Arba Minch - Gamo Area -The Gifted Land of Nature & Culture

  • Home
  • Arba Minch - Gamo Area -The Gifted Land of Nature & Culture

Arba Minch - Gamo Area -The Gifted Land of Nature & Culture To promote Tourist and Investment attractions in Gamo Zone

ከ30 በላይ  የውጭ ሀገር ዜጎች  ለጉብኝት አርባምንጭ  ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።አርባምንጭ ፣ መስከረም 26/2015 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦ጎብኝዎቹ ከዚህ ቀደም...
06/10/2022

ከ30 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ለጉብኝት አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው ።

አርባምንጭ ፣ መስከረም 26/2015 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦ጎብኝዎቹ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ በETAD ጉብኝት ኦፕሬተር አማካኝነት በግል አውሮፕላን ወደ አርባምንጭ ከተማ መምጣታቸውን የETAD ካምፓኒ ባለቤት አቶ ትዕግስቱ አዳኔ ተናግረዋል።

ጎብኝዎቹ በጀርመን ሀገር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ የሚሰሩና የትላልቅ ካምፓኒ ባለቤት መሆናቸው ተጠቁሟል ።

በኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻ ከሆኑ አካባቢዎች አርባምንጭ ግንባር ቀደም እና በሠላም እሴቷ የምትታወቅ ከተማ በመሆኗ ለጉብኝት መምረጧን አቶ ትዕግስቱ ገልጸዋል

ጎብኝዎቹ በቆይታቸው በዞኑ የሚገኙ የቱርስት መዳረሻ ቦታዎችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ታውቋል።

ቱሪስቶቹ አርባምንጭ ኤርፖርት ሲደርሱ የጋሞ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

በያዕቆብ ገጃ
Gamo Zone Office of Com.Affairs

ዮ ማስቃላ የማስ ስፖርት " ስፖርት ለባህላችን እና ለጤናችን" በሚል መሪ ቃል ተካሄደ ።ስፖርቱን ያስጀመሩት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከተላላፊ እና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታ...
24/09/2022

ዮ ማስቃላ የማስ ስፖርት " ስፖርት ለባህላችን እና ለጤናችን" በሚል መሪ ቃል ተካሄደ ።

ስፖርቱን ያስጀመሩት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከተላላፊ እና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ለመከላከል የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዘውተር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

ዘውትር ብቁና ጤናማ እንድንሆን እና አሁን ያለንበት የበዓል ወቅት በመሆኑ እየበላንና የአካል ብቃ እንቅስቃሴ ካልሰራን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ብለዋል።
የዮ ማስቃላ በዓልን ስናከብር በሠላምና በፍቅር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የደቡብ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው አርባምንጭ ከተማን ከሚያሳውቁ ከዓሣው ፣ ሙዙ ፣ ሐይቆች በተጨማሪ የሠላም ፣የፍቅርና የአንድነት እና የስፖርት ከተማ መሆኗን አንስተው በዚህ አርባምንጭ ከተማ ተገኝተው በጋራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል ።

መስቀል በደቡብ ፣በጋሞ ፣በአርባምንጭ ልዩ ቦታ ያለው መሆኑን ገልጸው በመስቀል የተራራቀ የሚቀራረብበት ፣የተጣላ የሚታረቅበት ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶቻችን መጎልበት አለባቸው ብለዋል።

በዚህ ጊዜ ሜዳ ላይ ወጥቶ ያለስጋት ስፖርት መስራት የሕዝባችን እሴት መሆኑን አቶ ጥላሁን ተናግረዋል።

ሠላም ሲኖር ነውና ብልጽግና የሚታሰበው ያሉት አቶ ጥላሁን አንዳንድ ኃይሎች የሀገራችንን ሠላም በማደፍረስ ሀገራችንን ለማፈረካከስ ሲጥሩ ይታያሉ ሆኖም ይህ ምኞት እንጂ እውን አይሆንም ብለዋል።

ሁላችንም ከሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ጎን መሠለፍ አለብን ብለዋል።

የማስ ስፖርቱን ኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ እና ሌሎችየስፖርት አሰልጣኞች መርተውታል።
በማስ ስፖርቱ ላይ የዮ ማስቃላ በዓልን ለማክበር የመጡ የፌደራል ፣ የክልል ፣ የዞን የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የአካባቢ ተወላጆች እና ስፖርት አፍቃሪው የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ በማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፈዋል።

S- Gamo Zone Govt.Comm.A.O.

የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነትን የሚዘክር ሐውልት ተመረቀ *********************** የጋሞ አባቶች እርጥብ ሳር ይዘው ሰላም ያወረዱበትን የሰላም እሴት የሚዘክር ሐውልት ተመርቋ...
24/09/2022

የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነትን የሚዘክር ሐውልት ተመረቀ
***********************

የጋሞ አባቶች እርጥብ ሳር ይዘው ሰላም ያወረዱበትን የሰላም እሴት የሚዘክር ሐውልት ተመርቋል።

ሐውልቱ 4 ሜትር ከ70 ሴንቲ ሜትር ርዝማኔ ሲኖረው ሙሉ በሙሉ በፋይበር ግላስ መሠራቱ ተገልጿል።

አጠቃላይ ሥራውን ለማጠናቀቅ አራት ወራት የፈጀ ሲሆን በምረቃ በዓሉ የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሀገር ሽማግሌዎች መገኘታቸውን ከጋሞ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የተመረጡ አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/

EBC

21/09/2022
ኤሊ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ በዳራማሎ ወረዳ ስለሚገኘው እና የ578 ዓመት ዕድሜ ጠገቡ ታላቁ የኤሊ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን በሁለት ክፍሎች መረጃዎችን ለ...
20/09/2022

ኤሊ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ

በዳራማሎ ወረዳ ስለሚገኘው እና የ578 ዓመት ዕድሜ ጠገቡ ታላቁ የኤሊ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን በሁለት ክፍሎች መረጃዎችን ለማካፈል ወደድን አብራችሁን ቆዩ፦

የጋሞ ዞን የተለያዩ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ኃይማኖታዊ ቅርሶች ባለቤት ነው በዞኑ ረዥም እድሜን ካስቆጠሩ ታሪካዊ ገዳማትና ደብሮች በጋሞ ጎፋ ሀገረስብከት ከሚገኙ ጥንታዊ ገዳማት መካከል የኤሊ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዋነኛው ነው ።

የዳራማሎ ወረዳ ባህል ቱርዝም ጽ/ቤት በታላቁ የኤሊ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ውስጥ በቅስና አገልግሎት ከሚያገለግሉ መምህሬ እሸቴ ቢትው እና መምህሬ ዳንኤል ገለሱ በገዳሙ አመሰራረት ዙሪያ ያደረገውን ቆይታ የዳራማሎ ወረዳ መ/ኮሙኒኬሽን ለማስቃኘት ወደናል ።

ታላቁ የኤሊ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መገኛው በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ኤሊ ኮዶ ቀበሌ ሲሆን ገዳሙ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዘርዓ-ያዕቆብ ዘመነ መንግስት
እንደተመሠረተ በቅስና አገልግሎት የሚያገለግሉ አባቶች ይናገራሉ ።

