Debre elias culutre and tourism page

  • Home
  • Debre elias culutre and tourism page

Debre elias culutre and tourism page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Debre elias culutre and tourism page, .

26/05/2017

ሽብር አምባ ገዳም

26/05/2017

ከዋሻው ውስጥ የተሰራው አዲሱ የሽብር አምባ ገዳም

26/05/2017

በገዳሟ ውስጥ የሚገኙ መስቀሎች

26/05/2017

ንዋየ ቅዱሳቱ በንብ እና በነብር የሚጠበቁባት ደብረወርቅ ማርያም ገዳም ።
(ጎንደር ፋና FM 98.1)
June 7 at 10:38am •
ጎንደር፤ ግንቦት 30/2008ዓ.ም፤ (ጎንደር ፋና FM 98.1): ንዋየ ቅዱሳቱ በንብ እና በነብር የሚጠበቁባት ደብረወርቅ ማርያም ገዳም ። ከጎንደር ከ580 በላይ ኪሎ ሜትር ተጉዘን ጎጃምን አቆራርጠን ምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋው ወረዳ ደብረወርቅ ከተማ ደርስናል ።ቀደም ሲል " ምስካበ ቅዱሳን " የምትባለው ገዳሙዋ በ 351 ዓም እንደተገደመች ተነግሮኛል ። በሁዋላም በዩዲት ጉዲት ተቃጥላለች። በ1372 በቀዳማዊ አጼ ዳዊት እንደገና ታንጻ በድጋሜ በ1533 በአጼ ገላውዲዎስ በኖራ ውብ ሆና ታድሳለች ።በገዳሟ ከ 711 በላይ ልዩ ልዩ ንዋየ ቅዱሳት ይገኛሉ ። ሉቃስ የሳላት የወይኒቱ ማርያም ስዕል ፣ ከአልማዝና ወርቅ የተሰሩ የ አጼ ዮሃንስ ዘውዶች ፣ የብራና መጽሃፍትና ሌሎችም ቅርሶች በገዳሟ ይገኛሉ ። ትልልቅና እድሜ ጠገብ የጽድ ዛፎች ቤተክርስቲያኗን አስውበዋታል ። ደብረወርቅ ከተማን ከላይ ሆነው እንዲያዩዋት በሚያመች ከፍ ያለ ቦታ ላይም ታንጻለች ። በዙህ ገዳም የ አምስቱ ጉባያት ትምህርት ማለትም የድጓ ፣ የአቋቋም ፣ የቅኔ ፣ የቅዳሴና የመጻይፍት ትምህርቶች በበቁ አባቶች ትምህርቱ ሲሰጥ ተመልክቻለሁ ። ድንቅና ሃገር በቀል እውቀቶቻችን ነፍስ ከሚዘራባቸው ቅዱስ አድባራት መካከል አንዱን ማየት ደስ ያሰኛል ። የደብሯ አስተዳዳሪ መላከ ጸሃይ ታምር ጀንበር እንዳጫወቱኝና እንዳሳዩኝ ደብሯ ዘመናዊ ሙዚየም ተገንብቶላታል ። ከምንም በላይ የደነቀኝ ግን የንዋየ ቅዱሳቱ ቤት የሚጠበቀው በንብ እና ቁጥራቸው በማይታወቅ ነብሮች መሆኑ ነው ።አባ መላክ እና ሌሎች ነብሮች ጣራው ላይ እንደሚኖሩና ሰው እንደማይተናኮሉ ነግረውኛል። ንቦችን ግን እኔም ተመልክቻለሁ ። አባን ስለጉዳዩ ስጠይቃቸው " ልጀ ይህ መለኮታዊ ተአምር ነው" አሉኝ ።
በሰለሞን ሙጨ

15/05/2017
15/05/2017

በኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተዘጋጀ
ሳምንታዊ አቋም መግለጫ
ግንቦት 04 ቀን 2009 ዓ.ም
በሳዑዲ የሚገኙ ዜጎቻችን የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ከማብቃቱ በፊት ወደአገራቸው እንዲመለሱ ሁላችንም እንረባረብ!
የሳዑዲ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የሁሉም አገራት ዜጎች ካለፈው መጋቢት 21 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በ90 ቀናት እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል። ጉዳዩ እንደታወቀ የኢፌዴሪ መንግሥት ሳይውል ሳያድር ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁሞ ልዩ ልዩ ተግባራትን በማካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ለተመላሾች በሚወጡበት አገር ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ጀምሮ ወደአገር እስኪመለሱና ብሎም ወደየቀያቸው ሲመለሱ አቅም በፈቀደው መልኩ በዘለቄታ እስከሚቋቋሙበት ድረስ ከክልል መንግሥታት ጋር በመሆን ዝርዝር ጉዳዮችን በማጥናትና ሥርዓት በማበጀት ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል፡፡
በሳውዲ ዓረቢያም አንድ ግብረ ሃይል በማቋቋም በዚያ የሚገኙ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎቻችን የመውጫ ቪዛ የሚያገኙባቸው ተንቀሳቃሽ ጽሕፈት ቤቶችን በመክፈት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ እና መረጃ እየሰጠም ይገኛል። ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎችን ያለቀረጥ እንዲያስገቡም መንግሥት ፈቅዷል፡፡
የመንግስት ፍላጎት ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎቻችን አንዳችም ዓይነት ጉዳት እና እንግልት ሳይደርስባቸው በተሰጣቸው የእፎይታ ጊዜ ገደብ ውስጥ ወደ አገራቸው በሰላም እንዲመለሱ ማስቻል ነው፡፡ በመሆኑም በእስካሁኑ ሂደት የተወሰኑ ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፤ አሁንም በየዕለቱ በመመለስ ላይ ናቸው። ይሁን እንጅ የተመላሾቹ ቁጥር ከሚጠበቀው አንጻር ሲታይ አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
ምክንያቱም ዜጎቻችን የሳዑዲ መንግስት ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ወደ አገራቸው ካልተመለሱ አዋጁን ተግባራዊ በማድረግ የዜጎቻችን ሰብዓዊ መብቶቻቸው ይጣሳሉ፣ ንብረቶቻቸው ይወረሳሉ፣ ለእንግልት ይዳረጋሉ። በመሆኑም በሳዑዲ የሚገኙት ዜጎቻችን ይህንኑ ከወዲሁ ተገንዝበው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ በቀሪዎቹ ቀናት ፈጥነው ወደ ትውልድ አገራቸው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
የጊዜ ገደቡ ሳይጠናቀቅ ወደ አገር ቤት እንዲመለሱ በማድረግ በኩል በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው ደህንነት ሲሉ ከፍተኛ ግፊት ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን መንግሥት፣ ሚዲያዎች፣ ማህበራት፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እና መላው ህዝባችን የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ዜጎቻችንን ቶሎ እንዲመለሱ በማድረግ በኩል የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል።
ህገ ወጥ ስደት ዘመናዊ ባርነት በመሆኑ ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን እና ደላሎችን ለመቆጣጠር የሚካሄደውን ጥረት መላው ህዝባችን አጠናክሮ እንዲቀጥል በዚህ አጋጣሚ የኢፌዴሪ መንግሥት ጥሪውን ያስተላልፋል። ስደት ለአገርና ለወገን ውርደት ነው! በአገር ሰርቶ መለወጥ ግን ኩራት ነው

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre elias culutre and tourism page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share