ቤተ-ኤጲፋንዮስ

  • Home
  • ቤተ-ኤጲፋንዮስ

ቤተ-ኤጲፋንዮስ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቤተ-ኤጲፋንዮስ, .
(2)

ኤጲፋንዮስ ማለት ገላጭ ማለት ነው።ይህም ሥም የአንድ የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጻድቅ ስም ሲሆን ከሙሴ ቀጥሎ ሥነ-ፍጥረትን አብራርቶ ተንትኖ የጻፈ "መጽሐፈ አክሲማሮስ"ን እና ሌሎች የጥበብ መጻሕፍትን የደረሰ ተወዳጅ አባት ነው። እኛም በዚህ ስም መጠራትን የመረጥነው ያልታዩ ያልተነገሩ ያልበሩ ሃሳብ ትምህርት እና መልእክትን ስለምናስተላልፍ በገጻችን ቤተ-ክርስቲያንን እና ወንጌልን ስለምንገልጥበት ነው።

    ዛሬ ተጀምሯል  ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው  ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ...
24/11/2024

ዛሬ ተጀምሯል

ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

=> ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።

የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።

የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡

የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም « » ይባላል፡፡

ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።

24/11/2024
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜንኅዳር 15-ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ አንገቱን ተሰይፎ ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ፡- የዚህ ታላቅ ሰማዕት አባቱ ...
23/11/2024

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 15-ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ አንገቱን ተሰይፎ ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡

ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ፡- የዚህ ታላቅ ሰማዕት አባቱ አውዶክስዮስ ሲሆን ሀሩም አናቅዮስ ይባላል፡፡ እርሱም ሀገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በሐሰት ነገር በመሥራት ከንጉሡ ጋር አጣላው፡፡ ንጉሡም አፍራቅያ ወደምትባል ሌላ ሀገር ልኮት በዚያ ገዥ አድርጎ ሾመው፡፡ አውዶክስዮስ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበት ደግ ሰው ስለነበር በአፍራቅያ የሚገኙ ሕዝቦችም ደስ አላቸው፡፡ የአውዶክስዮስም ልጅ አልነበረውና ሚስቱ ወደ እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን እየሄደች እመቤታችንን ትለምናት ነበር፡፡ አንድ ቀን ጸሎቷን ስትጨርስ ከእመቤታችን ሥዕሏ ድምፅ ወጣና አነጋገረቻት፡፡ ልጅ እንደምትወልድና ስሙንም ሚናስ እንደምትለው ነገረቻት፡፡ ሚናስም ተወለደና ወላጆቹ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ በ12 ዓመቱ አባቱ ዐረፈ፣ ከ3 ዓመት በኋላ እናቱም ዐረፈችና ሚናስ ብቻውን ቀረ፡፡ መኳንንቱም አባቱን በጣም ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ መስፍንነት ሹሙት፡፡
እግዚአብሔርንም መንግሥትንም በትጋትና በቅንነት እያገለገለ እያለ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ነገሠና ክርስቲያኖችን ማረድ ጀመረ፡፡ ቅዱስ ሚናስም ይህን ሲሰማ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባና በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብቻ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ፡፡ አንድ ቀን ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታት የብርሃን አክሊል ሲቀዳጁ አየ፡፡ በዚህም ጊዜ ወደ ከተማው ተመለሰና የጌታችን የመድኃታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ አምላክነት መመስከር ጀመረ፡፡

