
08/03/2025
የማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የ2017 ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
ሌሞጌንቶ፣ የካቲት 29/2017 ዓ.ም (ማወብፓ)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለፉት ስድስት ወራት በፓርቲው የተከናወኑ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶች ላይ የተመሰረተ የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ን/ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ብሩክ ታደሰ የግምገማ መድረኩ ዋና ዓላማ በፓርቲው ተግባራት በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ በጥንካሬ የተገኙትን ለማካበት እና በጉድለት የተለዩትን በማረም የትኩረት አቅጣጫዎች ማስቀመጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
በመድረኩ የወረዳው መንግሥት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙሃባ ሙሄ የመንፈቀ ዓመቱን የሥራ አፈፃፀም የያዘ ሰነድ አቅርበዋል።
በፖለቲካዊ እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ረገድ፣ ፓርቲው ከህዝቡ ጋር አንድነትን እና ትብብርን ለማጠናከር በመስራት ላይ ሲሆን፣ የጋራ ግቦችን ለማሳካት እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ትኩረት አድርጓል ሲል ከሪፖርቱ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የሴቶች ክንፍ በተለይ በማህበራዊ አገልግሎቶች ረገድ ተሳትፎ ያሳዩ ሲሆን የጤና ዘመቻዎችን እና የትምህርት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ሴቶችን ለማብቃት እና በማህበራዊ ልማት ረገድ እንዲሳተፉ ማድረግ ተችሏል።
በተደረገው ድጋፍና የግንዛቤ ማስጨበጫ በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት 147 ሴቶች የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ ተደርገዋል፣ እንዲሁም 11,584 ሴቶች በትምህርት ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ሆነዋል።
በመድረኩ የቀበሌያት ሊቀመናብርት እና የወረዳው አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ከተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
በቀጣይ ፓርቲው የአደረጃጀት መዋቅሮቹን ለማጠናከር፣ የአባላት መዋጮን ለማሳደግ እና ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተገኙትን ድክመቶች ለመፍታት እንደሚሰራም በመግባባት መድረኩ ተጠቃሏል።