Raya Rayuma Tourist Attractions

Raya Rayuma Tourist Attractions Wel come to Raya Rayuma tourist destination promotion page

ራያ አላማጣ
22/06/2023

ራያ አላማጣ

Raya rayuma ✅the home of Raya people ስለ ጥምቀት በዓል ስነሳ መጠየቅ የምፈልጋቸው ጥያቄዎች 1  ጥምቀትን በራያ እንዴት ለማክበር እያሰባችሁ ነው? እና የት ነው የምናከ...
29/12/2022

Raya rayuma
✅the home of Raya people
ስለ ጥምቀት በዓል ስነሳ መጠየቅ የምፈልጋቸው ጥያቄዎች

1 ጥምቀትን በራያ እንዴት ለማክበር እያሰባችሁ ነው? እና የት ነው የምናከብረው ?
2 ባህልችን ኦርጅናሊቲው ሳይለቅ በምን መልኩ ነው ነው በዓሉን የምናሳልፈው ?
3 ምን አይነት አለባበስስ ነው መልበስ ያለብን?
4 ወንዶች ጥለት ወደታች አድርገን መታጠቅስ ከባህላችን አንፃር አግባብ ነወይ ?
5 ለሴቶች ደሞ አርት እና makeup ሳይደረግ የባህል መልበስ አይቻልም ወይ?

Timeket celebration in Raya Alamata
የጥምቀት በዓል አከባበር በ ራያ አላማጣ
ናጥሙቐት ብዓል አኸባብራ አብ ራያ አላማጣ
photo from social media

ሓሸንገ/ጌ ሃይቅ ራያ ኦፍላ💚💛❤
14/11/2022

ሓሸንገ/ጌ ሃይቅ
ራያ ኦፍላ💚💛❤

ሸጋዋ💚💛❤ድንቅ ውበት ውብ ባህል ራያራዩማጉዞ ወደ ራያ አላማጣ the land of beauty 💚💛❤
28/10/2022

ሸጋዋ💚💛❤
ድንቅ ውበት
ውብ ባህል
ራያራዩማ
ጉዞ ወደ
ራያ አላማጣ
the land of beauty 💚💛❤

ግሸን ማርያም 💚💛❤እንኳን አደረሳችሁ
01/10/2022

ግሸን ማርያም 💚💛❤
እንኳን አደረሳችሁ

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!


ግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ ከደሴ ከተማ 82 ኪ/ሜ ርቃ ከፍ ብሎ በሚታይ መስቀለኛ ተራራ ላይ ትገኛለች።በተለይ አቡነ ሚካኤል ጳጳስ ዘጎንደር መንፈሳዊ መናኝ በመባል የሚታወቁት ደገኛ አባት ባሠሩት ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሆነው የተራራውን ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ሲመለከቱ አንድ ጥሩ ዐናጢ ከጥሩ እንጨት ባማረ ጌጥ ጠርቦ የሠራውን ግሩም የእጅ መስቀል ይመስላል።

በአቅራቢያዋም ከሚገኙ በርካታ ታሪካውያንና ጥንታውያን መካናት መካከልም፦ ጥንታዊው የደብረ ሐይቅ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም፣ የድጓ ምስክር የነበረው ደብረ እግዚአብሔር፣የቅኔ ትምህርት ምንጭ የሆነው ዋድላ/ደላንታ፣የ19ኛው ክፍለ ዘመን የሃይማኖት ውሳኔ የተደረገበት የቦሩ ሜዳ ሥላሴ፣ የውጫሌ ውል የተፈረመበት የውጫሌ ከተማ፣የመቅደላ አምባ ፣የበሽሎ ወንዝ ሸለቆና ሌሎችም ናቸው።

ግሸን ደብረ ከርቤ የሚለውን ስያሜ ከማግኘቷ በፊት በልዩ ልዩ ታሪካዊና ምሥጢራዊ ምክንያቶች ደበረ ነገሥት፣ ደብረ ነጎድጓድ፣ ደብረ እግዚአብሔር በሚባሉ ስሞች ትጠራ ነበር።ግሸን ደብረ ከርቤ መጀመሪያ የተመሰረተችው በዘመነ አክሱም በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ነበር።