በወቅቱ የግራኝ መሃመድ ጦርን በመሸሽ ፅላቱን በመያዝ አሁን ወዳለበት ስፍራ መምህሬ ይገዙ፣ መምህሬ ተገኝ፣ እና መምህሬ መንግስቱ የተባሉ የኃይማኖት አባቶች ይዘው መምጣታቸውን በገዳሙ ለበርካታ አመታት እያገለገሉ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ያስረዳሉ፡፡

በገዳሙ ህንፃ መቅደስ ውስጥ ከብሮ ስርዓተ አምልኮ መፈፀም ከጀመረ 578 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን በቅስና አገልግሎት የሚያገለግሉ አባቶች ያክላሉ ።

ታላቁ የኤሊ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በ1924 ዓ.ም ወደ ገዳምነት እንዲያድግ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ለረዥም ዓመታት ቆይቶ በ1954 ዓ.ም እንዲገደም ተፈቅዶ ወደገዳምነት መቀየሩን እና በወቅቱ ሀገረ ስብከት ባለመቋቋሙ ምክንያት በወቅቱ ኢትዮጵያ ከሚመሩ ነገስታት በሚመረጡ ባላባቶች እና ደጃዝማቾች ሲተዳደር ቆይቷል ብለዋል ።
በዳራማሎ ወረዳ ስለሚገኘው እና የ578 ዓመት ዕድሜ ጠገቡ ታላቁ የኤሊ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም.

የገዳሙ አሰራር እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክብ ቅርጽን ይዟል፡፡ የውስጡ ጣሪያ በጽድና ወይራ እንጨት የተሰራ ሲሆን ያለምንም ሚስማር በአከባቢው እንደሚገኝ ባህላዊ የሳር ክዳን ቤት ገመድ በሚመስል ማገር ዙሪያውን የተጠናከረ ነው፡፡ ይህ ማገር መሠል ገመድ የተማገረበት ልጥ እንዳይበጠስ በቅቤ የታሸ መሆኑን አባቶች ይናገራሉ፡፡

ሁለቱ አባቶች እንደሚያስረዱት የታላቁ ኤሊ ቅ/ገብርኤል ገዳም ውስጥ የነበሩ ፅላቶችንና ውድ የሆኑ ንዋዬ ቅድሳትን በደጃዝማች ገኔሜ አማካኝነት ወደ ሸዋ የአፄ ሚንሊክ ሰራዊት ወደ አከባቢው በመጣ ወቅት ከስፍራው መወሰዱን አስረድተው የአከባቢው ተወላጆች የኛ የሆነው ቅርሳችን ይመለስልን በማለት አዲስ አበባ ድርስ በንጉስ ችሎት በእግራቸው በመጓዝ መጠየቃቸውን ያስረዳሉ ።

በወቅቱ የጦር ሚኒስቴር የነበሩት ኃብተ ጊዮርጊስ የመጡበትን ጉዳያቸውን አስረድተው ደጃዝማች ገነሜን አሳመኗቸው ንጉሱም ጽላቱን ወደቦታው ይዘው እንደሄዱ ፈቀዱላቸው ፤በወቅቱ ጥያቄዎችን ይዘው አዲስ አበባ የሄዱ የአካባቢ ተወላጆች አቶ ፈልኣ አብ ፣ አቶ ዙላ ጫፍቆ፣ አቶ ሳዋሬ ሳንዶ ፣ አቶ ዱቃ ዕንጋ፣ አቶ ሻሜ ሰዋ፣ አቶ ማቃኝሳ እና ጫባኮ አንጮ የተባሉ ሽማግሌዎች መሆናቸውንም አስረድተውናል ።

በዚህ ታላቁ ገዳም ውስጥ ከ400 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ የተለያዩ ቅርሶች እንደሚገኙም አባቶች ይናገራሉ ከቅርሶች መካከል የወርቅ መስቀልን ፣የወርቅ ለምድ ካባ፣በብርና በነሃስ የተለበጡ አክሊሎች ከዝሆን ጥርስ የተሰራ መቋሚያ፣የተለያዩ የብራና መፃህፍት እና የሠጎን እንቁላሎች ይገኙበታል ።

እነዚህ ቅርሶች በሚፈለገው ልክ ጥበቃ እየተደረገላቸው አለመሆኑን የሚናገሩት የሃይማኖት አባቶች የሚመለከተው አካል ቅርሶችን አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደረግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

የዳራማሎ ወረዳ ባህል ቱርዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን በገዳሙ የኢትዮጵያ ቅርሶ ጥበቃ ባለስልጣን ገዳሙ በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ገዳሙን በቅርስነት የተረከበው ቢሆንም ለአጥር ማሳጠሪያ ሰባት መቶ ሺህ ብር ልኮ ከማሰራት ውጪ ቅርሶች የመንከባከብ እና ጥበቃ ስራ ላይ እየሰራ አለመሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም የጽ/ቤቱ ኃላፊ በገዳሙ የሚገኙ ቅርሶች ለቱሪሰት መስህብ ከመሆኑ ባሻገር በዞኑ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ ጉልህ ድርሻ ሊያበረክቱ የሚችሉ በርካታ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች በመኖራቸው የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባልስጣን እና ሀገረ ስብከቱ እንዲሁም የሚመለከተው አካል ለቅርሶች አስፈላጊውን ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የዳራማሎ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።

«ዮ …ማስቃላ» - የጋሞ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ*****************በጋሞ ብሔረሰብ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀውን «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓልን በድምቀት ለማክበር ሁሉም በየፈር...
20/09/2022

«ዮ …ማስቃላ» - የጋሞ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ
*****************

በጋሞ ብሔረሰብ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀውን «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓልን በድምቀት ለማክበር ሁሉም በየፈርጁ ዝግጅቱን ቀደም ብሎ ይጀምራል።

«ዮ ማስቃላ» በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ቅበላው ተከብሮ በዚሁ ወር መጨረሻ የ«ማስቃላ» ሽኝት በዓል በድጋሚ በድምቀት ይከበራል።

በብሔረሰቡ በተለያዩ ማህበራት በመደራጀት ገንዘብ የማሰባሰብ ዝግጅት የሚጀምሩት ቀደም ብሎ ነው፡፡ በዚሁ መልኩ ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል።

ይህ ተግባር በሁለቱ ፆታዎች የሚከናወን ዝግጅት ሲሆን ወንዶች ለበዓሉ የሚሆን ሠንጋ መግዣ፣ ለልጆች ልብስ እና ጌጣጌጥ ማሟያ፤ እናቶች ደግሞ በበኩላቸው ለቅቤ፣ ለቅመማ ቅመም፣ ለባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች እህል መግዣ የሚሆን ገንዘብ ማጠራቀም ያጠራቅማሉ።