መኰንኑም የመንግሥት ወገን መሆኑን ዐውቆ በማባበል ብዙ ለመነው፡፡ ‹‹የንጉሡን ትእዘዝ አትተላለፍ›› እያለ ቢለምነው ቅዱስ ሚናስ ግን አልሰማ አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮች ያሠቃየው ጀመር፡፡ ማሠቃየቱም በሰለቸው ጊዜ አንገቱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘና ቅዱስ ሚናስ ኅዳር 15 ቀን ተሰይፎ ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡
ቅዱስ ሚናስ ምክንያት ብዙዎች በክርስቶስ አምነው ሰማዕት ሆኑ፡፡ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ እሳት አንድደው በዚያ ጨመሩት፡፡ ነገር ግን እሳቱ አልነካውም፡፡ ክርስቲያኖችም ሥጋውን ወስደው የመከራ ዘመን እስኪያልፍ ደብቀው በክብር አኖሩት፡፡ የመርዩጥ አገር ሰዎች ወደ አምስት አገሮች ሲጓዙ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው አብረው ወሰዱት፡፡ በባሕርም ላይ በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያሉ አውሬዎች ከባሕር ወጡና የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ይልሱት ዘንድ አንገታቸውን ዘረጉ፡፡ ነገር ግን ከቅዱስ ሚናስን ሥጋ ውስጥ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጥላ ገደለቻቸው፡፡ ሰዎቹም ይህን አይተው እጅግ ተደሰቱ፡፡ ወደ እስክንድርያ አገር ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ይዘው ሊመለሱ ወደው በግመል ላይ ጫኑት፡፡ ነገር ግን ግመሏ አልንቀሳቀስ አለች፡፡ ሁለተኛም በሌላ ግመል ቢጭኑትም አሁንም አልንቀሳቀስ አለች፡፡ አብዝተውም ቢደበድቧት እምቢ አለች፡፡ አሁንም ሌላ ሦስተኛ ግመል ቢሞክሩ እርሷም እምቢ አለች፡፡ ከዚያም ‹‹ይህ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት ቦታ ነው›› ብለው ቦታውን አዘጋጅተው በዚያ ቀብረውት ሄዱ፡፡

ሥጋውም ተሰውሮ ለብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ በአንድ በግ ጠባቂ እረኛ አማካኝነት ያለበት ታወቀ፡፡ ይኸውም አንድ የታመመች በግ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ተደብቆ በሚኖርበት ኮረብታ አካባቢ ባለው ውኃ ውስጥ ገብታ ስትወጣ ዳነች፡፡ እረኛውም መዳኗን አይቶ ሌሎች የታመሙ በጎቹንም በውኃው ውስጥ እየከተተ ሲሞክራቸው ፍጹም ጤነኛ ሆኑለት፡፡ ቦታውም የታወቀ ሆነና ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ሁሉም እየመጣ በውኃው እየተጠመቁና አፈሩን በውኃው እየለወሱ እየተቀቡ ይፈወሱበት ጀመር፡፡ ወሬውም እስከ ሮሙ ንጉሥ ድረስ ደረሰ፡፡ ንጉሡም የታመመች ሴት ልጅ ነበርችውና ወደ እረኛው ዘንድ ላካትና እርሷም ፍጹም ተፈወሰች፡፡ የንጉሡም ልጅ ይህ ፈውስ የሚደረግበት ነገር ምን እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ወደደች፡፡ ቅዱስ ሚናስም በሕልሟ ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋውን አስቆፍራ እንድታወጣ እግዚአብሔር ያዘዛት መሆኑን ነገራት፡፡ እንደታዘዘችውን ቅዱስ ሥጋውን አስወጥታ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን አሠራችለት፡፡ ንጉሡም በቦታው ላይ ታላቅ ከተማ እንዲሠራ አዘዘና ከተማ ሆነች፣ ስሟንም መርዩጥ አሏት፡፡ እግዚአብሔርም በቅዱስ ሚናስ ሥጋ እስከዛሬ ድረስ እጅግ አስገራሚ ተአምራት እያደረገ ይገኛል፡፡ ለመናገር የሚከብዱ እጅግ ብዙ ተአምራት ይሠራሉ፡፡ ይህችም ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ሰኔ 15 ነው፡፡

የቅዱስ ሚናስ ረድኤት በረከቱ ይደረርብን በጸሎቱ ይማረን።
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜንኅዳር 14-የሞተን ሰው አስነሥተው እውነትን እንዲመሰክር ያደረጉት አባ መርትያኖስ ዐረፉ፡፡ + አረማዊ ለነበረው ለፋርሱ ንጉሥ ታ...
23/11/2024

