ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ / Mahbere St.Philpos

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ / Mahbere St.Philpos

ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ / Mahbere St.Philpos “መኑ ያርእየነ ሠናይቶ? - በጎውን ማን ያሳየናል?” መዝ ፬፥ ፮
«ንእምሮሙ አበዊነ ቅዱሳን ወመካኒሆሙ ይቄድሶ ለሰብእ» This page is created in the name of St. Philip the Deacon.
(12)

And We have several Spiritual Tours in the Memorial of St.

06/12/2024

ከጥንቁልና በንስሐ ወደ ምንኩስና!
👉 ጌታችን በወንጌሉ፦ “ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፥ ፲፮

➡ ለብዙ ዘመናት በጥንቆላ ሥራ የተጠመደና በርካቶችን ከእውነተኛው የመዳን መንገድ አስወጥቶ በባዕድ አምልኮ አስሮ የነበረ ሰው በንስሐ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ተመልሶ ተጠምቆ ለምንኩስና ዝግጁ ሆነ።
➡ በባዕድ አምልኮ የተጠመዱ 275 ነፍሳት ወደ እውነተኛዋ የድኅነት መንገድ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ተመለሱ።

⛪ ዛሬም በተለያዩ የሃገራችን ክፍል የሚገኙና በተለያዩ የባዕድ አምልኮዎች የተጠመዱ ነፍሳት ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተመልሰው የልጅነት ጥምቀትን በመጠመቅ በትክክለኛዋ የጽድቅ መንገድ እንዲጓዙ የሁላችንንም ትብብር ይጠበቃል።

ኦርቶዶክሳውያን ታረዱ ‼😭 በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ኦነግ ሸኔ በሚል መጠሪያ በሚታወቁ ታጣቂዎች 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል፡፡😭 ከግድያው በእግዚአብ...
30/11/2024

ኦርቶዶክሳውያን ታረዱ ‼

😭 በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ኦነግ ሸኔ በሚል መጠሪያ በሚታወቁ ታጣቂዎች 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል፡፡

😭 ከግድያው በእግዚአብሔር ፈቃድ ያመለጡት የአካባቢው ኗሪ እንደገለጹት የ13 ዓመት አዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተወስደው በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ በግፍ ሲገደሉ 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አልታወቀም።

😭 እንደ ተለመደው በዓላማና በእቅድ በኦርቶዶክሳውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ዛሬም ቀጥሎበታል። እየተገደሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን አርሰው የሚያድሩና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎና ግንዛቤ የሌላቸው መሆናቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሞቱትን ከመቅበር ባለፈ የተሻለ መፍትሔ አላመጡልነም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

😭 በርካታ የአካባቢው ምእመናን ከአካባቢው የሸሹ መሆኑን ያነሱት መረጃ ሰጭው ሰው ተወልዶ ባደገበት ሀገር በሃይማኖቱ ምክንያት እየተገደለ ነው ያሉ ሲሆን ሀብት ንብረታችንን ጥለን ለመኖር ተገደናል ብለዋል፡፡

😭 በመላዋ ሀገሪቱ ኦርቶዶክሳውያንን የሚታደግ ሀገር አቀፍም ሆነ ዓለም አቀፍ ኃይል አልተገኘም። በሌላው ላይ ሲሆን ትንሽ ኮሽ ባለ ቁጥር ይንጫጩ እንዳልነበረ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ሲሆን ድምፃቸው አይሰማም። ሲኖዶሱም በዝምታው ገፍቶበታል። እየመሰለን ነው እንጂ ይህ ነገር ነገ ተነገ ወዲያ የሲኖዶሱን በር ማንኳኳቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። አንዳንዶችም የአህያ ሥጋ ማስታወቂያ ሥራ ላይ ናቸው። የሚገዳቸው የአህያ ሥጋ ነገር እንጂ የመነኮሳቱ፥ የካህናቱና የምእመናኑ መታረድ አይደለም። ሊቃውንቱ ሲታረዱ፥ የአብነት ተማሪዎቹ ሲረሸኑ ትንፍሽ አይሉም። አሁን ላይ ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉ ሲሆን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በስደት ላይ ናቸው።

😭 በመጨረሻም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ወረዳ 140 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን የተገደሉ ሲሆን መላው የዓለም ሕዝብና ኦርቶዶክሳውያን ሞታችንን ባታስቆሙልን እንኳን የነዚህን ሰማዕታት ምስክርነት በማሳወቅ የድርሻችሁን ተወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

😭 እግዚአብሔር ሆይ! ኢትዮጵያ ሀገራችንን፥ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ከነደደ እሳት አውጣልን፤ ስለ ንጹሐን ደም አንተ ተበቀልልን።

28/11/2024

ጉዞ ከበኩረ ገዳማት ደብረ ዳሕምሞ ወደ አክሱም ጽዮን ማርያም

22/11/2024

ገባሬ መንክራት ወተአምራት አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ

ጻድቁ ከአለት ድንጋይ ውሃ እያፈለቁ ብዙ ድውያንን የፈወሡና ዛሬም የሚታደጉ የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳምም “ደብረ ሊባኖስ” ተብሎ በስማቸው የተሰየመላቸው ታላቅ አባት ናቸው።

አባ ሊባኖስ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት የሚባሉ በወርቅና በብር እጅግ የበለጸጉ ሮማዊያን ናቸው፡፡ ልጃቸውን አባ ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ፦ “ፈጽሞ ወደጫጉላቤት አልገባም!” ብሎ እምቢ አለ፡፡ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም ፫ ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና “ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም” አላቸው፡፡ አባታችንም “ወዴት እሄዳለሁ? ምንስ ላድርግ?” ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም ለአባ ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን፣ አስኬማ መላእክትን፣ ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ አባ ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ፡፡ በአክሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ዕውራንን አበሩ፡፡በዓታቸውንም ከአክሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡
ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአክሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡

ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው «ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል» አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን “ደብረ ሊባኖስ” ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አክሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም «ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ» አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ «ሊባኖስ ዘመጣዕ» የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው ዐፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡
ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡

ጻድቁ ከአንድ ወጥ የከበረ ድንጋይ ፈልፍለው ብዙ ጊዜ ተጋድሎ የፈጸሙበት አስደናቂው የዋሻ ገዳማቸው ከአክሱም ጽዮን በ24 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ደረቃል (ደብረ ቃል) ላይ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡

በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው ጥር 3 ቀን ባታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ቀን ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡የአባ ሊባኖስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

20/11/2024

“ሰው አይዘንብህ...”
🎤 ክቡር አባታችን ቀሲስ መንግሥቱ (የእናቴ ልጅ)