ለማስቃላ በዓል የሚዘጋጁ ተወዳጅ ባህላዊ ምግቦች መካከል የገብስ ቅንጬ፣ ከቡላ ቆጮ እና ገብስ የሚዘጋጅ ቂጣ፣ የቡላ ፍርፍር፣ የሐረግ ቦዬ ሲሆኑ ቦርዴ፣ የማርና የቦርዴ ውህድ የመሳሰሉ ባህላዊ መጠጦችም በስፋት ይዘጋጃሉ።

በጋሞ ብሔረሰብ ዘንድ የማስቃላ በዓል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንሳስት እና ለአዕዋፋም ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል፤ በዕለቱ ምግብ ከሰው አልፎ ለእንሳስት እና ለአዕዋፍም ይትረፈረፋል፡፡ ለከብቶችም የግጦሸ መሬት በየአካባቢው ይከለላል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድረግ የጋሞ ማስቃላ በዓል መገለጫ ነው።

መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ብሔረሰብ ”ሂንግጫ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጀት የሚደረግበት ቀን ነው። የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ቀናትም ይገኛሉ።

ከገበያ ቀናቱ መካከል
• “ጋሜ ጊያ” የእርድ ከብቶች እና ለማስቃላ በዓል የሚሆኑ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ የሚገዛበት ነው፤
• “ዩሼ ጊያ” ወላድ እናቶች በማስቃላ በዓል ገበያ ወጥተው ዘና የሚሉበት ነው፤
• “ጎሻ ጊያ” የማስቃላ ዝግጅት ካበቃ በኋላ የመጨረሻው ገበያ ሆኖ እንደ ቅመማቅመም የመሳሰሉ ጥቃቅን ነገሮች የሚሸምቱበት እና ፈጥነው የሚመለሱበት በመሆኑ እንደወትሮው የደራ ገበያ አይሆንም።

ለ«ዮ…ማስቃላ» የሚደረጉት ዝግጅቶች ከተጠናቀቁ በኃላ ቀደም ሲል ለሶስት ወር ያህል ተከልሎ የቆየው የግጦሽ መሬት ለከብቶች ልቅ ይሆንና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በዓሉን ማክበር ይጀምራሉ።

በጋሞ ብሔረሰብ የማስቃላ የእርድ ሥነ-ሥርዓት ከቦታ ቦታ ይለያያል። የመጀመሪያው በደመራው ዕለት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በማግሥቱ ይፈፀማል።

እርዱ በየቡድኑ በተደራጁ ቤተ-ዘመዶች ወይም ጎረቤቶች ገበያ ላይ አልያም አማካይ በሆነ ቦታ ይከናወናል።

ከቡድኑ አባላት ሴቶች ቦርዴ እና ማባያ ይዘው በእርዱ ቦታ ይገኛሉ።

ከየሥጋው ዓይነት የተመተረውን ተሰባስበው ከቀማመሱ እና በቦርዴ ካወራረዱ በኋላ የድርሻቸውን ሥጋ ተከፋፍለው ይለያያሉ። ወደ ቤት እንደደረሱም ቤተሰብ ተሰብስቦ ቁርጥ ሥጋ ይበላል።

ከሰዓት በኋላ ወይም ማታ ለሁሉም ቤተሰብ የሚበቃ ጎረድ ጎረድ በቅቤ ተለውሶ በትልቅ ወጭት ላይ ቀርቦ በባህላዊ ማንኪያ ይበላል።

በ2ኛው እና በ3ኛ ቀናት ጎድን ጥብስ በቂጣ ይበላል። ከሐረግ ቦዬ ብቻ የሚዘጋጅ ተሰርቶ ዮ...ዮ...ማስቃላ በመባባል ለሚመጡ ሰዎች ከባህላዊ መጠጥ ጋር ሣምንቱ እስኪያልቅ ድረስ ይቀርባል።

በባህሉ መሠረት ችቦ የሚወጣበት ሰዓት ሲደርስ አባት የራሱን ችቦ ለኩሶ የቅቤ ምንቸቱን፣ የቤቱን ምሰሶ፣ የከብቶቹን ጋጣ እና የበር ጉበኖችን ግራ እና ቀኝ በችቦው ጫፍ ያነካካል።

ከዚያም ወደ ውጪ ሲወጣ ወንድ ልጆች የየራሳቸውን ችቦ ተራ በተራ እየለኮሱ እና አባትን ተከትለው ዮ..ዮ..ማስቃላ እያሉ በመጨፈር ወደ ደመራው ቦታ ከደረሱ በኋላ አባት በቀዳሚነት ልጆች ደግሞ በተከታይነት ደመራውን ይለኩሳሉ።

በዕለቱ የሚዘጋጀው ባህላዊ ምግብ ገንፎ ሲሆን ይህንን ወንዶች ከጭፈራ ሲመለሱ ተሰባስበው ከአንድ ወጭት ዮ...ዮ ማስቃላ እያሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድ እና ጎረቤቶች ያለ ልዩነት በጋራ ይመገባሉ።

በጋሞ ብሔረሰብ የሚከበረው የማስቃላ በዓል በሶፌ ሥርዓት የታጀበ ነው። የቀደመው ዓመት ማስቃላ በዓል ከተከበረ በኃላ የተጋቡ ሙሽሮች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ማምሻውን በአደባባይ ከመላው ህብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበት እና ሁለቱም ተጋቢ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ሥርዓት ነው።

በዚህ ወቅት የሚወጡ ሙሽሮች በተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጥ ተውበው ስለሚታዩ እንደቁንጅና ውድድር የተመልካችን ትኩረት ይስባል።

የመጨረሻው የማስቃላ ሽኝት በዓል ነው፤ ይህ ሥርዓት እንደየአባወራው አቅም በፈቀደ መጠን የሚፈፀም ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም ያለ ፆታ ልዩነት በአደባባይ ላይ ወጥተው ያኑረን እስከ ወዲያኛው እንኖራለን እያሉ ይጨፍራሉ።

ከዚህ በኋላ ለመጪው ዓመት በሠላም በጤና ያድርሰን ተባብለው ፈጣሪን በመማፀን ዝግጅቱ ይቋጫል።

የዘንድሮው የ2015 የጋሞ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል "ዮ....ማስቃላ"ን በድምቀት ለማክበር በልዩ ሁኔታ ዝግጅት መደረጉን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

« ዮ ማስቃላ!»

