Asme Tour Service

Asme Tour Service Asme Tour Service from Addis Ababa Ethiopia by Asmelash Mare in 2022 Student of Tourism management.

01/11/2023
 #ትዝብት! #የቱሪዝም ኤግዚቢሽን በሳይንስ   ሙዚየም ከመስከረም 28 ጀምሮ ለአንድ  ወር እስከ ጥቅምት 28 በአድስ አበባ ሳይንስ ሙዝየም እየታዬ ነው። ትናንት ወደ ስፍራው አቅንቼ ነበር ...
25/10/2023

#ትዝብት!
#የቱሪዝም ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም

ከመስከረም 28 ጀምሮ ለአንድ ወር እስከ ጥቅምት 28 በአድስ አበባ ሳይንስ ሙዝየም እየታዬ ነው።

ትናንት ወደ ስፍራው አቅንቼ ነበር ያለው ነገር በጣም ያምራል ከጠበኩት በላይ ነው፤ ሁሉም ክልሎች፤ የአድስ አበባና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በአከባቢያቸው የምገኘውን የቱሪዝም መስህብ በፅሁፍ፣ በቪዲዮ፣ እንድሁም በምስልና በቅርፅ አስደግፈው አቅርበዋል።
ሆቴሎች፤ አስጎብኚ ድርጅቶች፤ ፤የሆቴልና የቱሪዝም ማህበራት እንድሁም ለሎችም በርካታ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው ለእይታ ቀርበዋል።

ነገር ግን ብዙም ሰው የለም በጣም ጥቅት ሰው ብቻ ነበር የምጎበኘው ከዝግጅቱ አንፃር በሰልፍ ተሰልፈን ማየት ነበረብን ነገር ግን ያለው ነገር በተቃራኒው ነው።
ከ 6-8 ሚልዮን ህዝብ ይኖርበታል ተብሎ በሚገመትባት አድስ አበባ በነፃ ሀገራችሁን እወቁ ብለው ይሄን የመሰለ ውብ አውደርእይ ተዘጋጅቶ አለመሳተፍ በእውነት ያስተዛዝባል!

አስቡት አንድ ዘፋኝ ከውጭ መቶ ብሆን ከፍሎ ለመግባት ያለው ሰልፍ፤ የእግር ኳስ ጫወታ ለማየት ያውም የውጭ ሀገር ክለቦችን ለመደገፍ የምናደርገውን ትንቅንቅ ያዬ ሰው አሁን በነፃ ሀገርህን እወቅ ተብሎ ሰው ስጠፋ በእውነት ያሳዝናል! የሀገር ፍቅር ከዝህ ነው የምጀምረው ስለ ሀገርህ ሳታውቅ ሀገሬን እወዳለሁ ማለት ጥያቄ ውስጥ ይከታል?

ስለእውነት ሁላችንም ኢትዮጵያ ያላትን ሀብቷን ፤ ታርኳን፤ ቅርሷን ከቦታው ተገኝተን መጎብኘት ነበረብን! ባይሆን ይሄን መልካም አጋጣሚ ተጠቅመን ሁሉንም ቅርሶች በአንድላይ መጎብኘት ይገባን ነበር!

እኛ ኢትዮጵያዊያን በራሳችንን ታርክ ለመኩራት ግዴታ ፈረንጆች መተው እስክነግሩን መጠበቅ አለብን?
አብዛኞቻችን እንደዚህ አይነት ሀገራዊ ድግስ ውስጥ ለመሳተፍ ግዜ የለንም ሀገራችን ስላላት የቱሪዝም መስህብ አይጨንቀንም።
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ምኞቱ ሀገሩ ያለውን ላሊበላን ለመጎብኘት ሳይሆን የፈረንሳዩን" Eiffel Tower" ለመጎብኘት የሚያልም ነው!
የራስን ንቆ የሰውን አደናንቆ የት ይደረሳል? ፈረንጆች እንደሆኑ መጀመሪያ ስለሀገራቸው ጠንቅቀው አውቀው ነው ስለላው ሀገር የምያስቡት! ብናውቅ ከአመርካም፤ ከአውሮፓም የምበልጥ በዝህ አለልን።

