Finote Tebeb

Finote Tebeb ጥበብ

19/10/2023
21/09/2023

07/09/2023

07/09/2023
06/09/2023
🌼🌼ለአዲስ አመት አዲስ መላ ከቤቴን ኢትዮጵያ !🌼🌼ለቤቶ ጉዳይ እንደ ቤተስቦ የሆነው ቤቴን ኢትዮጵያ ከቤት ከግንባታ እስከ እድሳት ባለሞያዎች፣ከኢንቴርየር ዲዛይነር እስከ የእንጨት ሰራተኛ፣ከ...
05/09/2023

🌼🌼ለአዲስ አመት አዲስ መላ ከቤቴን ኢትዮጵያ !🌼🌼
ለቤቶ ጉዳይ እንደ ቤተስቦ የሆነው ቤቴን ኢትዮጵያ ከቤት ከግንባታ እስከ እድሳት ባለሞያዎች፣
ከኢንቴርየር ዲዛይነር እስከ የእንጨት ሰራተኛ፣
ከሴራሚክ ሰራተኛ እስከ ሙሉ ፊኒሺንግ ሰራተኛ፣
ከቀለም ቀቢ እስከ ዉሃ እና ፍሳሽ መስመር ሰራተኛ፣
ከብረት ሰራተኛ እስከ ኤሌክትሪክ ሰራተኛ፣
ከቆርቋሪ እስከ ግንባታ ሰራተኛ፣
ምን ጠፍቶ! ሁሉንም በአንድ ቦታ ከባለሙያዬ ያገኛሉ ።
https://t.me/betenethiopiachannel

እኛን ሲመርጡ ፈልግዉ የሚያጡት ንብረት የለም፡፡ ከማማከር እስከ ግዥ ድረስ በምንሰጠዉ አገልግሎት ይረካሉ።ከቪላ ቤት እስከ አፓርትመንት፤ከመኖሪያ እስከ ንግድ ህንፃ፤ከቤት መስሪያ ቦታ እስከ ...
31/08/2023

እኛን ሲመርጡ ፈልግዉ የሚያጡት ንብረት የለም፡፡ ከማማከር እስከ ግዥ ድረስ በምንሰጠዉ አገልግሎት ይረካሉ።
ከቪላ ቤት እስከ አፓርትመንት፤
ከመኖሪያ እስከ ንግድ ህንፃ፤
ከቤት መስሪያ ቦታ እስከ መጋዘን፤
አረ ምኑ ጠፍቶ! ከእርሶ የሚጠበቀዉ ፍላጎቶን ማሳወቅ ብቻ ነዉ።
👉 ያግኙን! 090 700 0111 https://www.facebook.com/betenethiopia

31/08/2023



አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ አምስት በዚች ቀን በሰማዕትነት ሞተ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሃያ አራቱ ባልንጀሮቹ በሰማዕትነት ሞቱ፣ ቅዱሱ አባት አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞



ነሐሴ ሃያ አምስት በዚህች ቀን ቅዱስ እንድርያኖስ በሰማዕትነት ሞተ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሃያ አራቱ ባልንጀሮቹ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም እንድርያኖስ ከመክስምያኖስ መኳንንቶች አንዱ ነበር እርሱም የጐልማሶች አለቃ ነበረ። ለጣዖት መስገድን እምቤ ስለአሉ ንጉሡ ምእምናንን ሲአሠቃያቸው ቅዱስ እንድርያኖስ የሰማዕታትን የልባቸውን ቆራጥነትና በመከራቸው ላይ መታገሣቸውን ተመልክቶ አደነቀ።

እንዲህም አላቸው ይህን ያህል ስትታገሡ ምን ታገኛላችሁ ቅዱሳን ሰማዕታትም የሚጠብቀንን ተሰፋ ለመናገር አንደበታችን አይችልም አሉት ስለ ዓለም ድኅነትም ክርስቶስ መከራ እንደ ተቀበለ ከብሉይና ከሐዲስ መጽሐፍ ነገሩት።

እንድርያኖስም በሰማ ጊዜ ጽሕፈትን ወደ ሚያውቁ ብልሆች ሰዎች ሔደና እኔ ከዛሬ ጀምሮ ክርስቲያን ነኝ ስሜን ከገድለኞቹ ጋራ ጻፉ አላቸው።

ለንጉሥ መክስምያኖስም እንዲህ እንዳለ በነገሩት ጊዜ ጠርቶ እንድርያኖስ ሆይ አበድክን አለው እንድርያኖስም ከቀድሞው እብደቴ ተመለስኩ እንጂ እኔ አላበድኩም ብሎ መለሰለት።