➡ “እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፤ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፤ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን፥ መጻተኛውንና ችግረኛውን አትበድሉ፤ ከእናንተም ማንም በወንድሙ ላይ ክፉውን ነገር በልቡ አያስብ።” ዘካ ፯፥ ፱- ፲
➡ “ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፤ እንዳትበድል አትቅና። ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ።” መዝ ፴፮፥ ፰- ፱
➡ “ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡ የሚል ነው።” ገላ ፭፥ ፲፬
➡ “አፍቅር ካልአከ ከመ ርእስከ - አፍቅር ቢጸከ ከመ ነፍስከ” ዘሌ ፲፱፥ ፲፰

ወደ ጥንታዊቷ ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም ለሚኖረን የ10 ቀናት ጉዞ ምዝገባ ላይ ነን።
★ መነሻ ኅዳር 16 መመለሻ ኅዳር 25
★ የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር
በጉዟችን ላይ ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ እና አቡነ አሞኒ፣
👉 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና ሌሎችም
★ ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877

• ባላችሁበት አካባቢ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ቤተሰብ በመሆን ያግዙን

• በዩቲዩብ ☞ https://youtube.com/

• በቲክቶክ 👉🏿 http://tiktok.com/

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mekoreta

• በቴሌግራም 👉🏿 https://t.me/waldiba እና

https://t.me/negeretewahido

18/11/2024

👣 እግሮች ሁሉ ወደ አክሱም ጽዮን ያመራሉ... 🚶

የማይቀርበት መንፈሳዊ የንግሥ ጉዞ ወደ ጥንታዊቷና ታላቋ የታሪክ ማኅደር መካነ ነገሥት ርእሰ ገዳማት ወአድባራት

* መነሻ ኅዳር 16
* መመለሻ ኅዳር 25
* የጉዞ ዋጋ፦ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር
★ ውስን ወንበሮች ብቻ ስለቀሩን አክሱም ጽዮንን ለመሳለም የምትሹ ያልተመዘገባችሁ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ልጆች ሁሉ ደውሉልንና አብረን እንጓዝ!
👉 0901070707 / 0911289877

👉 ርእሰ ገዳማት ወአድባራት፣ ሙጽአ ሕግ ወሥርዓት፣ ነቅዐ ክህነት ወመንግሥት ዘሀገር ዐባይ ኢትዮጵያ፤ ቅድስት አክሱም ሁላችንንም ትጣራለች፡፡ የሚቻለን ሁሉ ወደ እርሷ እናቅና፤ ከበረከቷም እንጥገብ፡፡

በጉዟችን ላይ ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉🏿 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉🏿 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉🏿 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉🏿 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉🏿 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉🏿 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉🏿 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉🏿 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉🏿 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉🏿 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉🏿 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉🏿 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉🏿 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉🏿 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉🏿 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ እና አቡነ አሞኒ፣
👉🏿 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉🏿 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉🏿 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና ሌሎችም...

✥ መነሻ ቦታዎች፦ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ እና መገናኛ

• ባላችሁበት አካባቢ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

★ ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም
በድርሣነ ዑራኤል ላይ ከተገለጸው ታሪኳና ክብሯ ውስጥ፦

👉 አረመኔው ንጉሥ ሄሮድስ በ3ዓ.ም የሞት አዋጅ አውጥቶ ጌታችንን ለመግደል በገሊላና አካባቢው ሁሉ የተወለዱ 144000 ሕፃናትን ሲያስጨፈጭፍ የጌታችን ክብርት እናቱ እግዝትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ፣ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅድስት ሰሎሜ እግዚእነ ወአምላክነ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ይዘው በመሸሽ ወደ ግብጽ ከተጓዙ በኋላ ጌታ በእመቤታችንና በሰሎሜ ላይ ሆኖ በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ ፊቱን አዙሮ 3 ጊዜ ይባርክ ነበር። በአንድ ወቅት ለምን እንዲህ እንደሚያደርግ እመቤታችን ጠየቀችው፤ ጌታም፦ «እናቴ ሆይ የምባርከው ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ነው፤ በቅዱስ ወንጌል ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ተብሎ የሚነገረው ሕያው ቃሌ የሚፈጸምባቸው ክቡራን ንዑዳን ሕዝቦች ያሏት የተባረከች ሃገር ናትና...» ብሎ መለሠላት።

የሃገረ ግብጽ ቆይታቸውን ሲያጠናቅቁም ጌታችን ለክብርት እናቱ “ወደዚያች ቅድስት ሀገር ልውሰድሽ ብሎ ደመናን ጠቀሠና በብሩህ ደመና ጭኖ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸው። ከየመን በስተደቡብ በኤርትራ ሰሜን ዞባ ውስጥ ናቅፋ ከተማ አካባቢ የምትገኘውን አሁን የግኁሣንና የኅቡዓን በዓተ ጸሎት ኋላም ብዙ ቅዱሳን ሰማዕታት ሀገር የተባለችውን ናግራንን፣ ከአስመራ በስተሰሜን ምስራቅ በ91 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘውንና በጥንት ስሟ «ገዳመ ሲሃት» በ484 ዓ.ም አካባቢ ደግሞ በ፱ቱ ቅዱሳን «ደብረ ሲና» የተባለችውን፣ በሕዛ ማርያምን፣ ደብረ ቢዘንን፣ ማርያም ዓይላን እየባረኩ መጥተው አክሱም አረፈው ባረኳትም።

ቅዳሴ ማርያምን የደረሠው የብሕንሳው ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስም ስለ ኢትዮጵያ ቅድስና ሐዋርያው ቅ/ዮሐንስ ወንጌላዊ በጻፈው መጽሐፍ አንብቦ ኢትዮጵያን ለማየት 40 ቀን ሱባዔ ገባ። በፈቃደ እግዚአብሔርም በ4ኛው መ.ክ.ዘ. ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እየተዘዋወረ ጎበኘ። አቡነ ሠላማ ከሳቴ ብርሃንም ጵጵስና ሊሾም ወደ እስክንድርያ ከሄዱት ልዑካንም አንዱ አባ ሕርያቆስ ነበር። ከቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ ጋርም በአክሱም ከተማ ብዙ ጊዜ ተቀመጧል...።

