Visit Konta

Visit Konta Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Visit Konta, Travel Company, .

ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ወደ ተፈጥሮ እቅፍ ይግቡ ፤ እያንዳንዱ እርምጃ መንፈስን ያድሳል ። 📸 ሹሩር ጋሼ !
25/03/2024

ጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ወደ ተፈጥሮ እቅፍ ይግቡ ፤ እያንዳንዱ እርምጃ መንፈስን ያድሳል ።
📸 ሹሩር ጋሼ !

ይቺ በአካባቢያችሁ ቋንቋ ምን ትባላለች/ለምንስ ትጠቀማለች ?
25/03/2024

ይቺ በአካባቢያችሁ ቋንቋ ምን ትባላለች/ለምንስ ትጠቀማለች ?

በኮንታ ዞን -ኮንታ ኮይሻ ወረዳ -ኦሽካ ዴንቻ "የላስቴ" ⛰️ተራራ⛰️ውብ ገጽታ !
17/03/2024

በኮንታ ዞን -ኮንታ ኮይሻ ወረዳ -ኦሽካ ዴንቻ "የላስቴ" ⛰️ተራራ⛰️ውብ ገጽታ !

 በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ በቀን 7/7/2016 ዓ/ም  በተፈጠረው የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል።አደጋው የተፈጠረው በሁለት እግር ሞተር ከኮይሻ አንድ ተሳፋሪ ጭኖ...
17/03/2024


በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ በቀን 7/7/2016 ዓ/ም በተፈጠረው የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

አደጋው የተፈጠረው በሁለት እግር ሞተር ከኮይሻ አንድ ተሳፋሪ ጭኖ ወደ መሎ እየተጓዘ ከመሎ ሙዝ ጭኖ ሲመጣ ከነበረው አይሱዚ ጋር በተፈጠረው ግጭት ነው።

በዞኑ መሠል አደጋዎች እየተበራከቱ ስለሆነ አሽከርካሪዎች በእርጋታና በኃላፊነት በማሽከርከር ራስንና ሌላውን ከአደጋ መጠበቅ ይኖርባቸዋል።

ምንጭ: Balageru tube

ባለፈው አመት የአፈር ቆረጣና ከፈታ የተደረገውን የኡማ-ባኬ መንገድ ደረጃ የማሻሻል ስራን በዛሬው እለት አስጀምረናል።  ጠጠር ማልበስና ሌሎች የስትራክቸር ስራዎችን ጨምሮ  ከ22 ሚልዮን  ብ...
16/03/2024

ባለፈው አመት የአፈር ቆረጣና ከፈታ የተደረገውን የኡማ-ባኬ መንገድ ደረጃ የማሻሻል ስራን በዛሬው እለት አስጀምረናል። ጠጠር ማልበስና ሌሎች የስትራክቸር ስራዎችን ጨምሮ ከ22 ሚልዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ለማሰራት ከመንገድ ስራ ተቋራጭ ድርጅት ጋር ውል በመግባት የተጀመረ ሲሆን ስራው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የሚመለከታቸው አካላት ያልተቋረጠ ድጋፍን ይሻል።

ምንጭ : የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ !

በዩኔሲኮ የተመዘገበዉ የባዮስፈር አካል የሆነዉ የሸካ ደን ልዩ ገጽታ።               #ሸካ #ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀  ✅𝓽𝓱??  ✅𝓹𝓪𝓰𝓮https://www.f...
01/03/2024

በዩኔሲኮ የተመዘገበዉ የባዮስፈር አካል የሆነዉ የሸካ ደን ልዩ ገጽታ።


#ሸካ #
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

Ts'ooma shinchchale !
01/03/2024

Ts'ooma shinchchale !

