Qafar inkih inkimara by Hassen k.ibn Ayfe

  • Home
  • Qafar inkih inkimara by Hassen k.ibn Ayfe

Qafar inkih inkimara by Hassen k.ibn Ayfe Fact

24/05/2022

Yirabbow isimil rabah nasri.

ni agiira kaqlissah. bural raaqe

marak dooqaay ken kasnay. inkinnah hawwene waynay

12/05/2022

የዶክተር ዐቢይ መንግሥት
▬▬▬▬▬

➔ልክ እንደ ልማት ፕሮጀክት ጦርነትን Phase 1, Phase2, Phase 3... እያለ በምዕራፍ በምዕራፍ የሚከፋፍል፤

➔በጦር ሜዳ ተገኝቶ የቀለበሰውን ትግል ወደ ዘላቂ ድል ይቀይረዋል ተብሎ ሲጠበቅ ወደ ከባድ ትግል ቀይሮት የሚመለስ፤

➔የተዳከመን ጠላት ከማክሰም ይልቅ የዝግጅት ጊዜ ሰጥቶ እንዲያገግም ማድረግ የሚመቸው፤

➔የደብረ ጽዮንን ጦር ልክ እንደ ሞሶሎኒ ጦር ወራሪ አድርጎ የተወሰኑ ክልሎችን ተወራሪ ያደረገ፤

➔የጦር ሜዳ ድል ሲጨብጥ ፖለቲካዊ ትግሉን እርግፍ አድርጎ የሚተው፤

➔ሕዝብ "ተወረርኩ" ብሎ ሲጣራ የእርሻ ማሳ የሚጎበኝ፣ የሕዝብ ጩኸት ሲያባራ ደግሞ ከጦር ግንባር የሚገኝ፤

➔የፖርክና መናፈሻ ፕሮጀክቶችን እንጂ ጦርነትን የመጨረስ ፍላጎት የሌለው፤

26/04/2022
31/03/2022

ዓለም አቀፍ ለጋሾች ችግር ውስጥ ያለውን የአፋር ህዝብ አልፈው “ትግራይን እንርዳ” ማለታቸው አግባብ አይደለም-የአፋር ክልል

የአፋር ክልል ስድስት ወረዳዎች አሁንም በህወሓት ቁጥጥር ስር በመሆናቸው የተዘረፈውን ሀብት ማወቅ አልተቻለም ተብሏል

“የአፋር ሕዝብ እንደፍየል እና እንደዝንጀሮ በየቦታው ፈሶ እሱን ወደኋላ አድርገን የትግራይ ሕዝብ ብቻ ይረዳ የሚል ቋንቋ ትክክል” አይደለም ሲል የአፋር ክልል በዓለምአቀፍ ለጋሾች ላይ ቅረታውን አቅርቧል፡፡

የአፋር ጤና ቢሮ ኃላፊ ያሲን ሀቢብ እንደገለጹት በአፋር ክልል በርካታ ዜጎች በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው በየቦታው ነው ያሉት፡፡ የቢሮ ኃላፊው ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች በየቦታው እየወለዱ፤ ለውኃ ጥምና ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህ ባለበት ሁኔታ ዓለም አቀፍ ለጋሽ አካላት በአፋር አልፈው ዕርዳታ ለትግራይ ሕዝብ ማድረስ እንደሚፈልጉም የቢሮ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ዕርዳታ ማግኘት እንዳለበትና መጎዳት እንደሌለበት እንደሚያምኑ የገለጹት ኃላፊው፤ አፋር ክልል ላይ በችግር ውስጥ የፈሰሰውን ህዝብ ጥሎ ማለፍ ግን አስቸጋሪ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አቶ ያሲን ሀቢብ የአፋር ሕዝብ እንደሌላው ጉልበትና የዓለም ሚዲያ እንደሌለው አንስተው “እኛ ግን የምንችለውን ሁሉ እንሰራለን” ሲሉ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ ከጤናና ከሰብዓዊነት አንጻር አፋር ክልል ላይ የፈሰሰውን ህዝብ ጥሎ ማለፍ አስቸጋሪ እንደሆነም ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