Source - EBC

በጋሞ ዞን ዘንድሮ በልዩ ሁኔታ የሚከበረውን የ"ዮ' ' ' ማስቃላ"ን በዓል ለማክበር የኪነ -ጥበብ ሰዎች በአርባምንጭ ከተማ ገቡ።የአርትስ ቴሌቭዥን ባለሙያዎች ፣ ገጣሚዎች ፣ ደራሲዎች ፣ ሰ...
18/09/2022

በጋሞ ዞን ዘንድሮ በልዩ ሁኔታ የሚከበረውን የ"ዮ' ' ' ማስቃላ"ን በዓል ለማክበር የኪነ -ጥበብ ሰዎች በአርባምንጭ ከተማ ገቡ።

የአርትስ ቴሌቭዥን ባለሙያዎች ፣ ገጣሚዎች ፣ ደራሲዎች ፣ ሰዓሊዎች ፣ ድምፃዊያን እና ሌሎች የጥበብ ሰዎች በጋሞ ዞን የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአርትስ ቲቪ የጦቢያ ግጥም በጃዝና ዝግጅት አስተባባሪ ወ/ሮ ምስራቅ ተፈራ እንደገለጹት አንጋፋው ደራሲ ዘነበ ወላን ጨምሮ 36 የጥበብ ሰዎች እንደተገኙ ገልፀዋል።

የጥበብ ባለሙያዎች በዞኑ በልዩ ሁኔታ የሚከበረውን የዮ- ማስቃላ በአልን ለመታደም እና በቆይታቸው በዞኑ የሚገኙትን ታሪካዊና ባህላዊ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ የቱሪስት መስህቦችን ለሀገር እና ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ በዞኑ የቱሪስት መዳረሻዎችን በነገው እለት እንደሚጎበኙም ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው የጋሞ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ነው።

ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በአርባምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ከ15 ዓመት በታች የፓይለት ፕሮጀክት የምዘና ውድድር በወንዶች ድሬዳዋ በሴቶች አርባምንጭ ዩኒቨርስ...
08/08/2022

ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በአርባምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ከ15 ዓመት በታች የፓይለት ፕሮጀክት የምዘና ውድድር በወንዶች ድሬዳዋ በሴቶች አርባምንጭ ዩኒቨርስቲን አሸናፊ አድርጎ ተጠናቋል።

አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 1-0 ድሬዳዋ
(በሴቶች)

1’ ፅዮን መሌ

ድሬዳዋ 0-0 አርባምንጭ (በወንዶች)

* ወደ መለያት አምርቶ ድሬዳዋ 5-4 አሸናፊ ሆኗል።

በወንዶች ዘርፍ የኮከብ ተሸላሚዎች

- ኮከብ ተጫዋች - አንሙት ደለልከኝ

- በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ - ተራማጅ ሰለሞን (በስምንት ጎል)

- ኮከብ ግብ ጠባቂ ምህረት ደበበ (ድሬዳዋ)

- ኮከብ አሰልጣኝ - በረከት ደሙ (አርባምንጭ)

በሴቶች ዘርፍ የኮከብ ተሸላሚዎች

- ኮከብ ተጫዋች - ረቂቅ አሰፋ (ሲዳማ)

- በከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ - ትሁን ገበየው (በዘጠኝ ጎል)

- ኮከብ ግብ ጠባቂ - ሀና ሸጋው (አርባምንጭ)

- ኮከብ አሰልጣኝ - ሙልጌታ ደበበ (አርባምንጭ)

* በስፓርታዊ ጨዋነት በሁለቱም ፆታ አዲስ አበባ ከተማ

* ትክክለኛውን ዕድሜ ይዞ በመቅረብ በወንዶች ተሸላሚ አርባምንጭ ፣ አዳማ፣ አዲስ አበባ፣ አማራ ወልድያ እና ጋምቤላ

* ትክክለኛ ዕድሜ ይዞ በመቅረብ በሴቶች ጋምቤላ ፣ሐረሪ፣ ሶማሌ፣ አዲስ አበባ፣ ኦሮምያ አጋሮ እና አሞ ከተማ

ምንጭ-ሶከር ኢ.

GAMO DUBUSHA " Dubusha" Untold story about Dubusha Dubusha had been a source of the judicial system before the introduct...
07/08/2022

GAMO DUBUSHA

" Dubusha"
Untold story about Dubusha

Dubusha had been a source of the judicial system before the introduction of the modern Democratic system in the southern part of Ethiopia, in the Gamo Zone, for a long period of time. In the Gamo zone, Dubusha serves as parliament where local leaders and elders make administrative laws and orders in their community.

The Dubusha system generates peace and stability between disputes. In Dubusha, local leaders and elders discuss social, economic and political affairs. And they pass law and order according to the community standard.

According to the sources in most Gamo communities, the structure of the customary courts has three levels: Guta dubusha, at the village level; sub-dere dubusha, at the kebele level; and dere dubusha at the higher level. Hence, cases would be heard at the guta dubusha level, if not settled, referring to the second and third levels of the structure.

The Dubusha system is performed in all parts of the Gamo zone. But for today I would like to tell you about “Fango Dubusha", which is well known in Chencha Zuriya Wereda "Doko Mesho" Kebele.

This special system of justice preserving mechanism was practiced in a market place where local leaders and elders come together every Sunday to solve disputes among the marketers and other local people.

In Fango, Dubusha elders used to sit making square. The high elder’s site in their power hierarchy, Kawo comes first, then Dana, Huduga, Halaqa and other local leaders site accordingly their status and sit on sits which made in ancient time. Then, they hear, discuss and resolve disputes, and make laws.

In Doko Mesho , Sunday is market day, so the leaders and elderly people come to Fango Dubusha square starting from 5 ፡00 AM local time. When they arrive in the public square, elders stab their stick on the ground, which is called Xambaro or Hororsa, in the Gamo language. They also strew fresh grass on the ground saying blessing words.

Source: Chencha Zuria Woreda & Social Media outlets on Gammo Affairs

በጋልማ አርባምንጭ እርሻ ልማት እየተሰበሰበ ያለ የቃርያና ቲማቲም ምርት አቅርቦትSupport- Gamo Development Association /ጋሞ ልማት ማህበር ( ጋልማ)
06/08/2022

በጋልማ አርባምንጭ እርሻ ልማት እየተሰበሰበ ያለ የቃርያና ቲማቲም ምርት አቅርቦት

Support- Gamo Development Association /ጋሞ ልማት ማህበር ( ጋልማ)

06/08/2022

Asham Asham - Abay - new music released by korahu Babate group .

Enjoy it !

Road to Gamo - Arba Minch !Visit the gifted land !
05/08/2022

Road to Gamo - Arba Minch !

Visit the gifted land !

05/08/2022

Marvelous Arba Minch Circus Group Performance !

Support and Invest on different sports in Gamo Zone !!

የጋሞ ዞን አስተዳደር ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር  ዘወትር ማክሰኞ ምሽት የሚያቀርበዉ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የዛሬ ትኩረቱን በዞኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ዙሪያ ላይ አድርጓል።ዛሬ ከም...
19/07/2022

የጋሞ ዞን አስተዳደር ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር ዘወትር ማክሰኞ ምሽት የሚያቀርበዉ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የዛሬ ትኩረቱን በዞኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ዙሪያ ላይ አድርጓል።

ዛሬ ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ በዋልታ ቴሌቪዥን እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል ።
ምንጭ - ጋሞ ዞን ኮሚ.ቢ

በዞኑ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ያዩበታል።

ክፍል ሁለት  " እርጥብ ሣር ያስታርቃል "Buuccoysa goopite purccoyssa gidite"በእጄ ነጭቼ የያዝኩትን ሳይሆን ገና እየበቀለ ያለውን ሣር ሁኑ።"በተለይም ሴቶች "ማርዣም ...
19/07/2022

ክፍል ሁለት " እርጥብ ሣር ያስታርቃል "