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 14-የሞተን ሰው አስነሥተው እውነትን እንዲመሰክር ያደረጉት አባ መርትያኖስ ዐረፉ፡፡
+ አረማዊ ለነበረው ለፋርሱ ንጉሥ ታላቅ ተአምር በማድረግ በጌታችን እንዲያምን ያደረጉት ታላቁ አባት አባ ዳንኤል ዕረፍታቸው ነው፡፡
አባ መርትያኖስ፡- ይህም ቅዱስ ሶርያ ከምትባል አገር የተገኘ ነው፡፡ እርሱም በምግባር በሃይማኖቱ፣ በትሩፋት ነተጋድሎው የተመሰገነ ሆኖ ሃይማኖትን የሚጠብቅ ሆነ፡፡ አስተምሮና መክሮ እምቢ ቢሉት አርዮሳውያንንና ከሃድያንን የሚቃወማቸውና የሚያሳድዳቸው ሆነ፣ ከምእመናንም አንድነት አውግዞ ለያቸው፡፡ ስለዚህም አርዮሳውያኑ ብዙ መከራ አደረሱበት፡፡ በመንገድም ሲሄድ እየጠበቁ እየያዙት አብዝተው ይገርፉታል፡፡ እግሩንም ይዘው በሜዳ ላይ እየጎተቱ ብዙ ያሠቃየታል፡፡ ይህንንም ብዙ ጊዜ ደጋግመው አደረጉበት፡፡
ከዚህም በኋላ አባ መርትያኖስ ከአገሩ ወጥቶ ሄዶ ከኤርትራ ባሕር ዳር ደረሰ፡፡ በዚያም ከምድር የሚበቅሉ ቅጠሎችን ብቻ እየተመገበ በዋሻ ውስጥ ብዙ ዓመታት ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ የተጋድሎው ዜና በተሰማ ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ ጠራክያ በምትባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ ብዙ ታላላቅ ተአምራትን አደረገ፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ መርትያኖስ በመንገድ ሲሄድ አንድ ሰው ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት አየ፡፡ በዚያም ቦታ አንድ ዐመፀኛ ሰው በዚያ በሞተው ሰው ላይ ሐሰት በመናገር ‹‹ከዚህ ሰው ጋር አራት መቶ የወርቅ ዲናር አለኝ›› በማለት አላስቀብርም ብሎ አወከ፡፡ አባ መርትያኖስም የሞተውን ይቀብሩት ዘንድ ያን ዐመፀኛ ቢለምኑት እምቢ አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባ መርትያኖስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩ በማለዱ ጊዜ ያ የሞተው ሰው ተነሥቶ የማንም ሰው ምንም ዓይነት ዕዳ እንደሌለበት ተናገረ፡፡
ከዚህም በኋላ አባ መርትያኖስ ያንን ዐመፀኛ ሰው በሰው ሁሉ ፊት ‹‹ለምን በሐሰት ተናገርክ? የተሰወረውን የሚያውቅ እግዚአብሔርን አትፈራምን?›› አሉት፡፡ በዚያም ጊዜ ያ ዐመፀኛ ሞተ፣ ከሞት የተነሣው ግን በሰላም ወደቤቱ ተመልሶ ሄደ፡፡ ይህንንም ያዩ ሁሉ በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ድንቅ ነገርን የሚያደርግ እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ አባ መርትያኖስም መላ ዘመኑን እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡
የአባ መርትያኖስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
አባ ዳንኤል፡- ይህም አባ ዳንኤል የተባለ ጻድቅ የፋርሱን ንጉሡ አስተምሮ ያሳመነው ነው፡፡ የፋርሱ ንጉሥ በሆድ በሽታ ሲሠቃይ ከእርሱ ጋር አብሮ የሚያኖራቸው ሥራዬኞች ሊፈውሱት አልቻሉም፡፡ ንጉሡም አንዱን ሥራዬኛ ጠርቶ ‹‹ከእኔ ጋር የመኖርህ ጥቅሙ ምንድነው? ከሆድ ሕመሜ ካላዳንከኝ እገድልሃለሁ›› አለው፡፡ ሥራዬኛውም በተንኮል ‹‹የምንግርህን ነገር ካድረግህ ትናለህ›› አለው፡፡ ‹‹ምን ላድርግ?›› ቢለው ሥራዬኛውም ‹‹ለአባትና ለእናቱ አንድ ብቻ የሆነ ልጅ አስፈልገህ እናቱ አሥራ ትያዘው፣ አባቱ ደግሞ ይረደው፣ በእርሱም ደም ትድናለህ›› አለው፡፡ ይህንንም ማለቱ አንድም ንጉሡ ይህን አያደርግም ይፈራል አሊያም በልጁ ላይ እንዲህ የሚያደርግ ወላጅ የለም ብሎ ነው፡፡ ንጉሡም በሚገዛቸው ሀገሮች ውስጥ አንድ ሺህ የወርቅ ዲናር ሰጥቶ ሕፃን ልጁን የሚሸጥለት ሰው በአሽከሮቹ አስፈልጎ የተባለውን ዓይነት ልጅ አገኘ፡፡ የተገኘውም ልጅ ወላጆቹ ድኆች ነበሩና ሸጠው ንጉሡ ዘንድ ይዘውት ሄዱና እናቱ አሥራ ይዛው አባቱ ሊያርደው ተዘጋጀ፡፡ ሕፃኑ ግን ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ጀመር፡፡ በመሀል ንጉሡ በርኅራኄ ዐይን አየውና ልጁን ይለቁት ዘንድ አዘዘ፡፡ ንጉሡም ልጁንም ወደእርሱ አቅርቦ ‹‹ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ ከንፈሮችህን ስታንቀሳቅስ ምን እያልክ ነበር?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ሕፃኑም ‹‹ወደ እግዚአብሔር ስጸልይ ነበር›› አለው፡፡ ንጉሡም ‹‹ምን ብለህ ጸለይክ?›› ሲለው ሕፃኑ ‹‹ጌታዬ ሆይ ልጅን የሚገፋው ቢኖር እናቱና አባቱ ያድኑታል፣ ከዚያም የከፋ ቢኖር ንጉሥ ዳኛ ያድነዋል እኔ ግን ከሁላችሁም እርዳታ ባጣሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ለመንኩ›› አለው፡፡
ንጉሡም ተገርሞና አዝኖ አንድ ሺህ የወርቅ ዲናሩን እንዲሁ ሰጠው፡፡ እግዚአብሔርም የንጉሡን የልብ ርኅራኄ ተመልክቶ ሊምረው ፈቀደና አባ ዳንኤልን ላከለት፡፡ አባ ዳንኤልም ንጉሡ ዘንድ በደረሰ ጊዜ በፊቱ ብዙ ተአምራትን አድርጎ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሳመነው፡፡ ከበሽታውም ፈወሰው፡፡ ከቤተሰቦቹም ጋር አጠመቀው፡፡ አባ ዳንኤልም ወደ በዓቱ ተመልሶ እየተጋደለ ኖሮ ኅዳር 14 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡
የአባ ዳንኤል ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን አሜን።