ዐፄ ካሌብ በየመን የነበሩ ክርስቲያኖች እየደረሰባቸው ከነበረው መከራ ለመታደግ ወደ ናግራን ዘምተው ድል አድርገው መንግሥት አጽንተው ሲመለሱ በዚያ ይኖሩ የነበሩ አባ ፈቃደ ክርስቶስ የሚባሉት መነኰስ አብረው ተመልሰዋል።

አባ ፈቃደ ክርስቶስም ከናግራን ሲመለሱ ሁለት ጽላቶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት የበሽሎ ወንዝን ተሻግረው ወደ ግሸን ተራራ ጫፍ ለመውጣት የአምባውን ዙሪያ ሲመለከቱ በገደሉ ላይ ንብ ሰፎ ማሩ ሲንጠባጠብ አይተው የአምላክን ስጦታ ለማድነቅ በጥንታውያን ግእዝና ዓረብኛ ቋንቋዎች ቦታውን "አምባ " "አሰል " (አምባሰል) ብለው ጠሩት።

ትርጉሙም "የማር አምባ " ማለት ነው እስከ አሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል።
አባ ፈቃደ ክርስቶስም ይዘዋቸው የመጡትን ሁለት ጽላቶች ወደ አምባው በማስገባት ሁለት ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ደብሩን መሥርተዋል።

ይኽንኑ ታሪክ በመከተልም ይመስላል በጉዲት ጦርነት የስደት ዘመን የአክሱሙ ንጉሥ ድል ነዓድ በዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ከአምባሰል ባሻገር ከሐይቅ ባሕር አጠገብ ባለው ተራራ ላይ ደብረ እግዚአብሔርን መሥርቶ ኖሯል።ከዚህም በኋላ መንግሥት ከደብረ እግዚአብሔር በመራ ተክለሃይማኖት አማካኝነት ወደ ላስታ ሲሻገር የደብረ ከርቤ ክብር በላስታ ዘመንም አልተቋረጠም።

በቅዱስ ላልይበላል ዘመን እንደተፈለፈሉ የሚነገርላቸው ጅምር ዋሻዎች አሁንም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም ይገኛሉ።በዚህ ዘመንም ደብረ ከርቤ የነገሥታት መናኸሪያ የሊቃውንት መገኛ የቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት መፈጸሚያ ቅድስት ቦታ ነበረች።

በመጨረሻም በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መቀመጫ ሆናለች።፲፬፻፵፮ ዓ/ም መስከረም ፳፩ ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳትን አምጥተው በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም አስቀመጡ።

የግማደ መስቀል በረከት የእመቤታችን ምልጃና ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን! አምላካችን በኃይለ መስቀሉ ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን። አሜን!

💚💛❤
28/09/2022

💚💛❤

መስቀል እና ትግል በራያ አላማጣ✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️መስቀል ከሃይማኖታዊ በዓሉ ባህላዊ ክንውኑም የጎላ በዓል ነው። በመስቀል ዋዜማ በየቤቱ እየዞርክ የሚደረገው ሆታ ፤ በ...
27/09/2022

መስቀል እና ትግል በራያ አላማጣ
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
መስቀል ከሃይማኖታዊ በዓሉ ባህላዊ ክንውኑም የጎላ በዓል ነው። በመስቀል ዋዜማ በየቤቱ እየዞርክ የሚደረገው ሆታ ፤ በሆታ ግዜ ከብርሃኔ ሓገዞም እና ለምለም ጎረስ ቤት ገብተህ ተጪው የሚያጎነጭህ ንፁህ ጠጅ ፤ አጥር እየሰበርክ ደመራ መስራቱ ፤ 11 ሰዓት አከባቢ አንዳንድ አባቶች በየቤቱ እየዞሩ ችቦውን ለኩሰው ትዃን ውፃኢ ቑንፂ ውፃኢ እያሉ ችቦውን ደጃፍ ላይ አስነክተው የሚሄዱት ሂደት ፤ እርሻ ያለው ገበሬ እርሻ ለሌላው ጥንቅሽ እና እሸት ደጃፍ ላይ እያስቀመጠበት የሚሄደው ነገር ፤ ደመራው ሲለኮስ ግንባራችን ፣ኪንዳችን፣ሆዳችን የምንቀባው ነገር ፤ የደመራው የተቃጠለ ዕንጨት ሽንብራ የዘራ ሰው ይዞ ወደ እርሻው የሚወስድበት ክንውን መቼም ቢሆን ከውስጣችን አይጠፉም ።