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ "ጨበራ 🐘🐘ዝሆን 🐘🐘 ዳና ሎጅ በ3 ኪ.ሜ ርቀት በሚገኝ ጨበራ ማዘጋጃ ቤት ለንግድ እና መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በሊዝ ጨረታ እንዲጫረቱ አቀረበየካቲት 18/2...
26/02/2024

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ "ጨበራ 🐘🐘ዝሆን 🐘🐘 ዳና ሎጅ በ3 ኪ.ሜ ርቀት በሚገኝ ጨበራ ማዘጋጃ ቤት ለንግድ እና መኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ በሊዝ ጨረታ እንዲጫረቱ አቀረበ

የካቲት 18/2016 ዓ.ም "ኮንታ-አመያ"

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ የጨበራ ማዘጋጃ ቤት የ2016 ዓ.ም የ3ኛ ዙር የአንደኛ ጊዜ ለንግድ እና መኖሪያ ቦታ አዘጋጅቶ በሊዝ ጨረታ አቅርቧል።

ማዘጋጃ ቤቱም አየር ማረፊያ ገበታ ለሀገር ካምፕ፤ ወጊ አንድ እና ወጊ ሁለት መንደር ለመኖሪያ የሚሆኑ 6 ቁራሽ መሬቶችና ለንግድ የሚሆኑ 11 ቁራሽ መሬቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ አቅርቧል።

የጨበራ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ጋራደው አከባቢው ለመኖር ምቹ ከመሆኑም ባለፈ መሃል የቱሪስት መናገሻ እምብርት በሆነው በጨበራ ከተማ ላይ ለንግድ እና መኖሪያ የሚሆን መሬት በሊዝ ጨረታ መቅረቡን ገልጸዋል።

ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ 200 ብር፣ ለጨረታ ማስከበሪያ 2000 ብር የባንክ ማስረጃ "ሲፕዮ" የታሸገ እንዲሁም ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ከየካቲት 18 እስከ መጋቢት 2 ድረስ በተከታታይ አስር "10" በስራ ቀናት ውስጥ ጨረታ ሽያጭ በጨበራ ማዘጋጃ በመገኘት ሰነዱን መግዛት እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መጋቢት 3/7/2016 ዓ.ም ሲሆን ህዝብ በተሰበሰበበት ከጠዋቱ 3 ሰዓት እንደሚከፈት ገልጸው ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ተገቢው አካሄድ በመከተል ሊሆን እንደሚገባና በጨረታው ሂደት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎች መገኘት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አክለውም አቶ ታምሩ ለኢንቨስትመንት የሚሆን ምቹ ቦታ 10,000 (አስር ሺህ )ካሬ ሜትር ከይገባኛል ነጻ የሆነ ቦታ ለሁሉም ዘርፍ ምቹ ሜዳማ የመብራት፣የውሃ እንዲሁም መንገድ ዳር የሆነ ቦታ ኢንቨስት ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም አካል ዞን፣ወረዳና ማዘጋጃ ተቋም በመገኘት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ካፒታሉን አሳውቆ ቦታውን በሊዝ መነሻ ዋጋ ተወዳድሮ ማገኘት እንደሚቻል አሳውቋል ።
ለተመረጃዎችን መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRRወ

የኮንታ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሄዳልየኮንታ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ እንደሚያካሂድ...
26/02/2024

የኮንታ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 21ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሄዳል

የኮንታ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

ጉባኤው ከየካቲት 19-20/2016 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎም ይጠበቃል።

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

በከፍተኛ ውጤት መንትየዎቹ 👏👏👏    ትላንትና ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁለት መንታ እህትማማቾች     በክልኒካል ፍርማስ በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል። መንታዎቹ Lensa...
25/02/2024

በከፍተኛ ውጤት መንትየዎቹ 👏👏👏

ትላንትና ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁለት መንታ እህትማማቾች

በክልኒካል ፍርማስ በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል። መንታዎቹ Lensa Busho እና lense Busho።

እንኳን ደስ አላችሁ!

