Visit Lemi kura sub city

  • Home
  • Visit Lemi kura sub city

Visit Lemi kura sub city Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Visit Lemi kura sub city, Travel Company, .

03/01/2024
03/01/2024

ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ!

ኢትዮጵያዊያን እንደ ድር ተጋምደን ያስመዘገብናቸው በዓለም አደባባይ ከፍ ያደረጉን አንፀባራቂ ታሪኮች አሉን።

ለአፍሪካውያን እንዲሁም ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት፣ የእኩልነትና የአትንኩኝ ባይነት አብነት የሆነው የአድዋ ድል የብሔር፣ የሀይማኖት እና መሰል ልዩነቶች ሳይገድቧቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አሻራቸውን ያሳረፉበት የወል ታሪካችን ነው።

አባት እናቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በጋራ ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ ታሪክ ሰርተዋል፤ የጋራ ታሪካችንን በአብሮነት ለመዘከር ግን በረባ ባልረባው ስንነታረክ ቆይተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቧራ ተነስንሶበት የነበረው የአድዋ ድል ታሪክ ተገልጦ ወርቅነቱ እንዲታይ ለማድረግና በዓመት አንድ ጊዜ ከመዘከር ባለፈ ዓመቱን ሙሉ እንዲወሳ የሚያደርገውን ግዙፉን የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ላለፉት የለውጥ ዓመታት ሲገነባ ቆይቷል።

ሙዚየሙ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የአድዋን ድል ታሪክ በአብሮነት እንዲዘክር የሚያስችል ቦታ ላይ ያረፈ ከመሆኑም በላይ ታሪኩን በተሟላ መልኩ እንዲዘክር ተደርጎ የተሰራ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ አገራዊ ፕሮጀክት ነው።

የአድዋን የድል ታሪክ ከአርበኞችና ከመሪዎች ነጥሎ ማየት ስለማይቻል በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም በተገቢው መልኩ የሚዘከሩበት ዕድል ተፈጥሯል።

የአድዋን ድል ስናነሳ የፈረሶቻችን ውለታ ባናወሳ የአድዋ ተራሮችም ጭምር ይታዘቡናል። በመሆኑም በሙዚየሙ የፈረሶቻችንን አሻራ የሚዘክሩ የጥበብ ስራዎችም ተካተዋል።

የአርበኞቻችንን ድል ከፍ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ዘመናዊ ጦር ታጥቆ የመጣውን ወራሪ ሀይል ጦር፣ ጋሻ፣ እና ጎራዴን በመሳሰሉ መሳሪያዎች በልበ ሙሉነት ገጥመው ድል ማድረጋቸው ነው።

በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየምም የመሰባሰቢያ አዋጁ የተጎሰመበትን ታሪካዊ ነጋሪት ጨምሮ ጋሻ እና ጦራችን በሚገባ እንዲዘከሩ ሆኗል።

የአርበኞቻችንን መውጣትና መውረድ ለማሳየት በአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች አምሳል የተገነባው የአድዋ ሙዜም ባረፉበት የጥበብ አሻራዎች ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ ነው!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

02/01/2024
31/12/2023
21/12/2023

"ብቃትና ንቃት ያለው የብልጽግናችን አመራር አባል ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ሚና አላቸው!!"
ወ/ሮ በቀለች ገ/ሚካኤል
የለሚ ኩራ ወረዳ 10 የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ

በለሚ ኩራ ወረዳ 10 የብልጽግና ፓርቲ የመሰረታዊ የህዋስና አመራሮችና አጠቃላይ አባላቶቻችን "ከእዳ ወደ ምንዳ" በሚለው የስልጠና ርእስ ለተከታታይ አራት ቀናት ከእዳ ወደምንዳ የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል።
ታድያ ይህ ስልጠና በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅና ምቹ የስልጠና ቦታዎችና ዝግጁ በማድረግ ከወዲሁ ለሰልጣኞች ዝግጁ ማድረጋችንን እንገልፃለን።

ለሚ ኩራ ወረዳ 10 የብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ
ታህሳስ 11/2016

31/08/2023
17/08/2023

Wal kabajuu, wal dhaggeeffachuu fi heddumina yaadaatti amanuun nageenya biyyaatiif bu'uura waan ta'aniif qixaan hojiirra oolchuun murteessaadha.

