelalem

ቅኝት ኢትዮጵያ ! Visit Yem
23/10/2023

ቅኝት ኢትዮጵያ ! Visit Yem

ቅኝተ ኢትዮጵያ

የየም ብሔረሰብ ባህላዊና እና ታሪካዊ እሴቶች
**********

“የም” የሚለው ስያሜ የብሔረሰቡ መጠሪያ ሲሆን “የምሳ” ደግሞ የብሄረሰቡ መደበኛ ቋንቋ ነው። ብሔረሰቡ ከአስራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ታዋቂና ጠንካራ መንግስት መስርቶ ይኖር እንደነበርም የጥናት መዛግብት ያስረዳሉ።

የየም ብሔረሰብ አሰፋፈር እና የመሬት አቀማመጥን ስንመለከት ኮረብታማና ወጣ ገባ ነው። ከጊቤ ወንዝ አንስቶ እስከ ቦር ተራራ ያለው አቀማመጥም ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ የሚሄድ በመሆኑ ለመኖሪያነት አመቺ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የአየር ንብረት ይዞታው ደጋና ወይናደጋ ሲሆን ምስራቃዊው ክፍልና የጊቤ ተፋሰስ ደግሞ በቆላነት ይመደባል።

ብሔረሰቡ የራሱ የሆነ ባህል፤ ቋንቋ፤ ታሪክና ወግ አለው። በአካባቢው ታሪካዊ ቤተ መንግስት፣ የእምነት ስፍራዎች፣ እድሜ ጠገብ ደኖች፣ትክል ድንጋዮች፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ዋሻዎች በብዛት ይገኛሉ። በርካታ ትክል ድንጋዮች የሚገኙበት ስፍራ “ዞፍካር” ይባላል።

ይህ ስፍራ የየም የመጨረሻ ንጉስ በነበረው አባቦግቦ ዘመን ቀብር ይፈፀምበት ነበር፡፡ አካባቢው በታሪካዊነቱና በአንጋፋነቱ ከሌሎች የተመረጠ በመሆኑም በፓርክ ክልልነት እንዲለይ ተደርጓል። “አንጋሪ” የተባለው ጥንታዊ ቤተ መንግስትም በጥቅጥቅ ደኖችና በአገር በቀል ዛፎች የተከበበ በመሆኑ በመስህብነት ያገለግላል።

የየም ብሔረሰብ የቤት ውስጥ መገልገያዎች፣ የንጉሳውያን አልባሳት፣ ከዝሆን ጥርስ የተሰሩ የትንፋሽ ሙዚቃ መሳሪያዎችና የሸክላ ወጤቶች እድሜ ጠገብ ከመሆናቸውም በላይ የብሄረሰቡ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች ናቸው፡፡

በብሔረሰቡ በዋንኛ ምግብነት ከአስር የማያንሱ የእንሰት ውጤቶች ይዘጋጃሉ። በልዩ ማህበራዊ ግንኙነት ወቅት የሚዘጋጅ የቆጮ ድፎ “ኮባና” ይባላል። በገንፎና በቂጣ መልክ የሚዘጋጀው ቡላም “ኬዳኦ” የሚል መጠሪያ አለው። የቆጮ ገንፎ “ናቱ” ሲባል ከጎመንና ከቆጮ የሚዘጋጀው ፍርፍር ደግሞ “ዎቶ” ይሰኛል። “ፈጨ” የሚባለውም ለህፃናት ምግብነት የሚዘጋጅ ነው።

ከብሔረሰቡ ባህላዊ መጠጦች ዋናው “ቦርዴ ማኡሻ” ይባላል። የሚዘጋጀውም ከገብስ፣ ከዳጉሳ፣ ከቀይ ጤፍና ከብቅል ነው። ሌላው ባህላዊ መጠጥ ደግሞ “ኪአ” የሚል መጠሪያ አለው። ይህ የመጠጥ አይነት ውሃ ሳይጨመርበት ድፍድፉ ብቻ ተጨምቆ የሚቀርብ በመሆኑ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተወዳጅ መሆኑ ይነገርለታል። በልዩ ዝግጅት ወቅት የሚዘጋጀው ባህላዊ መጠጥም «ኡሻ» ይባላል። መረጃውን ከፌዴሬሽን ድምጽ መጽሔት 2001 እትም አጠናቅረነዋል።