25/02/2024

በከፍተኛ ውጤት መንትየዎቹ 👏👏👏

ትላንትና ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁለት መንታ እህትማማቾች

በክልኒካል ፍርማስ በከፍተኛ ውጤት ተመርቋል። መንታዎቹ Lensa Busho እና lense Busho።

እንኳን ደስ አላችሁ!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት የሀገር ዉስጥ ቱሪዝም ንቅናቄን አስመልክቶ በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ የሚገኘዉን ሸክሸኮ ፏፏቴ ፣ የባሮ ...
20/02/2024

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት የሀገር ዉስጥ ቱሪዝም ንቅናቄን አስመልክቶ በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ የሚገኘዉን ሸክሸኮ ፏፏቴ ፣ የባሮ ወንዝና በጨዋቃ ሻይ ልማት ፕሮጀክት ላይ የተደረገ ጉብኝት በፎቶ 📷

የሰላም መናገሻዋ ኮንታ ለኑሮ ፣ለንግድ ፣ ለሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም ለሌሎች ኢንቨስትመንት ተመራጭ  የሚያደርጓትን በርካታ አማራጮችን ይዛለች።ኮንታ ለሰው፣ እንስሳትና ለዕጽዋት ህይወት ተስማ...
19/02/2024

የሰላም መናገሻዋ ኮንታ ለኑሮ ፣ለንግድ ፣ ለሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም ለሌሎች ኢንቨስትመንት ተመራጭ የሚያደርጓትን በርካታ አማራጮችን ይዛለች።

ኮንታ ለሰው፣ እንስሳትና ለዕጽዋት ህይወት ተስማሚ የሆነውን ሁሉንም የአየር ንብረት ከእጅዋ አድርጋለች፤ ይህ አየር ንብረቷ በዙሪያዋ የተለያዩ ፍራፍሬዎችንና የሰብል ምርቶችን በብዛት እንድታመርት ያስቻላት ሲሆን በዋነኛነት ሙዝን ጨምሮ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ለማይከላዊ ገበያ ማቅረብ በመቻሏ የዞኑ መገለጫም እስከመሆን ደርሷል፡፡
- 🐝ማር🐝፣ 🧈ቅቤ🧈 ፣ ☕ቡና☕ ደግሞ ሌለኛው መገለጫዋ ሆኖለታል !

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

17/02/2024

ጨበራ 🐘🐘ዝሆን🐘🐘 ዳና ሎጅ በአሜርካው አንባሳደር አንደበት !
ኮንታ-አመያ

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

ከ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጋር ተያይዞ ያሉ አሁናዊ መረጃዎች*****************************• 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሯል፡፡  • የመሪዎ...
17/02/2024

ከ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጋር ተያይዞ ያሉ አሁናዊ መረጃዎች
*****************************

• 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሯል፡፡

• የመሪዎቹ ጉባኤ በዋነኛነት የሚያተኩረው በአፍሪካ የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራት ላይ ነው፡፡

• የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋኪ መሐመት የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

• ሊቀመንበሩ በንግግራቸው ከአጀንዳ 2063 አተገባበር ጋር ተያይዞ ያሉ ጠንካራ እና ደከማ ጎኖችን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን በመዳሰስ ላይ ይገኛሉ፡፡

• ጉባኤው ላይ ንግግር ከሚያደርጉ የሀገራት መሪዎች አንዱ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በንግግራቸው ኢትዮጵያ ከትምህርት ጥራት ጋር ተያይዞ እየሰራቻቸው ያሉ ስራዎችን በስፋት እንደሚያነሱ ይጠበቃል፡፡

• በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ንግግር ያደርጋሉ፡፡

• ኢትዮጵያ ከጉባኤው ጎን ለጎን በመሪዎች እና በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የሁለትዮሽ ምክክሮችን በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

• እስካሁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት እና ከዙምቧቤ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ዳምቡድዞ ምናንጋግዋ ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አካሂደዋል፡፡

• በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና (ዶ/ር) ጋር መክረዋል፡፡

• ከዋናው የመሪዎቹ ጉባኤ ባሻገር ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ እድገት ያለውን ሚና እና የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት የሚዳስሱ 2 ትልልቅ ጉባኤዎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዘጋጅታለች፡፡

• አንደኛው ጉባኤ ከመሪዎቹ ስብሰባ ጎን ለጎን ዛሬ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ባ/ቱ/ስ/ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የወረዳው ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በደማቅ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።ኮይሻ፦ የካቲት 08/2016 ዓ/ም በኮንታ ዞን ...
17/02/2024

በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ባ/ቱ/ስ/ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የወረዳው ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በደማቅ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።

ኮይሻ፦ የካቲት 08/2016 ዓ/ም በኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ ወረዳ በኮይሻ ከተማ ከተጀመረ 6ኛ ቀን ያስቆጠረው የወረዳው ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር በደማቅ ሁኔታ ቀጥሏል።

መርሐ ግብሩም በሁለት ስፖርት ዓይነት ሲካሄድ የቆዬ ሲሆን ውድድሩም ፍጽም ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላ መሆኑ ታይቷል።

በዚህ ሁኔታ የምድብ ጨዋታ ተጠናቆ ወደ ጥሎ ማለፍ የተቀላቀሉ፡ ኮይሻ ከነማ፣ ዊ ብውል (we build/Salin)፣ ኤምዲ (MD) እና ኮይሻ 01 ስሆኑ በየካቲት 10/2016 ዓ/ም ዕለተ እሁድ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል።

⏩ MD vs ኮይሻ 01
⏩ ኮይሻ ከነማ vs ዊ ብውል (we build/Salin

ዘገባው : ኮመኮ
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ "በባህል እሴቶች፣ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣በብዝሃ ባህል አብሮነት፣ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና አሉታዊ መጤ ባህሎች" ዙሪያ ለተከታ...
15/02/2024

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ "በባህል እሴቶች፣ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣በብዝሃ ባህል አብሮነት፣ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና አሉታዊ መጤ ባህሎች" ዙሪያ ለተከታታይ 2 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ "በባህል እሴቶች፣ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣በብዝሃ ባህል አብሮነት፣ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና አሉታዊ መጤ ባህሎች" ዙሪያ ለ6ቱም ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አመራሮች፣ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በኮንታ ዞን ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊና የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ለማ ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑን በመግለፅ የባህል ዕሴቶችን እና ሀገር በቀል ዕውቀት ከፍ ለማድረግ እንደዚሁም ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችንና መጤ ጎጂ ባህሎችን ለማስቀረት ባለድርሻ አካላትን በስልጠና መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ አክሊሉ አያይዘውም ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ከስልጠናው የሚያገኙትን ዕውቀት ወደ ተጨባጭ ተግባር መቀየር የሚያስችል ቁመና መያዝ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የኮንታ ዞን ባ/ቱና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ ደምሴ ለሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው

"የአለም ሚዲያዎች የተቀባበሉትእውነተኛ ታሪክ /በኬኒያ/        ---------------------------------------------------------አንዲት ወጣት ኬኒያዊት  ሴት ለ...
15/02/2024

"የአለም ሚዲያዎች የተቀባበሉት
እውነተኛ ታሪክ /በኬኒያ/
---------------------------------------------------------
አንዲት ወጣት ኬኒያዊት ሴት ለልጅነት ጓደኛዋ የከፈለችው መስዋዕትነት

በልጅነት ጊዜዋ የምታውቀው ጓደኛዋ ከስንት አመት በኋላ በአደገኛ የዕፅ ሱስ ተጠምዶ ከሰው ተራ ወርዶ ተጎሳቁሎ ማደርያውን ጎዳና ላይ አድርጎ ታገኘዋለች።

በጣም ትደነግጣለች።እርሱም የወየበ ጥርሱን ፈገግ እያደረገ ስሟን እየጠራ ሩጦ ተጠመጠመባት።
ልጂቷ ሰው በዛ ደረጃ ይቆሽሻል ተብሎ ባማይታሰብበት ደረጃ የቆሸሸውን መጥፎ ጠረን ሽታ ያለውን ሰው ሳትሳቀቅ እቅፍ አደረገችው።

በኋላም ወደቤቷ ትወስደውና ገላውን አጥባ ልብሱን አስቀይራ ወደማገገሚያ ክፍል ወሰደችው።

እቺ ጥበበኛና ብልህ ሴት አመሉን ስለምታውቀው እንደአመሉ እየሆነች በብልሃት ጓደኛዋን ወደ ጥንት ማንነቱ የመመለሱን ፈታኝ ትወና ጀመረችው።