ለዛሬ በመስቀል ከሚደረጉ ጫወታዎች መካከል ያንዱን ትውስታ ላካፍላችሁ ። በመስቀል ከሚደረጉ ጫወታዎች መካከል ትግል/ሕሽይ/ አንዱ ነው። በመስቀል አከባቢ የአንዱ ሰፈር ወጣቶች ተሰባስበው ትግል ለመግጠም ትላልቅ አባቶች አስከትለው ወደ ሌላ ሰፈር ወይም አከባቢ የሚሄዱት ሂደት በጣም ደስ የሚል እና ጀግናውን ለመለየት የሚጠቅም ክንውን ነው።

በየአካባቢው በርካታ የትግል ጀግኖች ቢኖሩም እኔ ለዛሬ የ03 አከባቢ የትግል ጀግኖችን ትውስታ ላካፍላችሁ ።03 አከባቢ በርካታ በትግል የሚታወቁ ወጣቶች ቢኖሩም በጣም የሚታወቀው እና አከባቢውን ወኪሎ ስሄድ የነበረው ግን #ሃይሉ ተሾመ ነበረ። የተስተካከለ ቁመና ያለው እና በትግል የተሻለ አቅም የነበረው ጀግና ነበረ። ሌሎች የትግል ጀግኖችም ነበረ። እነ ፍስሀ መኩሪያው፣እነ ብርሃኑ ረዳ፣እነ ተረፈ ገብሩ፣እነ ሀየሎም አለ እና ሌሎች በትግል የሚታወቁ ወጣቶች ነበሩ። ከነዚህ መካከል ግን አመለ ሸጋው ሃይሉ ተሾመ በጣም ጎበዝ እና ጠንካራ ነበረ። ልክ እንደ 03 ሁሉ በሌሎች ቀበሌዎች እና አከባቢዎችም የትግል ጀግኖች ነበሩ። እነ ንጉስ ካሕሳይ እና ሌሎች ወጣቶችም በየአከባቢያቸው እና በየግዜያቸው ጀግኖች ነበሩ። ለትውስታ ያክል ነው። በርግጥ ሌሎች ያልተጠቀሱ ወንድሞች ይኖሩ ይሆናል።እኔ ግን በዚሁ ላብቃ።እናንተም የምታውቃቸው ጀግኖች እና ስለ ትግል በኮሜንት እና በራሳችሁ ገፅ መፃፍ ትችላላችሁ ።

ባህሎቻችን ውበታችን ናቸው ።በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏🙏
ባራንቶ አባሴሩ እንደፃፈው

 ለመላው ኢትዮጵያውያን የ ኦሮቶዶክስ እምነት ተከታዮች በተለይ በስቃይ ውስጥ ላለሀው የራያ ህዝብ እንኳን ለመስቀል ብዓል  አደረሳችሁ አደረሰን ሰላም ለራያ ራዩማ ህዝብ ሰላም ለኢትዮጵያ 💚💛...
26/09/2022


ለመላው ኢትዮጵያውያን የ ኦሮቶዶክስ እምነት ተከታዮች በተለይ በስቃይ ውስጥ ላለሀው የራያ ህዝብ እንኳን ለመስቀል ብዓል አደረሳችሁ አደረሰን
ሰላም ለራያ ራዩማ ህዝብ
ሰላም ለኢትዮጵያ 💚💛❤
ድመላእ ኢትዮጵያዉያን ና ኦርቶዶክስ እምነት ትኻተልቲ በተለይ አብ ስቃይ ድነኹም ና ራያ ህዝቢ እንኳዕ ድመስቀል ብዓል አብፀሐኩምአብፀሐና
ስላም ድ ራያ ራዩማ ህዝቢ
ሰላም ድ ኢትዮጵያ (ራይኛ)💚💛❤

♪የራያ ባህላዊ ዘፈኖች ♬ ***********************   በግጥም፣ በዜማ፣ በርእሰጉዳይና በአተገባበር እጅግ የተለያዪ ባህላዊ ዘፈኖች ራያ ውስጥ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹን እ...
24/09/2022