ቅኝተ ኢትዮጵያ ጥቅምት 11/2016

20/10/2023

ጥቅምት 17 ደረሰ > ተጓዡ ጋዜጠኛ /ሄኖክ ስዩም/ ከባህር ጠለል በላይ 2,939 ሜትር ከፍታ ላይ በዕፀዋት ጥበብ ከ130 በላይ በሽታዎችን የሚፈውሰውን ጥበበኛውን የየም ሕዝብ ምስጢር ልብን በሚሰውር ምናባዊ ጉዞ እንዲህ ሊያስቃኘን ነው _ እስከመጨረሻው አብረውን ይጓዙ Visit Yem

- Travel & Explore The Yem people - The Land Of Healings -

የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን አባል ይሁኑ !

Follow Us On Facebook :
Follow Us On Instagram : https://instagram.com/visit_yem
Follow Us On TikTok : https://tiktok.com/

Video Credit : Travel Ethiopia - ጉዞ ኢትዮጵያ
Special Thanks : ለተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም
.............................. ‹‹”ሳሞ ኤታ”›› የየም ባህላዊ መድኃኒት ለቀማ ...............................

- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው የየም ብሔረሰብ ለጥቅምት ልዩ ሥፍራን ይሰጣል፡፡ ኅብረተሰቡ የጥቅምት አጋማሽ እንዳለፈ በየም ዞን በቦር ተራራ ላይ፣ የባህላዊ መድኃኒት ለቀማን ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የሚሳተፍበትን ኩነት ያደርጋል ፡፡ ‹‹”ሳሞ ኤታ”››

‹‹”ሳሞ ኤታ”›› በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን ቦር በሚባል ተራራ ላይ የባህላዊ መድኃኒቶች ለቀማ ይካሄዳል፡፡

‹‹”ሳሞ ኤታ”›› የሚለውና ፍችውም የከረመ መድኃኒት የሆነው የዕፀዋት መድኃኒት ለቀማ የሚከናወነው በየም ዞን ከባህር ወለል በላይ 2939 ሜትር ከፍታ ባለው የቦር ተራራ ላይ ነው፡፡

በቦር ተራራ የሚገኙ ዕፀዋት ለሰው ብቻ ሳይሆኑ ለእንሰሳትም እንደሚያገለግሉ በኅብረተሰቡ ይታመናል፡፡

‹‹የዓመት የመድኃኒት አስቤዛ ጥቅምት 17 ነው የሚሰበስበው፡፡ የም በዕፀዋት ጥበብ አስቀድሞ በሽታን ይከላከላል፡፡ ቀጥሎም ሕመምን ያስወግዳል፡፡ ፈውስን ከምድር ገጸ በረከት የሚያገኝ ጥበበኛ ሕዝብ ነው፡

አብዛኛው ማህበረሰብ ለመድኃኒት የሚጠቀምበትን እፅዋት የሚለቅመው በዚህ ተራራ ላይ ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያት ተደርጎ የሚቀርበውም የመጀመሪያው የማለዳ ፀሐይ የሚያገኘው በዚህ ስፍራ ላይ በመሆኑ በተራራው ላይ የሚገኙት መድኃኒቶች የመፈወስ አቅማቸው ከፍተኛ ነው ተብሎ ስለሚታመንበት ነው፡፡ በዓመቱ ተለቅሞ የሚቀመመው መድኃኒት በአካባቢው አጠራር ”ሳሞ ኤታ” ይባላል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በተራራው ላይ ካሉ በርካታ የእፅዋት አይነቶች ቅጠላቸውን፣ ስሮቻቸውን እና ቅርፊታቸውን በመሰብሰብ ቤታቸው ወስደው በአግባቡ በማዘጋጀት ለሰውና ለእንስሳት የሚሆን መድሃኒትነት ይቀምሙበታል፡፡

