Maale Woreda Prosperity Party

  • Home
  • Maale Woreda Prosperity Party

Maale Woreda Prosperity Party This is official page of Maale Woreda Prosperity Party

የማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የ2017 ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።ሌሞጌንቶ፣  የካቲት 29/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)➖➖➖➖➖➖➖➖➖የደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ...
08/03/2025

የማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የ2017 ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 29/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለፉት ስድስት ወራት በፓርቲው የተከናወኑ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶች ላይ የተመሰረተ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ብሩክ ታደሰ የግምገማ መድረኩ ዋና ዓላማ በፓርቲው ተግባራት በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ በጥንካሬ የተገኙትን ለማካበት እና በጉድለት የተለዩትን በማረም የትኩረት አቅጣጫዎች ማስቀመጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

በመድረኩ የወረዳው መንግሥት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሃባ ሙሄ የመንፈቀ ዓመቱን የሥራ አፈፃፀም የያዘ ሰነድ አቅርበዋል።

በፖለቲካዊ እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ረገድ፣ ፓርቲው ከህዝቡ ጋር አንድነትን እና ትብብርን ለማጠናከር በመስራት ላይ ሲሆን፣ የጋራ ግቦችን ለማሳካት እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ትኩረት አድርጓል ሲል ከሪፖርቱ ተመላክቷል።

በተጨማሪም የሴቶች ክንፍ በተለይ በማህበራዊ አገልግሎቶች ረገድ ተሳትፎ ያሳዩ ሲሆን የጤና ዘመቻዎችን እና የትምህርት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ሴቶችን ለማብቃት እና በማህበራዊ ልማት ረገድ እንዲሳተፉ ማድረግ ተችሏል።

በተደረገው ድጋፍና የግንዛቤ ማስጨበጫ በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት 147 ሴቶች የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ ተደርገዋል፣ እንዲሁም 11,584 ሴቶች በትምህርት ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ሆነዋል።

በመድረኩ የቀበሌያት ሊቀመናብርት እና የወረዳው አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

በቀጣይ ፓርቲው የአደረጃጀት መዋቅሮቹን ለማጠናከር፣ የአባላት መዋጮን ለማሳደግ እና ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተገኙትን ድክመቶች ለመፍታት እንደሚሰራም በመግባባት መድረኩ ተጠቃሏል።

“የግብርና ምርታማነት ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ርዕስ የማሌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2017 ዓ/ም በልግ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ፡፡ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 29/2017 ዓ/ም (ማወብፓ)➖➖➖➖➖➖➖...
08/03/2025

“የግብርና ምርታማነት ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ርዕስ የማሌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2017 ዓ/ም በልግ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ፡፡
ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 29/2017 ዓ/ም (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖➖➖

በማሌ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት “የግብርና ምርታማነት ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል የ2016 ዓም በልግ አፈፃፀምና 2017 ዓም በልግ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ፡፡

በመድረኩ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጽ/ቤቱ የኃላፊ ተወካይና የእርሻ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሳገኝ ፋሱጋ የመድረኩ ዋና ዓላማው በወረዳው የሚታየውን የምርታማነት ማነቆዎችን በመለየትና በመፍታት እንዲሁም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም መሠረታዊ ለውጥ በማምጣት የምርታማነት ግብ ማሳካት እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የግብርናው ዘርፍ የወረዳችንን ብሎም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት የጀርባ አጥንት የመሆኑ እውነታ ዛሬም እንደተጠበቀ መቀጠሉን የገለጹት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ግብርናን የማዘመን ጉዳይ ትልቅ ትኩረት ይፈልጋል ብለዋል፡፡

የግብርና ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የምችሉ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት በመጠቀም የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመድረኩ የግብርና ጽ/ቤት የኃላፊ ተወካይና እርሻ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሳገኝ ፋሱጋ የ2016 ምርት ዘመን አፈፃፀምና የ2017 የምርት ዘመን ዕቅድ አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሰነድ እንደተመላከተው የበልግ ግብርና ሥራዎች ዝግጅት በጠቅላላው 17,508 ሄክታር መሬት ታርሶ ከሁሉም የሰብል ዓይነቶች 810,408 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡

ሰነዱን ተከትሎ ከተሳታፊዎች ሰፊ ጥያቄና አስተያየት የተነሳ ሲሆን ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ ባስቀመጡት የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት በልዩ ትኩረት በፍጥነት ተጠናቀው ወደ ወደ ትግበራ እንዲገባ ጠይቀዋል፡፡

አጽንኦት ሰጥተውም በግብርናም ሆነ በሁሉም ዘርፍ የሚተገበሩ ተግባራት የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል አለበት ብለዋል፡፡

የደቡብ ኦሞ ዞን የኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሉቱረስ ካሬ በበኩላቸው በመድረኩ ባስቀመጡት አቅጣጫ “ያለንበትን ደረጃ በግልጽ ገምግመን ክፍተቶች ላይ በመተማመን ወደ ተግባር መግባት አለብን” ብለዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም አፈፃፀምን ለማሻሻል ቁርጠኝነትን ማሳየት እንደሚገባ ጠቁመው በሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ አሻራ ለማሳረፍ መነቃቃትን ለመፍጠር መሥራት አለብን ብለዋል፡፡

በመድረኩ የደቡብ ኦሞ ዞን ኢንበስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሉቱረስ ካሬ፣ የወረዳው አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የወረዳው አመራር፣ የግብርና ማናጅመንት እና የቀበሌያት ልቀመናብርትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የማሌ ወረዳ አጠቃላይ የወረዳ አመራሮች  እና የሁሉም የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ጋር  በጋራ በመሆን በሁሉም የፓርቲና የመንግስት የንቅናቄ ተግባራት ዙሪያ የግብረ መልስ መድረክ እያካሄዱ ይገኛል።...
07/03/2025