የአባ ሕርያቆስ ደቀ መዝሙር የሆነው መምህር ጌዴዎንም በአክሱም ቤተ ቀጢን ወንበር ተክሎ ጉባዔ ዘርግቶ በርካታ ቅዱሳን ደቀመዛሙርትን አስተምሯል፤ ከነዚህ ውስጥም ተሰዓቱ ቅዱሳንና ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይጠቀሳሉ።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ከመምህር ጌዴዎን ዘንድ ለ፮ ዓመታት ትምህርት አልገባው ቢል በ፯ኛው ዓመት መደባይ ታብር አካባቢ ወደሚገኙት ቤተሰዎቹ ሲሄድ ከአክሱም ከተማ በ2 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው ማይ ኪራሕ ከዛፍ ስር አረፍ ብሎ ትሏን ስድስት ጊዜ ወድቃ በ፯ኛው ዛፉን ስትወጣው በመመልከቱ ማስተዋልን አግኝቶ ፯ኛ ዓመት መሞከር አለብኝ ብሎ ወደ አክሱም ተመለሠ። ኢዮር፣ ራማና ኤረር በሚባሉ ፫ቱ ሰማያት የመላእክት ከተሞች በግእዝ በዕዝልና በአራራይ ዜማ የሚደረሠውን ስብሐተ እግዚአብሔር በ3 ወፎች የተመሰሉ መላእክት በአክሱም ሙራደ ቃል ላይ አስተማሩት። እመቤታችን ቅዱስ አባ ሕርያቆስ ዘብህንሳንና ቅዱስ ኤፍሬም ዘሶርያን በአጸደ ነፍስ አምጥታ ለቅዱስ ያሬድ እየነገሩት ቅዳሴዋንና ውዳሴዋን በዜማ ደረሠ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም በየዓመቱ ፪ ጊዜ በአካል መጥተው በአክሱም ይገለጡ ዘንድ ክቡር ቃል ኪዳን አላቸውና እየመጡ ይባርካሉ።

በዚሁ በአክሱም ጽዮን ውስጥ በሚገኘው የመምህር ጌዴዎን ቤተቀጢን ጊባዔ ቤት ተሰዓቱ ቅዱሳን ተምረውበታል፤ ታቦተ ጽዮንንም ለብዙ ጊዜ አገልግለዋል። ከዚህ በኋላም እነ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ እነ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን ጨምሮ በየዘመኑ የተነሡ በርካታ ቅዱሳን በአክሱም ተቀምጠው ታቦተ ጽዮንን በንጽሕና አገልግለዋታል።

ጥንታዊቷ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድረስ ለተነሡ ነገሥታት ሲመት ከሚፈፀምባቸው ከ፬ቱ መናብርቱ ጽዮን መካከል አንዷና ቀዳሚዋ ናት። አክሱም ከክርስትና ሃይማኖት ትምህርትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ማዕከልነት በተጨማሪ የሥርዓተ መንግሥትም ማዕከል ናትና ብዙ ድንቅ ታሪክ አላት። ነገር ግን ስለብዙው ታሪኳና ክብሯ ከዚህ በላይ ብተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና እዚህ ላይ አቆምኩ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ ፲፩፥ ፴፪ ላይ፦ "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና።" እንዲል።

አምላከ አበው የታቦተ ጽዮንን በረከት አይንሣን፤ አገር የሚያተራምሱትን የዘመናችን ፖለቲከኞች ልብ ሰጥቶ የቅድስት ሃገራችንን የቀደመ ክብርና ልዕልና የሕዝቦቿንም አንድነትና ወንድማማችነት ይመልስልን። እመብርሃን በከበረው ቃልኪዳኗ ሃገራችንን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ትጠብቅልን። እኛም ዘወትር በአንድነት ሆነን፦ “አግርር ጸራ ታሕተ እገሪሃ ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊቷ ለሃገሪትነ ኢትዮጵያ” እያልን እንጸልይ።

❖ ብዙዎች የበረከቱ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጦማሩን Share, Like, Tag & Comment አድርጉት፤ የቅዱሳት መካናትን የቃልኪዳን በረከት እንዲያገኙ ለሌሎች ምክንያት መሆን በራሱ ልዩ በረከት ያሰጣልና Share & Tag በማድረግ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።
👉 "ገዳምህን የረገጠ" ብቻ ሳይሆን "ገዳምህን ለሌሎች ያሳዬ ...እምርልሃለሁ!" ተብሎ ቃል የተገባላቸው ቅዱሳን እንዳሉን ገድለ አቡነ ዘርዓ ብሩክን ያስታውሱ!!!

❖ ከማኅበራችን ጋር ተጉዘው በርካታ ጥንታዊ ገዳማትን መሳለም ከፈለጉ ሳያመነቱ ቀድማችሁ ይደውሉልንና አብረን በረከት እናግኝ! ለበለጠ መረጃ፦
📞 0901070707
📱 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ቤተሰብ በመሆን ያግዙን

• በዩቲዩብ ☞ https://youtube.com/

• በቲክቶክ 👉🏿 http://tiktok.com/

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mekoreta

• በቴሌግራም 👉🏿 https://t.me/waldiba እና

https://t.me/negeretewahido

#መንፈሳዊ #ጉዞ #ወደ #የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን #ጥንታዊ #ገዳማት
to the of ゚viralシ

ተአምረኛው ደብረ ቆዘት አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም - ወለቃ➡ ጻድቁ ድንጋዩ በደመና ሠረገላ አምሳል እየታዘዛቸው በታላቅ ድንጋይ ላይ ተጭነው ወደ ኢየሩሳሌም የተመላለሱ መንክራዊ አባት ናቸ...
16/11/2024

ተአምረኛው ደብረ ቆዘት አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም - ወለቃ

➡ ጻድቁ ድንጋዩ በደመና ሠረገላ አምሳል እየታዘዛቸው በታላቅ ድንጋይ ላይ ተጭነው ወደ ኢየሩሳሌም የተመላለሱ መንክራዊ አባት ናቸው።
➡ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ እና አቡነ እጨጌ ዮሐንስን በዕረፍታቸው ጊዜ የገነዙ ቅዱስ አባት ናቸው።
➡ “አባ ቅዱስ” በተሰኘው ተአምረኛ ጠበላቸው ውስጥ ሁልጊዜ የትኛውም እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡

ደብረ ቆዘት አቡነ ገብረ እንድርያስ አንድነት ገዳም ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ስር ከወግዲ ከተማ በስተምዕራብ አቅጣጫ ከባሕር ጠለል 6652 ጫማ ከፍታ ላይ አቡን ውሃ አካባቢ ይገኛል። ገዳሙ በዓባይ ተፋሠሥ ዙሪያ ከወተት ወንዝ በስተሰሜን አቅጣጫ ላይ ይገኛል።

ገዳሙ የተመሠረተው በ995 ዓ ም 10ኛው መ/ክ /ዘ ላይ ነው። የገዳሙም መሥራች አባ ገብረ ክርስቶስ የተባሉ ታላቅ ጻድቅ መሆናቸውን የአቡነ ገብረ እንድርያስ ገድል ይናገራል።