Nageenyi amansiisaa fi itti fufiinsa qabu mirkanaahuu kan danda'u hirmaannaa fi gumaacha lammiileen hundi taasisan bu'uureffachuudhaani. Nageenyi dhabamuun carraalee of harkaa qabnutti sirnaan akka hin fayyadamnee fi tasgabbii akka hin qabaanne waan nu taasisuuf dhimma xiyyeeffannoo addaa barbaadudha.

Mirkanaahuun nageenyaa misoomaaf, badhaadhina biyyaaf, akkasumas, jiruu fi jireenya lammiileetiif murteessaa waan ta'eef dhimmoota nageenya keenyaaf qormaata ta'an maqsaa, qaamolee faallaa nagaa dhaabbatan tokkummaan dura daabbachuun irratti qabsaahaa adeemuun murteessaadha.

Biyya nageenya amansiisaa mirkaneeffattee fi lammiilee ishee hundaaf mijattuu taate dhugoomsuuf duudhaalee tokkummaa fi obbolummaa keenya jabeessan, nageenya biyyaatis waaressan sirnaan kunuunsuu fi hojiirra oolchuun dirqama lammii hunda irraa eegamudha.

Galma yaadne ga'uuf nageenya keenya haa tikfannu, iddoo jirrutti gahee keenya haa bahannu.


17/08/2023

ሰላማችንን አጥብቀን የብልፅግና ጉዞዋችንን እናፋጥናለን!

ፓርቲያችን ብልፅግና በአካታቹ የመደመር መንገድ ሁሉንም አሰባስቦ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የያዘው ግብ በህዝባችን ይሁንታ አግኝቶ በስኬታማ ጉዞ ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያን ለማበልፀግ፣ ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ና ዴሞክራሲን ለመትከል፣ የሰጠው አመራር በተጨባጭም ፍሬ እያፈራ ነው። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማችንም ሆነ በአገር ደረጃ በአይን የሚታዩ፣ በእጅ የሚዳሰሱ ስኬቶች መመዝገባቸው የማይታበል ሀቅ ነው።

የኢትዮጵያን ብልፅግና የማይፈልጉ የውስጥ እና የውጭ የጥፋት ሀይሎች ጉዟችንን ማስቆም እንደማይችሉ ቢያውቁትም፣ ባለ በሌለ አቅማቸው መሰናክል በመፍጠር ለማጓተት በሚችሉት ሁሉ ተፍጨርጭረዋል።

የብልፅግና ጉዟችን ግን ለአፍታም አልተስተጓጎለም፤ አይስተጓጎልምም! ህዝባችንን አስተባብረን 24 ሰዓት በመስራት ዕቅዶችን በተያዘላቸው በጀት እና በተቀመጠላቸው ጊዜ የመፈፀም ባህል አዳብረናል።

ከልማት ስራዎቻችን እጆቻችንን እንድናነሳ ዛሬም እንደ ትናንቱ የሚመኙና የሚጥሩ ቢኖሩም ፣ስለ ሰላማችን፣ ለአፍታም ሳንዘናጋ፣ ለጋራ ብልፅግናችን ተደምረን ወደ ፊት እንገሰግሳለን!

10/08/2023

Raayyaan Ittisa Biyyaa Wabii Itoophiyaanotaati!!

Gaachana sabaaf sablammoota hundaa kan ta'e gootichi raayyaa ittisa biyyaa nageenya lammiilee fi birmadummaa biyyaatiif aarsaa lubbuu taasisuudhaan Itoophiyaan diinota ishee injifattee kabajaan akka jiraattuuf gumaacha qooda hin qabne taasisuun kan beekamudha.