የማሌ ወረዳ አጠቃላይ የወረዳ አመራሮች እና የሁሉም የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በሁሉም የፓርቲና የመንግስት የንቅናቄ ተግባራት ዙሪያ የግብረ መልስ መድረክ እያካሄዱ ይገኛል።

ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 28/2017 (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖

በማሌ ወረዳ ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራት ላይ የወረዳው አመራሮች እና የቀበሌ ልቀ መናብርት በተገኙበት የግብረ መልስ እና የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ ከብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ብሩክ ታደሰ ጋር በጋራ እየመሩት የሚገኝ ሲሆን በሀብት ምዝገባ ፣ በጤና መድህን እና በፓርቲ አባላት ማጥራት እንዲሁም በተያያዥ ወቅታዊ ንቅናቄ ተግባራት ላይ በጥልቀት ግምገማ ተካሂዶ የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከተቀመጡ አቅጣጫዎች የመጀመሪያው ፓርቲውን ማጠናከርነዉ- አቶ ኦላዶ ኦሎየካቲት 28/2017 ዓ.ም(ማወብፓ)የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲየኢንስፔክሽ...
07/03/2025

በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከተቀመጡ አቅጣጫዎች የመጀመሪያው ፓርቲውን ማጠናከር
ነዉ- አቶ ኦላዶ ኦሎ

የካቲት 28/2017 ዓ.ም(ማወብፓ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲየኢንስፔክሽንና የሥነ- ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ለክልል ማዕከል ብልጽግና ህብረት፤ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የኮሚሽን አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ እየሰጠ ነዉ።

ስልጠናው በውስጠ ፓርቲ ዲሲፕሊንና ኢንስፔክሽን ፋይዳና ተሞክሮዎች፣ በተደጋጋሚ በሚጣሱ የአሠራር ሥርዓቶች፣ በተሻሻለው የፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እና ሌሎች መመሪያዎች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ታዉቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲየኢንስፔክሽንና ሥነ- ምግባር ኮሚሽን ሰብሳቢ አቶ ኦላዶ ኦሎ በቅርቡ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ከተቀመጡ አቅጣጫዎች የመጀመሪያው ፓርቲውን ማጠናከር እንደሆነ ተናግረዋል።

ለጠንካራ ፓርቲ መፈጠር ኮሚሽኑን ማጠናከር ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽን አመራሮች በተሰጣቸው ተግባርና ኃላፊነት ልክ እንዲንቀሳቀሱ አቶ ኦላዶ አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲየኢንስፔክሽንና ሥነ- ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሰማ ተስፋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዉ ተሳታፊዎች አቅም ፈጥረው የሚወጡበት ስልጠና እንደሚሆን ያላቸዉን እምነት ገልፀዋል።

በስልጠናው መክፈቻ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሶፎኒያስ ደስታን ጨምሮ የኮሚሽኑ አመራሮች፣ የክልል ማዕከል ብልጽግና ህብረት፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የኮሚሽን አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

!

የማሌ ወረዳ  ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችና 3ቱ ቋሚ ኮምቴዎች በአዦ ክላስተር ከሚገኙ የማህብረሰብ ተወካዮች ጋር  በLLRP የተከናወኑ ተግባራት እና የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ያለበትን...
06/03/2025

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችና 3ቱ ቋሚ ኮምቴዎች በአዦ ክላስተር ከሚገኙ የማህብረሰብ ተወካዮች ጋር በLLRP የተከናወኑ ተግባራት እና የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አካሄደ፡፡
ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 27/2017 ዓ/ም (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችና 3ቱ ቋሚ ኮምቴዎች በአዦ ክላስተር ከሚገኙ የማህብረሰብ ተወካዮች ጋር በLLRP የተከናወኑ ተግባራት እና የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አካሄደ፡፡

የአዦ የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታው 95%የተጠናቀቀለትና መስታወት የመግጠምና ጥቃቅን ሥራዎች የሚቀሩለትን በመስክ ምልከታው ተገምግሟል፡፡

ፕሮጀክቱ በLLRP Component 1 ስልታዊ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከሚተገበሩት አንዱ ሲሆን በ22.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በሐምሌ ወር ውል ተገብቶ በመስከረም ወር ወደ ሥራ የተገባ እንደሆነ በማሌ ወረዳ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ባኮ ጳማ ገልጸዋል፡፡

እንደ እሳቸው ገለፃ የክሊኒክ ግንባታው ሲጠናቀቅ ሁሉም ዓይነት የእንስሳት ህክምና አገልግሎቶች የቀዶ ጥገና፣ የተኝቶ ህክምና እና የክትባት አገልግሎት ይሰጣል።

በፕሮጀክቱ አማካኝነት ግንባታው ሲጠናቀቅ ለህክምና ግብዓት ተጨማሪ በጀት መኖሩን ገልጸው በሚቀጥሉት በዉስን ቀናት ግንባታው እንደሚጠናቀቅ አሳውቀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በአዦ ቀበሌ የአዦ ጤና ጣቢያ የነፍሰ ጡር እናቶች ማቆያ ግንባታም በLLRP ምዕራፍ 1 እና በማህበረሰብ ድጋፍ የሚመራ ሆኖ ግንባታው ከተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ መጓተቱን አስተባባሪው አመልክተዋል፡፡

የነፍሰ ጡር እናቶች ማቆያ ግንባታም ስጠናቀቅ ለሦስት ቀበሌያት ማለትም ለአዦ፣ለጎሎ እና ለማቃና ቀበሌያቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆንም ተገልጿል።