ከገዳሙ ፊት ለፊት ከጣቀት ወንዝ ማዶ ደግሞ ዲያቆን ውኃ (ደቶኑ) የሚባል አካባቢ ይገኛል። እነዚኽ አካባቢዎች ይኽንን መጠሪያ ያገኙት ቀድሞ በዚኽ አካባቢ በርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የነበሩበት እንደሆነና የቦታዎች መጠሪያም በቦታው ካሉ ምእመናን መኖሪያ ጋር የተያያዘ መሆኑን አባቶች ይናገራሉ። በወግዲና ከላላ ወረዳዎች ውስጥ በጥንት ጊዜ ከነበሩት 44 ፍልፍል ዋሻ ገዳማት ውስጥ እስካሁን 38ቱ እንደተሰወሩ መሆናቸውን ልብ ይሏል።

አቡን ውኃ በሚባለው አካባቢ አባ ኤልሳዕ፣ አባ ጎርጎርዮስ፡ አባ ገብረ ክርስቶስ አባ ቅዱስ አባ መስቀል አባ ጉባ የተባሉ ሰባት ቅዱሳን አባቶች በቦታው ይኖሩ እንደነበርና ከዚኽ ብዙ ሳይርቅ የዲያቆኖች መኖሪያ ሰፈር ስለነበር ቦታው ወደቆኑ የሚለውን ስያሜ እንደተሰጠው አባቶች ሲናገሩ አካባቢው ዛሬም ድረስ ይህንን መጠሪያ እንደያዘ ነው። አቡን በቀድሞው ዘመን ለጳጳስ ብቻ ሳይሆን ሥልጣነ ክህነት ላላቸው ቀሳውስትና መነኲሳት መጠሪያነት ያገለግል እንደ ነበር ፕሮፌስር ጌታቸው ኃይሌ ባሕረ ሀሳብ በሚለው መጽሐፍቸው ላይ ገልጠዋል።

የአቡነ እንድርያስ ዘወለቃ የቀድሞ ስማቸው «ንፍታሌም» ሲሆን አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ እናታቸው አርሴማ የተባሉ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው። ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጧቸው። መምህሩም ጸጋ እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ዐውቀው፦ “ብዙዎችን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ!” ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል። የመጻሕፍትን ትርጓሜ በሚገባ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሌም ይባል የነበረውን ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው። ጻድቁ በአቡነ ዮሐንስ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል። አባታችን ሙታንን በማስነሣትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል። የትዉልድ ቦታቸው ወለቃ ከገዳማቸው ቅርብ ርቀት ላይ "ደብረ ደብቄ ማርያም" ነው። እኚህ የአቡነ ገብረ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር የነበሩት ደገኛ ጻድቅ ካህንና የአምስት ልጆች አባትም እንደነበሩ በገድላቸው ላይ ተጽፏል።

አቡነ ገብረ ክርስቶስ ጽኑ የሆነውን ተጋድሏቸውንና መልካም አገልግሎታቸውን ፈጽመው በሞት ከማረፋቸው በፊት የገዳሙ አበምኔት ሆነው እንዲያገለግሉ ንፌታሌምን (አቡነ ገብረ እንድርያስን) መርጠው እንደሾሟቸው በመጽሐፈ ገድላቸው ላይ ተጽፏል። አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት ከወለቃ እስከ ጎጃም ድረስ ስብከተ ወንጌል እንዳስፋፉ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት በሚለው መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ይገኛል።

አቡነ ገብረ እንድርያስ በደብረ ርስኩር (በአሁኑ ደብረ ብርሃን ሰኮሩ ሥላሴ) ቤተ ክርስቲያን በሱባኤ ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በወርቅ ጽዋ ሰማያዊ ወይንና ሰማያዊ ኅብስት መግቧቸዋል። እንዲሁም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ጽዋ ማየ ሕይወት ካጠጣቻቸው በኋላ ሕሙማንን እንደፈወሱ፣ ዕዉራንን እንዳበሩ፣ ሙት እንዳስነሡ ገድላቸው ይገልጻል።

የአቡነ ገብረ እንድርያስ አባት የሆኑት የአቡነ ገብረ ክርስቶስ ጥንታዊ ውቅር ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ ጠፍ ሆኖ ስለቀረ ከዚሁ ገዳም አቅራቢያ የልጃቸው የአቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም ተመሥርቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ የተሠራው በዐፄ ድልነአድ ዘመነ መንግሥት ሲሆን ከዚያም በኋላ በተደጋጋሚ እድሳት ተደርጎለታል

ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስ እግዚአብሔር ኀጥአንን እንዲምርላቸው ከገዳሙ በስተደቡብ አቅጣጫ ጣቀት ወንዝ ከተባለው ቦታ ላይ በአንገታቸው ላይ ትልቅ ድንጋይ እየተሸከሙ ይጸልዩ እንደነበርና ይጸልዩበት ከነበረው ወንዝ ውስጥ በተኣምራት መቍጠሪያ የሚሠራ “አባ ቅዱስ” የተሰኘ ፈዋሽ ጠበል፣ የአባ ጎርጎርዮስ (ወንበረ ሥላሴ) ጠበል እና ሌሎችም በርካታ ጠበሎች እንደፈለቀላቸው በገድላቸው ላይ ተጽፏል።

እነዚኽም ጠበሎች ሕሙማን ከተለያዩ በሽታዎች ለመፈወስ ከማገልገላቸውም በላይ መነኰሳት ለጸሎት የሚገለገሉበትን መቍጠሪያ በተኣምራት ይሰጣሉ። አዘገጃጀቱም እንዲህ ነው- በመጀመርያ በጠበሉ ላይ ገመድ ሣር ወይም ቀጭን ዕንጨት በመንከር ከቆይታ በኋላ በተነከረው ገመድ፣ ሣር ወይም ዕንጨት ላይ ጠንካራ ዓለት ይሠራል፤ ጠበሉ ውስጥ በተነከረው ገመድ ወይም ክር ላይ ውኃው በተኣምራት ወደ ጠንካራ ዓለትነት ይቀየራል። ከዚያም ገመዱን ወይም ክሩን ወይም ዕንጨቱን እሾልኮ በማውጣት ውስጡ ክፍት ስለሚሆን ያንን አስተካከለው እየከረከሙ መቍጠሪያ መሥራት ይቻላል። እርሱም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው።

አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘወትር ዐርብ ዐርብ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው የጌታችን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን መካነ መቃብር ተሳልመው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው ለመምጣት ይመላለሱ የነበረው በአንድ ትልቅ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ነው። ድንጋዩንም እንደ ደመና ሠረገላ ይጠቀሙበት ነበር። ጻድቁን የዋርካ ዛፍ እንደ ጥላ ሆኖ ያገለግላቸውም ነበር። እርሳቸውም ድንጋይ እንደ ሠረገላ፣ ዋርካውን እንደ ጥላ እየተጠቀሙባቸው ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ እንደነበር በገድላቸው ላይ ተጽፏል። ያ እንደ ደመና ሠረገላ ሆኖ ለመጓጓዣነት ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል። በዓለ ዕረፍታቸውም ኅዳር 7 ቀን በገዳማቸው በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

አቡነ ገብረ እንድርያስ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ያሟሟቱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው። ማለትም አቡዬ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል በሚገኘው ገዳማቸው በምድረ ከብድ ባረፉ ጊዜ አቡነ ገብረ እንድርያስ ከደቡብ ወሎ ወለቃ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው በቅዱሳንም ጥሪ ተደርጎላቸው ወደ ምድረ ከብድ መጥተዋል። ይህም በአቡዬ ገድል ገጽ 83 ላይ እንዲህ ተብሎ በግልጽ ተጽፏል፤

➡ የአባታችን የገብረ መንፈስ ቅዱስ ዕለተ ዕረፍቱ በደረሰ ጊዜ ብዙ ኅቡዓን ቅዱሳን ወደእርሱ መጡ ስማቸውም ፍሬ ቅዱስ ዘርዐ ቡሩክ፡ ያዕቆብ ብንያም፤ ዮሴፍ ነው አባታችንም በሞት እንደሚያርፍና ቃልኪዳን እንደተሰጠው ነገራቸው። እነርሱም ስለ አባታችን ዕረፍት አዘነ እርሱ ርእሰ ባሕታውያን ነውና። በቀዳሚት ሰንበትም እያላበው በድካም እንደልማዱ ለፍጥረቱ ሁሉ ወደ አምላኩ መማለድን ሳያቋርጥ ዋለ። በመሸም ጊዜ ሰውነቱ ሁሉ ደከመ፤ መናገርም ተሳነው፣ እነዚያ ቅዱሳን ግን ዕረፍቱን አይቶ ምስክር ይሆን ዘንድ ገብረ እንድርያስን ሊጠሩት ሔዱ ቅዱሳኑም ወደ እርሱ ደርሰው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዕረፍት ነገሩት። እርሱም በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ መራራ ለቅሶንም አለቀሰ፤ ተነሥቶም ከእነርሱ ጋር ሔዶ ብፁዓዊ አባታችን ወዳለበት ደረሰ። ያንጊዜም ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ ነበረ።” የቅዱሳን አባቶቻችን የአቡነ ገብረ እንድርያስና የአቡነ ገብረ መንፈስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።

ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ገብረ እንድርያስ

ታሪካዊቷ ዱባርዋ ቁስቋም ገዳም (አሮጊት ገዳም) - ኤርትራ(ጥንታዊቷ የቃልኪዳን ምድር ደብረ ቁስቋም ገዳም)➡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ የባረከው ጥንታ...
15/11/2024

ታሪካዊቷ ዱባርዋ ቁስቋም ገዳም (አሮጊት ገዳም) - ኤርትራ
(ጥንታዊቷ የቃልኪዳን ምድር ደብረ ቁስቋም ገዳም)

➡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ የባረከው ጥንታዊ ቅዱስ ገዳም፣
➡ እመቤታችን ከስደቷ ወደ ሃገረ ገሊላ ስትመለስ ያረፈችበት፣ የጸለየችበትና በኪደተ እግሯ የባረከቺው ታሪካዊ ቅዱስ ቦታ፣
➡ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ የጸለዩበትና የባረኩት ዕፁብ ድንቅ ቦታ፣
➡ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን በቦታዋ ላይ እየጸለየ ለወራት ከመቀመጡም በተጨማሪ 19 ቀሳውስትና ዲያቆናትን በአንብሮተ ዕድ ባርኮ ሾሞባታል።
➡ ተሰዓቱ ቅዱሳን ያረፉባት፣ የጸለዩባትና የባረኳት ታሪካዊ መካነ ቅዱሳን ናት ዱባርዋ ደብረ ቁስቋም ገዳም፣
➡ በ1515 ዓ.ም የተነሣው ግራኝ ገዳሟን አውድሞ በውስጧ የሚገኙ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ቅርሶችን አቃጥሎና ዘርፎ ቢሄድም ከወረራው የተረፉ አንዳንድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትና ቅርሶች ዛሬም ድረስ አሏት።

✞ ይህንን ቦታ የተሳለመ ሁሉ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ አርጋኖን ዘሰኑይ ድርሰቱ፦ “የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበትን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ። ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ። የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ። የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ።” ብሎ ያመሰገናትን ያስባል።

✞ በእርግጥ እመቤታችን ከ2014 ዓመታት በፊት ነው ይህንን ቦታ በኪደተ እግሯ የባረከችው፤ በፍፁም ልቡ ላመነ ሰው ግን የስደቷን በረከት ያፍሣል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፦ “አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አላንስም፤ ሃሳቤን ከዚያ እንዳለሁ አድርጌያለሁና። በሥጋ አልነበርኩም በመንፈስ ግን አለሁ፤ ባነዋወር አልነበርኩም በሃይማኖት ግን አለሁ፤ በገጽ አልነበርኩም በማመን ግን አለሁ።” እንዲል [መጽሐፈ አርጋኖን ዘሰኑይ ፪፥ ፲፩- ፲፪)

✞ ስለዚህም ወደ አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም በምናደርገው የዙር ጉዟችን በሃገረ - ኤርትራ ከተሳለምናቸው ከ20 በላይ አስደናቂ ገዳማት ውስጥ አንዷ ናት። ገዳሟ ከአስመራ ከተማ ወደ መንደፈራ በሚወስደው መንገድ በ30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ካለችዋ በመዳብ ማዕድን ከምትታወቀዋ ዱባርዋ ከተማ ዳር በምትገኝ ኮረብታ ላይ ነው የተመሠረተቺው።

✞ ገዳሟ ጥንታዊት የታሪክ ባለቤትና ታይታ የማትጠገብ መካነ ቅርስ በመሆኗና በአመሠራረት ዘመኗ ምክንያት አሮጊቷ ገዳም ይሏታል። በገዳሟ ከ58 በላይ ነገሥታት እንደነገሡባት የቦታዋ የታሪክ ምሁራን ይገልጻሉ። የጊቢዋ ድባብና ግርማ፣ በገዳሟ ያሉ አበው ትሕትናና እንግዳ ተቀባይነታቸው ግሩም ነው። አምላከ አበው የቅድስት ሃገራችንን ሰላም መልሶልን መሪዎቻችንንም አገርሞ በድጋሜ ደጇን እንድንረግጥ ሁላችንንም ይርዳን!!!