“እኛ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ችግር የለብንም፤ ቢረዳም ችግር የለብንም፤ እኛ የምናየው ከጤናው ረገድ ነው” የሚሉት ኃላፊው የአፋር ሕዝብ ድጋፍ ሳያገኝ እሱን በማለፍ ትግራይን ብቻ እንርዳ የሚለው ጉዳይ “ትንሽ ከእርዳታ አለፍ ያለ ሌላ ነገር ነው የሚመስለው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እሱን እንደክልል መንግስት እየተሰራበት መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት በአፋር ክልል አንድ ሆስፒታል፣ 21 ጤና ጣቢያዎች፤ 55 ጤና ኬላዎች በህወሃት ኃይሎች መዘረፋቸውንም የጤና ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ በጦርነት ከወደሙት የጤና ተቋማት መካከል 17 ጤና ጣቢያዎች እና 30 ጤና ኬላዎች እንዲሁም አንድ ሆስፒታል ስራ እንዲጀምሩ መደረጉን የክልል ጤና ቢሮ አስታውቋ፡፡

አሁን ላይ ወደ አገልግሎት የተመለሰው የከልዋን ሆስፒታል ሲሆን ጭፍራ ጤና ጣቢያን ደግሞ ወደ ሆስፒታል ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑም ክልሉ ገልጿል፡፡ እንደክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ገለጻ በአፋር ክልል ስድስት ወረዳዎች በህወሃት ቁጥጥር ስር ስለሆኑ ምን ያህሉ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ማወቅ አልተቻለም፡፡

በአፋር ክልል በህወሃት ቁጥጥር ስር በሚገኙ ወረዳዎች ጦርነት እንደነበረ አል ዐይን አማርኛ በሰመራ ከተማ ተገኝቶ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

አንድ አመት ከሰባት ወር የሞላው በኢትዮጵያ ተቀሰቀሰው ግጭት፤ በሰላም እንዲፈታ አሜሪካ እና የአፍሪካ ህብረት ጥረቶች እያደረጉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

በግጭቱ በትግራይ፣በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው በመፈናቀል ኑሯቸው እንዲመሰቃቀል ሆኗል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ማንኛውንም የሰላም አማራጭ እንደሚከተል አስታውቆ ነበር፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ መንግስት የሰብአዊ እርዳታ በአግባቡ ወደ ትግራይ እንዲደርስ ለማስቻል የተኩስ አቁም ማወጁን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የመንግስትን መግለጫ ተከትሎ ህወሓት ባወጣው መግለጫ ሰብአዊ እርዳታ በአግባቡ ወደ ትግራይ የሚገባበት ሁኔታ ከተፈጠረ ተኩስ ለማቆም ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መንግስት ከግጭት ማቆም ውሳኔው በኋላ ወደ ትግራይ እርዳታ ለማድረስ ቢሞክርም፣ ህወሃት በአፋር ክልል በኩል ያለውን አብአላ መንገድ በመዝጋቱ እርዳታ አለመድረሱን ቀደም ብሎ ጠይቋል፡፡ ህወሓት ግን እርዳታ አልደረሰም እያለ ይገኛል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዛሬው እለት አፋር ሰመራ የነበሩ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በአብአላ በኩል ወደ ትግራይ መጓጓዛቸውን ገልጿል፡፡

30/03/2022

" አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ሊኖር አይችልም " - አቶ ሰዒድ ሙሳ ኢብራሒም (የኤሬብቲ ጎሣ መሪ)

አፋር ክልል ውስጥ የቀጠለው ጦርነት " ለሰብዓዊነት ሲባል በታወጀው ግጭት ማቆም " ውሳኔ ላይ አደጋ መደቀኑን ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

ሮይተርስ፤ አፋር ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን 2 የሰብአዊ ርዳታ ሠራተኞች እንዳረጋገጡለት አስነብቧል።

በአፋር 6 ወረዳዎች በትግራይ ኃይሎች መያዛቸውን ዘገባው ገልጿል።

የአፋር ኤሬብቲ ጎሣ መሪ አቶ ሠዒድ ሙሳ ኢብራሒም ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፥ " አፋር ውስጥ ጦርነቱ ቀጥሎ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም ሊኖር አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አህመድ ሃሪፍ ፤ በትግራይ ኃይሎች ተይዘዋል ካሉት 6 ወረዳዎች 2ቱ ውስጥ ጦርነቱ መቀጠሉን፤ በክልሉ መዳረሻ ላይም በከፍተኛ ሁኔታ የትግራይ ኃይሎች እየተበራከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የህወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት ቃል በተጠቀሱት አካባቢዎች ውጊያ የለም ሲሉ አስተባብለዋል።

በአፋር ክልል አቅራቢያ ተዋጊዎቻቸውን እያሰፈሩ ነው ስለመባሉ ግን ማስተባበያ አልሰጡም ሲል ሮይተርስ ገልጿል።

በሌላ መረጃ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።

አምባሳደር ጃኮብሰን ፤ አሜሪካ በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የገለፁ ሲሆን አቶ አወል አርባ ህወሓት እያደረሰ ነው ያሉትን ስቃይ የዓለም ህብረተሰብ በፅኑ ሊያወግዘው ይገባል ብለዋል።

