Zambo Media

Zambo Media Visit Gamo Zone

ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት G+1 ጊዜያዊ ህንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረአርባምንጭ፡ግንቦት 7/2016 ዓ/ም(አርባምንጭ...
15/05/2024

ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት G+1 ጊዜያዊ ህንጻ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አርባምንጭ፡ግንቦት 7/2016 ዓ/ም(አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን)

በምረቃው ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በከተማው ውስጥ በአስተዳደሩ የተጀመሩ በርካታ ፕሮጀክቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በቅርብ ጊዜ ግንባታው ተጀምረው የተጠናቀቀው የከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ህንፃ ሌሎች ኘሮጀክቶችንም ለመጨረስ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ከተማዋ ላይ ከዚህ በኋላ ግንባታዎች እየሰፉ መሄድ እንዳለባቸው ተናግረው ምቹ የሥራ ቦታና ምቹ የሥራ ዕድል መፈጠር አለበት ብለዋል።

በከተማው የሚገነቡ ህንጻዎች ከተማዋን በሚመጥን መልኩ መሆን እንዳለበት አቶ አባይነህ ተናግረው የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በጊዜ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሰራ መሆኑን ተናግረው ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው ጊዜያዊ የከንቲባ ጽ/ቤት ህንጻ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ጉሊህ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡

ህንፃው በውስጡ 16 ክፍሎችን የያዜ የከንቲባ ጽ/ቤትን ጨምሮ የካቢኔ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት፣ሌሎች እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በምረቃው ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ፣የጋሞ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ፣የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ጨምሮ የጋሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የከተማውና የቀበሌው አመራሮች፣የጋሞ ሽማግሌዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

Gamo Arba Minch!
13/05/2024

Gamo Arba Minch!

Gamo Arba Minch!Ethiopia!
12/05/2024

Gamo Arba Minch!Ethiopia!

11/05/2024

Gamo Zone Holistic Media/የጋሞ ዞን መረጃ ማዕከል

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል  የተጣበቁ መንታ ህፃናት ተወለዱ፡፡አርባምንጭ፤ ግንቦት 2/2016 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን )፦ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል  የፅንስና ማህፀን ...
11/05/2024

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የተጣበቁ መንታ ህፃናት ተወለዱ፡፡

አርባምንጭ፤ ግንቦት 2/2016 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን )፦ በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የፅንስና ማህፀን ስፔሻሊስት ዶክተር አረጋኸኝ ሙሉጌታ እንዲህ አይነት ክስተቶች የሚከሰቱ ሲሆን የመከሰት እድላቸው አናሳ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተሩ በሰጡት ማብራሪያ ህፃናቱ ሁለት ጭንቅላት፣ አራት እጅ፣ አራት እግር ያላቸው ሲሆን የጋራ የሆነ አንድ ልብና አንድ እትብት እንዳላቸው አስረድተው ሁለቱም ጾታቸው ወንድ መሆኑን ተናግረዋል።

ለምርመራ ወደ ሆስፒታሉ ከመጡበት 8ኛ ወር ጀምሮ ክትትል ሲደረግላቸው የቆዩት እናት በቀዶ ጥገና በሠላም መገላገላቸው ተገልጿል።

ስፔሻሊስቱ በአንዳንድ ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ እንደዚህ አይነት ክስተቶች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ መሆናቸውን ገልፀው እናቶች የእርግዝና ምርመራ በወቅቱና በአግባቡ ቢያደርጉ ችግሩ ሊፈታ የሚችልበትም አጋጣሚ አለ ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት እናት በጥሩ ሁኔታ ላይ የምትገኝ ሲሆን ሕፃናቱም ዜናው እስከደረሰን ሰዓት በህይወት እንዳሉ አስረድተው ነገር ግን ጥብቅ የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጋሞ ልማት ማህበር የተዘጋጀ
11/05/2024

በጋሞ ልማት ማህበር የተዘጋጀ

ይህ ከታች በፎቶ የሚትመለከቱት ዱር እንስሳት በጋሞ ዞን ማዜ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ  ናቸው፡፡Maze National Park! in Gamo ZoneThe Maze national park was es...
11/05/2024

ይህ ከታች በፎቶ የሚትመለከቱት ዱር እንስሳት በጋሞ ዞን ማዜ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ናቸው፡፡
Maze National Park! in Gamo Zone

The Maze national park was established in 1997 E.C /2005/. The distance of Maze NP from Addis Abeba and Hawassa is 468 km and 248 km respectively. The MNP is surrounded by 5 wordas. These are Kucha, Alpa kucha, Daramalo and Kamba Wordas are found in Gamo zone, Zala worda is Gofa zone.