ሕፃናት ልጆች፣ ወጣቶች ከተራራው፣ ከገደሉ ላይ ተንጠልጥለው መድኃኒት ይለቅማሉ፡፡ አዲሱ ትውልድ በአባቶቹ መንገድ እየሄደ ነው፡፡ ከዚህ ዕፅ አንዱ ምናለ ሀገሬን በፈወሳት ስል ተመኘሁ!!››

‹‹”ሳሞ ኤታ”›› የባህላዊ መድኃኒት ለቀማ ትውፊቱ ከአባቶች ወደ ልጆች መተላለፉን በክብር በማመልከት ነው፡-

የመረጃ ምንጭ : በሔኖክ ያሬድ / ሪፓርተር ጋዜጣ
.............................. ‹‹”ጥቂት ስለ የም ማህበረሰብ ”›› ...............................

- ከአዲስ አበባበ ጅማ በሚወስደው መንገድ በ243 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ድንቅ ማህበረሰብ ነው

«የም» የሚለው ስያሜ የብሄረሰቡ መጠሪያ ሲሆን «የምሳ» ደግሞ የብሄረሰቡ መደበኛ ቋንቋ ነው።

- ከጊቤ ወንዝ አንስቶ እስከ ቦር ተራራ ያለው አቀማመጥም ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ የሚሄድ በመሆኑ ለመኖሪያነት አመቺ ነው ። የአየር ንብረት ይዞታው ደጋና ወይናደጋ ሲሆን ምስራቃዊው ክፍልና የጊቤ ተፋሰስ ደግሞ በቆላነት ይመደባል።

ብሄረሰቡ የራሱ የሆነ ባህል፤ ቋንቋ፤ ታሪክና ወግ አለው። በአካባቢው ታሪካዊ ቤተ መንግስት፣ የእምነት ስፍራዎች፣ እድሜ ጠገብ ደኖች፣ትክል ድንጋዮች፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ዋሻዎች በብዛት ይገኛሉ።

በርካታ ትክል ድንጋዮች የሚገኙበት ስፍራ «ዞፍካር» ይባላል። ይህ ስፍራ የየም የመጨረሻ ንጉስ በነበረው «አባቦግቦ» ዘመን ቀብር ይፈፀምበት ነበር። አካባቢው በታሪካዊነቱና በአንጋፋነቱ ከሌሎች የተመረጠ በመሆኑም በፓርክ ክልልነት እንዲለይ ተደርጓል። «አንጋሪ» የተባለው ጥንታዊ ቤተ መንግስትም በጥቅጥቅ ደኖችና በአገር በቀል ዛፎች የተከበበ በመሆኑ በመስህብነት ያገለግላል።

የብሄረሰቡ የቤት ውስጥ መገልገያዎች፣ የንጉሳውያን አልባሳት፣ ከዝሆን ጥርስ የተሰሩ የትንፋሽ ሙዚቃ መሳሪያዎችና የሸክላ ወጤቶች እድሜ ጠገብ ከመሆናቸውም በላይ የብሄረሰቡ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች ናቸው።

በብሄረሰቡ በዋንኛ ምግብነት ከአስር የማያንሱ የእንሰት ውጤቶች ይዘጋጃሉ። በልዩ ማህበራዊ ግንኙነት ወቅት የሚዘጋጅ የቆጮ ድፎ «ኮባና» ይባላል። በገንፎና በቂጣ መልክ የሚዘጋጀው ቡላም «ኬዳኦ» የሚል መጠሪያ አለው። የቆጮ ገንፎ «ናቱ» ሲባል ከጎመንና ከቆጮ የሚዘጋጀው ፍርፍር ደግሞ «ዎቶ» ይሰኛል። «ፈጨ» የሚባለውም ለህፃናት ምግብነት የሚዘጋጅ ነው።