ቱሪዝም ምንስቴር በዚህ ስራው ልመሰገን ይገባዋል ይሄ ለዘርፉ በጣም ጥሩ መነቃቃትን ይፈጥራል የምል እምነት አለኝ። ለዘርፉ ባለሙያዎች እንድሁም ለድርጅቶችም መልካም አጋጣሚ ነው።

በዚሁ ለመንግሥት ማስተላለፍ ምፈልገው መልክት እባክህ ሀገራችንን ሰላም አድርግልን!
ይሄን አውደርእይ ማዘጋጀትህ በጣም ጥሩና የምታበረታታ ነው፤ ነገር ግን ቱሪዝም እና ሰላም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ማለት ሰላም ከለላ ቱሪዝም የምባል ነገር የለም አይታሰብም።
እንደዚህ አይነት አንድ ሽ አውደርእይ ብታዘጋጅ አንድ ሽ ፓርክ ብትገነባ ሰላም ከለሌ ከንቱ ልፋት ይሆንብሃል። የሀገራችን ሁኔታ የምናየው ነው እንኳን የውጪ ሀገር ዜጋ ለእኛም ለእንቅስቃሴ ያሰጋል አሁን ማንም ከ አድስ አበባ 100 ክ.ሜ ወቶ መጎብኘት የምፈልግ የለም ስለዚህ እባክህን መንግስታችን ከፈጣሪ በታች አሁን ሀገራችን ኢትዮጵያ በርሶ እጅ ነው ያለችው ከሁሉም በላይ ሰርቶ ለመኖር ወቶ ለመግባት ሰላም ያስፈጋታል እባክህን ሰላሟን ስጣት!

ኤግዚቢሽኑ ለተጨማሪ አስራ አራት ቀናት እስከ ጥቅምት 28 ከእሁድ እስከ እሁድ ክፍት ነው ሁላችንም በነፃ በተመቸን ቀን እና ሰዓት ለአንድ አፍታ ጎራ ብለን የሀገራችንን ባህል፤ታርክ፤ ቅርስ አውቀን በሀገራችን እንድንኮራ የቱሪዝም ምንስቴር ጋብዞናል።

ሐምሌ 9 እሁድ ደረሰ ታላቅ የበረከት ጉዞ ወደ አባታችን ወደ ፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እንሄዳለን ይህ የበረከት ጥር እንዳያመልጣችሁ አሁኑኑ ደውላችሁ ተመዝገቡ ።09 45 49 82 0609 ...
11/07/2023

ሐምሌ 9 እሁድ ደረሰ ታላቅ የበረከት ጉዞ ወደ አባታችን ወደ ፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት እንሄዳለን ይህ የበረከት ጥር እንዳያመልጣችሁ አሁኑኑ ደውላችሁ ተመዝገቡ ።
09 45 49 82 06
09 85 41 59 61
አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት 22 አመት በሁለት እግራቸው 7 አመት ደግሞ በአንድ እግራቸው ለሀገራቸው ለኢትዮጵያ 29 አመት የፀለዩበት ከጌታችን፤ ከመዳንታችን ከ እየሱስ ክርስቶስ ቃል ክዳን የተቀበሉበት ፤ በገዳምህ በ ደብረሊባኖስ መቶ መቃብርህን የተሳለመውን አስር ትውልድ እምርልሀለሁ፤ የነን መቃብር እንደተሳለመ እቆጥርለታለሁ ብሎ ቃል ክዳን የገባለት ቅዱስ ስፍራ፤ በፀበሉ ብዙዎች የተፈወሱበት እየተፈወሱም ያሉበት ሥፍራ ኑ አብረን እንሳለም፤ ፀበሉን ተጠምቀን፣ እምነት ተቀብተን ፣ መስቀሉን ተሳልመን በረከት ይዘን ለነፍስ ለስጋችን ድኅነትን አግኝተን እንመለስ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/asmetourservice

ጉዞ ወደ ታላቁ ደብረሊባኖስ ገዳም ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም።     ኑ አብረን እንሳለም!አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከጌታ ቃል ክዳን የተቀበሉበት፣ ደማቸውን ባፈሰሱበ፣ መከራና ፈተና ባሳለፉ...
08/07/2023