👉 ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ለምናደርገው ዓመታዊ የንግሥ ጉዟችን ምዝገባ ላይ ነን።
* መነሻ፦ ኅዳር 16
* መመለሻ ኅዳር 25
* የጉዞው ዋጋ፦ በቦታው ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 9000 ብር
➡ የቀሩን ወንበሮች ጥቂት ብቻ ናቸው።

በጉዟችን ላይ ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ እና አቡነ አሞኒ፣
👉 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና ሌሎችም

• ባላችሁበት አካባቢ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

➡ ይህንን መንፈሳዊ መልዕክት እርሶ በሚጠቀሙበት ድህረገጽ ላይ ሼር በማድረግ ይተባበሩን።

★ ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

👇 በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
👉🏿 https://t.me/waldiba
👉🏿 https://t.me/negeretewahido

14/11/2024

አስደናቂው ደብረ ዓሣ አባ ዮሐኒ ወአቡነ አሞኒ ገዳም
ወደ በሚኖረን #መንፈሳዊ #ጉዞ እንሳለመዋለን።
👉 መነሻ ኅዳር 16 መመለሻ ኅዳር 25
👉 የጉዞ ዋጋ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር
👉 በጉዟችን ላይ በርካታ ጥንታዊ ገዳማትና አድባራትን እንሳለማለን።

➡ ለበለጠ መረጃ፦
0⃣9⃣0⃣1⃣0⃣7⃣0⃣7⃣0⃣7⃣
0⃣9⃣1⃣1⃣2⃣8⃣9⃣8⃣7⃣7⃣

#ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ ゚ to the ゚viralシ

14/11/2024

ሰው ሆይ፦
🎤 የኔታ ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

12/11/2024

በእንተ ደብረ ቢዘን ገዳም
ለሁሉም እንዲዳረስ #ሼር ማድረግ አይርሱ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።
ጥንታዊው ደብረ ቢዘን አቡነ ፊልጶስ ገዳም በኤርትራ የሚገኝ አንጋፋ ገዳም ሲሆን ገዳሙን የመሠረቱት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ፊልጶስ ናቸው። ጻድቁ ዕፀ መስቀሉን ወደ ኢትዮጵያ አምጥተው በግሸን ደብረ ከርቤ ካስቀመጡት አስሩ ቅዱሳን አንዱ ሲሆኑ እነዚህን ቅዱሳን በመንፈስ ቅዱስ የመረጡትና የመሯቸውም እሳቸው ናቸው። ገዳሙ ከእሳቸው በኋላ በርካታ ደጋግ ቅዱሳንን አፍርቷል። ከደቀመዛሙርቶቻቸው አንዱ የሆኑት አቡነ ስልዋኖስ ጌታችንን እግሩን አጥበው በእንግድነት በመቀበላቸው በክብር ላይ ክብር አግኝተውበታል። ደገኛው ጻድቅ አቡነ ዮሐንስም የአቡነ ፊልጶስ ደቀመዝሙር ናቸው።

ገዳሙ ከአስመራ ከተማ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ባለቺው ነፋሲት ከተማ ጋር በተያያዘ ትልቅ ተራራ ላይ ሲሆን በውስጡ ከሚገኙት ከ200 በላይ መናኒያን ውስጥ እጅግ የተጠቀሙ (ብቃት ደረጃ የደረሱ) በርካታ አበው አሉበት። እነዚህ መናኒያን ሠርከ ኅብስታቸውን የሚያሟሉት ክረምት ብቻ ጠብቆ ብቻ በሚከወን ባሕላዊ ግብርና በመጠቀም ነው። የወቅቱን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ ወደ ዘመናዊ ግብርና በማበልጸግ የገዳሙን ገቢ አሳድጎ የመናኒያኑን የድርጎ (ሠርከ ኅብሥት) ችግር በቋሚነት ለመቅረፍ የሁላችንንም ድጋፍ ይጠይቃል። ስለዚህም ለዚህ ዓላማ “በዓብዕ ፕሮጀክት” ቀርጸን ገቢ በማሰባሰብ ላይ ነን።

የበዓብዕ ፕሮጀክት ከባህላዊው ግብርና ወደ ዘመናዊው ግብርና ማሸጋገር ሆኖ እነዚህን ሦስት ዓበይት ዓላማዎች አሉት።

ሀ. አስተማማኝ የውሃ ምንጭ ማበልጸግ፣

ለ. ደረጃውን የጠበቀ የውሃና መስኖ ሥርዓት መሥራት፣

ሐ. ቴክኖሎጂያዊና ውሃ ቆጣቢ የሆነ አጠቃቀም መስኖው ላይ መዘርጋት የሚሉ ናቸው።

ይሁን እንጂ ይህ ፕሮጀክት ትልቅ እንደ መሆኑ የበጀት ወጪውም ከገዳሙ ዓቅም በላይ በመሆኑ የቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ ይህን በመረዳት ዓቅሙ በሚፈቅድላችሁ እንዲታግዙን በጻድቁ አቡነ ፊልጶስና በጻድቁ አቡነ ዮሐንስ ስም እንጠይቃለን። የፕሮጀክቱ ይዘት ከታች ተያይዞ ከቀረበው ማስፈንጠርያ (ሊንክ) ባለው ዶክመንተሪ ፊልም ጠለቅ ባለ መልኩ መመልከት ትችላላችሁ። ይህ ፕሮጀክት በንኡሳን ቅርንጫፍ ተከፋፍሎ በግል ወይም በቡድን ማገዝ ለሚችሉም ምቹ ሆኖ በቪድዮው መጨረሻ በሰንጠረጅ መልኩ ቀርቦላችኋል።

በመሆኑም የተከበራችሁ ምእመናንና ምእመናት ሕዝበ እግዚአብሔር የዚህ በጥናታዊ ጽሑፍና በተንቀሳቃሽ ምስል የቀረበው ሰነዳዊ ፊልም በሀገር ውሥጥና በሀገር ውጭ ያላችሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች የቤተ ክርስቲያን ዕድገት በገዳም ዕድገት መሆኑን አምኖ ባለበት ቦታ ሆኖ እንዲመለከተውና “ብፁዕ ዘይሁብ እምዘ ይነሥእ - ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው።” የሐዋ. ፳፥ ፴፭ የሚለው የአምላክ ቃል አብነት በማድረግ የዓቅሙን ድጋፍ እንዲያደርግ ተብሎ የተዘጋጀ ነው። ልዑል እግዚአብሔር አዕይንተ ልቡናችሁ እንዲያበራላችሁ፡ እጃችሁን እንዲሞላላችሁ የማኅበሩ ጸሎት መሆኑ እያስታወስን፡ ቸሩ ፈጣሪያችን ከናንተው ጋር ይሁን እንላለን። የእናቱ ድንግል ማርያም፡ የአባቶቻችን አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፡ አቡነ በኪሞስ፡ አቡነ ፊልጶስ፡ አቡነ ዮሐንስ እና የሁሉ ቅዱሳን ጸሎት ከናንተ ጋራ ይሁን። ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን እና ለሀገራችን እንዲሁም ለዓለማችን ሰላሙን ሰጥቶ በእምነታችን ያጽናን። አሜን!