በመቀጠልም የአዦ ገበያ ማዕከል በBRFON project 13 ሚሊዮን ብር የተገነባዉን ምልከታ አድርጓል።ገበያ ማዕከሉም በአንድ ግዜ ወደ 37,000 የቁሚ እንስሳቶች መያዛ የሚችልና ተጓዳኝ መስፈርቶችን ያሟላ መሆኑን በመረዳት ጎበኝዎች አዎንታዊ አስተያየታቸዉን ሰተዋል።

በስተመጨረሻም ለማህብረሰቡ የፊትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥ በቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአገልግሎት ክፍት የሆነዉን የአዦ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ማነቆዎች ዙሪያ ቋሚ ኮምቴዎች ተዟዙሮ ተመላክቷል።

ለማህብረሰቡ የፊትህ ተደራሽነትን በቅርበት ለመስጠት የተከፈተ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ፍርድ ቤቱ እንደአድስነቱ ብዙ ያልተሟላ ግብአቶች፣የሰዉ ኃይል፣ የተሽከራካር እና የደመወዝ መዘገየት የተቋሙ ቁልፊ ማነቆዎች እንደሆነ የምድብ ችሎት ፍርድ ቤት ዳኛዉ አቶ ምኞት ናዝረት ገልፀዋል።

ጉዳዩን በትኩረት የተመለከቱት የማሌ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችና 3ቱ ቋሚ ኮምቴዎች ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮችን አንደ ባንድ ለሚመለክተዉ አካል ለማድረስ ለችግሩ የመብትሄ አማራጭ ሚናዉን ለመወጣት ቃልም ተገብቷል።

ተጀምሮ ለ12 ዓመታት ለታለመለት ዓላማ ሳይዉል የቆየዉ የጎሎ ቀበል የመጠጥ ዉሃ ችግርን የምክር ቤቱ ቋሚ ኮምቴዎች የመጨረሻ ምልከታዉን አድርጓል።ይህ በDRSLP የተጀመረዉን 48 ሚሊየን ለታንከርና የዉሃ መስመር ዝርጋታ እንድሆን እንድሁም ለ569 የዉሃዉ መሳብያ ሶላሮች ይዉል ዘንድ 42 ሚሊዮን ብር በድምሩ 90 ሚሊዮን የሚሆን የመንግስት ወጪ ተደርጎ ለህብረተሰቡ የዉሃ ችግር ሳይቀርፊ ለአሰራ ሁለት ዓመት በመቆየቱ የወረዳዉ ምክር ቤት ቋሚ ኮምቴዎች በቁጭት ለሚመለክተዉ አካል ግብረ መልስ ለመስጠትም አጽንኦት ተሰቷል።

የጎሎ ህዝብም የቀጣይ የመኖር እጣ ፈንታ የሚወስነዉ በዚህ በመጠጥ ዉሃ ችግር ስቀርፊ ብቻና ብቻ እንደሆነም የቀበሌ ነዋሪዎች የሀደራ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አድነዉ አልበነ በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተናገሩት ፕሮጀክቶቹ ወሳኝ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ለመስጠት በተቀመጠላቸው የጊዜ ሠሌዳ መሰረት እንዲያልቁ ከቀበሌው ማህበረሰብ ጀምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እና ተገቢውን ክትትል እንዲያደርግና መንግስትም በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የሚታየዉን የግብአት ጉድለት ለማሟላት ቁርጠኛ እንድሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አድነዉ አልበነ፣የማሌ ወረዳ ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ አሊያ አካታ፣የምክር ቤቱ ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሀካ ማጃ፣የምክር ቤቱ ህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ባምኤ ቦርቻ፣የምክር ቤቱ ኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጋሻበዛ ኩዳ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በስፍራዉ ተገኝተዋል።

በማሌ ወረዳ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ከሴቶች ክንፍ ጋር በመሆን የሴቶችን ቀን በማስመልከት እና የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የተዘጋጀ የሴቶች ውይይት...
06/03/2025

በማሌ ወረዳ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ከሴቶች ክንፍ ጋር በመሆን የሴቶችን ቀን በማስመልከት እና የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የተዘጋጀ የሴቶች ውይይት መድረክ አካሄዱ፡፡
ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 26/2017 ዓ/ም (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖➖➖

ወረዳዊ የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) በማሌ ወረዳ በቦሽኮሮ ቀበሌ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ በደማቅ ኩነት ተከበረ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ49ኛ ጊዜ በሚከበረው በዚህ የሴቶች ቀን የወረዳው የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኩብት ዛርቄ ለበዓሉ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እንዲሁም በአመራር ሰጭነት አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በየአካባቢው እየተመዘገቡ ላሉ ውጤቶች የሴቶች ተሳትፎና ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል።

በመድረኩ እንደ ቁጠባ፣ የጤና አገልግሎት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች የተሰጡ ሲሆን በተጨማሪም ዕለቱን በማስመልከት ለ11 አቅመ ደካሞች የአልባሳት ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ዕለቱን በማስመልከት ከኦኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት አኳያ በሴቶች የተሰሩ ተግባራት ምልከታ በጉዶ ቀበሌ ተካሂዷል፡፡

በተካሄደው ምልከታ በሴቶች ልማት ኅብረት 0.25 ሄክታር መሬት ላይ የለማን የቲማቲም ማሳ እንዲሁም በወ/ሮ ይዘት ሂጌ ጓሮ የተተከለ የግራንድነን ዝሪያ ያለው ሙዝ ጉብኝት ተደርጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቦሽኮሮ ቀበሌ “ከቃል እስከ ባህል'' በሚል መሪ ሀሳብ በሁለተኛው ብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተወሳኑ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች የክንፍ ወረዳዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩም የማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ማይሳን አስረስ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ለአባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጡ፡፡