ንጉሡም ሰምቶ ወደ ወህኒ ቤት ከንጹሐን ሰማዕታት ጋራ እንዲጨምሩት አዘዘ። ከአገልጋዮቹም አንዱ ሒዶ ለሚስቱ እንጣልያ ነገራት በስማችም ጊዜ ደስ እያላት ወደ ወህኒ ቤት ሔደች ሃያ አራቱ ቅዱሳን ሰማዕታት የታሠሩበትን ማሠሪያቸውን ሳመች በሥቃዩ እንዲታገሥ የባሏን ልብ ያጽናኑ ዘንድ ለመነቻቸው። እርሱንም እንዲህ አለችው ላህይህ ደምግባትህም ርስትህም ጥሪትህም አያስትህ ሁሉም ከንቱ ነውና ነገር ግን በእርሱ ዘንድ የማያልፍ መንግሥትን ትወርስ ዘንድ የክብር ንጉሥ ክርስቶስን ተከተለው ይህንንም ብላ ወደቤቷ ገባች።

ከዚህም በኃላ እንድርያኖስ ለፍርድ እንደ ሚአቀርቡት በአወቀ ጊዜ ሊሰናበታት ወደ ሚስቱ ሔደ መምጣቱንም ሰምታ የሸሸ መሰላት ደጇንም ዘግታ በውስጥ ሁና እንዲህ እያለች ዘለፈችው ትላንት ሰማዕት ተብለኽ ዛሬ ክርስቶስን ካድከውን እንድርያኖስም ሰምቶ የሃይማኖቷን ጽናት አደነቀ እንዲህም አላት እኅቴ ሆይ እንድስናበትሽ ክፈችልኝ አላት።

በሰማችም ጊዜ ከፈተችለት ከዚህም በኃላ ሁሉን እያነጋገራት እስከ በኃላ ሁሉን እያነጋገራት እስከ እሥር ቤት ወሰዳት እንጣልያም ከዚያ በደረሰች ጊዜ የታሠሩትን ቅዱሳን ተሳለመቻቸው ቅስላቸውንም አጠበች።

ከዚህም በኃላ ንጉሡ ቅዱሳኑን ከእሥር ቤት እንደአመጧቸው አዘዘ በመጡም ጊዜ ከሥቃይ ብዛት የተነሣ እንደደከሙ አያቸው። እንድርያኖስንም በፊቱ አቁሞ ለአማልክት ሠዋ አለው ቅዱሱም እርሱንና የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ ንጉሡም የሆድ ዕቃው እስኪፈስስ ሆዱን እንዲደበድቡት አዘዘ በዚያን ጊዜም የእንድርያኖስ ዕድሜው ሃያ ስምንት ዓመት ነበር።

ከዚህም በኃላ እንድርያኖስን ከባልንጀሮቹ ሰማዕታት ጋራ ወደ እሥር ቤት መለሱት እንጣልያም መጥታ የቅዱሳንን ደማቸውን ጠራረገችላቸው። እሊህ ቅዱሳንም እንድርያኖስን እንዲህ ብለው ተሳለሙት እንድርያኖስ ሆይ ስምህ ተሳለሙት በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎአልና ደስ ይበልህ ።

ንጉሡም መሰፍ አምጥተው የቅዱሳኑን ሁሉ ጭናቸውን በድጅኖ ይሰብሩ ዘንድ አዘዘ እንጣልያም የእንድርያኖስን እጆቹንና እግሮቹን በመስፍ ላይ ለማኖር ቀደመች ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ እስከ ሰጠ ድረስ የእንድርያኖስን ዐጥንቶቹን ወታደሮች ቀጠቀጡ የቅዱሳኑንም ሁሉ ጭናቸውን ሰብረው ወደ እሳት ወረወሯቸው እሳቱ ግን ከቶ አልነካቸውም ።

ምእመናንም መጥተው በጭልታ ወደ ሌላ ቦታ ወሰዱአቸው የመከራውም ወራት እስቲያልፍ ሠወሩአቸው። እንጣልያም የእንድርያኖስን የእጁን ቁራጭ ወስዳ በትርአሷ ውስጥ አኖረችው።

ከዚህም በኃላ የሀገሩ ገዥ እንጣልያን ሊአገባት ወደደ በአወቀችም ጊዜ የባሏን የእጅ ቁራጭ ይዛ በመርከብ ሸሸች የቅዱሳኑ ሥጋ ወዳለበትም ደርሶ ወደ እነርሱ ይቀበሏት ዘንድ ለመነች ጌታችንም ልመናዋን ተቀብሎ አሳረፋት ከእነርሱም ጋራ ተቀበረች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞



በዚህችም ቀን ቅዱሱ አባት አባ ቢጻርዮን አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምእመናን ነበሩ። በአደገም ጊዜ የምንኵስና ልብስን ለብሶ እግዚአብሔርን ሊአገለግል ወደደ ዓለምንም ንቆ ወደ አባ እንጦንስ ሔደ ለእርሱም ደቀ መዝሙር ሆኖ ብዙ ዘመናት አገለገለው።

ከዚህም በኃላ ወደ አባ መቃርስ ሒዶ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትንም አገለገላቸው። በአስቄጥስም ገዳም ይዘዋወር ነበር በቤት ውስጥም አያድርም ነበር። ምንጣፍና ልብስ እስኪአጣ ድረስ ምንም ምን ጥሪት አልነበረውም መነኰሳቱም የማቅ ጨርቅ ይሰጡት ነበር። ወገቡንም ታጥቆ በመነኰሳቱ መንደር ይዞር ነበር በቤቶቻቸውም ደጃፍ እያለቀሰ ይቀመጥ ነበር።

የማያውቀውም ወደርሱ በደረሰ ጊዜ አባቴ ሆይ ምን ያስለቅስሃል ይለው ነበር። እርሱም ንብረቴን ስለዘረፉኝ እንዳልሞት ሸሸሁ ከወገኔም ክብር ተለይቼ በጉስቁልና ወደቅሁ ይለው ነበር። የቃሉንም ምልክት የማያውቅ የጠፋውን ገንዘብህን እግዚአብሔር ይመልስልህ ብሎ ካለው ይሰጠው ነበር። እርሱም ተቀብሎ ይሔድና ለሌለው ይሰጥ ነበር።

የቃሉን ምልክት የሚያውቅ ግን በፈቃደ ነፍስ የሚሠሩ ትሩፋትን ሰይጣን ከሰዎች የማረካቸው መሆኑን ልብ ብሎ ያስተውል ነበር። አባቶችም ጭንቅ የነበረ ተጋድሎውን ስለርሱ ይናገሩ ነበር። እርሱ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት ከቶ ሳይተኛ ቁሞ ኖሮአልና ።

በምንኩስናውም ወራት ብዙ ጊዜ በየአርባ ቀን ጾመ እነሆ እንዲህ እየተጋደለ ድንቆችንም እያደረገ ኀምሳ ሰባት ዓመታት ኖረ። ቅዱሳን አባ ዱላስና አባ ዮሐንስም ከተአምራቱ ተናገሩ እነርሱ ከርሱ ጋር ወደ ኤርትራ ባሕር ዳርቻ ሔዱ። እጅግም በተጠሙ ጊዜ እንደተጠሙ አውቆ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ መራራውንም ውኃ ጣፋጭ አድርጎላቸው ጠጥተዋል።

በሁለተኛም ጊዜ ወደ ፈሳሽ ውኃ ደርሶ መሸጋገሪያ አጣ ወደ ጌታችንም ጸለየ ያን ጊዜም እንደ የብስ በባሕሩ ላይ ሔደ። በአንዲት ቀንም የከበሩ አባቶች በጸሎታቸው ያድኑት ዘንድ ጋኔን ያደረበትን ሰው ወደ አስቄጥስ ገዳም ሰዎች አመጡ አባቶችም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ እርሱ ከከንቱ ውዳሴ ስለሚሸሽ ብንነግረው ይህን ጋኔን የያዘውን አያድነውም ።

አባ ቢጻርዮን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለጸሎት ወደሚቆምበት ቦታ ያንን ጋኔን ያደረበትን ሰው አስተኙት። አባ ቢጻርዮንም በገባ ጊዜ ያን ጋኔን ያደረበትን ሰው ተኝቶ አገኘውና ቀሰቀሰው እጁንም ይዞ ተነሥ አለው ያን ጊዜም ድኖ ተነሣ አእምሮውም ተመለሰ። ያዩትም እጅግ አደነቁ ለሚፈሩት ስለሚሰጠው ጸጋውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት።

የዚህም ቅዱስ ተአምራቶቹ ከነገርናችሁ የበዙ ናቸው እግዚአብሔርንም አገልገሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

( )

30/08/2023

TikTok

መካሪ ወንድማችን ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ተከታዪን መልዕክት አስተላልፎልናል።Henok Haile + ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል? +"ከረሃብ ሰይፍ ይሻላል" የሚል የአበው ብሂል ቢኖርም አሁን ሁለቱም...
28/02/2023

