Amen Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amen, kebena, Addis Ababa.

09/04/2024

ሰበርርር ዜናናናናናናናናናና‼የድል ዜና
ፋኖኖኖ👇👇👇👇👇👇👇
በቴሌግራሜ ተከታተሉኝ👉
https://t.me/fanoethiopiawlta
ፋኖ💪

ፋኖኖኖ💚💛❤
Today,s Best photo
❤❤❤




















07/04/2024
07/04/2024

Asegedech Wolde, mother of the famous singer,Kuku Sebsibe.

Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም

07/04/2024

የአዲስ አበባ 'ልማት ኮሪዶር' ፕሮጀክትን በተመለከተ ዘ ጋርዲያን የተነሺዎችን ቅሬታ የያዘ መረጃ አጋርቷል

ተነሺዎች ለዘመናት ከኖሩበት ቤት እንዲወጡ አምስት ቀን ብቻ እንደተሰጣቸው፣ ከዛም ከሶስት ቀን በኋላ ውሀ ሆን ተብሎ እንደተቋረጠባቸው እና ንብረታቸውን በማውጣት ትርምስ ውስጥ ዝርፊያ እና ውድመት እንደደረሰባቸው ለሚድያው ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ኮመንት ላይ ያግኙ።

04/04/2024
03/04/2024

ይኸውልህ ወዳጄ ልቤ፣ ከተማ የሚታደሰው እንዲህ ነው

Zekeriya Mohammed
(መጀመሪያ በFeb. 26, 2021 የተለጠፈ።)

(ፒያሳ ግድም እንዲህ ታድሰው የከተማው ውበትና የቱሪስት መስህብ ሊኾኑ ስንት የድንጋይና የጣውላ ሕንጻዎች ያለ ርኅራኄ ተደርምሰው ይኾን?!😢)
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የከተማይቱን ቅርስና ውበት ሳታጠፋ፣ ትናንትን ከዛሬ እና ከመጪው ዘመን ጋር የሚያገናኙ ድልድዮችን ሳታፈርስ፣ ሕዝብ ከመኖሪያ ቀዬው ጋር ያዳበረውን ስነ ልቡናዊ ቁርኝት ሳትንድ፣ የስነ ሕንጻ ቅርስ አሻራዎችን ሳታበላሽ፣ እንዲህ ከተማን ብታድስ ትውልዶች ያከብሩሃል።

ለዚህም ነው በአዲስ አበባ፣ አራዳ ጊወርጊስ ቤተስኪያን አቅራቢያ የሚገኘው የቢትወድድ ኃ/ጊዮርጊስ ወ/ሚካኤል ሕንፃ፣ "ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል" ተሰኝቶ ኅያውነቱ ሊቀጥል መሆኑን ብንሰማ ጊዜ ደስ ያለን።

ከ117 ዓመት በፊት እንደተገነባ የሚነገረውና የመጀመሪያው ማዘጋጃ ቤት፣ በጣሊያን ወረራ ዋዜማ በኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ፍቅር ማኅበር የሕዝብ ማነቃቂያ ዲስኩር ይካሄድበት የነበረና ሌሎችም አገልግሎቶች ሲሰጡበት የቆየው ይህ ውብ ሕንፃ፣ እርጅና ተጫጭኖት ሊፈርስ መቃረቡ በግልጥ ይታይ ነበር።

ይህ ታሪካዊ ሕንጻ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሆኖ ሲያገለግል፣ ስንት አሠርት ዓመታት ተቆጥረዋል። አሁን ግን ታድሶ፣ ገጽታውን ለሚመጥን አገልግሎት እንዲውል ተወስኗል።

በዕቴጌ ጣይቱ ብጡል ስም የተሰየመ የባህል እና የትምህርት ማዕከል ሆኖ ያገለግል ዘንድ፣ ለዕድሳቱ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል ብለዋል የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ አንጋፋዋ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ።