በግንዛቤው ማስጨበጫ ወቅት ወ/ሮ ማይሳን እንደናገሩት የፓርቲው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ መደረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ የወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኩብት ዛርቄ፣ የማሌ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማይሳን አስረስ እና የሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ማናጅመንትን ጨምሮ ሌሎች ከወረዳውና ከቀበሌያት ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችና 3ቱ ቋሚ ኮምቴዎች በአዦ ክላስተር ከሚገኙ የማህብረሰብ ተወካዮቻቸዉ ጋር የምክክር መድረክ ተካህዷል።ሌሞ-ጌንቶ፦የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)==...
06/03/2025

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችና 3ቱ ቋሚ ኮምቴዎች በአዦ ክላስተር ከሚገኙ የማህብረሰብ ተወካዮቻቸዉ ጋር የምክክር መድረክ ተካህዷል።
ሌሞ-ጌንቶ፦የካቲት 26/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)
============================

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎችና 3ቱ ቋሚ ኮምቴዎች በአዦ ክላስተር ከሚገኙ የማህብረሰብ ማለትም ከአዦ፣ከእርቦንና ከጎሎ ቀበሌያት ተወካዮቻቸዉ ጋር የምክክር መድረክ በአዦ ማዕከል ተካህዷል።

የምክክር መድረኩ የወረዳዉ አፈ-ጉባኤዎች፣የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ፣የኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ እንድሁም የህግ ፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮምቴዎች በየሩብ ዓመት አንዳንድ ግዜ ከተወከሉ ማህብረሶች ጋር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የመለየትና ለሚመለከተዉ አካል ግብረ መልስ ማሳወቅ የምክር ቤቱ ቁልፍ ዓላማ እንደሆነ የማሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አድነዉ አልበነ ገልፀዋል።

የማህብረሰብ ተወካዮችም የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጣሪ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል #ከኢኮኖማ ዘርፊ አንፃር፦ የመጠጥ ዉሃ ችግር፣የመብራት ችግር፣የመንገድ ተደራሽነት ችግር፣ደንና የመሬት ወረራ ዘመቻ ችግር፣የተሌ ኮሙኒኬሽን የአገልግሎት ተደራሽነት ችግር ስሆኑ

#ከማህበራዊ ዘርፊ አንፃር፦የትምህርት ጥራት ችግር፣የመምህራን እጥረት ችግር፣ የጤና ተቋማት ግብአት አቅርቦት ችግርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣የባለሙያ እጥረት፣የግብአት ጉድለት፣የስራ አጥ ወጣቶች መበራከት ችግር ስሆኑ

#ከህግ ፍትህ መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮምቴ ዘርፊ አንፃር፦የፍትህ ተቋማት የግብአት አቅርቦት ችግር፣በፍትህ ዘርፍ የሰለጠኑ የባለሙያዎች እጥረት፣የዳኞች አጥረት፣የክትትልና አቀራረብ ዘርፍ የፈፃሚዎች እጥረት ችግር መኖርንና በእነዚህ ምክንያት የተለያዩ የፍርድ ቤት በተሳለጠ መልኩ በጊዜ ዉሳነዎች አለመስጠት ችግሮች መኖሩ ከተወካዮች በሰፊዉ ተነስቷል።

ቋሚ ኮምቴዉም ለተነሱ ጥያቄዎች በየዘርፉ ገንብ አስተያየትና ምላሽ በመስጠት ቀሪ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ለሚመለክተዉ አካል ግብረ መልስ ለመስጠት ቃል በመግባትና በመግባባት መድረኩ ተጠናቋል።

የማሌ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አድነዉ አልበነ፣የማሌ ወረዳ ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ አሊያ አካታ፣የምክር ቤቱ ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሀካ ማጃ፣የምክር ቤቱ ህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ባምኤ ቦርቻ፣የምክር ቤቱ ኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጋሻዉ ኩዳ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በስፍራዉ ተገኝተዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ እና በኃይለማርያም እና ሮማን ፋወንዴሽን ትብብር የ2017 በጀት ዓመት የበልግ አዝመራ ተግባራት ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል   ዲመካ የካቲ...
05/03/2025

በደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ እና በኃይለማርያም እና ሮማን ፋወንዴሽን ትብብር የ2017 በጀት ዓመት የበልግ አዝመራ ተግባራት ማስጀመሪያ ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

ዲመካ የካቲት 26/2017 ዓ.ም(የማወብፓ)

የኃይለማርያምና ሮማን ፋወንዴሽን ም/ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሶስና ኃይለማርያም ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦላዶ ኦሎ፣ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ፣ የሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሎስንዴ ሎኛስዋ ፣የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደሰ ጋልጶክ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ ታድመዋል ።

በአሁኑ ሰዓት በዞኑ ግብርና መምሪያ ም/ኃላፊና ሰብል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ መርደኪዮስ አማካኝነት የተለያዩ የበልግ ወቅት የግብርና ንቅናቄ ሰነዶች እየቀረቡ ይገኛል ።

✍️✍️✍️የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቢ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይረክቴር አቶ አቅናው ካውዛ  ከሆስፒታሉ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ከቀበሌ ከመጡ የቀበሌ አመ...
04/03/2025

✍️✍️✍️የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቢ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይረክቴር አቶ አቅናው ካውዛ ከሆስፒታሉ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ከቀበሌ ከመጡ የቀበሌ አመራሮች ጋር በኮይቤ መጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ውይይት አካሂደዋል።

ኮይቤ የካቲት 25/2017 ዓ.ም

የኮይቤ መጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ወንዱ ቤራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው የውይይት መድረኩን በይፋ ከፍተዋል።

