ቀለም ኢትዮጵያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን-Kelem Ethiopia Tourism Promotion

  • Home
  • ቀለም ኢትዮጵያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን-Kelem Ethiopia Tourism Promotion

ቀለም ኢትዮጵያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን-Kelem Ethiopia Tourism Promotion Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቀለም ኢትዮጵያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን-Kelem Ethiopia Tourism Promotion, Travel Company, .

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል አደረሳችሁ። አደረሠን። #ደብረታቦር #ቡሄ
18/08/2023

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል አደረሳችሁ። አደረሠን።
#ደብረታቦር
#ቡሄ

🔹 የቡሄ በዓል መሰረት ነሐሴ ፲፫ ቀን ➖ የዚህ በዓል መሰረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን ደብረ ታቦር ማለት በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብ...
17/08/2023

🔹 የቡሄ በዓል መሰረት
ነሐሴ ፲፫ ቀን

➖ የዚህ በዓል መሰረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን ደብረ ታቦር ማለት በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ የሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሶስት ደቀመዛሙርትን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበት፣ ፊቱ እንደፀሀይ የበራበትና ልብሱም እንደብረሀን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው፡፡
👉ማቴዎስ 17፣1-7፦
1- ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
2- በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።
3- እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
4- ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡— ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ፡ አለ።
5- እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፡— በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፡ የሚል ድምፅ መጣ።
6- ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።
7- ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡— ተነሡ አትፍሩም፡ አላቸው።
ደብረ ታቦር መሰረቱ ይሄ ሲሆን፦

➖ በአገራችን ክረምቱ፣ ጭጋጉ፣ ደመናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለ ኾነ በዓሉ ‹ቡሄ› ተብሎ ይጠራል፡፡ [ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ፣ በራ፣ብርሃን፣ደማቅ ማለት ነው] ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡

በዓለ ደብረ ታቦር ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን የገለጠበት፤ ብርሃን የታየበትና ድምፀ መለኮቱ የተሰማበት ዕለት ስለ ኾነ ‹የብርሃን› ወይም ‹የቡሄ› በዓል ይባላል፡፡

☑️በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፡፡ በዚህም በዓል ጅራፍ መግመድና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለዉ ፡፡
የመጀመሪያዉ ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህመም እናስብበታለን ፡፡ ሁለተኛዉ ደግሞ ድምጹ ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማዉ ሲገለጽ የተሰማዉን ነጎድጓድ ያስታዉስልናል፡፡የጅራፉ መጮኽ የድምፀ መለኮት ምሳሌ ሲኾን፣ ጅራፉ ሲጮኽ ማስደንገጡም ነቢያትና ሐዋርያት በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡

☑️ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን በገለጠበት እለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሳ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆችን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጡ፡፡ ታድያ ያንን ማስታወሻ “ቡሄ” ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የምናከብረውም ከዚህ በመነሳት ነው፡፡
------
#ኢትዮጵያ #ምድረቀደምት
Ⓒ📸Binyam

Address


Telephone

+251945562411

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቀለም ኢትዮጵያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን-Kelem Ethiopia Tourism Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቀለም ኢትዮጵያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን-Kelem Ethiopia Tourism Promotion:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share