The maze national park passed two phases before it gets the naming maze national park, the first phase during this time becomes a controlled hunting area. To create a chronological time sequence b/n first and second phases, there is no exact time. The second phase is called a wildlife reserve area. Again, this time span is long before the park bears the naming maze national park.

The total surface area of the park is 202 km2. The largest area coverage of the park is plain topography. The rainfall extends from March to September, among these months there is variation in rainfall in the area. From December to February, there is little or no rainfall.

The park fortune possesses a number of rivers and streams which ultimately drain into Omo river. The name of the park is derived from the river called the maze river. The maze river has a number of tributaries, these are dumb, sage, llamas and Doha.

Maze national park is endowed with a large number of wildlife. It is much more pronounced over natural attraction. These are vegetation and animals. Vegetations:- the park is covered by the savannah grassland with scattered deciduous broad-leaved trees as well as riverine forest association along the main water courses. No endemic plant is registered.

Wild animals: the park embraces a large number of wild animals. There are different kinds of wild animals including the endemic animal. The park supports a large number of precious animals so-called Swayne's hartebeests. So far, 39 large and medium-sized mammals and 196 birds, ships have been recorded.

10/05/2024

ጋሞ ዞን!

Horse ride competition at Gamo Zone
09/05/2024

Horse ride competition at Gamo Zone

08/05/2024

በጋሞ ልማት ማህበር የአርባምንጭ ግብርና ልማት!
Koyrottidi Issippeteththa Dichchas!

08/05/2024
05/05/2024

ዴሬ ዳሮ፣ ዴሪያን ጋሞይ ሎኦ!

የተከበራችሁ የልማት ማህበራችን አባላትና  መላው የክርስቲና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለትና ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!አደረስን!የስቅለት በዓል ኢየ...
03/05/2024

የተከበራችሁ የልማት ማህበራችን አባላትና መላው የክርስቲና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለትና ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!አደረስን!

የስቅለት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች መከራ የተቀበለበት፣ በትንሳኤው ደግሞ ሠላምን ያበሰረበት በዓል ነው።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍና በመጠየቅ ልሆን ይገባል::

በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የአብሮነትና የአንድነት እንዲሆን እንመኛለን!

ቅድሚያ ለጋራ ልማት
ሚያዝያ 25/2016 ዓ/ም

የካምባ ዙሪያ ወረዳ ለጋሞ ልማት ማህበር 15 ሄክታር የእርሻ መሬት መስጠቱን ገለፀ------------------------------------------------ጋሞ ልማት ማህበር/ጋልማ/ ትኩረ...
03/05/2024

የካምባ ዙሪያ ወረዳ ለጋሞ ልማት ማህበር 15 ሄክታር የእርሻ መሬት መስጠቱን ገለፀ
------------------------------------------------
ጋሞ ልማት ማህበር/ጋልማ/ ትኩረት አድርገው ከሚሰራባቸው ዘርፎች አንዱ ግብርና ሲሆን በጋሞ ዞን የካምባ ዙሪያ ወረዳ ለጋሞ ልማት ማህበር 15 ሄክታር የእርሻ መሬት እንዲያለማ ሰጠ::

የካምባ ዙርያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተካ ውዴ፣ የጋሞ ልማት ማህበር ዋና ሥራ አሰፈፃሚ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ እና በጋልማ የካምባ ቅርንጫፍ ሥራ አሰኪያጅ አቶ መንግስቱ ማርቆስ የእርሻ መሬቱን በሚያለሙበት ጉዳይ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመዋል::

የዴሬ ልማትና ቢዝነስ ኮርፖሬሽን ም/ሥራ አስፈፃሚ አቶ ማጌሶ ማሾሌ ልማት ማህበሩ በተሰጠው የእርሻ መሬት የእንስሳት እርባታ እንዲሁም የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በማልማት ለአካባቢው ህብረተሰቡ እንደተለመደው በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ ባሻገር በሚገኘው ትርፍ ለአካባቢው ህብረተሰብ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል::

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሚያዝያ 25/2016 ዓ.ም!