Buuccoysa goopite purccoyssa gidite

"በእጄ ነጭቼ የያዝኩትን ሳይሆን ገና እየበቀለ ያለውን ሣር ሁኑ።"

በተለይም ሴቶች "ማርዣም "ወይም "ማርያም" ተብለው ስለሚከበሩ እርጥብ ሳር ይዘው እና መቀነታቸውን ፈትተው በተጋጩ ወገኖች መካከል ከተኙ እነሱን ረግጦ ማለፍ ነውር ስለሆነ ፀቡ ይቆማል፡፡

የጋሞ አባቶች ፣ጎልማሶችና አመራሮች በአርባምንጭ ከተማ በተፈጠረው ክስሰት ከተቆጡ ወጣቶች ፊት ለፊት የተጋፈጡት ይህንኑ እውነታ ነው፡፡

በእርግጥ ሳርም ይሁን ሌሎች ሁከትን የሚገቱ የግንኙነት መሣሪያዎች (ቡሉኮ፣ጋቢ፣ኩታ፣የእንስሳት ቆዳ፣የነብርና የአንበሳ ቆዳ፣በሬ በአካል) ሥራ ላይ ሲውሉ ሶስተኛ ገለልተኛ አካል በቆመበት ሆነው ምልክቱን የማሳየት ልምድ ያዳበሩ ቢሆንም በአርባምንጭ ክስተት ግን አንዳንዶቹ ከባህሉ ወጣ ባለ መልኩ ተንበርክከውም ጭምር ወጣቶችን ተማጽነዋል፡፡

ወጣቶችም ይህንን ፍፁም ቅንነትና ትሕትና ያለበትን መንበርከክ ከእውነተኛ የሰላም ፍላጎት እንጂ ከፍርሃት ወይም ለሞቱት ወገኖች ካለማዘን የመነጨ ያለመሆኑን በውል በመገንዘባቸው ቁጣቸውን በማለዘብ መመለስ በመቻላቸው የበቀል ዱላ ሊያርፍባቸው የነበሩ ተቋማትና ግለሰቦች ሕይወትና ንብረት መትረፍ ችሏልና ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ሌላው የእርጥብ ሳር አገልግሎት ምርቃት ነው፡፡ የአንድ ግለሰብ ቤት ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ምክንያት ከተቃጠለ የማህበረሰቡ አባላት ሌላ ሁለትና ሶስት ቤት ወዳለው አባወራ ቤት በመሄድ እርጥብ ሳር በእቅፉ አስቀምጠው ይመርቃሉ፡፡

የመጡበትን ጉዳይም አብራርተው አንዱን ቤቱ ለታቀጠለበት እንዲሰጡት ይማጸኑታል፡፡ ከርህራሄም ለበረከትም ጭምር አብዛኛዎቹ አባወራዎች ለቀረበው ጥያቄ አወንታዊ መልስ ይሰጣሉ፡፡በዕለቱም የአካባቢው ማሕበረሰብ በሕብረት ቤት ሰርተው ለተቃጠለበት ቤተሰብ ያስረክባሉ፡፡

እንደዚሁም ሰፊ ወጪ የሚጠይቁ የማህበራዊ አገልግሎት ሥራ ካለ በቂ ሀብት ወደ አላቸው ነዋሪዎች ቤት እርጥብ ሳር ይዘው በመሄድ መርቀው ስጦታ በዓይነት ወይም በገንዘብ ይወስዳሉ፡፡

እርጥብ ሳር ከበሬታን ለመግለጽም ያገለግላል፡፡ የጋሞ ማህበረሰብ በዱቡሻ ወይም በሕዝብ መሰብሰቢያ መጥተው ከመቀመጣቸው በፊት ቀድሞ ለገቡት ታዳሚዎች ለከበሬታ ሳር ነጭተው ከያዙ በኋላ ቡጮይሳ ግዲፕቴ ፑርጮይሳ ግድቴ (Buuccoysa goopite purccoyssa gidite) ይላሉ፡፡በእጄ ነጭቼ የያዝኩትን ሳይሆን ገና እየበቀለ ያለውን ሣር ሁኑ ማለት ነው፡፡ለምልሙ ፣እድጉ ፣ብዙ የሚል መልዕክት የያዘ ቡራኬ ነው፡፡

ራሳቸው ከመቀመጣቸው በፊት ደግሞ ዱቡሻው ላይ ሳር ወይም አረንጓዴ ቅጠል አስቀምጠው ይቀመጣሉ፡፡ መልዕክቶቹ ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው ተቋሙን ማክበር ሲሆን ሌላው የምነጋገረው ጉዳይ በሰላም ፣በእርቅ ይለቅ የሚል ፀሎትን ያዘለ ነው፡፡በዱቡሻ አቤቱታ የሚያሰማ ባለጉዳይም አቤቱታን ከማቅረቡ በፊት ሳር ይዞ ሕዝቡን ከባረከ በኋላ ንግግሩን ይጀምራል፡፡

የአረንጓዴ ሳርና ቅጠል ዘርፈ ብዙ አገልግሎቱ በዚህ አያቆምም፡፡ የሁለት ተጋቢዎች የጋብቻ ሥነ- ሥርዓት ማሳረጊያ የሚከናወነው አያት ወይም አባት በእርጥብ ሳርና ቅጠል (ኡጹማና ጋልጋሳ) በሚደርጉት ጸሎት ነው፡፡

የኮበሌዋን እግር ከታች የጎርምሳውን እግር ከላይ ካነባበሩ በኋላ እንዲወልዱ፣እንዲበዙና እንዲሰፉ ይባርካሉ፡፡ በጋሞ ሕዝብ ከጎሜ የማንፃት ሥርዓት የሚከናወነው በእርብ ሳር፣ቅጠልና ውኃ ነው፡፡ የጋሞ ባህላዊ ቄስ (ማካ) ፣አባወራ ወይም የጎሳ ሃላቃ ወይም ኤቃ በለምለም ሳርና ቅጠል ምህረትና ይቅርታን ይለምናሉ፡፡

"ጋሞ ዎጋ" ፡- የጋሞ ሕዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታትና ሰላም ግንባታ ሥርዓት ከተሰኘው የአቶ ዘነበ በየነ ቶልባ መጽሐፍ የተወሰደ
(S- Gamo Zone Govt.Communication Affairs )

Congratulations !The third gold medal with record time breaking!Ethoipian hero - Goitotom G/Silassie !
18/07/2022

Congratulations !
The third gold medal with record time breaking!
Ethoipian hero - Goitotom G/Silassie !

