29/02/2024
ሁለቱ ኩላሊቶቹ እየሰሩ አይደለም!
‹‹ የእኔ አንዱ ኩላሊቴ ለልጄ ስጡልኝና ›› - አባት
| ህፃን ልኡል አለማየሁ ኮሩ ይባላል።
የተወለደው አዲስ አበባ መጋቢት 2012 ዓ/ም ነው፡፡ ህፃን ልኡል በተወለደ 11ኛ ወሩ ላይ ነበር ቤተሰቦቹ ያልጠበቁት መርዶ ከጤና ተቋም የሰሙት ፡፡
ህፃን ልኡል አለማየሁ ሁለቱ ኩላሊቶቹ አይሰሩም፡፡ ወላጆቹ ይህንን ያልጠበቁት ዜና ከሰሙ ጀምሮ የልጃቸውን ህይወት ለመታደግ ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም አልፎ አልፎ የግል የጤና ተቋማት… ያረገጡት የመንግስት ሆስፒታል የለም፡፡
አባት የልጁን ህይወት ለመታደግ ‹‹ የእኔ አንዱ ኩላሊቴ ለልጄን ስጡልኝና ልጄ በህይወት አቆዩልኝ ›› ሲል ጥያቄ ቢያቀርብም ሆስፒታሉ የህፃኑ ኩላሊት ከአባትየው ኩላሊት ወስዶ ንቅለ ተከላ ማካሄድ የልጁ እድሜ እንደማይፈቅድ ተነግሮታል፡፡
ነገር ግን ሌላው አማራጭ የኩላሊቶቹ ህመም ለማስታገስ በሀኪሞች የታዘዘ መድኃኒት እየወሰደ ይገኛል፡፡ አባትየው ውጭ ሀገር ሄዶ ሌላ ሙከራ እንዳያደርግ የገንዘብ አቅም የሌለው በአንድ የመንግስት ተቋም በአነስተኛ ደሞዝ ተቀጥሮ እየሰራ የሚኖር ነው ፡፡ እናትየውም ቢሆን ስራ የላትም፡፡
ሌሎች ሁለት የልኡል ወንድሞችም ወንድማቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ያጋጠመው ከባድ በሽታ እየተመለከቱ እነሱም የወንደማቸው ስቃይ ዘወትር እንዳስጨነቃቸው ነው፡፡ አባታቸው አለማየሁ ሁሌ ጨንቀት ፣ ሀሳብ ውስጥ ላይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በዚህ መከራ ውስጥ ሙሉ የቤተሰብ አባላት ችግር እየተጋፈጡ እንሆ 4 ዓመታትን ተቆጠሩ፡፡
ልኡል እንደ እኩዮቹ ሜዳ ላይ ሆኖ መቦረቅ ይፈልጋል ግን አልቻለም፡፡ ይነሳል ፤ ይወድቃል፡፡
ህፃን ልኡል የካቲት 12 ሆስፒታል፣ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም የተለያዩ የግል የህክምና ተቋማት የጤናው ሁኔታ ለመከታተል በተለያዩ ጊዝያት ቢሄድም የጤናው ሁኔታ እስካሁን መሻሻል አላሳየም፡፡ አንዴ ደህና ሌላ ጊዜ የከፋ ህመም እየተፈራረቀበት እስካሁን በህመም ውስጥ አለ፡፡
ከአንዴም ሁለት ጊዜ የልዑል አባት አቶ አለማየሁ ስራ በነበረ ጊዜ ልጅህ ሞቷል ተብሎ ተነግሮት ወደ ቀብር ለመውሰድ በለቅሶ ላይ ሆነው ህጻን ልዑል በህይወት አለሁ ሲል የሲቃ ድምጽ አሰምቶ ከሞት ተርፏል፡፡
በአሁኑ ወቅት ህጻን ልኡል በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልተመላላሽ ታካሚ ነው፡፡ ሙሉቀን ደህና ውሎ ባልተጠበቀ ሰዓት ተዝለፍልፎ ይወድቃል፡፡ የኩላሊት ህመም ምን ያህል ከባድ መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡
የህክምና የመድሀኒት ወጪ እጅግ ከፍተኛ ገንዘብ በየጊዜው እየጠየቀ ቤተሰቦቹ ከሚችሉት አቅም በላይ ሆኖባቸዋል፡፡
እግዝአብሔር በፈቀደ ጊዜ ሙሉ የጤና ህክምና እስኪያደርግ ድረስ መድሀኒት እየተሰጠው እስካሁን በህይወት አለ፡፡ በመሆኑም ልጄ እያየሁት እንዳይሞትብኝ ውጭ ሀገር የተሻለ ህክምና እንዳደርግለት አለያም እዚሁ ሀገር ውስጥ በየቀኑ እያስቸገረኝ ያለውን የመድሀኒት መግዣ ገንዘብ እንዲሆነኝ የቻላችሁት እገዛ በማድረግ ህመሜን ተካፈሉኝ ሲል የህፃን ልኡል አባት እርዱኝ ሲል በትህትና ይጠይቃል፡፡
ህፃን ልዑል ለመርዳት
በወላጅ አባቱ በተከፈተው አካውንት ቁጥር
1000261011852
እንድትረዱት ይጠይቃችኋል።
የታማሚው ህፃን ልጅ አባት አለማየሁን ስልክ 09-13-21-40-27
ለሌሎች ወገኖች ሼር በማድረግም መልካምነታችሁን አሳዩ፡፡