24/01/2025
የምጽፉ እጆች ይበረታታሉ!!
ከጊዜ ወደ ጊዜ የጌዴኦ ህዝብ ምሁራን ተወላጆች በብሔሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መጽሐፍቶች በመጻፍ አሻራቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
''ዳማንቆ'' የተሰኘው በጸሐፊው አገላለጽ እንንቃ የሚል ዕሳቤ ያለው በርካታ የብሔሩን ታሪካዊ ስነምህዳራዊ እንቅስቃሴዎችን የምያስቃኝ መጽሐፍ በወጣት ጸሐፊ አቶ ወንድማገኝ አሰፋ ተጽፎ እሁድ በ18/5/2017 ዓ.ም በጌዴኦ ባህል አዳራሽ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ምሁራንና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በይፋ ይመረቃል።