የኢትዮዽያዊው ጃንደረባ ትውልድ የ2017 ዓ.ም የአእላፋት ዝማሬ ዝግጅት በሳምንታዊ የመሐረነ አብ ጸሎት ጉዞ እና መዝሙር ጥናት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ በይፋ መጀመሩን እናበሥራለን...
23/11/2024

የኢትዮዽያዊው ጃንደረባ ትውልድ የ2017 ዓ.ም የአእላፋት ዝማሬ ዝግጅት በሳምንታዊ የመሐረነ አብ ጸሎት ጉዞ እና መዝሙር ጥናት በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ በይፋ መጀመሩን እናበሥራለን:: በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ ጉዞው ተጀምሮአል:: ይህንን የምታዩ ሁሉ በጸሎታችሁ አግዙ::

23/11/2024

ለማወቅ መጠበብ ላያስፈልግህ ይችላል።
ለመጠበብ ግን ማወቅ ያስፈልግሃል።
ጥበበኛ ለመሆን መጀመሪያ አዋቂ መሆን አለብህ።

ምን እንሥራ?                          ✍️ በመምህር ዳዊት ሚዛና።"የሚሠራ ሰው ከአንድ ሰይጣን ጋር ይዋጋል።የማይሠራ ሰው ግን ከሺህ ሰይጣናት ጋራ ይዋጋል።መከራችን የሚቀንሰው...
23/11/2024