18/07/2022

*Bayra Hiking | ጉዞ ወደ ጨንቻ | ሐምሌ 16 እና 17
*Package price | 1599 ETB | ቅዳሜ ፣ ዕሁድ

*stop at Amarana bodo view point
*Visit Dorze st.George church
* Take time @ Dorze market place
*Trekking through Dorze village [3 km]
*Enjoy @ Dorso water falls
*Vist Laka Dubusha
*Visit Historical Chencha town
*Visit Ayalew lake
*Overnight campfire
*Sura Mountain trekking [5 km]
*Visit Cultural house & waving
*Taste Cultural food and drinks
*Attend Caltural event and dancing
*Game and enjoyment

👉 ስለ ጉዞው መረጃ ከፈለጉ
☎️ በ 0913187332/ 0910285570/ 0984945346

Telegram
https://t.me/bayrahikinggroup
you tube
https://youtube.com/channel/UCTMmbkpexIaxS6UCKXy9V9w
Ticktock
https://vm.tiktok.com/ZMNDh3R1g/

Bayra Hiking ;
We Explore the hidden beauties 🌿
(S- Asmamaw Dires)

የጋሞ ልማት ማህበር የእርሻ ስራውን የማዘመን ተግባር እያከናወነ  መሆኑን ገለጸ።የጋሞ ዞን አስተዳደር እና የጋሞ ልማት ማህበር ቦርድ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ  በሆነ ወጪ የተገዙ ዘመናዊ የእ...
18/07/2022

የጋሞ ልማት ማህበር የእርሻ ስራውን የማዘመን ተግባር እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

የጋሞ ዞን አስተዳደር እና የጋሞ ልማት ማህበር ቦርድ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ ዘመናዊ የእርሻ ቁሳቁሶችን ለአርባምንጭ እርሻ ልማት አስረክበዋል።

አርባምንጭ ፣ሐምሌ 11/2014 ዓ.ም(ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)፦የጋሞ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በማህበሩ የአርባምንጭ እርሻ ልማት በአንድ ዓመት የተገዛበትን ዕዳ በመክፈል ወደ ትርፍ መግባቱን ገልጸው የእርሻ ስራውን በማዘመን ትርፉማ እንዲሆን በዘመናዊ ቁሳቁስ እና በሰው ኃይል የማጠናከር ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር ቦርድ ከጋሞ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር በ8 ሚሊዮን 18 ሺህ 405 ብር ሁለት የእርሻ ትራክተሮችን በመግዛት ለማህበሩ አስረክቧል ።

በቀጣይ ልማት ማህበሩ በሁሉም መዋቅሮች የራሱ እርሻ እንዲኖረው እየሰራ መሆኑን ገልጸው ልማት ማህበሩ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ለዞኑ አርሶ አደሮች ምርጥ ዘር በማምረት ለማሰራጨት እየሰራ ነው ብለዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር የቦርድ አባል አቶ ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው ዞኑ በርካታ ሀብቶች ቢኖሩትም የሚገባውን ያህል አለመጠቀሙን ገልፀው በተለይም የአርባምንጭ እርሻ ልማት የውጭ ምርቶችን መተካት እና ገበያውን ማረጋጋት የሚያስችሉ ምርቶችን የማምረት አቅም ያለው በመሆኑ በዘመነ መልኩ መስራት ይገባዋል ብለዋል።

የእርሻ ስራው ማጠናከር በአከባቢ ያለውን ምጣኔ ሀብት የሚጨምር መሆኑን የገለጹት አቶ ጥላሁን ህብረተሰቡም ከልማት ማህበሩ ጋር በትብብር በመስራት የአከባቢውን ልማት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የጋሞ ልማት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አለነ አበጀ ማህበሩ ላለፉት ሁለት አመታት ባከናወነው ሪፎርም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ማህበሩ የአርባምንጭ እርሻ ልማትን በመረከብ ውጤታማ ስራ ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀው አሁን የተደረገው ድጋፍ ከዚህ ቀደም ለእርሻ ትራክተር ኪራይ የሚወጣውን ወጭ ያስቀራል ብለዋል።

የአርባምንጭ እርሻ ልማት ለህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ምርቶች በዘመናዊ መንገድ እንዲያመርት በሰው ሀይል እና በማሽነሪ የማጠናከር ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በጋሞ ልማት ማህበር የሚተዳደረው የአርባምንጭ እርሻ ልማት 900 ሄክታር ስፋት ሲኖረው 107 ቋሚ እና ከ700 በላይ ጊዜያዊ ሰራተኞች አሉት።

(S- Gamo Zone Govt.Communication Affairs Dept.)

"እርጥብ ሳር ያስታርቃል"በጋሞ ሕዝብ ባህላዊ አስተዳደር ውስጥ የእርጥብ ሳር አገልግሎትእርጥብ ሳር በጋሞሶ እርፃ ማታ (irxxa maata) ይባላል፡፡እርጥብ  ወይም ለምለም ሳር በጋሞ ህዝብ...
18/07/2022

"እርጥብ ሳር ያስታርቃል"
በጋሞ ሕዝብ ባህላዊ አስተዳደር ውስጥ
የእርጥብ ሳር አገልግሎት

እርጥብ ሳር በጋሞሶ እርፃ ማታ (irxxa maata) ይባላል፡፡እርጥብ ወይም ለምለም ሳር በጋሞ ህዝብ ዘንድ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ይሰጣል ፡፡

እርጥብ ሳር ለጋሞ ሕዝብ ሰፊ መልዕክት ያለው ፣የሰላም፣የመስከን ፣የምርቃት ፣የምህረት እና የእርቅ ተምሳሌትና ምልክት ነው፡፡

ከዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል አንዱ ግጭትን በተለይም ገሃድ ሁከትን (visible violence) የመከላከል ወይም የመግታት ሚናው ነው፡፡

ይህንን የአከባቢው ማህበረሰብ "እግንሴስ " ( irxxa maatay iginththees)ይላል፡፡ ትርጉሙም "እርጥብ ሳር ያስታርቃል" ማለት ነው፡፡ ለጋሞ ሕዝብ እርጥብ ሳር የሰላም ተምሳሌትና የግንኙነት መሳሪያ ነው፡፡

ይህ ለምለም ሳር የሰላም አምጪ ሆኖ በጋሞ አባቶች፣በእናቶችና በወጣቶች በጥቅም ላይ ይውላል፡፡ሁለት በመፋጠጥ ላይ ያሉ ወገኖች ወደ ብጥብጥ እንዳይገቡ ገብተውም ከሆነ ድርጊቱን እንዳይቀጥሉ ለመግታት በእጃቸው እርጥብ ሳርን ነጭተው ይይዛሉ፡፡

በመካከላቸው ገብተው ማሬ(mare) ይላሉ፡፡አንተም ተው፣አንቺም ተይ ፣እናተም ተው እንደማለት ነው፡፡ አንድ የጋሞ አከባቢ ሰው ሁለት አካላት ፀብ ውስጥ መሆናቸውን እያዬ ሳያገላግል አልፎ መሄድ "ጎሜ" እንዳይሆንበት ስለሚፈራና የሞራል ግዴታም ስላለበት ያገላግላል፡፡