በኢትዮጵያ የሚገኘው ኮሚቴ የፊታችን ሐሙስ ኅዳር 5 ቀን በ4ኪሎ በሚገኘው የቅድስት ሥላሴ አዳራሽ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል። በመርሐ ግብሩ ላይ ከበርካታ ገዳማት የመጡ አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ሰባኪያነ ወንጌል፣ መዘምራንና መዘምራት ይገኙበታል። እናንተም በመርሐ ግብሩ ታድማችሁ ገዳሙን በማቃናት ሂደት ውስጥ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በቅዱሳን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የኮሚቴው አካውንት፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000657812734
አቢሲኒያ ባንክ 208093479

ለበለጠ መረጃ፦ ዲያቆን ሰሎሞን 0983340375
0944188983

ስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን !!!

https://www.gofundme.com/f/support-debre-bizens-modern-agriculture-project

11/11/2024

የሰባቱ ጊዜያት ጸሎታትና የምንጸልይባቸው ምክንያቶች
🎤 በየኔታ ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

07/11/2024

- ፰


★ ተስዓቱ ቅዱሳን እመቤታችን ከተወደደ ልጇ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አረጋዊ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ስትሰደድ ወደባረኳት በመጽሐፍ ቅዱስም ብዙ ጊዜ ወደ ተጠቀሰቺው ኢትዮጵያ በራእይ ተገልጦላቸው በመጻሕፍት ተረድተው በአፄ አልዓሜዳ ዘመነ መንግሥት ከጥንቷ የሮም ግዛትና ከታናሿ እስያ መጡ። እነዚህ እጅግ የከበሩ ቅዱሳን በቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ሥርዓተ ምንኩስናን እና ገዳማዊ ሕይወትን አስፋፍተዋል።

★ ከሕዝቡ ጋርም ዘርና ነገድ፣ ቋንቋና ቀለም ሳይለያቸው በክርስቶስ አንድ ሆነው ለ12 ዓመታትም በፍጹም አንድነት አብረው ከተቀመጡ በኋላ ‹‹እርስ በራሳችን እየተያየን ብንኖር ተድላ ደስታ ይሆንብናልና ተለያይተን እንቀመጥ›› ብለው ተማከረው በተለያየ በዓት አቡነ ሊቃኖስ በደብረ ቁናጽል፣ አቡነ ጰንጠሌዎንም በደብረ አጥገባ፣ አቡነ ገሪማ በደብረ መደራ፣ አቡነ ጽሕማ በዕዳጋ ዓርቢ ደብረ ጸድያ፣ አቡነ ይምአታ በገረዓልታ ደብረ ጎሕ፣ አቡነ አፍጼ በደብረ የሓ፣ አቡነ አሌፍ በአኅድዓ ደብረ በሕዛ፣ አቡነ ጉባ በማይጨው እንድርቃይ እና አቡነ አረጋዊ በደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) በአጽንዖ በዓት በብሕትውና ሕይወት ጸንተው በዋሻና በፍርኩታ ውስጥ በተራራም ላይ መኖር ጀመሩ፡፡

★ አቡነ ይምዓታ ከአክሱም ተነስተው በየመንገዱ ወንጌልን እየሰበኩና ከእመቤታችን ፍቅር የተነሳ "ቅዳሴ ማርያም" እየጸለዩ ሲሄዱ "አብ ጎሕ ወልድ ጎሕ መንፈስ ቅዱስ ጎሕ" እያሉ ሳሉ፤ አሁን ገዳማቸው ከሚገኝበት "ጎሕ" የሚባልበት ቦታ ላይ ደረሱና "ይኩን ስምኪ መካነ ጎሕ" ብለው ሰየሟት! በትሕርምትና በብሕትውናም በገዳማቸው ኖረው ጥቅምት 28 ቀን በዚሁ በጎሕ ሥላሴ ሸለቆው ውስጥ አንገታቸውን ተሰይፈው ዕረፍታቸው ሆኗል! የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘትም በመላእክት እጅ ተከናውኖላቸዋል፡፡

★ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስገራሚው ቤተ መቅደሳቸው ትግራይ ገረዓልታ ልዩ ስሙ ‹‹ጎሕ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡ ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡ እርሱም ቢሆን በገዳሙ አባቶችና በአካባቢው ሰዎች እገዛና ድጋፍ ካልሆነ ለመውጣት አስቸጋሪ ነው፡፡ ለእጅና ለእግር ማሳረፊያ ትንንሽ ቀዳዳዎችን ብቻ በመጠቀም ነው ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ የሚቻለው፡፡ በታላቅ ጭንቅና በፍርሃት ሆነው በአካባቢው ካህናት እየታገዙ እንደምንም ብለው ጫፍ ላይ ከደረሱ በኋላ ቁልቁል መመልከት ደግሞ ከአቡነ የምዓታ ጋር የነበረ ጌታ አሁንም እየረዳን እንዳለ ይረዱበታል!