ምን እንሥራ?
✍️ በመምህር ዳዊት ሚዛና።
"የሚሠራ ሰው ከአንድ ሰይጣን ጋር ይዋጋል።
የማይሠራ ሰው ግን ከሺህ ሰይጣናት ጋራ ይዋጋል።
መከራችን የሚቀንሰውም ሆነ የሚጨምረው በተግባራችን ነው።"መፍትሄው?
#1ኛ. #መማር ፦አለማወቅን ያህል አስቸጋሪነት የለም የተማረ ሰው ቢያንስ ለመካሪ አያስቸግርም።የኔታ ደጉ ዓለም ካሣ እንዲህ ይሉ ነበር፦"የተማረ ሰው እና የተገጠበ አህያ አንድ ነውደ የተገጠበ አህያ የሚጫነው እየተቁነጠነጠ ነው ።የተማረ ሰውም ቢያጠፋ እንኳን እየተጨነቀ እየተቁነጠነጠ ነው።"ብለዋል።ዕውቀት ከብዙ ችግር አርነት ታወጣለች። ሲያጠፉ እንኳን በህሊና ትገስጻለች።እውነተኛ ጥርት ያለ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን መማር ዐይነ ብዙ ያደርጋል።በቀዳማውያን አበው ዐይን ያያል፣በአበው ልብ ያስባል፣በክርስትና አስተምህሮ የግል ዕውቀት የለምና። ከጥንት በቅብብሎሽ የወረደውን በመቀበል የምናውቀው እና የምንኖረው ነው እንጂ።
#2ኛ. #መረዳት፦ዕውቀት ብቻ መረዳት ከሌለው እንደ ሚሞሪ ካርድ መሆን ነው።ሚሞሪያችን ብዙ ቃላት ቢሸከምም ካልከፈቱት አይጮህም።ባልተረዳ ልብ ዕውቀት ብቻ ካልከፈቱት የማይናገር ይሆናል ።ይህ ያልሰላ ሕይወት፦ የማይበላ ሀሳብ ነው።ያልተረዳ ልብ በድንቁርና ያዳቃል።የእህል ጣዕም በጉረሮ፣ የሀሳብ ጣዕም በአእምሮ ይታወቃልና።በደንብ መረዳት ጣዕመ አእምሮ ነው።
#3ኛ. ፦ከማንም በፊት ከማንም በላይ ለክርስትናው ቅድሚያ መስጠት ። መቅደም የማይገባቸው ሲቀድሙብን ደጋፊ እና ከዳሚ ያደርጉናል።በዐይን ሌላውን ያዩበታል እንጂ እርሱን ዐያዩትም በሃይማኖትም ሌላውን ያዩበታል ሌላውን ያውቁበታል እንጂ እርሱን አያውቁትም።ልዑል ውእቱ ዘኢይትረከብ.. እንዲል።ዐይን ጤነኛ ከሆነ የምናየው ትክክል ነው።በሃይማኖችን ማያነት ካየንበት ምሥል ሳይሆን አካል እናያለን።
#4ኛ ፦መለኪያ የሌለው ሰው የውኀ ስፍር ነው። ውኀ በጠርሙስ ቢቀዱት የጠርሙስ ቅርጽ ይይዛል።በሳፋ ቢያደርጉት የሳፋ ቅርጽ ይይዛል።እንዳደረጉት ከመሆን ውጪ የራሱ ቅርጽ የለውም።ቅርጽ የለሽ እንዳደረጉት የሚፈስ ልበ ቢስ ከመሆን በላይ ምን ችግር አለ! ? ሲያሞቁን የምንግል ሲያበርዱን የምንቀዘቅ መሆን የለብንም የሚያኖረን ዓላማችን ብቻ ነው።
#5ኛ ፦ ትናንት የሆነብንን። ዛሬ እየተደረገብን ያለውን። ነገ ሊያደርጉብን ያቀዱትን በፈጣን አእምሮ መገንዘብ ከማን?ለምን?የት?እንዴት?መቸ?ወዘተ በሚሉ መጠይቆች ማብሰል።
#6ኛ ፦ እየጸለይን እንሠራለን እየሠራን እንጸልያለን እንደተባለ በእግዚአብሔር ረድኤት መሥራት የምንፈልገውን ሁሉ ማድረግ።
#7ኛ #መተግበር፦በቁስላችን ላይ ጨው እየጨሠሩ አይዞህ እናድንኃለን የሚሉን አዳኞች አይደሉም አፋዛዦች ናቸው እንጂ።
#8ኛ ፦አንድ ሰው ከተነካ የሁላችን እንደሆነ እንዳለ መውሰድ። የክፉዎቹ ተግባር በተናጠል እያደከሙ ኅብረተ ክርስትናችንን ማማሰን ስለሆነ።
#9ኛ ሊለካ ሊጨበጥ የሚችል የመፍትሄ መተግበሪያ ማስቀመጥ እና ያስቀመጥነውን መሆን።
ነገ እንዲህ ለመወያየትም ሆነ አቅጣጫ ማስቀመጥ ጊዜው ሊያልፍ ይችላል።
#10በሰው አጀንዳ ለማስታገስ እንጂ አቅምን አለማጥፋት፦
መሆን የምንፈልገውን ለመሆን ብቻ ተግቶ መሥራት። የሚፈልጉት ብኩን ሰው እንድንሆን ስለሆነ።....

እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ከተራራው ላይ የተቀመጠችው እናታችን ገና ደጇን ተሳልመው ሲገቡ ነፋሻው አየር የእጣኑን መዓዛ ሲያመላልሰው ታስተውላላችሁ።ከወፎች ድምጽ በቀር ም...
23/11/2024

እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
ከተራራው ላይ የተቀመጠችው እናታችን ገና ደጇን ተሳልመው ሲገቡ ነፋሻው አየር የእጣኑን መዓዛ ሲያመላልሰው ታስተውላላችሁ።ከወፎች ድምጽ በቀር ምንም ድምጽ አይሰማባትም። የእረፍት እና የመረጋጋት ስሜትን በውስጣችን ትፈጥራለች።የእንጦጦዋ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ልዩ ነች።

እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም በ 1903 ዓ.ም ተመሠረተች።

ህዳር 14/2017                                                      " ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን                          ዋጋ ...
23/11/2024

ህዳር 14/2017


" ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን
ዋጋ ይወስዳል ማቴ.10፥42 "

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን እና ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን

👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ፃድቅ ናቸው ፃድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ #ይስሐቅና ቅድስት #አድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው

👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መፃሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ

👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል

👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው ተመልሰውም ለስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ

👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን #አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል

👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል

👉እንደ ወጡም ፤ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ ደብረ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል

👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም ይባላሉ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል

👉 አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች

👉መድኃኒታችን የቅዱሣኑን ረድኤትና በረከት ለሁላችንም ያድለን የተባረከ ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

22/11/2024

? #ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። ።እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋል
ት.ሚልክያስ 3÷8-9
የቀጭን ወንዝ አጣብቂኝ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ከአዲስ አበባ 250 ኪ.ሜ ርቀት በመንዝ ማማ ምድር የሚገኝ ከ100ዓመታት በላይን ያስቆጠ በጸሎት ሰሚነቱ እና በፈዋሽ ጸበሉ የሚታወቅ ሲሆን በጣልያን ወረራ ጊዜ ንጉሱ ይህን ታቦት ይዘው ተስለው ተዋግተዋል።በታቦቱ እርዳታ በአማራ ሳይንት በማይጨው፣በወሎ፣በይፋት፣በመንዝ ጌራ ምድር እና ማማ ምድር ጠላትን ድል ነስተውበታል።ሲመለሱም አሁን ያለውን ሕንጻ መቅደስ አሰርተው አክብረውታል።በፍቅሩ ብዛት እየተመላለሱ ሳሉ ፍቅርህ አጣበቀኝ ሲሉ "አጣብቂኝ ቅዱስ ሚካኤል" ብለው ሰይመውታል።
ይህ በንጉሱ የተሰራው ሕንጻ ቤተ-መቅደስ ከዘመን ብዛት ከማርጀቱ እና ለምዕመናን ከማነሱ የተነሳ አዲስ ሕንጻ ቤተ-መቅደስ መስራት አስፈላጊ ሆኖ ይኸው ከተጀመረ 6 ዓመታትን አስቆጠረ። ይህንንም ሥራ ወደ ገዳማት ከሚጓዙ ምዕመናን በመንገድ ላይ ልመና እና በማስተባበር የምናከናውን ቢሆንም አሁን ካለው ወቅታዊ ችግር የተነሳ ምዕመናን ከአመት በላይ ወደ ገዳማት የሚያደርጉት ጉዞ የተቋረጠ በመሆኑ ሕንጻውን ለመጨረስ ከመቸገራችን አልፎ አዲሱም ሕንጻ ለአደጋ ሊዳረግብን ነውና የእርስዎን ትብብር እንሻለን።እርስዎም ድጋፍዎትን በቤተ ክርስቲያኑ አካውንት

1,በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ➯1000529855196
2,በአቢሲኒያ ባንክ ➯130222398

"የቀጭን ወንዝ አጣብቂኝ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል" ብላችሁ ማገዝ ትችላላችሁ።

🤲በጸሎት እንድናስባችሁ ያገዛችሁ ወዳጆቹ በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ስመ ክርስትናችሁን ላኩልን።