አስቡት እንግዲህ ሆደ ሰፊ መሆን የሚጠይቅ ስራ ነው።
ቅንነት ትእግስት አስፈላጊዎች ናቸው።ይሄን አይነት #ድራማዊ ትእይንት በኛ ሀገር ፊልም ላይ ነው ያየሁት።
የዚች ሴት ግን ልበ ብርሃን እና ፈጣሪዋን የምትወድ በመሆኗ የወሰደችው ሀላፊነት የሚከብድ ነው።

ትግሏን ቀጠለች።ወጣቱ ከሱስነቱ ቀስ በቀስ እየተላቀቀ ሰውነቱ እያገገመ አጥንቱ በስጋ እየሞላ በፎቶው እንደሚታዬው ሌላ አዲስ ሰው ሆኗል።
በፍቅር ለመኖር ወስነው ተጋብተዋል።

እናም በየአካባቢያችን የምናያቸውን ህመምተኞች ፍቅር እንክብካቤ ብንሰጣቸው እንደ ኬኒያዊው ወጣት የማይታደሱበት ምንም ምክንያት የለም።

⚂የፍቅር ሀያልነት የፈረሰውን ይሰራል ይሉታል⚂
ይሄ ነው።✔

♥ከይቅርታ ጋር ፎቶዎችን
እዪትና የተሰማችሁን ኮሜንት ላይ
አስቀምጡልን♥

♥እውነተኛ ♢ፍቅር♢ አያርጅም♥👍

አስተማሪ ስለሆነ. በየ ጉሩፑ ↩ሼር ↩ያርጉት ♢
Share
share
share

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ...
12/02/2024

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
ግበረሰዶም የሚያራምዱ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በሀገራችን ግበረሰዶምን ለማስፋፋት የሚያደርጉትን ድብቅ ጥረት በፅኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል። ፆታ መቀየር፣ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እንዲሁም ሁለት አይነት ፆታ መጠቀም በጥብቅ የተወገዘ ነው ብሏል።

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

*******ሱልሱዋ  (Sulsuwa)******የኮንታ ተወዳጅ ባህላዊ ምግብ ስሆን የሚዘጋጀዉ ከስጋ ተመርጦ ቀይ ስጋ ጎረድ ጎረድ ተደርጎ ይከተፍና ከሃሞት/ማንጼ እና ለመድሀኒትነት የሚውሉ የተ...
11/02/2024

*******ሱልሱዋ (Sulsuwa)******

የኮንታ ተወዳጅ ባህላዊ ምግብ ስሆን የሚዘጋጀዉ ከስጋ ተመርጦ ቀይ ስጋ ጎረድ ጎረድ ተደርጎ ይከተፍና ከሃሞት/ማንጼ እና ለመድሀኒትነት የሚውሉ የተለያዩ ቅመማቅመም እንዲሁም ሆድ የሚያርስ ቅቤ እንደልብ ከተጨመረ በኋላ በተለበለበና ክብ በተቆረጠ የእንሰት ቅጠል ላይ እየተደረገ/ወጭት ለክብር እንግዳና ለቤተሰብ አባላት ይሰጥና በተመረጠ ቆጮ ቂጣ ሱልሱዋ እንደመጠጣት ተደርጎ ይበላል።
ይህ ምግብ በዋናነት ከብርድ እና ጉንፋን መሰል በሽታዎች ያሸራል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ "የወርቅነህ 🏨 ሆቴል 🏨 " በዛሬው ዕለት የተመረቀ ስሆን እንደ ስሙ ጽዱ፣ ማራኪ እዲሁም ወርቅ የሆነ አልጋ ሙቅና ቀዝቃዛ ሻወር፣ ፖርክንግ፣ የህፃናት መጨዋቻ ከነ ...
11/02/2024

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ "የወርቅነህ 🏨 ሆቴል 🏨 " በዛሬው ዕለት የተመረቀ ስሆን እንደ ስሙ ጽዱ፣ ማራኪ እዲሁም ወርቅ የሆነ አልጋ ሙቅና ቀዝቃዛ ሻወር፣ ፖርክንግ፣ የህፃናት መጨዋቻ ከነ ምርጥ መስተንግዶ ጋር ዝግጁ በማድረግ እንግዶች ይምጡ ይዝናናሉ ይላቸዋል !