ከብሄረሰቡ ባህላዊ መጠጦች ዋናው «ቦርዴ ማኡሻ» ይባለል። የሚዘጋጀውም ከገብስ፣ ከዳጉሳ፣ ከቀይ ጤፍና ከብቅል ነው። የጥራት ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ የሚዘጋጀው ሌላው ባህላዊ መጠጥ ደግሞ «ኪአ» የሚል መጠሪያ አለው። ይህ የመጠጥ አይነት ውሃ ሳይጨመርበት ድፍድፉ ብቻ ተጨምቆ የሚቀርብ በመሆኑ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተወዳጅ መሆኑ ይነገርለታል። በልዩ ዝግጅት ወቅት የሚዘጋጀው ባህላዊ መጠጥም «ኡሻ» ይባላል።

በየም ብሄረሰብ በዘመን መለወጫነት የሚታወቀው በዓል መስቀል ሲሆን በብሄረ ሰቡም ዘንድ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ተወላጆቹ በዓሉን «ሄሄቦ» ሲሉ ይጠሩታል። ትርጓሜውም የዓመቱ የመጀመሪያ ወር እንደማለት ነው።

በዘመድ አዝማድ መካከል የቆየ ቅሬታና መቀያየም ቢኖር ከበዓሉ በፊት መስከረም አስራ አራት ቀን እርቅ እንዲወርድ ይደረጋል። ቂምና ጥላቻን ይዞ ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገር ነውር ነው።

የመረጃ ምንጭ : www.sewasew.com

እነሆ ጥቅምት 17 ደረሰ - ሳሞ ኤታ _ የየም ፈውስ ተራራ እና ዓመታዊ የእጽዋት ለቀማ ኩነት፡፡ ቦር ተራራ ላይ እንገናኝ !
19/10/2023

እነሆ ጥቅምት 17 ደረሰ - ሳሞ ኤታ _ የየም ፈውስ ተራራ እና ዓመታዊ የእጽዋት ለቀማ ኩነት፡፡ ቦር ተራራ ላይ እንገናኝ !

Travel & Explore The Yem people - The Former Kingdom of Yamma ! አስደናቂውን የየም ህዝብ ባህል ፣ ታሪክ ፣ ቋንቋ እና ቅርስ እንዲሁም በዞኑ የሚገኙ ተፈ...
12/10/2023

Travel & Explore The Yem people - The Former Kingdom of Yamma ! አስደናቂውን የየም ህዝብ ባህል ፣ ታሪክ ፣ ቋንቋ እና ቅርስ እንዲሁም በዞኑ የሚገኙ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም መስህቦችን ይጎብኙ !

Click Visit Yem to Follow & See Updates On Facebook

Checkout Our Instagram Page -

Follow Us On Instagram !
12/10/2023

Follow Us On Instagram !

Travel & Explore The Land Of Wonders ! Follow Visit Yem የደጋ አጋዘን እና የየም ህዝብ ምን ያገናኘዋል ? የምታውቁ Comment ላይ አሳውቁን ...      ...
07/10/2023

Travel & Explore The Land Of Wonders ! Follow Visit Yem

የደጋ አጋዘን እና የየም ህዝብ ምን ያገናኘዋል ? የምታውቁ Comment ላይ አሳውቁን ...

Visit Yem _ Beautiful Mountain Ranges For An Adventure Trip.በየም ዞን የሚገኙ ሰንሰለታማ ተራራዎችን ይጎብኙ !Travel & Explore The Land Of...
06/10/2023

Visit Yem _ Beautiful Mountain Ranges For An Adventure Trip.

በየም ዞን የሚገኙ ሰንሰለታማ ተራራዎችን ይጎብኙ !

Travel & Explore The Land Of Wonders !

Photo Credit : Asegid Sisay

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን23/01/16 ዓ.ምPhoto Credit : Asegid Sisay
04/10/2023

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን

23/01/16 ዓ.ም

Photo Credit : Asegid Sisay

Address

Saja

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Yem posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category