አባቶች ፣እናቶችና ወጣቶች እርጥብ ሳር ይዘው ”እኛ በመካከላችሁ ገብተናል፡፡

እኛን አልፋችሁ አትደባደቡ ፣አትጎዳዱ ፣አትቆሳሰሉ ፣አትገዳደሉ፣ሰላምን አውርዱ፣ተቆጥታችኋል፣ስሜት ውስጥ ያስገባችሁን ሁኔታን እኛም ተመልክተናል፡፡ግን ተረጋጉ፣ሰከን በሉ፣ተመለሱ፡፡ እኛ ጉዳዩን እናጣራለን፡፡ በመሃላችሁ ያለውን ነገር እልባት እንሰጣለን፡፡እኛን ውሰዱ ፡፡እንደታጨደው ሣር ሳይሆን ገና እንደሚበቅለው ሣር ለምልሙ ፣እደጉ፣ዘራችሁ፣ ትዳራችሁ ይለምልም” የሚል መልዕክት ያስተላልፋሉ (ዘነበ ፡ 2015 ፣ ዎጋ ፣ 2018 ፣ ደቡብ ንጋት ፣ 2018)፡፡

እርጥብ ሣሩን የያዘውን ግለሰብ ወይም ቡድን መልዕክት እየተመለከቱ ሁከቱን መቀጠል ”ጎሜ” ሆኖ ያስቀጣል የሚል እምነት በማህበረሰቡ ውስጥ ስላለ ግጭት ውስጥ የገቡ ወገኖች መስከንን፣ማረጋጋትንና መመለስን ይመርጣሉ፡፡

አገልጋዮቹም እንደ ሶስተኛ ገለልተኛ ወገን ጉዳዩ ቀላል ከሆነ በቦታው ፣ጉዳዩ ውስብስብና ሰፊ ከሆነ በቀጠሮ ለማስታረቅ ቀጠሮ ወስደው ይጨርሳሉ፡፡ይህም የበረከታቸው ምንጭ እንደሆነም ያምናሉ፡፡
ይቀጥላል . . .

"ጋሞ ዎጋ" ፡- የጋሞ ሕዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታትና ሰላም ግንባታ ሥርዓት ከተሰኘው የአቶ ዘነበ በየነ ቶልባ መጽሐፍ የተወሰደ

(S- Gamo Zone Govt.Communication Affairs )

Congratulations !
17/07/2022

Congratulations !

Visit the land of Nature and culture !Arba Minch - Gamo - Ethiopia !የሰላም:  የፍቅር : በገራሚ የተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች :  በባህል ትውፊቶች የታጨ...
17/07/2022

Visit the land of Nature and culture !
Arba Minch - Gamo - Ethiopia !

የሰላም: የፍቅር : በገራሚ የተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች : በባህል ትውፊቶች የታጨቀች : እንደ አቅምዎ ዘና የሚሉበት ማራኪ የሆኑ ዘመናዊ ሆቴሎችን የተጎናጸፈች ውብ የሆነች ከተማና አካባቢዋን ይጎብኙ !

አሻም አሻም. . ብላ ትቀበላችኋለች !
ከሚገምቱት በላይ ደስተኛ ሆነው መንፈስዎን አድሰው ይመለሳሉ !

Gamo Dinguza ! The land of traditional cloths art !
17/07/2022

Gamo Dinguza ! The land of traditional cloths art !

የእናት ውለታዋ !
17/07/2022

የእናት ውለታዋ !

የወንዶች ማራቶን በመካሄድ ላይ ይገኛል።  መልካም ዕድል ለጀግኖች አትሌቶቻችን ።
17/07/2022

የወንዶች ማራቶን በመካሄድ ላይ ይገኛል። መልካም ዕድል ለጀግኖች አትሌቶቻችን ።

Congratulation to all Ethiopians !
17/07/2022

Congratulation to all Ethiopians !

 ኢትዮጵያዊውያን አትሌቶች የማጣርያ ውድድራቸውን አለፉ !በ1,500 ሜትር ሴቶች የማጣርያ ውድድራቸውን ያደረጉት አትሌታችን ሂሩት መሻሻ (ከምድቧ 1ኛ)፤ ፍሬወይኒ ሀይሉ (ከምድቧ 3ኛ)፤ ጉዳ...
16/07/2022



ኢትዮጵያዊውያን አትሌቶች የማጣርያ ውድድራቸውን አለፉ !

በ1,500 ሜትር ሴቶች የማጣርያ ውድድራቸውን ያደረጉት አትሌታችን ሂሩት መሻሻ (ከምድቧ 1ኛ)፤ ፍሬወይኒ ሀይሉ (ከምድቧ 3ኛ)፤ ጉዳፍ ፀጋይ (ከምድቧ 1ኛ) ደረጃን በመያዝ ማጣርያቸውን ስላለፉ ለግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህ መሠረት ሀገራችን ኢትዮጵያ የ1,500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ በነገው ዕለት ሌሊት 11:05 ሲካሄድ በሶስቱም አትሌቶቻችን ሂሩት መሸሻ ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ እና ጉዳፍ ፀጋይ የምትወከል ይሆናል።

በወንዶች የ3ሺ ሜ መሰናክል ሶስቱም አትሌቶች ወደ ቀጣዩ የፍፃሜ ውድድር አልፈዋል። ለሜቻ ግርማ 1ኛ (ከምድቡ)፣ ኃይለማርያም አማረ 1ኛ (ከምድቡ) ፣ ጌትነት ዋለ 4ኛ ሁነው አጠናቀዋል። በዚህም ኢትዮጵያ በ 3,000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር በአትሌቶቻችን ለሜቻ ግርማ ፣ ጌትነት ዋለ እና ኃይለማርያም አማረ የምትወከል ይሆናል።

የ 3,000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር የፊታችን ሰኞ ሌሊት 11:20 ላይ የሚደረግ ይሆናል።

🇪🇹እንኳን ደስ አለን

Sport is the culture in the area !For today, you are invited to enjoy with football history.Arba Minch and the surroundi...
15/07/2022

Sport is the culture in the area !
For today, you are invited to enjoy with football history.

Arba Minch and the surroundings are significantly contributing to Ethiopian national F.ball team .

ለሀገርም ለክለቦችም ከፍተኛ አበርክቶ የነበራቸውና አሁንም ያላቸው የእግር ኳስ ጥበበኞች መፍለቅያም ናት !

ከብዙዉ በጥቂቱ ከተለያዩ ምንጮች የተሰበሰቡ ምስሎችን እንሆ. . .

Support Gamo Development Association !The association contributing best effort in Gamo Zone on diversified development a...
13/07/2022

Support Gamo Development Association !

The association contributing best effort in Gamo Zone on diversified development activities.

Be a member and contribute your effort to the community !