መካሪ ወንድማችን ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ተከታዪን መልዕክት አስተላልፎልናል።
Henok Haile
+ ረሀብ ስንት ቀን ይፈጃል? +
"ከረሃብ ሰይፍ ይሻላል" የሚል የአበው ብሂል ቢኖርም አሁን ሁለቱም እሳቶች ወገናችንን እየፈጁ ነው:: ከጦርነት እሳት ያመለጠውን የረሃብ እሳት ይቀበለዋል:: ረሃብን በምን ቃል እንግለጸው? በዚህች ደቂቃ ውስጥ አንተ ይሄን ጽሑፍ ስታነብ በረሃብ አለንጋ ክፉኛ ተገርፎ እያሸለበ ያለ ብዙ ወገን አለ::
ረሃብን ለመግለጽ ምን ቃል አለ?? ነፍሳቸውን ይማርና ሁለቱ ዕንቁ ደራስያን ጋሽ ጸጋዬ እና ጋሽ ስብሐት እንዲህ ብለው ነበር :-
ረሃብ ቀጠሮ ይሰጣል?
ወይስ ቀን ቆጥሮ ይፈጃል?
“የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል”
ይባላል፣ ድሮም ይባላል
ይዘለዝላል ይከትፋል
ብቻ እስከሚጨርስ ድረስ ሆድ ለሆድ ጊዜ ይሰጣል?
ወተት አንጀት ነጥፎ ሲላብ
ሆድ ዕቃ ደርቆ ሆድ ሲራብ
ተሟጦ አንጀት በአንጀት ሲሳብ …
የጣር ቀጠሮው ስንት ነው?
ለሰው ልጅ ሰው ለምንለው?
ላይችል ሰጥቶ ለሚያስችለው?
ስንት ቀን ነው? ስንት ሌት ነው?
(ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን)
"የተራቡ ልጆች አባት ምሬት :-
አበላቸው እህል ከልክለህ አምስት ልጆች የሠጠኸኝ ምነው?
አምስት ልጅ ተሰብስቦ አንድ ላይ ሲውል አንዲት ሳቅ ብቅ ሳትል መምሸቱ ምነው?
ልጆቼ አንዲት ቀን እንኳን አኩኩሉ ሳይጫወቱ ማለቃቸው ምነው?
ልጆቼን በአንድ ቀን ስቀብር ዝም ብለህ ማየትህ ምነው?"
(ጋሽ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር)
በያለንበት ለምግብ በተቀመጥን ጊዜ እያንዳንዱ ጉርሻ የሆነን ሰው ዕድሜ ሊያራዝም ይችል እንደነበረ እናስብ::
ጠጥተን የምንታጠብበትን ውኃ አጥቶ በዚህች ቅጽበት የሚያሸልብ ወገናችንን አንርሳ:: ደግመን እንላለን ጦርነት ክፉ ነው:: ረሃብ ደግሞ የባሰ ነው:: ሀገራችንን ከሁለቱም ዕረፍት ትፈልጋለች:: እስከዚያው ግን ለወገኖቻችን በየአቅጣጫው እንረባረብ!
በቦረና በረሃብ ወገኖቻችን እያለቁ ነው:: ከሰኞ ጀምሮ የእርዳታ ዘመቻ ይጀመራል::


በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ ጾም መሠረት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት “ቅድስት” ይባላል፡፡ ‹ቅድስት› ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታች...
27/02/2023

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ ጾም መሠረት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት “ቅድስት” ይባላል፡፡ ‹ቅድስት› ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፣ የተቀደሰች፣ የከበረች፣ ልዩ፣ ንጹሕ፣ ክቡር መሆኗን ያመለክታል፡፡

በዚህ ሳምንትም የሚዘመሩ መዝሙራትና የሚሰበኩት ትምህርቶች በሙሉ እግዚአብሔርን ስለ ማመስገንና ስለ ቅድስና ናቸው፡፡ ቅዱስ ያሬድ “ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው፤ ለስሙም ምስጋናን ስጡ /አቅርቡ/፤ ሰንበትን አክብሩ፤ እውነትንም አድርጉ፤ ብል የማያበላሸው፣ ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችሁም ተቀመጡ፤ ክርስቶስ ወዳለበት ወደ ላይ አስቡ” ብሎ ለእግዚአብሔር ስለሚቀርብ ምስጋና ገልጿል፡፡ (ጾመ ድጓ)

