19/06/2024
የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች መምሪያ "የሕፃናት የትምህርት ተሳትፎ ጥራት ማሳደግ ጊዜዉ አሁን ነዉ" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ህፃናት ቀን እያከበሩ ነው
#ዲላ #ግንቦት 28/2016 ዓ.ም
ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች መምሪያ "የሕፃናት የትምህርት ተሳትፎ ጥራት ማሳደግ ጊዜዉ አሁን ነዉ" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ህፃናት ቀን በአፍሪካ ለ34ኛ ጊዜ እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአፍሪካ ህፃናት ቀን በደማቅ እያከበሩ ይገኛሉ።
የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ፓለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ዳይረክቶሬት ዳይረክቴር አቶ ዳንኤል ፀጋዬ መድረኩን በመሩበት ሰዓት እንዳስተላለፉት ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር እንደመሆኑ የህፃናት ህይወት ጉዳይ በቀዳሚነት ያሳስበዋል ለዚህም ለዜጎች ምቹና ሀገርን የሚያሻግር ትውልድ የሚፈጠርበትን አውድ መፍጠር ከዚህ የሚጀምር በመሆኑ ዛሬ የህጻናት ቀን በሚከበርበት አጋጣሚ ሁሉም የምጠቅበትን ኃላፊነት ጭምር የሚወስድበት ነው ብለዋል።
በየደረጃው የሚያጋጥሙ የበጀት እና የሎጅስትክ ችግር ለመፍታት ወደ መንግስት ብቻ ከመመልከት ይልቅ በአደረጃጀት መፍታት ስለምቻል አመለካከት እና ቁርጠኝነት ማስተካከልን ይፈልጋል ያሉት አቶ ዳንኤል በፓርቲ ሥር ተደራጅተው የሚገኙ የትኛውም የሴቶች አደረጃጀቶች ውጤት በሚያመጣ መልኩ ሥራቸውን ማከናወን አለባቸውም ብለዋል።
የጌዴኦ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ዘመናይ ህርባዬ በተለያየ አጋጣሚ ህፃናት ያለአግባብ ተወልዶ የሚጣሉበት እና ከሰበዓዊነት የጎደሉ ተግባራት ሲፈጸሙ ይስተዋላሉ ይህንን ሁኔታ ከአካባቢያችን በዘላቂነት ለማስወገድ ቀኑን ከማክበር ባሻገር ሁሉም አካል ኃላፊነቱን መወጣት አለባቸው ብለዋል።
የህፃናትን ትምህርት ጥራት ያለው እንዲሆን አስቀድመን የህፃናትን ደህንነት መጠበቅና ከጉልበት ብዝበዛ መጠበቁ መቅደም አለበት ያሉት ወ/ሮ ዘመናይ በየአካባቢው የሚስተዋለው የህፃናት ዝውውር የመከላከል ሥራ በትኩረት መሰራት አለባቸውም ብለዋል።
ወ/ሮ ዘመናይ አክለውም ከሚመለከታቸው ሰክቴሮች ጋር በቅንጅት በመሥራት በተለይም ከህግ ጉዳዮች ጋር ለሚፈጠሩ ችግሮች ከፍትሕ ተቋማት ጋር፣ እንዲሁም ለሰብዓዊ ድጋፎች ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ጋር በቅርበት ተግባቦት በመፍጠር ችግሮችን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
እያንዳንዱ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከበጀታቸው ላይ ቋሚ ድጋፍ በማድረግ በድንገት በጎዳና ላይ የሚጣሉ ህፃናት በቅቱ እየተነሳ ተገቢውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያገኙ መደረግ አለበትም ብለዋል።
እለቱን በማስመልከት መምሪያው ከዲላ ከተማ ለተወጣጡ አቅመ ደካማ እናቶች የምግብ ዱቄት ስጦታ ተሰጥቷል።
በመድረኩ መጨረሻም በእቅድ አፈጻጸም የተሻሉ የሆኑትን ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ማበረታቻ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። ዘገባው የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።