♪የራያ ባህላዊ ዘፈኖች ♬
***********************
በግጥም፣ በዜማ፣ በርእሰጉዳይና በአተገባበር እጅግ የተለያዪ ባህላዊ ዘፈኖች ራያ ውስጥ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹን እነሆ።

1- ባሕር ጉማ
☞አስገራሚ ራፕ ነክ ዜማ ሲኖረው ብዙውን ጉዜ በህዝብ በዓላት፣ በወጣቶች የክረምት ጨወታዎች ወቅትና ከስራ መልስ (ኦፎራ ወይም ደቦ) ላይ ይዘወተራል። አንዱ እያዜመ ብዙሀን እየተቀበለ የሚዘፈን የወጣቶች ዘፈን ነው።

2 - ጎራዴው ሰው በላ !!!
☞ በቡዛሀን (mass) የሚከናወን ዘፈን ሲሆን አንድ ሰው በመሪነት የሚያዜምበት ሌላው ደግሞ የሚቀበልበት ዓይነት ዘፈን ነው።
☞ ይህ ዘፈን መሪ ዘፋኙ እስከ 8ቤት የሚደርስ የግጥም ዜማ እያነበነበ የሚዘፈንበት ሲሆን ተቀባዪቹ ደግሞ መሪ ዘፋኙን ተከትለው 4ቤት ያለው የግጥም ዜማ እየደጋገሙ የሚቀበሉበት ነው።
(8ቤት የሚባለው ግጥም ልቃውንት በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስም የሰየሙት ሲሆን "ፀጋየቤት" እንደሚባል ይታወቃል።)

♪እሕምነው! እሕምነው! ጎራዴው ሰውበላ!! እያሉ 4ቤት ያለው የግጥም ዜማ ይቀበላሉ።

3 - እሕም_ብይ_በል!

ይኛው ዜማም ቢሆን በብዙሀን ተቀባይነት በአንድ አቀንቃኝ መሪነት ተሚከናወን ሲሆን 2ቤት ያለው የዜማ ግጥም የያዘና ፈጠን ጠን ያለ ዘፈን ነው።
☞ተቀባዮቹ ዘፋኙን ተከትለው
እሕም_ብይ_በል!!!
እሕም_ብይ_በል!! እያሉ ይቀበላሉ።

4 - ላለይ ጉማሆ!!

ይህ ዘፈን በአሸንዳ በዓል ብቻ በልጃገረዶች ዘንድ የሚዘፈን ሲሆን "ጉማዬ ... ጉማዬ ላሎ" (ሳይጠብቅ ይነበብ) እያሉ የሚያዜሙበት እጅግ ጥፍጥ ያለ ዜማ ነው። በአሸንዳ በዓል ብቻ ሳይሆን አረም በሚያሩምበት ጊዜም ጭምር ልጃገረዶች ያዜሙታል። (ይህ ዜማ ወደ እንደርታ ከተመነተፉ ዜማዎች ውስጥ አንዱ ነው)

5 - ንዒማ ዋለ!!

እስከ 6ቤት የሚደርስ የግጥም ዜማ ያለው ሆኖ በአሸንዳ በዓልና በእርሻ ስራ ላይ ልጃገረዶች የሚያዜሙት እጅ ጣፋጭ ዜማ ነው። በቅርብ ዓመታት ውስጥ በተወሰነ ደረጃ ለወጥ ተደርጎ ወደ እንደርታ ከተወሰዱ ዜማዎች ውስጥ አንዱ ነው።

6 - ገዳይ_ማማዬ!