21/03/2022

05/03/2022
05/03/2022

📕ያለፍክበት የሕይወት መንገድ አስሮ ሊይዝህ አይገባም ፤ ነገህን መወሰን የራሳህ ምርጫ ነው፡፡

📕በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሐዘን ምክንያት አትኹን፡፡

📕ዝምታ ፣ በውስጡ ትልቅ ጩኸት የያዘ የማይጠየቅ ጠያቂ ፣ የማይመረመር መርማሪ ነውና ከዙሪያህ ካለ የሰዎች ጫጫታ በላይ በላይ የውስጥ ዝምታህን አድምጥ ፡፡

📕በምድር ላይ ምንም ፍጹም ነገር የለምና አንተም ፍጹም ለመሆን አትሞክር ሰዎችም ፍጹም እንዲሆኑ አትጠብቅ ነገር ግን ኹሉን በመልካምነትና በቅን ልቦና አከናውን ፡፡

📕ያለህን ችሎታ ፣ አቅም ፣ ዕውቀት አንተ ካላከበርከውና ካላወጣኸው ማንም መቶ ሊያከብርልህና ሊያወጣልህ አይችልም ፡፡ ስለዚህ ከተቀምጥክበት ተነሳና ከምኞት ወተህ ወደ ተግባር ተሻገር ፡፡

📕በሕይወትህ ትልቅ መከራ ፣ ችግር ፣ ሀዘን ደርሶ ሊሆን ይችላል ፤ "ሰው እንዴት በዚህ ውስጥ ያልፋል?" ብለህ አዝነህ ፣ ተክዘህ ሊሆንም ይችላል ፡፡ ግን በሕይወት ዘመን መዘንጋት የሌለብህ ነገር "ተስፋ" የሚባል ነገር መኖሩን ነው ፡፡

📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖
ከሜሎሪና መጽሐፍ የተወሰዱ ሃሳቦች
📚📚📚📚📚📖📖📖📖📖📖

ሜሎሪና - ታሪካዊ የሥነልቦና ልብወለድ

መልዕክቱን ለሌሎች ያጋሩት፤ ይጠቀሙበታልና መጽሐፉ በተገኘበት ተገዝቶ ይነበብ፡፡

21/02/2022
20/02/2022
16/02/2022
15/02/2022
15/02/2022
13/02/2022

👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍

24/01/2022

አሸባሪው ህወሀት በአፋር ውስጥ ገብቶ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ አሁንም በኪልበቲ ረሱ /ዞን/ ጦርነት ከፍቷል!

አሸባሪው ህወሀት በአፋር ክልል ውስጥ ገብቶ የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ለማካካስ በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በአብአላና በመጋሌ ወረዳ የከፈተውን ውጊያ አጠናክሮ ቀጥሏል። ምንም አይነት ሰብአዊነትና ርህራሄ ፈፅሞ የሌለው አሸባሪው ቡድን በንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመክፈት እያሸበረ ይገኛል።

ሁሌም ከትንኮሳ አርፎ የማያውቀው የሽብር ቡድኑ ለዘመናት የቆየውን በድንበር የሚዋሰኑ የአፋር እና የትግራይ ህዝቦችን ግንኙነት ከምንም ሳይቆጥረው ሁለቱን ህዝቦች በማጋጨት የማይረባ ትርፍ ለማግኘት ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል። እያደረሰ ባለው ጥቃትም የአፋር ንፁሃን ኢላማ በማድረግ የሽብር ተግባሩን በማስፋት ላይ ነው።

በዛሬው እለት እንኳን በኪልበቲ ረሱ (ዞን) በተለያዩ ቦታዎች የአፋር ክልልን ወሰን ጥሶ በመግባት በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁሀንን ለጉዳት ዳርጓል።

ይሁንና ሁሌም በማጭበርበርና በውሸት ፕሮፖጋንዳ እድሜውን የሚያራዝመው ጁንታው በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በኩል ዘልቆ በመግባት ንፁሀን የጎዳ ቢሆንም ጥቃት እንደተፈፀመበት አስመስሎ በማቅረብ አሁንም ማደናገሪያውን እየነዛ ይገኛል።

