Efrem oramo oda

  • Home
  • Efrem oramo oda

Efrem oramo oda Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Efrem oramo oda, Eco tour agency, .

እረፍት   አርባምንጭ ከተማ 2 - 1  ነጌሌ አርሲመልካም ዕድል!
08/05/2024

እረፍት


አርባምንጭ ከተማ 2 - 1 ነጌሌ አርሲ
መልካም ዕድል!

07/05/2024
04/05/2024

ወደብ ጠቃሚ ሆኖ አንገብጋቢ የማይሆንበት ወቅት ይኖራል! የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያለ ወደብ ባለቤትነት በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) ደካማ የሚባል አይደለም! (በአፍሪካ ከ100ቢሊዮን ዶላር በላይ GDP ካላቸው ጥቂቶች መካከል አንዱ ነው (የIMF ሪፖርት ዋቢ ከተደረገ!)። ይህ ቁጥር ሰፋፊ ወደብ ካላቸው የምስራቅ እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ነው።

በዓለም ላይ 44 ሀገራት የወደብ ባለቤትነት የላቸውም! ከአፍሪካ 16 ሀገራት፤ ከአውሮፓ 16 ሀገራት (የበለጸጉትን ሉግዘምበርግ፤ ኦስትሪያ እና ሲዊዘርላንድን ጨምሮ) እና ከላቲን አሜሪካ 2 ሀገራት (ቦሊቪያ እና ፓራጓይ)፡፡ በዓለም ላይ ካዛኪስታን እና ኢትዮጲያ ግዙፍ ቆዳ ስፋት ይዘው ወደብ አልባ ከሚባሉት ሀገራት መካከል ናቸው፡፡

በዓለም ላይ ጎረቤቶቻቸው ሳይቀር ወደብ አልባ የሆኑ ሀገራት (Double Landlocked Countries) ሁለት ሲሆኑ፡ Liechtenstein (ጎረቤቶቿ ኦስትሪያ እና ሲዊዘርላንድን ሲሆኑ ወደብ የላቸውም) እና Uzbekistan (በአምስት ወደብ አልባ ሀገራት ተከባለች) ናቸው፡፡

ብዙ ድሃ ሀገራት ወደብ ቢኖራቸውም በየብስ ከጎረቤቶቻቸው ጋር የንግድ ግንኙነት በማድረግ ከወደብ የሚገኝን እድል ያልተጠቀሙ አሉ (ደካማ የውጪ ንግድ ተሳትፎ አላቸው)፡፡ የሱዳን፤ የጅቡቲ፤ የኤርትራ፤ የሴራሊዮን፤ የላይቤሪያ፤ የጊኒ፤ የቡርኪና ፋሶ፤ በአፍሪካ የግዙፍ ወደብ ባለቤቶች መካከል ሞዛምቢክ እና ማዳጋስካር፤ ወዘተ ኢኮኖሚ ከወደብ ጋር በጣም ደካማ ነው፡፡

ወደብ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የውጪ ንግድን ከማሳደግ ጀምሮ የውጪ ባለሃብቶችን እስከመሳብ የደረሰ ሰፊ እድል ይሰጣል፡፡ በፖለቲካል ሪፎርም የተነሳ ወደብ አልባ ቢሆኑም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ያሉት ቦትስዋና እና ሩዋንዳ ደግሞ ከወደብ ውጪ ኢኮኖሚ ሪፎርም ሊደረግ እንደሚችል ያሳያሉ፡፡

ኢኮኖሚ ከወደብ ሊያስቀድመው የሚችለው አንገብጋቢ ችግር ሊኖርበት ይችላል! በብዙ የአፍሪካ ሃገራት ፖለቲካል አለመረጋጋት ኢኮኖሚውን ወደብ ከማጣቱ በተጨማሪ ይፈትነዋል፡፡ ለምሳሌ፡ ባለፉት 3 ዓመታት ማሊ፤ ሱዳን፤ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በድምሩ ወደ 7 ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት ድርጊት እና ሙከራ ኢኮኖሚያቸው ይንገዳገዳል)፡፡