በውይይት መድረኩ የኮይቤ መጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ወንዱ ቤራ የሆስፒታሉ የስራ ክፊል ኃላፊዎች፣ የማኔጅመንት አባላትና የቀበሌ አመራር አካላት ተገኝተዋል።

በውይይት ወቅት የተነሱ ሀሳቦች፦ አጠቃላይ የሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ እና ከዚህ ቀደም ከነበረው ችግር አንፃር ሆስፒታሉ ምን ዓይነት ደረጃ ላይ እንደምገኝ ጥያቄ በማንሳት የተጀመረ ሲሆን፣

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንዱ ቤራ እንደ አብራሩት ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ስሰጥ ከነበረው አገልግሎት አንፃር ስታይ አሁን ላይ በይበልጥ የተሻለ አገልግሎት እየሰጠ እንደምትገኝና የተገልጋዮች ቁጥርም በዕጥፍ እየጨመረ መምጣቱን በማንሳት ለዚህም ደግሞ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አሁን ላይ ግን በዞኑ እና በወረዳው መንግሥት ድጋፊ ግዥ ተፈፅሞ የተገጠሙ ማሽኖች ተጠቃሽ መሆናቸውን በማንሳት ቀጣይ ላይም እንደነዚህ ዓይነት ውይይቶች የሆስፒታሉን ችግር ለይቶ ለማወቅ ወሳኝ መሆናቸውንም ጭምር በማብራራት ተናግረዋል።

ሆስፒታሉ በዞኑ ስር ካሉት የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል አንዱና ብቸኛው ሆስፒታል እንደመሆኑ መጠን የዞኑ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መምራት እንዳለበት እና እንደ ከዚህ ቀደም እንደደገፉት አሁንም ከዚህ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መደገፊና መከታተል እንደለበት የማኔጅሜንት አባላት ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

በውይይት መድረኩ አጠቃላይ በተነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ የሰጡት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይረክቴር አቶ አቅናው ካውዛ ፣ ባለፈው መጥቼ ከሄድኩ በኋላ በጣም ጥሩ ነገሮችን አይቼአለሁ፣ ለውጦች አሉ ጥሩ ነው በርቱ እኛም ከህክምና ግብዓቶች ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች አሁን ባይሆንም በጊዜ ሂደት ምላሽ እየሰጠን እንሄዳለን ያሉት የፓርላማ አባሉ ከሴሮ ወንዝ ድልድይ ጋር ተያይዞ ለሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች በቅርቡ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን(ERA) ጋር ሰፋ ያለ ውይይት እንደ አካሄዱ እና ስምምነት ላይ እንደ ደረሱ በማስረዳት፣ ስምምነቱም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን(ERA) በቅርቡ ድልድዩን መስራት እንደምጀምርም ጭምር ምላሽ ሰጥተዋል።

ከውይይቱ በኋላ በየ ስራ ክፊሉ ተዘዋውረው የተለያዩ ስራዎችን ሚልከታ አድርገዋል።

አስደሳች ዜና በማሌ ወረዳ ከቦሽኮሮ--ኬንቾ ድልድይ  የመንገድ ጥገና ፕሮጀክት ሥራ የሳይት ርክክብ ተደረገ።ሌሞ-ጌንቶ፦የካቲት 25/2017 ዓ.ም(ማወብፓ)=======================...
04/03/2025

አስደሳች ዜና
በማሌ ወረዳ ከቦሽኮሮ--ኬንቾ ድልድይ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክት ሥራ የሳይት ርክክብ ተደረገ።
ሌሞ-ጌንቶ፦የካቲት 25/2017 ዓ.ም(ማወብፓ)
=============================

በማሌ ወረዳ ከቦሽኮሮ እስከ ኬንቾ ድልድይ 22.23 ኪሎ ሜትሪ የሚሆን በRCAFS ፕሮጀክት በDC 2 ድዛይን የሚሠራዉ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክት ሥራ የሳይት ርክክብ ተደርጓል።

የመንገድ ጥገና ሥራዉ የድልድይ፥ ካልበርት እና ሌሎች ዋና ዋና የስትራክቸር ሥራዎች የሚከናወኑበት አስፈላጊ በሆኑ አከባቢዎች የመስመር ለዉጥ ሥራ የሚኖረዉ ሆኖ ሥራዉ እንደ አዲስ ግንባታ የሚሠራና በአለም ባንክ ድጋፍ የሚሠራ ሥርነቀል የግንባታ ፕሮጀክት መሆኑን የክልሉ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ደሳለኝ ገለፃ አድርገዋል።

ዳይረክተሩ አክለዉ የፕሮጀክቱ ባህሪ ከቀላል ሥራ ወደ ከባድ እያደገ የሚሄድ መሆኑን ጠቁመዉ የመንገዱ የስራ ድዛይን DC 2 መልክ የሚሰራ ሥራዉ ዉጤታማ ሆኖ እንድሠራ የወረዳዉ መንግሥት በቅርበት እየተከታተለ መወጣት ያለበትን ኃላፊነቶች እንዲወጣ አሳስበዋል።

ሀገራዊ የጨረታ ደንብና መመሪያ መሠረት የዚህ መንገድ ጥገና ስራ በአሸናፊነት የተረከቡት አቶ ዳንኤል አሻ ጠቅላላ የሥራ ተቋራጭ ኃላፊዉን የመንገድ ጥገና ሥራዉ ከአራት ወር እስከ ስድስት ወር በተያዘለት ጊዜ ገደብ እንድጠናቀቅ የወረዳ መንግሥት መሥራት የሚጠበቅበትን ሁሉ ሠርቶ ለሥራዉ ስኬታማነት መወጣት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።