★ ጻድቁ ሰማእት አቡነ ይምዓታ ይህንን ተራራ በተአምራት በፈረስ እንደወጡት ገድላቸውን ጠቅሰው የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ከአገልጋዮቻቸው አንደኛው ለፈረሱ ራት ሳር ሳይሰጠው በውሸት "ለፈረሱ ሳር ሰጥቼዋለሁ" ብሎ አቡነ ይምዓታን ይዋሻቸዋል፡፡ እርሳቸውም የተሰወረውን ሁሉ ያውቁ ነበርና "...ውሻ እንጂ የሰው ልጅ በሐሰት አይጮህም" ብለው ሐሰትን ስለመናገሩ ገሠጹት፣ ወዲያውም በተአምራት ከአንገቱ በላይ የውሻ መልክ ያለው ሆነ፡፡

★ ቤተ መቅደሱ እጅግ የሚደንቀው በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ ብቻ አይደለም ውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም በ6ኛው መ/ክ/ዘመን የተሣሉ እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡ ስለዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ገድለ አቡነ አረጋዊ ‹‹በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት በመላእክት እጅ ነው የተከናወነው፡፡ ይልቁንም ቁመቱና ርዝመቱ ከታላላቅ ገደል እጅግ በጣም የሚበልጥ የድንጋይ ዓምድ ከወንዝ ማዶ ዘንበል ብሎ መጥቶ ሥጋቸውን በክብር ተቀብሎ በተራራው ጫፍ ላይ እስከዛሬም ድረስ ፈጽሞ ሳይነቃነቅና ሳይናወፅ ቀጥ ብሎ ቆሞ ይገኛል›› በማለት ይገልጸዋል። የተሰዓቱ ቅዱሳን ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡

★ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዘንድሮው የአክሱም ጽዮን ጉዟችንም ከ፱ኙ ቅዱሳን ገዳማት 6ቱን የምንሳለማቸው ይሆናል፡፡ ውስን ወንበሮች ስላሉን ከማኅበራችን ጋር ተጉዛችሁ የበረከቱ ተካፋይ መሆን የምትሹ ክቡራንና ክቡራት የተዋህዶ ልጆች ቀድማችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

†★† ለበለጠ መረጃ፦
👉👉 0901070707 / 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

👇 በቴሌግራም ይቀላቀሉን 👇
👉 https://t.me/waldiba
👉 https://t.me/waldiba
👉 https://t.me/negeretewahido
👉 https://t.me/negeretewahido

07/11/2024

“በጾም የንስሐ ይሰጣልን? በጾም ላይ ጾምስ ይታዘዛል?”
🎤 ክቡር አባታችን ቀሲስ መንግሥቱ (የእናቴ ልጅ)

ወደ ጥንታዊቷ ርእሰ ገዳማት ወአድባራት አክሱም ጽዮን ማርያም ለሚኖረን የ10 ቀናት ጉዞ ምዝገባ ላይ ነን።
★ መነሻ ኅዳር 16 መመለሻ ኅዳር 25
★ የጉዞ ዋጋ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያን ጨምሮ 9000 ብር
በጉዟችን ላይ ከምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት ውስጥ፦
👉 ደብረ አጥገባ አቡነ ጰንጠሌዎን፣
👉 ደብረ ቆናጽል አቡነ ሊቃኖስ፣
👉 ደብረ መደራ አቡነ ገሪማ፣
👉 ደብረ የሐ አቡነ ሐፍፄ፣
👉 ደብረ ዳሞ (ደብረ ሃሌሉያ) አቡነ አረጋዊ፣
👉 ደብረ ጎሕ አቡነ ይምዓታ፣
👉 ጥንታዊው ውቕሮ ቂርቆስ፣
👉 ገርዓልታ አብርሃ ወአጽብሃ፣
👉 ሐውዜን ቅ/ጊዮርጊስ ወአቡነ ተክለሃይማኖት፣
👉 ማኅበረ ዴጎ ጻድቃን እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣
👉 ማኅበረ ዴጎ አቡነ አቤል ግብጻዊ፣
👉 ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣
👉 ዋልድባ ደብረ ዓባይ አቡነ ሳሙኤል፣
👉 ማይበራዝዮ አቡነ አላኒቆስ፣
👉 ደብረ ዓሣ አቡነ ዮሐኒ እና አቡነ አሞኒ፣
👉 ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
👉 ሳርአምባ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ክርስቶስ ሠምራ፣
👉 አርማኒያ ቅዱስ መርቆሬዎስ እና ሌሎችም
★ ለበለጠ መረጃ፦ 0901070707 / 0911289877

• ባላችሁበት አካባቢ ትኬት ለመቁረጥ (ለምዝገባ)፦
👉 በሚከተሉት የመ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በካሽ (በሞባይል ባንኪንግ) አስገብታችሁ ደረሰኙን የጉዞው ቀን ይዞ መምጣት ወይም Screenshot አድርጋችሁ በቴሌግራም ልትልኩልን ትችላላችሁ።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000099794899
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABYSETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ ዓባይ ባንክ 1931019728607012
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707

በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ቤተሰብ በመሆን ያግዙን

• በዩቲዩብ ☞ https://youtube.com/

• በቲክቶክ 👉🏿 http://tiktok.com/

• በራምብል 👉 https://rumble.com/c/Mekoreta

• በቴሌግራም 👉🏿 https://t.me/waldiba እና

https://t.me/negeretewahido

07/11/2024

ሌሊት ጸልዩ...
🎤 በየኔታ ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

06/11/2024

“የጽዋ ማኅበር እና ልማዶቻችን”
🎤 በቀሲስ መምህር አንድነት አሸናፊ
(የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ መምህር)
🎤 በመጋቤ ሃይማኖት ታሪኩ አበራ
(የመርካቶ ቅ/ራጉኤል ሰባኬ ወንጌልና በማኅበረ ቅዱሳን የኦዲዮ ቪዲዮ ክፍል አርታዒ)
👉 አወያይ ሊቀዲያቆናት ቀዳሜፀጋ ዮሐንስ የቀንድል ሚዲያ ባለቤትና ሥራ አስኬያጅ

ተአምረኛው ዓዲቖሾ መድኃኔዓለም👉 በእንጨት ሰረገላ የሚከፈት በር ያለው👉 ግድግዳው በየዓመቱ ለጥንተ ስቅለቱ (የመጋቢት መድኃኔዓለም) 3 ዓይነት ቀለም ያለው ማር የሚያነባ👉 ከአንድ ወጥ ድንጋ...
06/11/2024

ተአምረኛው ዓዲቖሾ መድኃኔዓለም
👉 በእንጨት ሰረገላ የሚከፈት በር ያለው
👉 ግድግዳው በየዓመቱ ለጥንተ ስቅለቱ (የመጋቢት መድኃኔዓለም) 3 ዓይነት ቀለም ያለው ማር የሚያነባ
👉 ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ በ120ው ቤተሰብ ምሳሌ የታነጸ እጅግ አስደናቂ ጥንታዊ የዋሻ ኪነሕንፃ፣
👉 ታላቁ ጻድቅ አቡነ አብርሃም ዘገርዓልታ ድንቅ ተጋድሎ አድርገውበት ቦታውን ለተሳለመ 20 ትውልድ የሚያስምር ቃልኪዳን ተቀብለውበታል።

04/11/2024

የኢትዮጵያን ሱባኤ አንቆ የያዘው ምንድነው?
🎤 በአንጋፋው መምህር ብርሃኑ አድማስ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ / Mahbere St.Philpos posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category