ኢትዮጲያ 9 የየብስ የወደብ በሮች ሲኖራት 95 ከመቶ የውጪ ንግዷን በጅቡቲ ወደብ በመጠቀም ከቢሊየን ዶላር በላይ በዓመት ታወጣለች፡፡ የወደብ ባለቤት ሆና ቢሆን ኖሮ የውጪ ንግድ መጠኗን ከማሳደጓ በተጨማሪ የወደብ ክፍያን በማስቀረት በዓለም ገበያ በቀነሰ የትራንስፖርት ዋጋ በሚቀርብ ምርት የገበያ ተፎካካሪነቷን ማሳደግ ትችል ነበር፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ ፖለቲካሊ በነበረ ሂደት ወደብ በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ውስጥ የለም! ወደብ አስፈላጊ ቢሆንም በወቅታዊ ሁኔታ አንገብጋቢው የውስጥ ፖለቲካል አለመረጋጋት እና የምርት አቅም መዳከም ነው፡፡ ፖለቲካል አለመረጋጋት የወደብም ሆነ የከፍተኛ ማዕድን ባለቤት ለሆኑ የአፍሪካ ሀገራት እያመጣ ያለው መከራ ከባድ ነው፡፡

ኢትዮጲያ በሊበራላይዜሽን መርህ Comparative Advantage የያዘችባቸውን ሴክተሮች (በጋራ ተጠቃሚነት ስልት) ኢኮኖሚያዊ እድል በምታገኝባቸው የውጪ ኢንቨስትመንቶች ላይ በመሳተፍ ወደብ ለማግኘት ብትችል መጥፎ አይሆንም፡፡ ነገር ግን ወደብ ለማግኘት ሰፊ Opportunity Cost ያለውን አይነት መንገድ (ጦርነት ተያይዞም ዓለም አቀፍ ውግዘት) ከተከተለች ግን ኢኮኖሚው ይበልጥ ፈተና እንዳያገኘው ያሰጋል፡፡

🇪🇹🇪🇹GAMO GAMO 💪🇪🇹🇪🇹
03/05/2024

🇪🇹🇪🇹GAMO GAMO 💪🇪🇹🇪🇹

~~~~~🇪🇹እንኳን ደስ አላችሁ🇪🇹💪 ~~~~~የአርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ጨዋታ አቻውን ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ እና ቀሪ ጨዋታ እያለው ወደ ፕሪምየር ሊ...
02/05/2024

~~~~~🇪🇹እንኳን ደስ አላችሁ🇪🇹💪 ~~~~~
የአርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ጨዋታ አቻውን ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ እና ቀሪ ጨዋታ እያለው ወደ ፕሪምየር ሊጉ መቀላቀሉን ተከትሎ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል።
በ23ኛ ሳምንት ምድብ ለ ተጠባቂ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም አርባ ምንጭ ከተማ ሶስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከአንድ የውድድር ዘመን በኃላ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ በ2015 የውድድር ዘመን ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ የሚታወስ ሲሆን÷በዓመቱ ወደ ሊጉ መመለስ መቻሉንም የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡

~~~~~🇪🇹እንኳን ደስ አላችሁ🇪🇹💪 ~~~~~አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰአዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚ...
02/05/2024

~~~~~🇪🇹እንኳን ደስ አላችሁ🇪🇹💪 ~~~~~
አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል።
በ23ኛ ሳምንት ምድብ ለ ተጠባቂ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም አርባ ምንጭ ከተማ ሶስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከአንድ የውድድር ዘመን በኃላ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል፡፡

አርባ ምንጭ ከተማ በ2015 የውድድር ዘመን ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ የሚታወስ ሲሆን÷በዓመቱ ወደ ሊጉ መመለስ መቻሉንም የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡

~~~Ginger production~~~ginger farming has for many years been A regularised form of farming in some African countries be...
01/05/2024

~~~Ginger production~~~

ginger farming has for many years been A regularised form of farming in some African countries because of its economic reward ,export rate and various other benefits ..

quick things to know about ginger ..