በሰርግ እና በእርሻ ስራ ላይ የሚዘወተር፣ ከወጣት እስከ አዛውንት የሚያቀነቅነው ዜማ ሲሆን 6ቤት የግጥም ዜማ አለው። ይህን ዜማም ቢሆን በትግራይ ዘፋኞች ከዓመታት በፊት ተወስዶ፣ አንዳንድ ለውጦች በማድረግ በዘመናዊ ቅኝት ተዘፍኗል። የዘፋኙን ስም በቅርብ ቀን አሳውቃችኋለሁ።

ቁ 2 ይቀጥላል
ሕሉፍ ፒያን እንደፃፈው

💚💛❤ ቁጥር (1)ዛሬ ደሞ አላማጣ ከሌሎች የራያ አከባቢዎች በማገናኘት የተገጠሙ ግጥሞች እናያለን እኔ እነዝህን አልኩኝ እናንተ ደሞ የምታውቁትን   ላይ መፃፍ ትችላላችሁ ቀጠይ ደሞ ጨርጨር ...
15/09/2022

💚💛❤ ቁጥር (1)
ዛሬ ደሞ አላማጣ ከሌሎች የራያ አከባቢዎች በማገናኘት የተገጠሙ ግጥሞች እናያለን
እኔ እነዝህን አልኩኝ እናንተ ደሞ የምታውቁትን ላይ መፃፍ ትችላላችሁ ቀጠይ ደሞ
ጨርጨር
ቆቦ
ኮረም
ሞኾኒ
ዋጃ እና ሌሎችም እንጨምራለን
"የአላማጣ ልጅ ናት የላይኛው ኮረም
አሳዲ ሙናዋ ከራያ ልጅ ድካ የሚለያት የለም"
(መንግስቱ ዘገየ)
"ቆልዓ አላማጣ ሞኾኒ
ፀበል ምችአል ኹንኒ"
(በላይ ዘነበ)
"አላማጣ ውየ ቆቦ ነው አዳሬ
ካንተ ብያገናኘኝ የወሰደኝ እግሬ"
(አምሳል ምትኬ)

ቆቦአላማጣሞኾኒኮረምጨርጨር 💚💛❤ራያ ራዩማ💚💛❤
14/09/2022

ቆቦ
አላማጣ
ሞኾኒ
ኮረም
ጨርጨር 💚💛❤
ራያ ራዩማ💚💛❤

አየ ግዜ 💔
05/09/2022

አየ ግዜ 💔

መልካም ቀን❤❤❤ የራያዋ
14/08/2022

መልካም ቀን❤❤❤ የራያዋ

1 ራያ አላማጣ =አሸንዳ/ሶለል 2 ኦፍላ/ኮረም =አሸንዳ3 ራያ ቆቦ=ሶለል አሸንዳ/ሶለል በ ራያ ራዩማ 💚💛❤
11/08/2022

1 ራያ አላማጣ =አሸንዳ/ሶለል
2 ኦፍላ/ኮረም =አሸንዳ
3 ራያ ቆቦ=ሶለል
አሸንዳ/ሶለል በ ራያ ራዩማ 💚💛❤

"አላማጣ በታች ስሙ ዓዲ ሙህየእመጣልሻለሁ ግመል ጠፋኝ ብየ"
09/08/2022

"አላማጣ በታች ስሙ ዓዲ ሙህየ
እመጣልሻለሁ ግመል ጠፋኝ ብየ"

15/07/2022
መች ይሆን እንዲህ ተሰባስበን ከ አባቶቻችን ተምረን ልዩነታችን ወደጎን ትተን ስለህዝባችን የምንመክረው ?ዘወልድመዛርድአቦ ገረብ........ ራያ ራዩማ 💚💛❤
12/07/2022

መች ይሆን እንዲህ ተሰባስበን ከ አባቶቻችን ተምረን ልዩነታችን ወደጎን ትተን ስለህዝባችን የምንመክረው ?
ዘወልድ
መዛርድ
አቦ ገረብ........
ራያ ራዩማ 💚💛❤

ራያ ራዩማ  💚💛❤
11/07/2022

ራያ ራዩማ 💚💛❤

21/06/2022
ራያ ራዩማ 💚💛❤Photo ከ ፌስቡክ የተገኘ
27/05/2022

ራያ ራዩማ 💚💛❤
Photo ከ ፌስቡክ የተገኘ

ገረብ(ሓንስ) ኦዳ የአባቶች ጥላ🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳 #በራያ አላማጣና አካባቢዋ አቦ ገረብ የሚባል የሽምግልና ስነ-ስርዓት እንዳለ እውቅ ሆኖ እነዚህ አባቶቻችን ለነፍሳቸው ሲሉ ወንድም ከወንድሙ ሲጋጭ...
23/04/2022