አድራሻ : አመያ 03 ቀበሌ ጋስት ሀውስ ፊት ለፊት !

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

በዛሬው ዕለት የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር በደረጃ 4 በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሰልጠኞችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል ።ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!...
10/02/2024

በዛሬው ዕለት የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር በደረጃ 4 በተለያዩ ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ሰልጠኞችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል ።

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

ለአድዋ ጦርነት ሰበብ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀፅ 17
10/02/2024

ለአድዋ ጦርነት ሰበብ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀፅ 17

እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሰን! ባጋ ናገኢክ ገልትኔን! ባጋ ናገኢክ ገኔኔን!ሀዋሳ የካቲት 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ የአሬንጓዴ ፈርጥ፣ በጌዴኦ አባቶች አገር...
10/02/2024

እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሰን! ባጋ ናገኢክ ገልትኔን! ባጋ ናገኢክ ገኔኔን!

ሀዋሳ የካቲት 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ዛሬ የደቡብ ኢትዮጵያ የአሬንጓዴ ፈርጥ፣ በጌዴኦ አባቶች አገር-በቀል ዕውቀት የዓለም ሳንባ ተምሳሌት እና የባለልዩ ጣዕም ይርጋጨፌ የተፈጥሮ ቡና ማህጸን በሆነችው ጌዴኦ ዞን፣ ሻላይቱ ዲላ፤ የጌዴኦ ዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች የፕሮግራሙ ተካፋይ መሆናቸውን የባሕልና ስፖርት ሚኒሰቴር መረጃ ያመለክታል።

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

09/02/2024

በኮንታ ዞን *ጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ገጽታ ! *

መነሻውን ከመቀሌ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ያደረገ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በወልዲያ ከተማ በቁጥጥር ሥር ዋለ። መነሻውን ከመቀሌ ከተማ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በማድረግ መዳረሻውን ባህርዳር  ያደረ...
07/02/2024

መነሻውን ከመቀሌ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ያደረገ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በወልዲያ ከተማ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

መነሻውን ከመቀሌ ከተማ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በማድረግ መዳረሻውን ባህርዳር ያደረገ ሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ.አ 18770 ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ መኪና በወልዲያ ከተማ በተለምዶ ጎንደር በር በሚባል ኬላ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሚሽነር ዘመዴ ግርማው እንደገለጹት መነሻውን መቀሌ በማድረግ ተደራቢ ስፖንዳ አስበይዶ የያዘውን የጦር መሳሪያ በጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አስረድተዋል።

በዚህም 48 የሞርተር ቅንቡላ፣ 64 ፊውዝና ካምሱር፣ 5867 የክላሽ ጥይት፣ 855 የዲሽቃ ጥይት 389 የብሬን ጥይት መያዙን ገልጸዋል፡፡

በቁጥጥር ሥር የዋለው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ጽንፈኛ ቡድን የክልሉን ሰላም ከማይፈልጉ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነ ትልቅ ማሳየ መሆኑን ጠቁመዋል።

Amhara Police Commission
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ !!!
✅𝓯𝓸𝓵𝓵𝓸𝔀 ✅𝓽𝓱?? ✅𝓹𝓪𝓰𝓮
https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR

አትሌት ጎይትቶም ገብረ ሥላሴ ለኢትዮጵያ አቦ ሸማኔ ጥበቃ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ኾና ተሾመች። የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዛሬ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደ ስነስርዓት ነ...
06/02/2024

አትሌት ጎይትቶም ገብረ ሥላሴ ለኢትዮጵያ አቦ ሸማኔ ጥበቃ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ኾና ተሾመች።

የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዛሬ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደ ስነስርዓት ነው የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆና የተሾመችው።