1.Ginger is planted using RHIZOMES (it doesn't produce true seed that can be used for planting)
2. It does well in well drained fertile loam soil..
3.water availability is necessary.
4.you need 1500 kgs of ginger seedlings to grow a Hector and the potential yield is 18 to 40 tones per Hector.
5. Ginger takes 8 - 9 months to be ready for harvest( it requires patient farmers to yield good results)
6.you can grow ginger organically ( using compost manure..no fertlizer)
7.GINGER has a ready market because it is used as a spice in many area,as a herb for some remedies,it is used in production of things like drinks,smoothies,GINGER TEA e.t.c
8.Ginger is easy to grow and manage and does very well in some parts of Africa
9.the profit margin is good because you produce Alot of tones per Hector compared to other crops. E.G the farm gate price can be 1 USD to 4 USD per kg so one Hector produces a minimum of 18 tones(18,000 kgs) so 18000 x 1 USD = 18,000 usd.. anyway that for the next lesson.
10. you need irrigation to grow ginger of course you can grow it under rain fed but you need a back up irrigation system for you to use once the rain has stopped... remember I said ginger takes 9 months..

በአዲስ አበባ የጋሞ ጨንቻ ማሊያ ሀሽያጭ ላይ ይገኛል::አድራሻ አበበ ቢቅላ ስታድዬም እናአውቶብስ ቴራ አከባቢ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፊት ለፊት ደጃች ውቤ ህንፃ👉09104555...
29/04/2024

በአዲስ አበባ የጋሞ ጨንቻ ማሊያ ሀሽያጭ ላይ ይገኛል::
አድራሻ አበበ ቢቅላ ስታድዬም እና
አውቶብስ ቴራ አከባቢ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፊት ለፊት ደጃች ውቤ ህንፃ👉0910455566 እስራኤል ሻመና🙏ጋሞ ጨንቻ ማልያ 👏👏👏

~~~~🇪🇹  ተነስቷል🇪🇹~~~  | አርባምንጭ - ከለምለም አደባባይ ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ያለው ወጣት በከፍታ ተነስቷል - ከኋላው በርካታ ወጣቶችን ይዞ እየመጣ ነው!ይህ ወጣት ለአገር እና ለ...
28/04/2024

~~~~🇪🇹 ተነስቷል🇪🇹~~~

| አርባምንጭ - ከለምለም አደባባይ ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ያለው ወጣት በከፍታ ተነስቷል - ከኋላው በርካታ ወጣቶችን ይዞ እየመጣ ነው!
ይህ ወጣት ለአገር እና ለሕዝብ ብሎም ለ"ጨለማው አህጉር" አፍሪካ ታላቅ ራዕይ ይዞ ተነስቷል።

የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም አርጋው በክብር እንግድነት ታድመው መርሃ ግብሩን በንግግር አስጀምረዋል፡፡

የጋሞ ዞን ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ አብረነው እንሰራለን ሲሉ ዳግም ቃል ገብተዋል።

እሰይ!

በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውና በአለም ደረጃ ተወዳዳሪ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የስፖርት እና የስነ ምግባር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በአርባምንጭ ከተማ ሊገነባ ነው!

YP (Yeleththha Pinththa) የስፖርት እና ሥነ ምግባር ማሰልጠኛ ተቋም ፕሮጀክት፤ በጋሞኛ ቋንቋ ''ትውልድ ማሻገር'' የሚለውን የአማርኛ ፍቺ ይዟል።

ይህ ፕሮጀክት በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል በአርባምንጭ ከተማ የሚገኝና የተቋሙ መስራች ወጣቱ ባለራዕይ ማስተር ሳምሶን ሻምበል፤ የውሹ ማርሻል አርት፣ ጅምናስቲክና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፖርቶች አሰልጣኝ ነው።

ማስተር ሳምሶን በውሹ ስፖርት በሀገር ውስጥ ውድድሮች ከ19 በላይ ሜዳልያዎችን🥇🥇🥇 እና 8 ዋንጫዎችን 🏆🏆🏆 እንዲሁም በ2012ዓ.ም ቻይና በተደረገው የውሹ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ በሁለት ምድብ ተወዳድሮ 1የወርቅ🥇 እና 1የብር🥈 ሜዳልያ ያሸነፈ ዝምተኛ ጀግና ነው።

የፕሮጀክቱ ዋና ራዕይ በአካሉ እና በአእምሮው የዳበረ ንቁ፣ አምራችና ሀገር ወዳድ፤ እንዲሁም የወደፊቷን ኢትዮጵያ መረከብና በአግባቡ ማስተዳደር የሚችል ትውልድ መፍጠር ነው።