ኮንትራክተሩ ሥራዉን በተሰጠዉ ጊዜ ቀድሞ ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት የሚሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ ከአራት እስከ ስድስት ወር ዉስጥ ተሰርቶ የሚያልቀዉ ይህ መንገድ ለማሌ ማህብረሰብ የመንገድ ችግርን ከስሩ ነቅሎ የሚጥል ምላሽ መሆኑን በማንሳት ይህም ለህዝባችንም ትልቅ ምስራች ነዉ ብለዋል።

ሥራዉ በጊዜ በጥራት እንዲሠራና ህብረተሰቡም ለመንገዱ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት ድጋፊና ክትትል እንድታደርጉና ይህን ስራ ለማደናቀፊ የተለያዩ የካሳ ክፊያ የሚጠይቅና አደናቃፊ አጀንዳ ለሚያራምዱ ግለሰቦች ብኖርም ትግል በማድረግ ማህብረሰቡም መንገዱ የሚሰጠዉን ጥቅም በአግባቡ በመጠቀምና ጥራት ያለዉ መንገድ ተሠርቶ አገልግሎት እንዲሠጥ እንደ ወረዳ ስትሪንግ ኮምቴ ከኮንትራክተሩ ሠራተኞች ጋር በቅርብ ክትትል እንደምሰራም ተናግረዋል።

አስተዳደሩም አክሎ መነሻዉን ቦሽኮሮ መድረሻዉን ኬንቾ ድልድይ ድረስ የሚሰራ በRCAFS ፕሮጀክት በDC 2 ድዛይን የወረዳ መንግሥትም በመጀመሪያ ዙር ለመሥራት የታቀደዉን 22.23 ኪ/ሜ ሙሉ በሙሉ እንዲሠራ መረባረብ እንደሚያስፈልግና ከስትሪንግ ኮሚቴ እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመነጋገር የሚሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዛሬዉ ዕለት ኮንትራክተር ዳንኤል አሻ ፣የክልሉ ዲዛይንና ኮንትራክተር አስተዳደር ዳይሮክተር አቶ ደመላሽ ደሳለኝ፣የክልሉ የመንገድ ግንባታ ባለሙያ አቶ ሚልኒክ ሙሉነህ ፣የስትሪንግ ኮምቴ ስብሳቢና የወረዳዉ ዋና አስተዳደር አቶ አልጋጋ ባልንሴንና ሌሎች ስትሪንግ ኮምቴ አባላትና የወረዳዉ ፊት አመራሮች በተገኙበት ኮንትራክተሩ የርክክብ ዉል ተፈራርመዋል።

የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት አባላት ከዞን ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛልዲመካ የካቲት 24/2017 ዓ.ምየደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ...
03/03/2025

የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት አባላት ከዞን ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛል

ዲመካ የካቲት 24/2017 ዓ.ም

የደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሎስንዴ ሎኛስዋ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው የውይይት መድረኩን በይፋ ከፍተዋል።

በውይይት መድረኩ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ የዞን ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ የፌደራል ፖርላማ አባላት አቶ አቅናው ካውዛ ፣ አቶ አጉ ደባን ፣ ወ/ሮ ጎይቲ ዋንጮ ፣ ወ/ሮ አሌ በላቸው እና የክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዱንጋ ናኩዋ ተገኝተዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የውክልና ስራ ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።

ከውይይቱ በኋላ በየወረዳ ተዘዋውረው የተለያዩ የልማት ስራዎች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም እየተገመገመ ነው ።   ዲመካ የካቲት 24/2017 ዓ.ም በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓ...
03/03/2025

የደቡብ ኦሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም እየተገመገመ ነው ።

ዲመካ የካቲት 24/2017 ዓ.ም

በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የፓርቲው ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን በዞኑ የሚገኙ ስምንት መዋቅሮች ተገኝተዋል ።

የደቡብ ኦሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደሰ ጋልጶክ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት የፓርቲ መደበኛ ስራዎች ፤ የሀብት አሰባሰብ ፣የአቅም ግንባታና የአደረጃጀት ስራዎች ላይ አፅንኦት በመስጠት ተሳታፊዎች ልወያይ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

በመድረኩ የዞኑ የፓርቲ አመራሮች, የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደርጰ የፓርቲ ን/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች0,የፖለቲካና የህዝብ ግኑኝነትና የአደረጃጀት ዘርፍ ዳይሮክተረቶች አመራሮች,የወጣቶችና የሴቶች ክንፍ አመራሮች እንድሁም የሰዉ ሀብት ዘርፍ ባለሙያዎች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከየካቲት 24 ጀምሮ የአፈጣጠር ችግር ላለባቸው ማህበረሰብ ክፍሎች በዘመቻ በክልሉ ባሉ ሆስፒታሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ ።የካቲት 21...
28/02/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከየካቲት 24 ጀምሮ የአፈጣጠር ችግር ላለባቸው ማህበረሰብ ክፍሎች በዘመቻ በክልሉ ባሉ ሆስፒታሎች ነፃ የህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ ።
የካቲት 21/2017 ዓ/ም(የማወብፓ)

የላቀ ብሔራዊ የመከላከል፣ ህክምናና አካታች ስርዓት ለአፈጣጠር ችግሮች በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 24 እስከ 29 ነጻ የቀዶ ህክምናና በማህበረሰብ ውስጥ ግንዛቤ በመፈጠር እንደሚከበር ተገልጿል።

ቀኑን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎት የጥራት ማሻሻያ ባለሙያ ዶ/ር አካሉ አድፋ፤ በክልሉ በአፈጣጠር ችግሮች ምክንያት በማህበረሰቡ ውስጥ ተደብቀው ለማህበራዊና ለስነ ልቦናዊ ችግሮች የሚጋለጡ ማህበረሰብ ክፍሎችን በነጻ ቀዶ ህክምናና ቀድሞ መከላከል በሚቻልባቸው ዘዴዎች ዙሪያ ከዘርፉ ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችል ዘመቻ መሆኑን ተናግረዋል።