አትሌት ጎይትቶም የ18ኛው የዓለም አትሌቲክ ሻምፒዮና የማራቶኝ ውድድር አሸናፊ ድንቅ አትሌት ናት።

ከኮንታ ዞን አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫየኮንታ ዞን አስተዳደር በአቶ ማሞ ዶዮ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል፡፡ የኮንታ ህዝብ የእኩልነት ታጋይ፣ የታሪክና ባህል አዋቂ የሆ...
04/02/2024

ከኮንታ ዞን አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

የኮንታ ዞን አስተዳደር በአቶ ማሞ ዶዮ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃል፡፡

የኮንታ ህዝብ የእኩልነት ታጋይ፣ የታሪክና ባህል አዋቂ የሆኑት አቶ ማሞ ዶዮ ከአባታቸው ከአቶ ዶዮ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሰካኬ ገሹ በ1913 ዓ.ም በከሪበላ በደጉቻ ቀበሌ የተወለዱ ሲሆኑ በተወለዱ በ103 ዓመታቸው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የኮንታ ህዝብ መብቱ እንዲጠበቅና እኩልነት እንዲረጋገጥ አጥብቀው በመታገል ህይወት ዘመናቸውን ለህዝብ የታገሉና አባታዊ ግዴታቸውን ሲወጡ የኖሩ አባት ነበሩ።

አቶ ማሞ ዶዮ የቀድሞዋ ዱፓ ሾሻ የአሁኗ የአመያ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሲሆን ባለትዳር የ6 ሴት ልጆች እና የ5 ወንድ ልጆች አባት እንዲሁም የ39 የልጅ ልጆች አያትም ናቸው።

የኮንታ ህዝብ ባለውለታ የሆኑት አቶ ማሞ ዶዮ በተወለዱ በ103 ዓመታቸው ጥር 25/2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆኑ በዛሬው ቀን ማለትም ጥር 26/2016 ዓ.ም በአመያ ደ/ኤ/ቅ/ማርያም ቤ/ያን የቀብር ሰነ ስርዓታቸው ተፈፅሟል ።
የኮንታ ዞን አስተዳደር ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የኮንታ ህዝብ መጽናናትን፣ ለነፍሳቸው እረፍትን ተመኝቷል፡፡

በደብረ ታቦር ከተማ  የሃገር ባለውለታ ለሆኑት እቴጌ ጣይቱ  የሐውልት ምረቃ ና  በአንድ በጎፈ ቃደኛ ግለሰብ የተሠራ አራት የመማሪያ ክፍል ተመርቆል፡፡የሃገር ባለውለታ ለሆኑት እቴጌ ጣይቱ ...
03/02/2024

በደብረ ታቦር ከተማ የሃገር ባለውለታ ለሆኑት እቴጌ ጣይቱ የሐውልት ምረቃ ና በአንድ በጎፈ ቃደኛ ግለሰብ የተሠራ አራት የመማሪያ ክፍል ተመርቆል፡፡

የሃገር ባለውለታ ለሆኑት እቴጌ ጣይቱ በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ሐውልት የቆመላቸው መሆኑና እቴጌ ጣይቱም የተወለዱት ነሐሴ 12/1832 ዓ.ም በጌምድር ደብረ ታቦር ከተማ ነው፡፡

እቴጌይቱ በታሪካዊው በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነስተዋል፤ በዚሁ ቤተክርስቲያንም ዳዊት ተምረዋል፡፡

በተጨማሪም የሐውልት አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቄስ መልካሙ ላቀው እንዳሉት እቴጌይቱ ለሃገር ባለውለታ መሆናቸውንና ስመ ጥር የሆኑ ጀግኖችን መዘከር ለተተኪ ትውልድ ታሪክ ለማስተማር ይረዳል ብለዋል፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ ከንቲቫ ደሴ መኮነን እንዳሉት ለሐውልቱ 13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጭ እንደተደረገና ሐውልቱ በከተማ ነዋሪዎችና በመንግስት በጋራ የተሰራ መሆኑን በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተናግረዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞም በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር በአንድ በጎፈ ቃደኛ ግለሰብ የተሠራ አራት የመማሪያ ክፍል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