Humnoota tokkummaa Itoophiyaanotaa diiguu, kabaja biyyaatis mulquuf hawwii qaban hunda dura dhaabbachuudhaan Itoophiyaan dachee kabajamtuu fi birmadummaa isheetis qaama biraatiif dabarsitee hin kennine akka taate gocha qabatamaadhaan agarsiisaa kan jiru gootichi raayyaa ittisa biyyaa har’as akkuma kaleessaa gootummaa addaatiin kabaja biyyaatiif kan dhaabbatedha.

Madaala gootummaa fi jaalala biyyaa kan ta’e gootichi raayyaa ittisa biyya keenyaa beelaa fi dheebuu , qorraa fi aduu , baddaa fi gammoojjii osoo hin jedhin kabajaa fi daangaa biyyaa eegaa jira.

Raayyan ittisa biyya keenyaa qaroo uummattoota biyya keenyaati.

10/08/2023

የምናተርፈው ከዘላቂ ሠላም እንጂ ከጥላቻና ቁርሾ አይደለም!!

ሠላም በጥላቻ፣በግጭትና በጦርነት ሲተካ ሀገራት በቀላሉ እንደሚፈርሱ ፣ ዜጎችም አገር አልባ ተሰዳጅ እንደሚሆኑ እነ ሊቢያና ሶሪያ የዛሬዎቹ አብነቶቻችን አይደሉምን?

ስለሠላም ሲባል ሁሉንም አማራጮች ማጤን ብልህነት ነዉ። ዘላቂ ሠላምን ማስፈን በራሱ የአንድ ሀገር ግንባታ ትልቁ አካል ነዉ ቢባል ትክክል ሊሆን ይችላል ።

ምክንያቱም የሠላም ግንባታዉ አስተማማኝ መሠረት ላይ ያልቆመ ሀገር አገራዊ ፍላጎቶችን ማሟላት ይቸገራልና።

ስለዘላቂ ሠላም ሲታሰብ ስለዘላቂ ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ማሰብ ነዉና ሠላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ማበርከት ይጠበቅበታል ።

የሠላም መደፍረስ የሥነ ልቦና ቀዉስን ሲያስከትል፣ ቁሳዊ ፣ ሰብአዊና ማህበራዊ ቀዉሶችን ሲያፈራርቅ ኖሯል።

የዛሬዉም ሆነ የነገዉ ትዉልድ የሚያተርፈው ከዘላቂ ሠላም ነዉ። ቂምና ጥላቻ ግጭትን ሲወልዱና ሲያዋልዱ እንጂ ለዘላቂ ሠላም መደላድል ሲፈጥሩ አልታዩም።

ዘላቂ ሠላም ኢትዮጵያ ለጀመረችዉ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነዉ። በዚህም መነሻ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ መንግስት ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ጭምር በሀሳብና በንግግር ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ተነሳሽነት ወስዶ እየሠራ ይገኛል።

ይህን ዘላቂ ሠላምን የማረጋገጥ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ።ልዩነቶችን በሀሳብና በንግግር በማረቅ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሁሉም ኃይሎች የየበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት አለባቸው ።

በተዛባ ትርክት ወደ ተዛባ አቅጣጫ የሚነጉዱ ኃይሎች በዜሮ ድምር ፖለቲካ ዉስጥ ከመዳከር የተለየ ዉጤት ሊያመጡ አይችሉም።

ማናቸዉንም ጥያቄዎች ማንሳት፣ መጠየቅ የሚያስችል ግልጽ የዴሞክራሲ ስርዓት ባለበት አዉድ ኃይልና ነፍጥ መፍተሔ መሆን አይችሉም።

ወደስክነት፣ ወደ ሚዛናዊነት፣ ወደ ህገ መንግታዊነትና ወደ ህጋዊነት መርህ መመለስ ያሻል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Lemi kura sub city posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share