ገረብ(ሓንስ) ኦዳ የአባቶች ጥላ
🌳🌳🌳🌳🌳🌳🌳
#በራያ አላማጣና አካባቢዋ አቦ ገረብ የሚባል የሽምግልና ስነ-ስርዓት እንዳለ እውቅ ሆኖ እነዚህ አባቶቻችን ለነፍሳቸው ሲሉ ወንድም ከወንድሙ ሲጋጭ አንተ ተው አንተ ተው እያሉ እያስታረቁ እና እያስማሙ ራዮችን አንድ እያደረጉ እያፋቀሩ ለዘመናት ኖረዋል፣ አሉ ይኖራሉም። እነዚህ አባቶች ፈጣሪ በሰጣቸው ለምለም ጥላ ሁነው ሽምግልናቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል ነገር ግን በዚህ ሰዓት የሚጠለሉበት ቦታ ወድሞና ሌላኛው ደግሞ ወድቆ እየተቸገሩ እንዳሉ እያየን ነው። ለምሳሌ ይሀክል በራያ አላማጣና አካባቢዋ የዕርቅ ስነ-ስርዓት የሚጠቀሙበት ዋናዎቹ እና እየተባሉ የሚጠሩ ሁለት አንጋፋ ጥላዎች ሲሆኑ፤ ዓብይ ኦዳ
ወደ ራርሄ፣ዓድብኩር መውጫ የሚገኝ ስሆን ዓብይ ኦዳ እየተባለ የሚጠራው ስመ ገናናው የአባቶች ጥላ በቅርብ ዓመታት ወድቆ ከጥቅም ውጪ ሁኗል። ሌላኛው ደግሞ ሓንስ እየተባለ የሚጠራው ለህብረተሰቡ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እየሰጠ የነበረ ሲሆን ከነዚህም ሁሌ አዲስ ዓመት ላይ ማህበረሰባችን ከከተማውና ከገጠሩ አሰባስቦ በፍቅር የሚውልበትና እሸት ጥንቅሹ እየተበላ ባህላዊ የራያ ዘፈኖች እየተዘፈኑ ትግል እየተታገሉ እየተጫወቱ የምያሳልፉበት ቦታ ነው። ሌላኛው ዋነኛው ጥቅሙ ደግሞ ብዙዎች ሲጣሉና ሲጋጩ አባቶች የዕርቅ ስነ-ስርዓት የሚያካሂዱበት ትልቅ የተከበረ ጥላ ነው። ስለዚህ ወገኖች እኔ ይህ ፕሮጀክት ከጀመርኩት የቆየሁ ብሆንም ነገር ግን አሁን ተቀናጅተንና ተጋግዘን ለሰላማችንና አንድነታችን ለቆሙልን የአባቶች ጥላ ብናስከብርላቸው አይበዛባቸውምና ካሁን ብኋላ ላለው ብንተጋገዝ ምን ይመስላችኋል
ምንጭ :- ለግዜው ስሙ ከማላስታውሰው ሰው

💚💛❤Rayan  Cultural Resources photo from ቆንጣጣው ቲዩብ and from FB
09/04/2022

💚💛❤Rayan Cultural Resources
photo from ቆንጣጣው ቲዩብ and from FB

ደጉ ያገሬ ሰው  🇪🇹
05/04/2022

ደጉ ያገሬ ሰው 🇪🇹

Raya  ራያ save our people 🙏🙏💚💛❤
25/03/2022

Raya
ራያ
save our people 🙏🙏💚💛❤

ራያ ራዩማ💚💛❤
19/03/2022

ራያ ራዩማ💚💛❤

ራያየ እግዚአብሔር  ይጠብቅሽ 💚💛❤
14/03/2022

ራያየ እግዚአብሔር ይጠብቅሽ 💚💛❤

ራያ አላማጣ❤
25/09/2021

ራያ አላማጣ❤

Raya cultural food mengeleየራያ የባህል ምግብ መንገሌናራያ ናባህል ምግብ መንገለ
25/06/2021

Raya cultural food mengele
የራያ የባህል ምግብ መንገሌ
ናራያ ናባህል ምግብ መንገለ

ራያ ራዩማ
09/04/2021

ራያ ራዩማ

Address

Alamat'a

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Raya Rayuma Tourist Attractions posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Raya Rayuma Tourist Attractions:

Share

Category