Visit Addis

Visit Addis Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Visit Addis, Travel Company, .

22/11/2023
22/11/2023

በሩብ ዓመቱ በሌማት ቱሩፋት ንቅናቄ ከ360 በላይ የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ እንደሆኑ ተገለጸ፡፡

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት አቶ በሪሁን አማረ የ2016 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት የሥራ አፈጻጻማቸውን አስመልክተው ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ እንደገለጹት ከከተማ ግብርና ጋር በተያያዘ በጓሮ አትክልትና የእንስሳት ተዋፅዖ ምርት በወረዳው ከ360 በላይ የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም የአካባቢውን ነዋሪ መሰረታዊ የምግብ ፍላጎቶች በጓሮው፣ በቤቱ ባለው ክፍት ቦታ በመጠቀም የጓሮ አትክልትና የዶሮ እርባታ እንዲጠቀሙ ግንዛቤ በመፍጠር ጤናማ የአመጋገብ ሥረዓት እንዲኖራቸው ማድረግ ተችሏል ሲሉ አቶ በሪሁን ጠቁመዋል።

በ3ኛው ዙር የሌማት ቱሩፋት ንቅናቄ ከ585 በላይ ቄብ ዶሮዎች ከ25 ዘመናዊ የዶሮ መኖሪያ ኬጅ ጋር እና የጓሮ አትክልት በዘር እና በችግኝ ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ሞዴል ተጠቃሚዎችን ማፍራት እንደተቻለ ጨምረውም ገልጸዋል።

በመጨረሻም የወረዳው ነዋሪዎች በከተማ ግብርና በመታቀፍ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችን የሚያገኝበት በተለይም ከድህነት ቅነሳ ያሥራ ዕድል ከመፍጠር አንጻር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ገቢ ከማስገኘት እና የአመጋገብ ስረዓት ከማሻሻልና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ከማሳደግ አኳያ ዘላቂ የጠፈጥሮ ሀብት አያያዝና አጠቃቀም ዋና መሣሪያ እንደሆነ በመግለጽ የከተማ ግብርናን በማስፋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንሰራለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

17/11/2023
Visit Addis
16/09/2023

Visit Addis

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Addis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share