ፕሮጀክቱ ዘጠኝ ንዑስ ፕሮጀክቶች አሉት። ከእነዚህ ውስጥ #የህጻናት ስፖርት እና ተግባራዊ ስነምግባር ትምህርት፣ (Green& Clean City)፣ #ለወጣቱ የተለያዩ የስፖርት ስልጠናዎች #ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ)፣ #የቴክኖሎጂ መስኮች (IT training )፣ #ለወጣቱ የሕይወት ክህሎቶች ስልጠና መስጠት፣ #ወጣቱን ባለራዕይ እናድርገው!(Let's make the young visionary!) እና የተለያዩ መሰል ንዑስ ፕሮጀክቶችን ይዞ የሚሰራ ነው፡፡

''ትውልድን አስቦ መስራት የሥልጣኔ ቁልፍ መንገድ ነው'' የሚለው ማስተር ሳምሶን አርባምንጭ ከተማ ላይ የሚጀምር ነገር ግን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ፕሮጀክት መሆኑን ይናገራል።

ለዚህ ለሀገር ትልቅና ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ላለው ፕሮጀክት ለግንባታ የሚሆን ቦታ የአርባምንጭ ከተማ እና የጋሞ ዞን አስተዳደር 3000 (ሦስት ሺህ) ካ.ሜ ቦታ ሰጥተውታል።

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 120,000,000 (አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን) ብር መሆኑ ተገልጿል!

ይህም ፕሮጀክት ከህዝብ፣ ከመንግሥት፣ ከረጂ ድርጅቶች እና ከተለያዩ ተቋማት ድጋፍ የሚገነባ ነው።

በዚህም መሠረት ፕሮጀክቱን ለመደገፍ ሐምሌ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ''የነገዋ ሀገር ተረካቢ ትውልድ በጋራ እንፍጠር'' በሚል መሪ ቃል 1ኛ ዙር ታላቅ የማስ ስፖርት ፌስቲቫል በአርባምንጭ ከተማ ለምለም አደባባይ ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ ተካሂዷል!

ከፌስቲቫሉ በኋላ አረንጓዴ አሻራ (የችግኝ ተከላ) ፕሮግራም እንደተዘጋጀ ለማወቅ ተችሏል።.

ፕሮጀክቱን መደገፍ ለምትፈልጉ

#ኢንተርናሽናል ማስተር ሳምሶን ሻምበል
#ስልክ+251911627686
+251916313389

e-mail: [email protected]

''ከነማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለመመለስ ከአራት ቀሪ ጨዋታዎች አድን ነጥብ ብቻ ይፈልጋል'' - አሰልጣኝ በረከት
28/04/2024

''ከነማ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለመመለስ ከአራት ቀሪ ጨዋታዎች አድን ነጥብ ብቻ ይፈልጋል'' - አሰልጣኝ በረከት

~~🇪🇹🇪🇹የሞርካ- ግርጫ-ጋሞ ጨንቻ🇪🇹🇪🇹 ~~~
26/04/2024

~~🇪🇹🇪🇹የሞርካ- ግርጫ-ጋሞ ጨንቻ🇪🇹🇪🇹 ~~~

🇪🇹🇪🇹💥 Vacation Time 💥 💥🇪🇹🇪🇹🇪🇹
26/04/2024

🇪🇹🇪🇹💥 Vacation Time 💥 💥🇪🇹🇪🇹🇪🇹

💘🇪🇹🇪🇹ድምቀትና ኩራት በጋሞነት 💘🇪🇹🇪🇹🇪🇹
26/04/2024

💘🇪🇹🇪🇹ድምቀትና ኩራት በጋሞነት 💘🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹Visit Arba Minch 🇪🇹Nice city 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
25/04/2024

🇪🇹🇪🇹Visit Arba Minch 🇪🇹Nice city 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

~~🇪🇹🇪🇹ፈታ በሉ ሁሌም🇪🇹🇪🇹~~  🇪🇹መልካም ጊዜ ነበረን ደስ ደስ ብሎኛል ተባረኩ🇪🇹
25/04/2024

~~🇪🇹🇪🇹ፈታ በሉ ሁሌም🇪🇹🇪🇹~~
🇪🇹መልካም ጊዜ ነበረን ደስ ደስ ብሎኛል ተባረኩ🇪🇹

🇪🇹🇪🇹 Vacation time on high land🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Arbaminch,🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
24/04/2024