አሸባሪው ህወሀት በአራት ዞኖች ውስጥ በ 21 ወረዳዎች ወረራ በማካሄድ የአፋር ህዝብን በአሰቃቂ ሁኔታ ቢጨፈጭፍም፣ በብዙ ቢሊየኖች የሚገመት ሀብት ንበረት ቢያወድም፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ እንዲሰደድ ቢያደርግም ለጎረቤት ትግራይ ህዝብ ሰብአዊነት ሲባል እርዳታ በአፋር አብአላ በኩል እንዲያልፍ እየተደረገ ነበር። ነገር ግን ጁንታው ለትግራይ ህዝብ እንኳን ምንም አይነት ርህራሄ እና እዝነት ባለመኖሩ በዚሁ ቀጠና ግጭት በመፍጠር አካባቢው የግጭት ቀጠና እንዲሆን እና ሰብአዊ እርዳታ እንዳያልፍ አድርጓል።

የትግራይ ህዝብም የዚህን አሸባሪው ህወሀት እብደት በቃህ ሊል ይገባል፣ በግልፅ እየወጣ ያለውን ሴራውን እና ተንኮሉን በመረዳት ከህዝብ የሚበልጥ የለምና እንደ ህዝብ ሊቃወም ግድ ይላል። በውሸት ማወናበጃው ፈፅሞ ባለመታለል ለጥቂት የቡድኑ አባላት ጥቅም ሲባል የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን መገበር አይገባቸውም።

በአፋር በተለያዩ አካባቢዎች ወረራ አካሂዶ በሁሉም ግንባሮች ሽንፈትን አስተናግዶ የወጣው አሸባሪው ህወሀት አሁንም እንደ አዲስ በኪልበቲ ረሱ (ዞን) በኩል በከፈታቸው ግንባሮች የምድር ድሮኖቹ አስፈላጊውን መከታና ማጥቃት በማካሄድ የጁንታውን እብደት የሚያመክን በመሆኑ አሸባሪው ቡድን ዘልቆ ገብቶ ለመውረር ያስገባውን ሀይሉን አስቀድሞ ሊያወጣ ይገባል!

Via: የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

Edirs Mohammed |waydolali . Qusba meqe gada❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
22/01/2022

Edirs Mohammed |waydolali . Qusba meqe gada❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

Y AFAR  alfom y Ethiopa Poloticgna
17/01/2022

Y AFAR alfom y Ethiopa Poloticgna

መቸም አፋር ጀግና መውለድ ያውቃል

እስከ አሁን ከማውቃቸው ፖለቲከኛ ነን ከሚሉም ሀይማኖተኛ ነን ከሚሉትም ከሀቅ አጠገብ የማይርቅ "እነ እንትና ምን ይሉኛል?" የማይል በራሱ አቋም ልክ የሚያወራና የሚሞግት ሰው እንደ M***a Adem Oumer አልገጠመኝም!!

ሙሳ ሳያፍር እና ምን ይሉኝ ሳይል ነው ነጭ ነጯን ተናገሮ የሚመሸው!!

16/01/2022
16/01/2022

ጁንታውን አፅድተን በቀጣይ ጠላት የሚያስባት ኢትዮጵያ ሳትሁን እኛ የምናስባት ኢትዮጵያን እንፈጥራለን።

አይዟችሁ እንኳን ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ የሚበቃ የተፈጥሮ ሃብት አለን። በትንሹ ደሎል ለአፍሪካ የሚበቃ ከ100 የአባይ ግድብ የሚበልጥ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ይችላል። ደሎል የተለያዩ የተፈጥሮ ማዕድናት ተሸክማለች ከዚህ ውስጥ።
1 ፖታሺዬም
2 ሰልፈር
3 አይረን ኦክስሳይድ
4 ጨው
5 ወርቅ
6 ማግኒዝየም
7 ቤንቶናይት
8 አልሙኒዬም
9 እምነበረድ
10 ጂፕሰን
11 ፔትሮሊየም

በጣም የሚገርማችሁ ይህ ሁሉ የአፋር የተፈጥሮ ሃብት ጁንታው ፎቶ ከመነሳት ያለፈ ለኢትዮጵያ ለአፋር ህዝብ ምንም ጥቅም እንዳይሰጥ አድርጎት ነበር።የነዚህ ሁሉ ማዕዶናት ጥናትና ምርምር የተደረገው በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ነበር። ወርቁ ነዳጁ ሁሉም የት እንዳለ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተጠንቶ አልቋል። በቀጣይ ግን ሀብታችን ተጠቅመን ድህነት ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጓዳ እንዲወጣ ማድረጋችን አይቀርም።Ahmed Habib Alzarkawi

🇪🇹🇪🇹 ኢትዮጵያ አሸንፋለች 🇪🇹🇪🇹

ቴሌግራም ቻናሌን ተቀላቀሉ
https://t.me/realahmedhabibalzarkawi

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Qafar inkih inkimara by Hassen k.ibn Ayfe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share