01/05/2024
28/04/2024

ጋሞ ባይራ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

28/04/2024

የሠላም ማይክሮ ፋይናንስ አክስዮን በመግዛት ተጠቃሚ ይሁኑ!

72 በመቶ ደርሷል ተብሏል ሰባት ከተሞችን የሚያገናኘው የሞርካ- ግርጫ- ጨንቻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 72 በመቶ ደረሰ ሞርካ፣ ዋጫ፣ ወይዛ፣ ሁሉ ቆዴ፣ ዛዳ፣ ዶኮ፣ ጨንቻ ከተሞችን የሚያ...
27/04/2024

72 በመቶ ደርሷል ተብሏል
ሰባት ከተሞችን የሚያገናኘው የሞርካ- ግርጫ- ጨንቻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 72 በመቶ ደረሰ

ሞርካ፣ ዋጫ፣ ወይዛ፣ ሁሉ ቆዴ፣ ዛዳ፣ ዶኮ፣ ጨንቻ ከተሞችን የሚያገናኘው የሞርካ- ግርጫ- ጨንቻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 72 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ።

ፕሮጀክቱን በ2017 ዓ.ም ሙሉ ለሙ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

72 ነጥብ ስድስት ኪሎ ሜትር የሚረዝመው ይህ መንገድ 39 ነጥብ አራት ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ቀሪ ዋና ዋና ስራዎችን ጨምሮ የማጠቃለያ ስራዎችን ለመፈጸም እየተሰራ ነው ተብሏል።

ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው የስራ ተቋራጭ ቤጂንግ አርባን ኮንስትራክሽን ግሩፕ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፤ መንገዱን ለመገንባት የሚያስፈልገውን አንድ ነጥብ 967 ቢሊዮን ብር በኢትዮጵያ መንግስት እየተሸፈነ መሆኑን ገልጿል፡፡

የማማከሩን ስራ ደግሞ ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ኃላ/የተ/የግ/ማ እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጿል።

በኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ የፕሮጀክቱ ተጠሪ ኢንጂነር አስቻለው ባልቻ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ቀድሞ ለመጓጓዝ ይወስድ የነበረውን የጉዞ ጊዜ በሁለት ሰዓት ተኩል ይቀንሳል።

ሌላው መንገዱ ሲጠናቀቅ የሚኖረው ፋይዳ ከተማን ከከተማ ማገናኘት፣ ለከተማ እድገት፣ ታካሚን በተሻለ ፍጥነት ጤና ተቋም ለማድረስ እና አምራች ምርቱን ለገበያ ማቅረብ እንዲችል ያደርጋል ብለዋል።

የመንገዱ ስፋት በወረዳ ከተማዎች 21 ነጥብ አምስት ሜትር፣ በቀበሌ ከተማዎቸ 12 ሜትር፣ በገጠር ስምንት ሜትር ስፋት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

መንገዱ ከዚህ ቀደም መንገዱ ጥርጊያ ደረጃ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት እየተሰራ የሚገኘው አስፓልት ኮንክሪት ግንባታ ነው ያሉት ኢንጂነር አስቻለው፤ በአሁኑ ወቅት መንገዱ 52 ነጥብ ሶስት ኪሎ ሜትር የደረሰ ሲሆን ይህም በመቶኛ 72 ከመቶ ነው ብለዋል።

ሁሉም የድልድይ ስራዎች በማጠናቀቅ 39 ነጥብ አራት ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ስራ ተሰርቷል።

ፕሮጀክቱ የተጀመረው 2012ዓ.ም ሲሆን ከወሰን ማስከበር ክፍያ መዘግየት ጋር በተያያዘ የመንገድ ግንባታው መዘግየቱን ገልፀው፤ በውሉ መሰረት የፕሮጀክቱን ግማሽ ክፍል በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ለማስረከብ እንዲሁም ቀሪውን በ2017 ዓ.ም ለማስረከብ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
(ኢ ፕ ድ)
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓም

Arba Minch Crocodile Ranch!
24/04/2024

Arba Minch Crocodile Ranch!