🇪🇹🇪🇹 Vacation time on high land🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Arbaminch,🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹We loves more🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
24/04/2024

🇪🇹🇪🇹🇪🇹We loves more🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹 CHENCHA APPLE🇪🇹 ENBLA 👌👌👌
23/04/2024

🇪🇹🇪🇹 CHENCHA APPLE🇪🇹 ENBLA 👌👌👌

🇪🇹🇪🇹🇪🇹 Vacation time on lakeChamo  Arbaminch,🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Ethiopia
23/04/2024

🇪🇹🇪🇹🇪🇹 Vacation time on lake
Chamo Arbaminch,🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹Ethiopia

~~~40 ምንጭ 40 ምንጭ ~~ምንጩ ዉሃ ከተባለ 40 ምንጭ አርባ ምንጭ በደንብ  ጠጣዉኮ እፎይ ደስ ደስ ስል🙏
23/04/2024

~~~40 ምንጭ 40 ምንጭ ~~
ምንጩ ዉሃ ከተባለ 40 ምንጭ አርባ ምንጭ በደንብ
ጠጣዉኮ እፎይ ደስ ደስ ስል🙏

~~በኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር~~ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራ የፌደራል ሱፐርቪዥን ልዑኩ በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ  የሚገኘውን የአፕል ችግኝ ብዜት ማዕከል እና የምርት ማሳን ጎበኙ። በ...
23/04/2024

~~በኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር~~
አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራ የፌደራል ሱፐርቪዥን ልዑኩ በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ የሚገኘውን የአፕል ችግኝ ብዜት ማዕከል እና የምርት ማሳን ጎበኙ።
በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ አፕል በማምረት የተሰማሩት አቶ አለማየሁ እስራኤል 153 የሚደርሱ የአፕል ዝርያዎች ቢኖሩም በወረዳው የሚታወቁት 28 ዝርያዎች ብቻ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከአንድ የአፕል ዛፍ ከ50 እስከ 70 ኪሎ ግራም ምርት እንደሚያገኙም አቶ አለማየሁ አብራርተዋል።

ርሆበት የአፕል ችግኝ ብዜት ማህበር ሰብሳቢ አቶ መሠለ ማቴዎስ ማህበሩ 28 ዓባላት እንዳሉት ገልፆ አሁን ላይ የተለያዩ የአፕል ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በማፍላት በመላው የሀገሪቱ ክፍል እያከፋፈሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

አምና ለአዲስ አበባ ጫካ ፖርክ 55 ሺህ ፣ ለቤተ መንግስት 300 እንዲሁም ለወንጪ ፓርክ 200 የአፕል ችግኝ መሸጣቸውን የማህበሩ ሰብሳቢ ተናግሯል።

አሁን ላይ በ6 ሔክታር ማሳ ላይ የአፕል ችግኝ እማረቱ እንደሚገኝ የጠቆመው አቶ መሠለ 10 ሚሊዮን ብር ካፒታል እንዳላቸውም ተናግረዋል።

የኢፌድሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በበኩላቸው በችግኝ ብዜትም ሆነ በአፕል ምርታማነት ዙሪያ ውጤታማ ተግባር መመልከታቸውን ገልፀው ከረጂ ድርጅቶች እና ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር የአፕል ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመስራት መታቀድ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ግብርና ያለ ኢንዲስትሪ አያድግም ያሉት ሚንስትሩ ከጥሬ እቃ አቅርቦት ባሻገር ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በወረዳው በግብርና ምርት ትልቅ አቅም እንዳለው መመልከታቸውን የገለፁት ልዑካኑ በተለይ ከአፕል ጋር ተያይዞ ዝርያዎችን በዞኒንግ ስፔሻላይዝድ የማድረግ ስራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በወረዳው 1 ሺህ 315 ሔክታር ማሳ በአፕል መሸፈኑን ታውቋል።

👉የት አካባቢ እስት ገምቱ ሽልማት አለ?
23/04/2024

👉የት አካባቢ እስት ገምቱ ሽልማት አለ?