ዶ/ር አካሉ አክለው ከቀጣዩ ሰኞ ማለትም የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአርባምንጭ ሆስፒታል ከአጋር ድርጀቶች ጋር በመተባበር ሙሉ የህክምና ወጪ ተሸፍኖ አገልግሎት ስለሚሰጥ በሁሉም መዋቅር የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና በጎ የጤና መልዕክተኞች መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግና የአፈጣጠር ችግር ያለባቸው ህጻናትና ታዳጊዎችን በማቅረብ ነጻ ህክምና እንዲያገኙ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በተፈጥሮ የአዕምሮ (ህብለ ሰረሰር) የነርቪ ችግር፣ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ፣ የሆድና የአንጀት አፈጣጠር እንዲሁም በተፈጥሮ ቆልማማ እግር ያላቸውን ማህበረሰብ ክፍሎችን ያካተተ ህክምናና ቅድመ መከላከል ተግባራት እንደሚከናወኑ ዶ/ር አካሉ ተናግረዋል።

ዘመቻው በዋናነት ነጻ ህክምና ዕድል መሰጠት፣ ግንዛቤ መፍጠርና በተሻሉ ህክምና ተቋማት አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ከአርባምንጭ ሆስፒታል በተጨማሪ በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል፣ በወላይታ ሶዶ ኮምፕርሄንሲፍ እስፔሻሊይዝድ ሆስፒታልና በሌሎችም ግል ጤና ተቋማት አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ምንጭ :-STV

የደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ  ሌሞ-ጌንቶ የካቲት 18/2017 ዓ.ምምክር ቤቱ በዛሬው ውሎ  4ኛ ዙር 3ኛ መደበኛ ጉባኤ...
25/02/2025

የደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ሌሞ-ጌንቶ የካቲት 18/2017 ዓ.ም

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎ 4ኛ ዙር 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ረቂቅ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት የቀረበውን ሪፖርት መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቀዋል ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ የ2017 ዓ.ም የአስተዳደር ምክር ቤት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከም/ቤቱ አባላት በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

የዞኑን ሠላምና አንድነት በፅኑ መሰረት ላይ ከማኖር አንፃር ፀጥታ ላይ ሰፊ ስራ የሚጠይቅ መሆኑ በምክር ቤቱ አባላት ተመላክቷል ።

በግብርናው ዘርፍ ተክኖሎጂን ከመጠቀም አንፃር አሁንም ዞኑ በተፈለገው ደረጃ ያልተሻገረ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

የገቢ አማራጮችን በመለየት የገቢ ዕቅድ አቅዶ ገቢ ከመሰብሰብ አኳያ ፤ ንግድና ገበያ ልማት የነዳጅ ግብይትን ስርአት ከማስያዝና ህገ ወጥ ንግድን ከመቆጣጠር አንፃር አጽንኦት በመስጠት መሥራት አለበትም ተብሏል ።

በሌላ በኩል በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው መሬቱን የማያለሙ ግለሰቦች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት ጠቁመዋል ።

እንደዚሁም ከማህበራት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የብድር አመላለስና የኢኮኖሚ ሽግግር ከማድረግ አንፃር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ያሉ ቢሆንም መሰረታዊ ችግር ያለባቸው በመሆኑ በቀጣይ ወስዶ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል ።

ከቁማ መስኖ ጋር ተያይዞ ውሃን መሰረት ያደረገ የመንደር ማሰባሰብ ስራ ለረዥም ጊዜ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት ባለመቻሉ ፕሮግራሙ ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ አለመቻሉ በምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል ።

በመጨረሻም የተከበረው ምክር ቤት የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እስከአሁን ያለውን የተግባር አፈፃፀም ከገመገመ በኋላ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አቶ ወንዱ ወሌን ከኃላፊነት አንስቷል ።

በዋና አስተዳዳሪ አቅራቢነት ምክር ቤት ላይ ቀርቦ የተለያዩ ሹመቶች ፀድቀዋል።

1) ወ/ሮ ዶቦ አውኖ ---የዞኑ ሽግግር ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ

2) አቶ ኦሉሉ ቻርኔሊ----- የፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

3) አቶ ተመስገን ጋርሾ------ የደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት

4) አቶ ምላርገው አዲሱ ---የግብርና መምሪያ ኃላፊ

5) ወ/ሮ ጎባ ናለማ---- የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ

6) አቶ ብርሃኑ በቀለ ----የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ

7) ወ/ሪት እታገኝ ሳሙኤል-----ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ

8) ወ/ሮ ነፃለም ኪዳነማርያም ----የፍትህ መምሪያ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል።

ቀድሞ ስሰሩ ከነበሩበት ተቋም ሽግሽግ የተደረገላቸው አመራሮች በፊት ቀርበው ቃለ መሀላ የፈፀሙ ስለሆነ ለተከበረው ምክር ቤት የማሳወቅ ስራ ተሰርቷል።

በዚህም መሰረት:----

1) አቶ መልካሙ ሺበሺ ከፐብሊክ ሰርቭስ ወደ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ

2) አቶ ቹመሬ የራር ከትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ወደ ኢንተርፕራይዝና ስራ ዕድል ፈጠራ መምሪያ ኃላፊ

3) አቶ ንጉሤ ማቴዎስ ከወጣቶችና ስፖርት ወደ መንግስት ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ

4 ) አቶ ጥጋቡ ጎርጊ ከትምህርት ወደ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ

5 ) አቶ አሸናፊ ጩንጩሌ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን ወደ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ

