
03/11/2023
ማሳሰቢያ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጥቅምት 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ሁሉም ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የሀገር ውስጥ በረራዎች በአዲስ መልክ ዕድሳት ወደተደረገለት የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ (Domestic Terminal 1) እንደሚዞሩ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡ ይኸው የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል 1 ሙሉ አገልግሎት መስጠት እስከሚጀምር ድረስ ወደሀገር ውስጥ የሚደረጉ በረራዎች በሙሉ ከዓለም አቀፉ የመንገደኞች ማስተናገጃ ማዕከል (Terminal 2) የሚቀጥሉ መሆናቸውን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
የስታር አላያንስ አባል
#የኢትዮጵያአየርመንገድ