~~"የሞርካ ግርጫ ጨንቻ" ኮንክሪት~~ አስፓልት መንገድ ግንባታ ሥራ በጥራት እና በፍጥነት ተቀላጥፎ እየተሰራ በጨንቻ ከተማ አስፋልት ማንጠፍ ሥራ እየተከናወነ ነው።በኢትዮጵያ መንገዶች አስተ...
23/04/2024

~~"የሞርካ ግርጫ ጨንቻ" ኮንክሪት~~
አስፓልት መንገድ ግንባታ ሥራ በጥራት እና በፍጥነት ተቀላጥፎ እየተሰራ በጨንቻ ከተማ አስፋልት ማንጠፍ ሥራ እየተከናወነ ነው።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ባለቤትነት በቤጂንግ አርባን ኮንስትራክሽን ጉሩፕ የግንባታ ተቋራጭ እየተሰራ ያለው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን "ሞርካ ግርጫ ጨንቻ" ኮንክሪት አስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ከግንባታ መነሻው ቦታ እስከ ጨንቻ ከተማ 72.6 ኪሎ ሜትር ርቀት ሽፋን ያለው መንገድ ከ1.9 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።

የኮንክሪት አስፓልቱ መንገዱ በወረዳ ከተሞች 21.5 ሜትር፥ በገጠር ከተሞች 12 ሜትር እና በገጠር 8 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን በጨንቻ ከተማ አስተዳደር ርዝመቱ ከ2.5 ኪሎ ሜትር ያላነሰ መንገድ በሁለት አቅጣጫ የትራንስፖርት ፍሰት የመሀል አካፋይ የአረንጓዴ ልማት ቦታና የእግረኛ መሄጃ መንገድን ጨምሮ 30 ሜትር ስፋት ያለው ሆኖ እየተሰራ ነው።

ጠቅላላ የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ ስራው ከ60% (ከስልሳ በመቶ) በላይ የደረሰ ሲሆን ከ35 ኪሎ ሜትር ሽፋን በላይ አስፋልት መልበሱን ከመንገድ ስራው የሳይት ማናጀር መረዳት ተችሏል።

የመንገድ ሥራውን ጥራት ክትትልና ቁጥጥር ስራውን ኮር ኮንሳልቲንግ ኢንጂነርስ ፕሮጀክት የሚያከናውን ሲሆን በጨንቻ ከተማ አስተዳደር ጨንቻ ከተማ የአስፓልት ማንጠፍ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየተሰራ ይገኛል።

ከዚህ የመንገድ ግንባታ ሥራ ጋር አያይዞ የጨንቻ ከተማ አስተዳደር መንግስት ተጨማሪ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ለማሰራት ባቀደው በከተማው የንግዱ ማህበረሰብ የሚፈለግበትን ሁሉ ደስተኛ ሆኖ ለማድረግ ተነሳሽነቱን አሳይቷል።

በመንገዱ ሥራ ጥራት እና ፍጥነት የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች እና የአካባቢው ሰው ደስታውን እየገለጸ ይገኛል። የጨንቻና አካባቢው ተወላጆችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ሁሉ ለዚህ ልማት የራሳቸውን ድርሻ ለመወጣ "ከእኔ ለጨንቻዬ" በሚል ለገቢ ማሰባሰቢያ ከውዲሁ እንዲዘጋጁ የጨንቻ ከተማ አስተዳደር መንግስትና የከተማው የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ ስራ አሰሪ (ከንግዱ ማህበረሰብ፥ ከህዝብ እና ከመንግስት) የተወከሉ ኮሚቴዎች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።🙏

~~~~ጨንቻ ( ቱካ )~~~~የጨንቻ ከተማ አመሰራረትጨንቻ ከተማ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ውስጥ የምትገኝ ፈርጅ 3 ከተማ ነች። ጨንቻ ከተማ በ1889 ዓ.ም በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ነበር...
23/04/2024