የደቡቡ የተራሮች ንጉስ የኢትዮጵያ 4ተኛው ከፍታ ጉጌ ተራራ በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል የተራራ ጉልላት የሆነውና በኢትዮጵያ አራተኛው ከፍታ ጉጌ ተራራ የሚገኘው በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ውስጥ ...
13/07/2022

የደቡቡ የተራሮች ንጉስ የኢትዮጵያ 4ተኛው ከፍታ ጉጌ ተራራ

በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል የተራራ ጉልላት የሆነውና በኢትዮጵያ አራተኛው ከፍታ ጉጌ ተራራ የሚገኘው በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ውስጥ ነው። የተራራው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 4207 ሜትር ነው።

ከጉጌ ተራራ አናት የሚወጣ ጎብኚ በአራቱም አቅጣጫ አይን የማያስከድን እንደ ዥረት የሚፈስ ውበት ይቃኛል።

ጥንታዊውን ኤሊ ገብርኤል ገዳም ጨምሮ የሶዴ ደሬዎች ጮዬ ማስቃላ ዓመታዊ በዓል ማክበሪያ ምድርን ፣ ከጉጌ ተራራ ስር የሚምዘገዘገውን ቶሽኬ መንቲያ ፏፏቴ እንድሁም አስደማሚውን የጋሞ ዞን መልከዓ ምድር እና የማሕበረሰቡን አኗኗር ዘይቤ ይጎበኛል።

ጉጌ ተራራ ክረምት ከበጋ ነጭ የደመና ጥምጣም የጠመጠመ ፤ አሬንጓዴ ካባ ደርቦ የተኮፈሰ ካህን ይመስላል። ታይቶ የማይጠገብ ውበት ያለው የጉጌ ተራራ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች መዳረሻቸው ከሚያደርጓቸው የዞኑ መስህቦች አንዱ ነው።

ጉጌ በተፈጥሮ ተማርከውና እጅ ሰጥተው የሚመለሱበት ለአንዱ ብለው እልፍ የሚያዩበት የውበት ምንጭ ነው።
S- Gamo Zone Gov. Com.A

"ሶፌ" የሙሽራዎች የቁንጅና ውድድር በጋሞ ባህልየጋሞ ብሔረሰብ የተለያዩ ያልተከለሱና ያልተበረዙ የቱባ ባህሎች ባለቤት  ነው፡፡ ከእነዚህ ባህልና ዕሴቶች መካከል ለየት የሚለውን ባህላዊ የሙሽ...
12/07/2022

"ሶፌ" የሙሽራዎች የቁንጅና ውድድር በጋሞ ባህል

የጋሞ ብሔረሰብ የተለያዩ ያልተከለሱና ያልተበረዙ የቱባ ባህሎች ባለቤት ነው፡፡

ከእነዚህ ባህልና ዕሴቶች መካከል ለየት የሚለውን ባህላዊ የሙሽራዎች የቁንጅና ውድድር/ሶፌ እናስቃኛችሁ።

ሶፌ በዓመቱ ያገቡ ሙሽሮች የአከባቢው ህዝብ በብዛት በሚሰበሰቡበት ገበያ በመውጣት ዕውቅና ተሰጥቷቸው ከህብረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበት ሥርዓት ነዉ።

በሶፌ ስርዓት ውስጥ ባል ፣ የባል ቤተሰብም ይገመገማሉ። የማን ቤተሰብ በደንብ ተንከባከበ ፣ የማን ሚስት አማረባት የሚለውን ህብረተሰቡ ይዳኛል።

የሶፌ ሥነ ስርዓት በጋሞ አካባቢዎች ሁሉ የሚከበር ሲሆን ከቦታ ቦታ የተወሰነ ለውጥ አለ። አንዳንድ አካባቢ በፈረስ፣ አንዳንድ አካባቢ ደግሞ በእግር ፣ አንዳንድ አካባቢ በርካታ ጨሌ በሙሽራዋ አንገት ላይ ይደረጋል። አንዳንድ አካባቢ ቅቤው በቅርጽ ተከምሮ ሲታይ በሌላ አካባቢ የሙሽራዋ ፀጉር በቅቤ ርሶ /ፑንጽሮ/ ይበጠራል፣ በአንዳንድ አካባቢ ካባ ይደረባ በአንዳንዱ አይደረግም።

ሶፌ በጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ የጋብቻ ደረጃዎችን አልፎ መጨረሻ ላይ ሙሽራዎች በባህላዊ መንገድ እንደተጋቡ ማሳወቂያ የባህል ስርዓት ነዉ፡፡

በጋሞ ባህል ያገባች ሙሽራ ከ1 እስከ 4 ወር ከቤት ሳትወጣ የተለያዩ ሰውነት ገንቢ የሆኑ ምግቦችን ለአብነት ገንፎ ፣ ቅንጬ ፣ ጩኮ ፣ ቡላ ፣ በማር የታሸ ቆሎ ወዘተ . . . እየተመገበች ትቆያለች።

በሙሽራውና ሙሽራዋ አብሮ አደጎች ፣ ጎረቤት የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃ በክራር ፣ ከበሮ ፣ ዋሽንት…ወዘተ ታግዘው ባህላዊ ዜማዎችን እያዜሙም ይጨፍራሉ።

በሶፌ ዕለት በአከባቢው ሁሉም ያገቡ ሙሽሮች በወዳጅ ዘመድ ታጅበው ፣ በቅቤ የራሰውን ጸጉራቸውን ፑንጽሮ አበጥረው ፣ በከበረ ጨሌ ፣ በጋሞዎች የጥበብ ቀሚስ አጊጠው ፣ በጋቢ ተሸፋፍነው ፣ በላዩ ሱፋሌ(ካባ) ደርበው ፣ እንስራ ሙሉ ጠላ አስይዘው ወደ ገበያ ይወጡና ሴት ሙሽራዎች ገበያውን አራት ጊዜ ይዞራሉ፡፡ወንድ ሙሽራዎች በተራቸዉ ሶስት ጊዜ ገበያውን ይዞራሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ጠላው እየተጠጣ ገበያተኛ ሁሉ ትዳራቹ ሙሉ ይሁን ፣ ያማረ ትዳር ይሁን፣ ውለዱ ክበዱ ፣ወንድ ውለዱ ፣ሴት ውለዱ፣እያሉ ይመርቃሉ፡፡ እግረ መንገዳቸውን የማን ቤተሰብ ጥሩ ቀልቦ ሙሽራዋ እንዳማረባት ፣ የማን ቤተሰብ እንዳጎሳቆለ ፣ አለባበሷ ፣ መዋቢያዋ ታይቶ ፣ የእከሌ ቤተሰብ ጥሩ ይዟል። ሙሽራዋ አምሮባታል። እያሉ ለቤተሰቡም ለባሏም ዕውቅና ይሰጣሉ።

ይህ ሥነ-ስርዓት ከተፈፀመ በኋላ ሙሽራዋ ከህብረተሰቡ ጋር በይፋ ትቀላቀላለች፡፡ የተለያዩ ማህበራዊ ክዋኔዎችን ለመስራት ወደ አዲስ ምዕራፍ ትሸጋገራለች።
S.- Gamo Zone Government Communication Affairs Department

Incredible Art of Traditional Clothes contribution to the country as well as to the world !!
11/07/2022

Incredible Art of Traditional Clothes contribution to the country as well as to the world !!

11/07/2022

Enjoy with Gamo cultural old music !

Enjoy with sweet fruits and Invest in the area !
11/07/2022

Enjoy with sweet fruits and Invest in the area !

11/07/2022
11/07/2022
11/07/2022

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch - Gamo Area -The Gifted Land of Nature & Culture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Arba Minch - Gamo Area -The Gifted Land of Nature & Culture:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share