![ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት G+1 ጊዜያዊ ህንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረአርባምንጭ፡ግንቦት 7/2016 ዓ/ም(አርባምንጭ...](https://img4.travelagents10.com/628/203/122119147106282033.jpg)
15/05/2024
ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት G+1 ጊዜያዊ ህንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
አርባምንጭ፡ግንቦት 7/2016 ዓ/ም(አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን)
በምረቃው ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በከተማው ውስጥ በአስተዳደሩ የተጀመሩ በርካታ ፕሮጀክቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በቅርብ ጊዜ ግንባታው ተጀምረው የተጠናቀቀው የከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ህንፃ ሌሎች ኘሮጀክቶችንም ለመጨረስ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ከተማዋ ላይ ከዚህ በኋላ ግንባታዎች እየሰፉ መሄድ እንዳለባቸው ተናግረው ምቹ የሥራ ቦታና ምቹ የሥራ ዕድል መፈጠር አለበት ብለዋል።
በከተማው የሚገነቡ ህንጻዎች ከተማዋን በሚመጥን መልኩ መሆን እንዳለበት አቶ አባይነህ ተናግረው የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በጊዜ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ተናግረው ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው ጊዜያዊ የከንቲባ ጽ/ቤት ህንጻ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ጉሊህ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡
ህንፃው በውስጡ 16 ክፍሎችን የያዜ የከንቲባ ጽ/ቤትን ጨምሮ የካቢኔ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ሌሎች እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በምረቃው ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ፣የጋሞ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ፣የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ጨምሮ የጋሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የከተማውና የቀበሌው አመራሮች፣የጋሞ ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።