ቴሌግራም ➯

ዋትስአፕ ➯https://Wa.me/+251980291967

ለበለጠ መረጃ 📱 +2519 16 55 80 80
📱 +2519 33 03 83 34

22/11/2024

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: እርሱም መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡

22/11/2024

ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡

22/11/2024

ወንድሙን በማስመሰል በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

22/11/2024

አንዳንዶች ቤተ-ክርስቲያን እንድትመልስላቸው እንጂ እንድትጠይቃቸው አይፈልጉም።ለምን?
የመመለስ ግዴታ ካለባት የመጠየቅ መብቷን ለምን እንነፍጋታለን?

ኅዳር13➯  አቡነ አስከናፍር፡- ቅዱስ አስከናፍር የተባለው ይህ ጻድቅ የ13 ወንበዴዎችን የእግራቸውን እጣቢ በታመመ ልጁ ላይ በመርጨት በፍጹም እምነቱ የታመመ ልጁን በማዳን 13ቱንም ወንበዴ...
22/11/2024

ኅዳር13➯
አቡነ አስከናፍር፡- ቅዱስ አስከናፍር የተባለው ይህ ጻድቅ የ13 ወንበዴዎችን የእግራቸውን እጣቢ በታመመ ልጁ ላይ በመርጨት በፍጹም እምነቱ የታመመ ልጁን በማዳን 13ቱንም ወንበዴዎች ወደ መዳን አምጥቶ እንዲመነኩሱ ያደረገ ታላቅ የእምነት አባት ነው፡፡ ይህም ጻድቅ ከሮሜ መኳንንት ውስጥ አንዱ ሲሆን ትልቅ ባለጸጋም ነበር፡፡ እንግዶችን የሚቀበል፣ ለድኆችም መመጽወትን የሚወድ ነው፡፡ እንግዳ ተቀባይነቱን ያወቁ ወንበዴዎች እነርሱም ሰውን ሁሉ የሚነጥቁና የሚያጠፉ 13 ሽፍቶች የመነኮሳት ልብስ ለብሰውና በመነኮሳት ተመስለው ገብተው እርሱን ገድለው ንብረቱን ሊዘርፉ ወደ ቅዱስ አስከናፍር ዘንድ ሄደው በደጁ ቆሙ፡፡ ቅዱስ አስከናፍርም ባያቸው ጊዜ ‹‹እነዚህ እንግዶች 12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ›› እንደሆኑ አሰበና ሰገደላቸው፡፡ ወደ ቤቱም አስገብቶ ማዕድ አቀረበላቸው፡፡ እግራቸውን አጠበና በፍጹም እምነት ሆኖ የእግራቸውን እጣቢ 35 ዓመት ሙሉ ሽባ ሆኖ በኖረው ልጁ ላይ እረጨው፤ ልጁም ወዲያውኑ ፈጽኖ ዳነ፡፡ ሽፍቶቹም የሆነውን ባዩ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፡፡
ቅዱስ አስከናፍር ግን ‹‹አባቶቼ ሆይ ጌታ ክርስቶስ ከእናንተ መካከል የቱ እንደሆነ ንገሩኝ እሰግድለት ዘንድ›› አላቸው፡፡ የአሀገሩ ሰዎችም የመኰንኑ ልጅ እንደዳነ ሰምተው ወደ ቅዱስ አስከናፍር ቤት መጥተው ለ13ቱ ሰዎች ሰገዱላቸው፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ቅዱሳኖች ሆይ ባርኩን፣ በሽተኞቻችንን አድኑልን›› አሏቸው፡፡ ወንበዴዎቹም ደብቀው የያዙትን ሾተላቸው መዘው እያወጡ ቅዱስ አስከናፍርን ‹‹ልንገድልህ በመጣንበት በዚህ ሾተላችን እያንዳንዳችን ግደለን›› አሉት፡፡ የቀደመ ክፉ ሥራቸውንም ሁሉ ዘርዝረው ነገሩት፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹በውንብድናና በሽፍትነት ሕይወት ሆነን እግዚአብሔር እንዲህ ከራራልንና በእኛ ላይ ይህን ተአምር ካደረገ እርሱን ብንከተልማ ምንኛ የጽድቅ ፍሬ እናፈራ ይሆን!?›› ተባብለው ዋሻ ለመግባት ተነሥስተው ወደ በረሃ ሄዱ፡፡ ቅዱስ አስከናፍር ለእያንዳንዳቸው ስንቃቸውን ሰፍሮ ሰጣቸውና 25 ቀን ያህል ተጉዘው አንድ ምድረ በዳ አገኙና በዚያ መኖር ጀመሩ፡፡ ቅዱስ አስከናፍር ስንቅ ብሎ የሰጣቸውን ምስር በዚያ አሸዋ ላይ በተኑት፡፡ ፀሐይ በሚገባ ጊዜ ከአሸዋው ውስጥ ሦስት ሦስት ፍሬ ምስር ብቻ ፈልገው ይቀምሳሉ፡፡ በእንደዚህም ዓይነት የተጋድሎ ኑሮ 30 ዓመት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሃዲ መኰንን በተነሣ ጊዜ መኰንኑ ወዳለበት ሄደው በጌታችን ስም መሰከሩ፡፡ መኰንኑም ብዙ ካሠቃያቸው በኋላ ገደላቸውና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ ቅዱስ አስከናፍርም በታላቅ ተጋድሎ ብዙ ካገለገለ በኋላ ኅዳር 13 በክብር ዐረፈ፡፡
የአቡነ አስከናፍር ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!