330 የጋሞ ባይራ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከ9 ሺህ ብር በላይ በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር አባልነት አደሱ🙏330 የጋሞ ባይራ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  ተማሪዎች 9...
24/04/2024

330 የጋሞ ባይራ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከ9 ሺህ ብር በላይ በመክፈል የጋሞ ልማት ማህበር አባልነት አደሱ🙏

330 የጋሞ ባይራ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 9,810 ብር የተማሪ አባልነት መዋጮ ለልማት ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ስኬት ድጋፍ ያደረጉ የትምህርት ቤቱ አመራሮችና ባለድርሻ አካላትን እናመሰግናለን🙏

ሌሎችም አባል ለመሆን የሚትፈልጉ በአካል ወደ ጋልማ ቢሮ በመምጣት አሊያም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋልማ አካውንት ቁጥር 1000021467174 ገቢ በማድረግ አባል መሆን እንደሚችሉ ልማት ማህበራችን ይገልጻል::

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
16/8/2016 ዓ.ም

የስብሰባ ጥሪ የጋሞ ልማት ማህበር ስብሰባ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ!--------------------------ሚያዝያ 20/2016 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ጋሞ ልማት ማህበር ከአባላትና ደ...
23/04/2024

የስብሰባ ጥሪ
የጋሞ ልማት ማህበር ስብሰባ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ!
--------------------------
ሚያዝያ 20/2016 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ጋሞ ልማት ማህበር ከአባላትና ደጋፊዎች ጋር ውይይት ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቅቋል፡፡

በመሆኑም በጌዴኦ ዞንና አካባቢው የሚትገኙ የጋሞ ልማት ማህበር አባላትና ደጋፊዎች የፊታችን እሁድ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በጌዴኦ የባህል አደራሽ ለውይይት እንድትገኙ ልማት ማህበራችን ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም

22/04/2024

#ጋሞ አርባምንጭ!

ተመራጭ የስብሰባ አዳራሽ ጋሞ ባህል ማዕከል!
22/04/2024

ተመራጭ የስብሰባ አዳራሽ
ጋሞ ባህል ማዕከል!

22/04/2024
🙏በጋሞ ልማት ማህበር ጋሮ ጋራዥ ለተገልጋዮች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገለፀ-----------------------------------------👉 በጋሞ ልማት ማህበር ጋሮ ጋራ...
22/04/2024

🙏በጋሞ ልማት ማህበር ጋሮ ጋራዥ ለተገልጋዮች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገለፀ
-----------------------------------------
👉 በጋሞ ልማት ማህበር ጋሮ ጋራዥ ለደንበኞቹ ፈጣን እና ቀልጣፋ የአውቶሞቲቭ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባሻገር ለተመጣጣኝ አገልግሎት ተመጣጣኝ ክፊያ እየተቀበለ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

👉በአርባ ምንጭ ሸቻ ጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አጠገብ የሚገኘው ጋሮ ጋራዥ ከፍተኛ ጥራት ባለው ጥገና፣ እና አጠቃላይ የአውቶሞቲቭ ብቃቱ ይታወቃል። በሰለጠነ መካኒኮች እና ቴክኒሻኖች ጋራዡ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል፣ ይህም ደንበኞች የአውቶሞቲቭ ፍላጎታቸው ምንም ይሁን ምን ከፍተኛ ደረጃ ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል።

👉አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የአውቶሞቲቭ አገልግሎት ፍላጎት እያደገ በመምጣቱ ጋሮ ጋራዥ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ልዩ አገልግሎት ለደንበኞቹ የመስጠት ተልእኮውን በመጠበቅ ላይ ይገኛል። ጋሮ ጋራዥ ባለው ጠንካራ ስም እና በጋሞ ልማት ማህበር ድጋፍ ለቀጣይ አመታት በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ያለውን አወንታዊ ተፅእኖ ለማስቀጠል ዝግጁ ነው።

👉ስለሆነም በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት የሚፈልግ አካል ምርጫውን ጋሮ ጋራዥ ያድርግ እንላለን። ለተጨማሪ መረጃ 0908772912 ይደውሉ!

🙏ቅድሚያ ለጋራ ልማት!
ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም

Address

Gamo Zone, Arba Minch
Arba Minch'

Telephone

+251949235632

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zambo Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zambo Media:

Videos

Share