የመማሪያ ክፍሉ በታቦር አንደኛ፣መካከለኛ እና ልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት የተሰራ ሲሆን የመማሪያ ክፍሉን ያሠሩት በጎ ፈቃደኛ አቶ ንጉሴ ክንዴ በትምህርት ቤቱ ያሉ የመማሪያ ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ ምክንያት ለመስራት እንዳነሳሳቸው ገልፀዋል፡፡

አክለውም በትምርት ቤቱ ተምረው ማለፋቸውን ተናገረው ለመማሪያ ክፍሉ ግንባታ 4 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ አድርገው መገንባቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፈረስ ጉግሱና ሌሎች ትእይንቶችም ይቀጥላሉ

የደቡብ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን 25/2016 ዓ.ም

ሀላላ ኬላ በዓለም ቅርስነት ይመዝገብልኝ የሚል ጥያቄ እንደቀረበለት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ ። "ሀላላ" የዳውሮ ንጉሥ መጠሪያ ሲሆን፤ “ኬላ” የሚለው የድንጋይ ካብ (የመከላከያ...
01/02/2024

ሀላላ ኬላ በዓለም ቅርስነት ይመዝገብልኝ የሚል ጥያቄ እንደቀረበለት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ ።

"ሀላላ" የዳውሮ ንጉሥ መጠሪያ ሲሆን፤ “ኬላ” የሚለው የድንጋይ ካብ (የመከላከያ ካብ) የሚል ትርጓሜ አለው። ካዎ ሀላላ ድንጋይ ካብ (ሀላላ ኬላ) በአንድ ረድፍ 175 ኪ.ሜ. እና አጠቃለይ ርዝመት በሰባት ረድፍ 1225 ኪ.ሜ ይሸፍናል። ከ2.5 እስከ 5 ሜትር ስፋትና ከ2.5 እስከ 3.8 ሜትር በላይ ከፍታ አለው።

በውበቱ አግራሞትን የሚፈጥረው ይህ ድንቅ ኪነ-ሕንጻ የዳውሮ ህዝቦችን ጥንታዊ ስልጣኔ የሚያሳይ ነው። የግንባታዉ ሂደት ከ15ኛው እስከ 18ኛው ክ/ዘመን የዳውሮ ህዝብን ያስተዳድሩ የነበሩ 14 ነገሥታት በቅብብሎሽ የገነቡት እንደሆነ በዘርፉ የተሰማሩ ምሁራን እና በተለያዩ የታሪክ ፀሀፊዎች ተገልጿል።

ድንጋይ በድንጋይ ላይ በማነባበር ግዙፍ የሆኑ አለቶችን በታትኖ ይህንን መሰል ያልተወራለት ረዥም ግንብ በመገንባት ለታሪክ ማኖር የቻሉት ቀደምት የዳውሮ ነገስታት ጥለውት ያለፉት ቅርስ ሊጎበኝና ከቱሪዝምም አኳያ ትልቅ ጥቅም ሊገኝበት የሚችል ሀብት ነው።

ይህንን ድንቅ ኪነ ህንፃ በተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፣ ሣይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የክልሉ መንግስት ከዳውሮ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመሰነድ በዓለም ቅርስነት ይመዝገብልኝ የሚል ጥያቄ ለኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አቅርቧል።

በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የዓለም አቀፍ ቅርስ ሠነድ ዝግጅት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ተስፋዬ አራጌ የሐላላ ኬላን ጨምሮ፣ የሾንኬ መንደርና መስጂድ፣ የኤርታሌና ዳሎል በዓለም ቅርስነት ይመዝገቡልኝ የሚሉ ጥያቄዎች ለባለስልጣኑ መቅረባቸውን ያነሱት አቶ ተስፋዬ አንድ ቅርስ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ጥያቄ ከመቅረቡ በፊት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ባለማጠናቀቃቸው ጥናት እንዲደረግባቸው በሚል በ46ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፣ ሣይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጉባዔ ላይ ሳይቀርቡ መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የአርኪዮሎጂ ሥፍራ የሆነውን መልካ ቁንጥሬ በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ 46ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፣ ሣይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጉባዔ ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል።
ምንጭ : የክልሉ ባ/ቱና/ስ/ቢሮ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Konta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share