
24/12/2024
Maye Daraariinxen, Itti Daraarrannon!!
ሕብረቱ ነገሮችን በስሌትና በብስለት ለማጤን ሲል ከማህበራዊ ሚዲያ መራቁን ተከትሎ አንዳዶች ጡንጎ እንደፈረሰና ዳግም ላይነሳ ወድቋል ብለዉ ተከታታይ የስም ማጥፋት ''በጭምብል የማህበራዊ ትስስር ገጽ'' ሆን ብለዉ ስራዬ ብለዉ በማራገብ ለሰናይ አላማ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የወጣቶችን የመደራጀት ህጋዊ መብት አዋጅ ቁጥር 621/2000 በግልፅ በሚቃረን መልኩ ህብረቱ ካነገበዉ ዓላማና ራዕይ ፍጹም ተቃራኒ ከአዉንታዊ ጎን ይለቅ አሉታዊ ጎኑን ብቻ ለሚያስቡ ጠባቦች ጥቂት የደስታ ጊዜ የፈጠረ ቢሆንም ሕብረቱ ከያዘዉ ዓላማ ፈቀቅ የማይልና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ፣እየጎመራና መልካም ፍሬን እያፈራ ከሚመለከተዉ ሁሉ ጋራ በጋራ የሚሄድ መሆኑን እየገለፅን፣
እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የጌዴኦ ህዝብ ዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሕብረታችን ጌዴኦ ጡንጎ ፉሊ ከጌዴኦ ባህላዊ የባሌ-ጋዳ ስርዓት መሪ አባ ጋዳ ቢፎም፡ዋቆ ጋር በህብረቱ ተወካዮች አማካኝነት በ15/4/2017 ዓ/ም በዲላ-ባዳቻ ሶንጎ ተገኝቶ ለስከዛሬዉ ሂደትና ለቀጣይ የህብረቱ ጉዞ ምርቃት በመቀበል የበዓሉን መራሃ ግብር መሠረት በዓሉን ለማድመቅ የበኩሉን እንደሚወጣ ከሕብረቱ አባላት ጋር በነበረዉ የዉይይት መድረክ ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን፡፡ በቀጣይ ሕብረቱ ካነገበዉ ዓላማና ራዕይ አንጻር ስራዎችን ተንቀሳቅሶ መስራት ይችል ዘንድ ከሚመለከተዉ አካል ለህብረቱ ህጋዊ ሰዉነት/ዕዉቅና የማግኘት ሂደት በአጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከሚመለከተዉ አካል ጋር እየተነጋገረ ሁኔታዎችን የሚያመቻች 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ ሰይመዋል።
ይህም ሂደቱን ከቀድሞ ይልቅ ምቹ እንደሚያደርግም አባ ጋዳ ቢፎም ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከፊታችን ያለዉ የዘመን መለወጫ ዳራሮ በዓል በሰላም እንዲከበር ወጣቶች ከመንግስት የጸጥታ አካላት ጋር በትብብር እንዲሰሩ አባጋዳ ቢፎም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህን ተከትሎ መላዉ የጡንጎ ሕብረት አባላት እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን አብሮ ደስ አለን እያልን የህብረታችን አባላት በቀጣይ ህጋዊ የሰዉነት እዉቅና ፈቃድ አሰጣጥ ሂደት እንደተጠናቀቀ ወደ ተግባር ለመግባት ሁሉም የሕብረቱ አባል ከቀድሞ ይልቅ ለበሬ ወለደ አሉባልታ ሳይረበሽ በዓላማ ጽናትና በቁርጠኝነት በአዲስ መንፈስ እንዲነቃቃ ህብረቱ የከበረ መልዕክቱን ከወዲሁ ያስተላልፋል!!
Xungotik herreginna oojjo XUNGOTEN.