ጉዞ ወደ ታላቁ ደብረሊባኖስ ገዳም ሐምሌ 9/2015 ዓ.ም።
ኑ አብረን እንሳለም!
አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ከጌታ ቃል ክዳን የተቀበሉበት፣ ደማቸውን ባፈሰሱበ፣ መከራና ፈተና ባሳለፉበት የበረከት ስፍራ
#ኑ አብረን እንሳለም!
አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የተሰጣቸው ቃል ክዳን ያልጎደለባቸው አሁንም ገድላቸው በምነበብበት ጽላታቸው በተቀረፀበት ታአምራትን ያደርጋል። ይልቁንም ገድላቸውንም በፈፀሙበት በታላቁ ደብረሊባኖስ ገዳም ድውያን ይፈወሳሉ፣ አጋንንት ይወጣሉ፣ የተራቡ ይጠግባሉ፣ ከ 8000 ያላነሱ አባቶች እናቶች የነገዋ ቤተክርስቲያን ተረካብዎች የአብነት ትምህርት ዘማ ይማሩበታል።
#ኑ አብረን እንሳለም!
ወደ አባታችን እንጋዝ ፀበሉን ተጠምቀን፣ እምነት ተቀብተን፣ መስቀሉን ተሻሽተን በረከት ይዘን እንመለስ!
መነሻ:- መክስኮ ሸበለ ሆተል ፍት ለፍት
ከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት,
ይህ ታላቅ የበረከት ጉዞ እንዳያመልጦት
አሁኑኑ ይደውሉልን!
#09 45 49 82 06
#09 85 41 59 61
ከላይ ባለው ቁጥር በ telegram በ whatsapp እንድሁም በ imo ያገኙናል ።
በተጨማር ከታች ባለው ልንክ የ telegram ጉሩፓችንን በመቀላቀል ተጨማሪ መረጃ እንድሁም ማንኛውም ጥያቄ ካላችሁ ማንሳት ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Asme Tour Service
https://t.me/asmetourservice

ጉዞ ወደ ታላቁ ደብረሊባኖስ ገዳም ሐምሌ 9/2015 ፤ ኑ አብረን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የፀሎት ሥፍራ የሆነውን የቃልኪዳን ቦታ ደብረሊባኖስን እንሳለም! በፀበሉ ተጠምቀን፣ እምነት...
04/07/2023

ጉዞ ወደ ታላቁ ደብረሊባኖስ ገዳም ሐምሌ 9/2015 ፤ ኑ አብረን የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የፀሎት ሥፍራ የሆነውን የቃልኪዳን ቦታ ደብረሊባኖስን እንሳለም! በፀበሉ ተጠምቀን፣ እምነት ተቀብተን፣ መስቀሉን ተሻሽተን፣ በረከትን ይዘን እንመለስ።
መነሻ:- መክስኮ ሸበለ ሆተል ፊት ለፊት
ይህ ታላቅ የበረከት ጉዞ እንዳያመልጦት አሁኑኑ ይደውሉልን
09 45 49 82 06
09 85 41 59 61
በዚህ ቁጥር በ telegram, በ WhatsApp እንድሁም በ imo ያገኙናል። 1000195797963 "አስመላሽ ማሬ" ብለው 700 ብር በንግድ ባንክ በማስገባት ደረሰኙን ከላይ ባለው ቁጥር በመላክ ይመዝገቡ።
ከታች ባለው ልንክ የቴሌግራም ጉሩፓችንን በመቀላቀል ስለጉዞው አስተያየት መስጠት ይችላሉ ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Asme Tour Service
https://t.me/asmetourservice

14/03/2023

A road trip in Ethiopia takes your breath away😍. It's a vast country with the most impressive landscapes in the world. With each passing kilometer the scenery can change from plateaus to endless outback vistas, and snow-capped mountains.

Take a trip to Ethiopia and witness some truly incredible landscapes.

📍: Key Afer to Turmi

Address

Lideta
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asme Tour Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share