ኅዳር 13- አእላፍ ቅዱሳን መላእክት   እልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክት፡- እነዚህም ተፈጥሮአቸው ረቂቅ የሆኑ ለዓለም ሁሉ ምሕረትን የሚለምኑ ናቸው፡፡ ሄኖክ ስለ እነርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹...
22/11/2024

ኅዳር 13- አእላፍ ቅዱሳን መላእክት

እልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክት፡- እነዚህም ተፈጥሮአቸው ረቂቅ የሆኑ ለዓለም ሁሉ ምሕረትን የሚለምኑ ናቸው፡፡ ሄኖክ ስለ እነርሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አጡኝ፣ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ፡፡ በዚያም አእላፋት መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሶቻቸውም እንደበረዶ ነጭ ነው፡፡››
ያዕቆብም እንዲህ አለ፡- ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ፣ የእግዚአብሔርም መላአክት በውሰጧ ይወጡ ይወርዱ ነበር፡፡›› ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ ‹‹የመላእክት ሠራዊት አየሁ›› አለ፡፡
ሙሴም እንዲህ አለ፡- ‹‹እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው የእግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደወሰናቸው፡፡ ሁለተኛም ‹‹እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ›› አለ፡፡
ዳዊትም እንዲህ አለ፡- ‹‹መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው፡፡›› ሁለተኛም ‹‹የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሽህ ናቸው›› አለ፡፡
ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ፡፡ ዳንኤልም እንዲህ አለ፡- ‹‹ዙፋኖችን እስኪዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነው፣ የራሱም ፀጉር እንደ ብዝት ነጭ፣ ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው፣ ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው፡፡ የእሳትም ጎርፍ በፊቱ ይፈሳል፣ የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል፣ የእልፍ እልፍ መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ፣ በአደባባይም ተቀምጦ መጽሐፍን ገለጠ፡፡››
ሉቃስም እንዲህ አለ፡- ‹‹ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ፣ እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ ‹በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ› እያሉ አመሰገኑ፡፡››
ማቴዎስም ‹‹እነሆ መላእክትም ሊያገለግሉት መጡ›› አለ፡፡ ሁለተኛም ‹‹የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል›› አለ፡፡
ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ፡- ‹‹እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮ ሲከፈቱ የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው›› የሚል ነው፡፡
ሐዋርያው ይዳም ‹‹እነሆ እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል›› አለ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የማዕረጋቸውን ደረጃ ‹‹መላእክት፣ አጋዕዝት፣ ሥልጣናት፣ ኃይላት፣ መናብርት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት፣ አርባብ፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌል›› ብለው ተናገሩ፡፡
የቅዱሳን መላእክት ጥበቃቸው አይለየን።

22/11/2024

የ13 ወንበዴዎችን እግር በማጠብ በእምነትና በየዋሕነት ሆነው በወንበዴዎቹ እግር እጣቢ ድውያንን የፈወሱት አቡነ አስከናፍር ዕረፍታቸው ነው፡፡

Address


Telephone

+251912804784

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤተ-ኤጲፋንዮስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share