14/10/2022
በክልላችን ከሚገኙ ከተሞች ውስጥ ግልፅ ብሎ የተሰመረ የከተማ ወሰን የሌላት ብቸኛ ከተማ የኛዋ #ቡሬ ናት።
የቡሬ የከተማ ወሰን ማለት አስተዳዳሪዎቿ በተቀያየሩ ቁጥር እንደየፍላጎቶቻቸው የሚያሰምሩት፤ አንዴ ወደላይ፣ ሌላጊዜ ወደጎን የሚያሰፉትና የሚያጠቡት፤ ስልጣንን መከታ በማድረግ የነዋሪውን ህዝብ ይሁንታ ጨፍልቀው ኪሳቸውን ሲያደልቡበት የዘለቀ ዋስትናቸው ሆኖ እስካሁንም አለ።
የቡሬ ከተማ ምክር ቤት ስራው ምንድን ነው? እስከየት ድረስ ያለውን ህዝብ ነው የወከላችሁት ቢባሉስ መልሳቸው ምንድን ነው? ለምን ወደመስክ ወጥቶ፣ መረጃ አሰባስቦ፣ ነዋሪዎች ጋር ተወያይቶ በአራቱም አቅጣጫ የከተማውን ወሰን አያሰምርም?