ቅዱስ ጳውሎስም ለተሰለንቆ የላከው መልእክት፣ የቅዱስ ጴጥሮስ አንደኛ መልእክቱ እንዲሁም በሐዋርያት ሥራ በምዕራፍ ዐሥር ላይ የሚገኘው ምንባብም በዚህ ወቅት ይነበባሉ፤ (፩ኛተሰ.፬÷፩-፲፫፣፩ኛጴጥ.፩÷፲፫-ፍጻሜ፣ሐዋ.፲÷፲፯-፴)

እነዚህም ምንባባት ቅዱሳን ሐዋርያት ያስተላለፏቸውን መልእክታት የያዙ ሲሆን በተለያም “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ” ብሎ ያስተማረውን የአምላካችንን ትምህርት ያዘክራሉ፡፡ (፩ኛጴጥ.፩፥፲፮) በክርስቶስ ክርስቲያን ለተበላልን ሰዎች ከኃጢአት የነጻና የቅድስና ሕይወት ሊኖረን እንደሚገባም ያስተምራሉ፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር በቅድስና ሕይወት እንድንኖር ይርዳን፤ አሜን!

________________________________
#ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስተዋህዶቤተክርስቲያን🙏❤ #ማርያም #መድኃኔዓለም #ኢየሱስ
#ሰንበት

#ገብርኤል #ሚካኤል
#ሀበሻ #አንድፓትርያርክ #ቅዱስሲኖዶስ #ማርያም

፩ኛ. ዘወረደ፡- በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስ...
27/02/2023

፩ኛ. ዘወረደ፡- በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡

________________________________
#ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስተዋህዶቤተክርስቲያን🙏❤ #ማርያም #መድኃኔዓለም #ኢየሱስ
#ሰንበት

#ገብርኤል #ሚካኤል
#ሀበሻ #አንድፓትርያርክ #ቅዱስሲኖዶስ
Edited · 10h

እኔ ከቤተክርስተቲያን ጎን ነኝ
23/01/2023

እኔ ከቤተክርስተቲያን ጎን ነኝ

"...በታክሲ ውስጥ ስትሄድ አንድ ጋጠ ወጥ ሰው ቢገጥምህና የማይሆን ቃል ቢናገርህ ለእርሱ ቦታ አትስጠው፡፡ አንዱ ፌርማታ ላይ ይወርዳል፤ ከዚያ በኋላ አታገኘውም፡፡ አንተን ግን ቀኑን ሙሉ ...
21/01/2023

"...በታክሲ ውስጥ ስትሄድ አንድ ጋጠ ወጥ ሰው ቢገጥምህና የማይሆን ቃል ቢናገርህ ለእርሱ ቦታ አትስጠው፡፡ አንዱ ፌርማታ ላይ ይወርዳል፤ ከዚያ በኋላ አታገኘውም፡፡ አንተን ግን ቀኑን ሙሉ ሲበጠብጥህ ይውላል፡፡

"ቁንጫ የጠረጉት ዕለት ባለጌም የመከሩት ዕለት ይብሰዋል" እንዲሉ ምክር ለሁሉ አይሰጥም፣ መልስ ለሁሉም አይመለስም፤ ክርክር ከሁሉም ጋር አይደረግም፡፡ ዕንቁዎችህን የምትሰጣቸውን ሰዎች ለይ፡፡ ዕንቁላሎችህንም የምታስታቅፋቸውን ዶሮዎች ምረጥ፡፡"

መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

ታኅሣሥ  ፳፬ኢትዮጵያ በፍጹም ፀሐይ የደመቀችበት ያጌጠችበት ቀን          እንኳን ለፀሐየ ጽድቅ ቅዱስ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል አደረሳችሁ"የአባታችሁ ስም አጠራሩ ተክለሃይማኖት ተብሎ...
02/01/2023

ታኅሣሥ  ፳፬
ኢትዮጵያ በፍጹም ፀሐይ የደመቀችበት ያጌጠችበት ቀን
          እንኳን ለፀሐየ ጽድቅ ቅዱስ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል አደረሳችሁ
"የአባታችሁ ስም አጠራሩ ተክለሃይማኖት ተብሎ በሚጠራ ጊዜ ሰማይ በከዋክብት እንደተሸለመ ምድርም በአበቦዎች እንደተጌጠች ያህል ምንኛ የተጌጠ ነው።

Emebete
17/12/2022

Emebete

እንኳን አደረሳችሁ
30/11/2022

እንኳን አደረሳችሁ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Finote Tebeb posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share


Other Private Plane Charters in Addis Ababa

Show All