24/11/2024
ዛሬ ተጀምሯል
ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።
ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።
=> ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።
የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።
የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።
የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡
የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም « » ይባላል፡፡
ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።