26/06/2023
የደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አዲስ የመገልገያ
አርማ (Logo) ይፋ አደረገ!!!
➖==➖==➖==➖==➖==➖==➖==➖==➖
ውድ የፔጃችን ተከታታዮች ካሁን በፊት በሠጣችሁን አስተያየትና ምክረ ሀሳብ መሠረት መምሪያው የዞኑን ህዝብ ባህልና ቱሪዝም ሀብቶችን የሚገልፅ አርማ (Logo) በማዘጋጀት ህዝብ አስተያየት እንድሰጥበት አድሱን አርማ ይፋ አድርገናል ።
የዞኑ የቱሪዝም መሪ ቃል / Slogan /
Hub of diverse beauty
(የአይነተ ብዙ ውበት እልፍኝ )
አርሂቡ ደቡብ ወሎ ሲሆን
የአርማውን መነሻ ሀሳብና ምንነት ማብራሪያ እንደሚከተለው ቀርቧል።
1, ጥበቡ :-
ወሎ ውስጥ ያለውን ዘመን ተሻጋሪ ኪነ ጥበብ የሀገር በቀል እውቀት ውህደትና መስተጋብር እና አቃፊነት
2, የሙዚቃ ቁልፉ:-
ለዓለማዊ ሙዚቃና እንደ መንዙማና መዝሙር ላሉ ልዩ መንፈሳዊ ፍልስፍናዎች እንድሁም ኪነ ጥበብ እድገት ያበረከተውን አስተዋፅኦ ለመግለፅ
3, ጨረቃና መስቀሉ:-
የሁሉም ሰማያዊ ሃይማኖቶች ተዋደውና ተፋቅረው በእኩልነት የሚኖሩባት የአምልኮ ቦታዎችና የአስተምህሮ ባለቤቶች የሚገኙባት ድንቅና ቅድስት ምድር
4, ጋሻ:_
የህዝቡን ጀግንነት፣ የነፃነት ተጋድሎ፣ አሸናፊነት፣ መከታነት፣ አብሮነት፣ ጥንታዊ ታሪክና ዘመን ተሻጋሪ ቅርሶች መገኛ
5, ተራራው:-
ውብ ተፈጥሮና ማራኪ መልካ ምድር የብሄራዊ ፓርኮችና ብርቅዬ እንስሳትና እፀዋት መገኛ
6, ውሃማ አካሉ:-
የበርካታ ሀይቆችና ዓመቱን በሙሉ የሚፈሱ ወንዞች መገኛና የአሳ ሀብትና የመዝናኛ ቦታዎች ማዕከል
7, የእጅ ሠላምታ:_
ሠው በሠውነቱ ብቻ የሚከበርበት አንድነት የተፈጠረበት፣ አብሮነት ተቦክቶ የተጋገረበት ፣ ተከብሮ ተዋዶ በአብሮነት የሚኖርበት የቱባ ባሕል እና ልዩ ልዩ እሴቶች ተሰናስለው መኖራቸው
8, የአድማስ ብርሀን ጮራ:-
በአካባቢው ያለውን እድገትና ብልጽግና ብሩህ ተስፋን የሚያመላክት
ያለችሁን ሀሳብና አስተያየት አጋሩን!!!
ደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ
South Wolo Zone Culture and Tourism Department prepared a new logo ➖=➖=➖=➖=➖=➖=➖=➖=➖
Dear followers, based on your suggestions, we have incorporated your comments on this logo that expresses the role of the people in Culture and Tourism of the Zone.
Tourism motto of the Zone indicated the thoughts of Wello people with promotional way. "Arhibu" is a typical word which is known in the area and shows hospitality.
Major points for the logo parts are as follows:
1, The decorated outside circle :
It shows that the integration, interaction and inclusiveness of the transcendental arts and indigenous knowledge found in Wolo
2, The key to music:-
It indicate that the contribution of the area for the unique spiritual thoughts, Arts and music it self
3, The Moon and the Cross:-
A wonderful and holy land where all the religions of the world live together and live as equals
4, Shield:
The heroism of the people, the fight for freedom, victory, unity and ancient histories and the origin of timeless heritage.
5, The mountain:
Beautiful nature and beautiful land, home to national parks and rare animals and plants species
6. The water body:
The location of many lakes and year-round rivers and the center of fisheries and recreational areas.
7, hand greeting:
Implies authentic culture where people are respected each other only by being human and the presence of different values
8, The light of the horizon:
Indicating the bright hope of growth and prosperity in the area Share your thoughts and opinions
South Wolo Zone Culture and Tourism Department