ሆነው እንዲሰሩ ሽግሽግ ተደርጎላቸዋል።

የደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።         የካትት 18/2017 ዓ.ም ዲመካየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት...
25/02/2025

የደቡብ ኦሞ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

የካትት 18/2017 ዓ.ም ዲመካ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ወላይተ ቢቶ እና የክልሉ ፌደረሽን ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዳርጌ ዳሼ እና ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ተገኝተዋል።

የተከበረው ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የሆኑት የተከበሩ አቶ ሎስንዴ ሎኛሱዋ ጉባኤው ነህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ውይይት በማድረግ የስራ አቅጣጫ አመላካች መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው በሶስት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፧

አጀንዳ 1. የ4ኛ ዙር 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ረቂቅ ሪፖርት መርምሮ ማፅደቅ ፦

አጀንዳ 2. የ2017 የአስተዳደር ምክር ቤት አፈጻጸም ሪፖርት መርምሮ ማፅደቅ እና

አጀንዳ 3. ስምርትና ሹመት መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በማሌ ወረዳ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥ እንቅሰቃሴ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ።ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 17/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖በማሌ ወረዳ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ...
24/02/2025

በማሌ ወረዳ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥ እንቅሰቃሴ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ።
ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 17/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

በማሌ ወረዳ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥ ዘመቻ ተጠናክሮ እየቀጠለ ሲሆን በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ እየተካሄደ ይገኛል።

የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሀገራችን ብቻም ሳይሆን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በህዝብ ተሣትፎ ከተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባር ቀደም ደረጃ እንደሚይዝ ገልጸዋል።

ባለፉት14 ዓመታት ለግድቡ ግንባታ የሀገራችን ዜጎች አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ የወረዳችን ማህበረሰቦችም እስካሁን ባለው 3 ዙር በስጦታና በቁጠባ መልክ ለግድቡ ግንባታ የጋራ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

በዚህም ትልቁን የቁጠባ ድርሻ የተወጣው መንግስት ሠራተኛው መሆኑ ይታወቃል።

እንደ ንግድ ማህበረሰብ፣ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮችና እና የተለያዩ ተቋማት በስጦታ እና በቁጠባ መልክ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት ወረዳው በማህበረሰቡ ተሳትፎ አራተኛውን የቁጠባ ቦንድ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚገዛ አስታውቀዋል።

የተለያዩ መጠኖች ያላቸው ቦንዶች ተዘጋጅተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሌሞ ጌንቶ ቅርንጫፍ ውስጥ ለግዢ የቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል።

በዛሬው ዕለት በተደረገው የባለድርሻ አካላት ውይይት ከ21,000 ብር በላይ የቦንድ ግዥ እንደተከናወነ ተገልጿል።

በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪው ማህበረሰቡ ሁሉ እና ተቋማት ቦንድ በመግዛት የቁጠባ ባህልን እንዲያሳድጉ ጥሪ አድርዋል። ሁሉም ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ተቋማት ለዚህ አገራዊ ጉዳይ የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በወይይቱ ማጠቃለያ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው የ4,000 /አራት ሺህ/ ብር ቁጠባ ቦንድ ግዥ ፈፅመዋል።

የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የማሌ ወረዳ የፐብሊክ ሰርቫንት አባላት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡ሌሞጌንቶ፣ የካቲት10/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖...
17/02/2025

የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የማሌ ወረዳ የፐብሊክ ሰርቫንት አባላት የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ሌሞጌንቶ፣ የካቲት10/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
“ከቃል እስከ ባህል “ በሚል መሪ ርዕስ ከጥር 23-25/2017 ዓ/ም ድረስ ሀገራዊ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዶ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

የፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የጉባኤ ውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የማሌ አጠቃላይ የፐብሊክ ሰርቫንት አባላት የውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡

መድረኩን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ተርቸላ እና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ እስራኤል ሰሊዛ በጋራ መርተዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ የጉባኤ ውሳኔዎችና ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የመወያያ ሰነድ የማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግሥት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ እስራኤል ሰሊዛ ያቀረቡ ሲሆን ባለፉት ዓመታት ፓርቲው ያከናወናቸውን ተግባራት ስኬቶችና ተግዳሮት እንዲሁም የጉባኤ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

የመወያያ ሰነዱን ተከትሎ ጥያቄና አስተያየት ከተሳታፊዎች ተነስቶ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በ2ኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተቀመጡ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን ተፈፃሚ በማድረግ ረገድ የፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር ብልጽግና ህብረት ሚና ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተጠቁሟል።

ምክር ቤቱ የፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አፅድቋልምክር ቤቱ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት አፅድቋል በተጨማሪ ከዚህ ቀደምየክልሉ ምክር ቤት ቀርበው ቃለመሃላ ያልፈፀሙ የክልል ቢሮ ኃላፊዎች በርዕሰ መስ...
15/02/2025

ምክር ቤቱ የፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አፅድቋል

ምክር ቤቱ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት አፅድቋል በተጨማሪ ከዚህ ቀደም
የክልሉ ምክር ቤት ቀርበው ቃለመሃላ ያልፈፀሙ የክልል ቢሮ ኃላፊዎች በርዕሰ መስተዳድሩ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ ቀደም መስተዳድር ምክር ቤቱ በውክልና ሲያሰራቸው የቆዩ የቢሮ ኃላፊዎች ቀርበው ቃለ መሃላ እንዲፈፅሙ ምክር ቤቱን በጠየቁት መሰረት

አቶ ፍቃደስላሴ ቤዛ የክልሉ ፕላን ቢሮ ኃላፋ

አቶ ኦላዶ ኦሌ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

ወ/ሮ ወይንቱ አልጎ የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፋ በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Maale Woreda Prosperity Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Maale Woreda Prosperity Party:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share