አርቲስት ዓለምፀሐይ፣ መጋቢት 4 ቀን 2013 የትውውቅና የገቢ ማሰባሰብ ሥራ በታሪካዊው ግቢ ውስጥ ስለማከናውን፣ ጉዳዩን ጉዳዬ ያላችሁ ወገኖች መጥታችሁ በጨረታውም፣ በገንዘብ ድጋፉም፣ በትውውቁም ተሳተፉልኝ ብላለች።

ድጋፋችሁ ካልተለየኝ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሕንፃውን አድሼ ለትውልድ የሚተርፉ ሥራዎችን ለመሥራት አስቤያለሁና እገዛችሁ አይለየኝም ብላለች።

አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ የመሠረተችው ጣይቱ የባህል ማዕከል፣ ለሀያ ዓመታት የተለያዩ የጥበብ ሥራዎችን በሀገረ አሜሪካ ሲያሰናዳ የቆየ ተቋም ነው።

01/04/2024

Best picture

Today best photo








30/03/2024
30/03/2024
29/03/2024

የድሆች አባት : ሀጂ ቱሬና የረመዳን ወር

አላህ እንደ ሀጂ ሀብት ይስጥህ እንደሳቸው ኼይር ያሰራህ

| ረመዳን በመጣ ቁጥር ሀጂ ቱሬን የሚያስታውሱ አቅመ ደካማ በየክፍለ ሐገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሽ በሽ ናቸው። ሀጂ ቱሬ ከምትገምተው በላይ የድሃ አባት ነበሩ። በረመዳን ሁሉም ከየአቅጣጫው ልክ እንደዘመዳቸው ወደሳቸው ዘንድ አዲስ አበባ ይጎርፍ ነበር። አዲስ አበባ ከተማ እስክትጨናነቅ ድረስ።

የሚገርመው ለዛ ሁሉ ህዝብ ገንዘብ አከፋፍለው ሁሉም ተደስቶ ወደየክፍለ ሐገሩ ይመለስ ነበር። የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እርስዎጋ የሚመጡ ድሃ እንግዶች፤ "ከተማዋን አቆሸሹ፦ ቀንሱልን!" ብሎ ቅሬታ ሲያሰማቸው የእርሳቸው መልስ ...

« ሁሉም የኔ እንግዶች ናቸው። ... አልቀንስም! ... እንዲያውም መጨመር እፈልጋለሁ። አንድም ሰው አይንካብኝ። በየዓመቱ ለማዘጋጃ ቤቱ ዳጎስ ያለ ብር እከፍላለሁ» ነበር ያሉት።

በዚህ ተስማምተው ይከፍሉ ነበር።

አቦ አላህ ሀብት ከሰጠህ እንደ ሀጂ ቱሬ፤ ሰጪ ካደረገህም እንደ ሀጂ ቱሬ የሚለው አባባል ያለምክንያት አልነበረም። ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር የእርሳቸው አሻራ ያላረፈበት በጎ ሥራ አታገኝም። ያሰሩት የመስጂድ ብዛት ቁጥር ስፍር የለውም። እርሳቸው ብሔር ፣ ሃይማኖት ሳይለዩ ሕይወቱን የለወጡለት ህዝብ ብዛትም እንደዛው።

ሀጂ ቱሬ ሃገራችን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ለጋሽ ሀብታሞች ቁጥር አንድ ላይ የሚቀመጡ ናቸው። ስለእርሳቸው ተፅፎ አያልቅም።

አዎ ሀጂ ቱሬ አሁን የዘመኑ ሐብታም ተብለው በሃገራችን ስማቸው የሚጠሩትን ሁሉ ያስንቁ ነበር። እርሳቸው ከዚህ ዲኒያ ከተጓዙ በኋላ ያ መልካም ስራቸው ከእርሳቸውጋ ተጓዘ።

አላህ ጀነቱል ፊርዶውስ ይስጣቸው!
በዱዓ አንርሳቸው ።
Afandi sufeyan

Address

Kebena
Addis Ababa

Telephone

+251929132400

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amen:

Share