~~~~ጨንቻ ( ቱካ )~~~~
የጨንቻ ከተማ አመሰራረት
ጨንቻ ከተማ በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ውስጥ የምትገኝ ፈርጅ 3 ከተማ ነች።
ጨንቻ ከተማ በ1889 ዓ.ም በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ነበር የተመሰረተችው፡፡
በወቅቱም የጋሞ ጎፋ ጠቀላይ ግዛት ዋና ከተማ ሆና የነበረች ሲሆን 1942 ዓ.ም ደጅ አዝማች ገርሱ ዱኪ የጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ገዥ ሆነው ከጃኖሆይ ተሹመው በመምጣት ከተማዋን ሲያስተዳድሩ ነበር፡፡

በወቅቱ ደጅ አዝማች ገርሱ ሲዘዋወሩ በምትካቸው ደጅ አዝማች ዘውዱ አባ ኮራን የጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ገዥ ሆነው የመሩ ቢሆንም ወዲያውኑ ከተማዋን አንስተው ወደ ጊዶሌ በመውሰድ የጋሞ ጋርዱላ ጠቅላይ ግዛት በማለት እሰከ 1949 ዓ.ም አስተዳድረዋል፡፡

ብዙም ሳይቆዩ ጨንቻ የጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ እንድትሆን አመጧት ፡፡

ይህ የሆነው ከ1949 ዓ.ም እሰከ 1954 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱም ጨንቻ የጋሞ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት ዋና ከተማ በመሆን በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር በድምሩ ለ12 ዓመታት አገልግላለች፡፡

በ1938 ዓ.ም ህጋዊ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት እውቅና አገኘች፡፡

የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ከአዲስ አበባ 542 ኪሎ ሜትር ከዞኑ ዋና ከተማ ከአርባምንጭ 37 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

ከተማዋ በፈርጅ ሶስት የከተማ አስተዳደር ደረጃ እውቅና ያገኘችው ጥር 2010 ዓ.ም ሲሆን ሁለት ቀበሌና 12 ቀጠና ይዛ ትገኛለች፡፡

በአሁኑ ሰዓት የህዝብ ብዛቷ 90 ሺ 815 ነው፡፡

የከተማዋ የቆዳ ስፋት በሄክታር 5685.177 ሲሆን
የከተማዋ አየር ንብረት 100% ደጋማ ሆና ከባህር ጠለል በላይ በ2732 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡

ጨንቻ ከ1943 ጀምሮ የሚታወቅበት ከፍተኛ የሆነ የአፕል ምርትና በቀን ከፍተኛ የሆነ የወተት አቅርቦትን ለተለያዩ ከተሞች የሚታቀርብ ከተማ ስትሆን የእደጥበብ ውጤት ከሆኑት የሸማ ስራ ድንጉዛን ጨምሮ በስፋት ይመረትባታል🙏

~~~ፈጣሪ ሲረዳህ~~💘‼️ ፈጣሪ ረድቶህ ያሰብከው ሲሳካ ቀጥሎ አላማህ መሆን ያለበት አንተ የደረስክበት ሰዎች እንዲደርሱ መርዳት ነው።ስኬታማ ስትሆን ሁሉን በራስህ ጥረት ያመጣከው ይመስል ራ...
22/04/2024

~~~ፈጣሪ ሲረዳህ~~💘‼️
ፈጣሪ ረድቶህ ያሰብከው ሲሳካ ቀጥሎ አላማህ መሆን ያለበት አንተ የደረስክበት ሰዎች እንዲደርሱ መርዳት ነው።ስኬታማ ስትሆን ሁሉን በራስህ ጥረት ያመጣከው ይመስል ራስህን ከፍ አድርገህ አትኮፈስ የረዳህን ፈጣሪ የምትከፍለው አንተ ከውጣህበት የስቃይ ህይወት እንዲወጡ አንተ ያለፍከውን ፈትና ሰዎች እንዲያልፉት በመርዳት ነው። ከፍታላይ ስትደርስ የመጣህበትን አትሬሳ ‼️

~~~ተስፉህ (ተስፉሽ) ማነው? ✍️ተስፉህ ገንዘብ  ነው? ገንዘብ ካለኝ ምንም አልሆንም ትላለህ? ተስፉህ ስልጣን ነው? ባለስልጣን ከሆንኩ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ነው ብለህ ታስባለህ? ተስፉህ...
22/04/2024

~~~ተስፉህ (ተስፉሽ) ማነው? ✍️
ተስፉህ ገንዘብ ነው? ገንዘብ ካለኝ ምንም አልሆንም ትላለህ?
ተስፉህ ስልጣን ነው? ባለስልጣን ከሆንኩ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ነው ብለህ ታስባለህ?
ተስፉህ ጉልበትህ ነው? በጉልበትህ ትመካለህ አቅም አለኝ ማንም አይችለኝም 💪 ትላለህ?
ተስፉህ እውቀትህ ነው? የተማሩኩ ነኝ! ከሁሉም እሻላለው ብለህ ታውቃለህ?

ተስፉህ ዝና ነው? መወደድ መከበር ነው? ሰው ስለሚወደኝ የተሻልኩ ነኝ ብለህ ታስባለህ?

ተስፉሽ መልክሽ ነው ቆንጆ ነኝ የፈለኩትን ማድረግ (ማግኘት) እችላለሁ ብለሽ ታውቂያለሽ?

ተስፉ ያደረከው (ያደረክሽው) ምን ላይ ነው? ማን ላይ ነው?

ተስፉው ገንዘብ የሆነ...ገንዘቡን ያጣው እለት ልቡ 💔 ይሰበራል። ለገንዘቡ የወደዱት ሲጠሉት ክፉኛ ይጎዳል። በራሱም ለመቆም አቅም ያጣል አቅሙ ገንዘብ ነበርና።

ተስፉውን ስልጣን ያደረገ ስልጣኑን ሲያጣ በሰው ፊት በድፍረት ለመቆም አቅም ያጣል። አቅሙ ስልጣኑ ነውና።

ተስፉው 💪ጉልበቱ (አቅሙ) የሆነ ሰው እርጅና ሲመጣ በወጣትነቱ ይሳለፈውን ሞኝነት የጎዳቸውን ሰዎች በማሰብ ሲተክዝ ይኖራል። አሁን ይታበይ ዘንድ አቅም የለውም አቅሙ ጉልበቱ ነበርና።

ተስፉውን እውቀት ያደረገ ከእሱ የሚበልጥ አዎቂ ሲመጣ ይበሳጫል። እንዳላዋቂ ያያቸው እንደ መሃይም የቆጠራቸው ሰዎች ከፍ ብለው ሲያያቸው ይደነግጣል በእነሱ ፊትም ለመቆም አቅም ያጣል አቅሙ እውቀቱ ነውና።

ተስፉው ዝና የሆነ ሰው ጠዋት ያጨበጨበለት ማታ ሲያጨበጭብበት ትላንት ያከበረው ዛሬ ሲንቀው ትላንት እሞትልሃለው ያለው ዛሬ ካልገደልኩህ ሲለው በመደነቅና በፍርሃት ውስጡ ይርዳል። ህይወቱንም ለመምራት አቅም ያጣል አቅሙ የሰው ከበሬታ ነውና።

ተስፉዋ መልኳ የሆነች ሴት እድሜዋን መሄዱን የፊቷን ውበት መቀነሱን ማርጀቷን ስታይ.. በፊት ልሙትልሽ የኔ "ሞናኒዛ" ሲላት የነበረ መልኳ ተቀይሮ ደምግባት ስታጣ ሲላት አስጠሊታ ምን ይሆን የዚች ልጅ እጣፈንታ? በፊት የነበራት በራስ መተማመን ከመልኳ ጋር አብሮ ሲረግፍ ሰው ፊት ለመቆም አቅም ታጣለች ቀድሞም የነበራት አቅም በመልኳ ነውና።

~~በጣም አሳዛኝ ዜና😭ወ/ሮ አለሚቱ አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። ወ/ሮ አለሚቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ።ወ/ሮ አለሚቱ የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃ...
22/04/2024

~~በጣም አሳዛኝ ዜና😭
ወ/ሮ አለሚቱ አሰፋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። ወ/ሮ አለሚቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ።
ወ/ሮ አለሚቱ የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የዞኑ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ በመሆንም አገልግለዋል።

በወ/ሮ አለሚቱ ድንገተኛ ሕልፈት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶኛል ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ፣ ለዘመዶቿ ለሁሉም እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጣቸው ።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Efrem oramo oda posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share