Laliebela Tour information

Laliebela Tour information Sunset Tour and Travel company provide quality tourism service.

Our page is aim to provide tourist site and tour service information for Independent and group travelers through all part of Ethiopia, which comes from all parts of the world or domestic travelers.

 የጥምቀት በዓል እጅግ በድምቀት የሚከበርባት ጎንደር ከተማ ዝግጅቷ በማጠናቀው እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው።ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመ...
12/01/2023



የጥምቀት በዓል እጅግ በድምቀት የሚከበርባት ጎንደር ከተማ ዝግጅቷ በማጠናቀው እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው።

ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና በክብር ለማስተናገድ ዝግጅታችንን ሁሉ አጠናቀናል ብለዋል።

ዘንድሮ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የከተማ አስተዳደሩ " የጥምቀት በዓልን የጥበብ መፍለቂያና የፍቅር ከተማ በሆነችው በጎንደር ኑ አብረን እናክብር " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" ጎንደር የሃይማኖት፣ የፍቅር ፣ የጥበብ መፍለቂያ፣ የቱሪስት ምስእብ ፣ የኩሩ ህዝብ ባለቤት ከተማ ናት " ያለው አስተዳደሩ ፤ የጎንደር ህዝብ እንግዳ ተቀባይ፣ ሰው አክባሪ ህዝብ ነው ፤ ኑ የጥምቀት በዓል በጋራ እናክብር ብሏል።

ምንጭ tikvahethiopia

23/12/2022
23/12/2022
01/12/2022

ወገናችሁን ጎብኙት!

ገና፣ ጥምቀት፣ የፈረስ ጉግስ ትርዒት የሚደረግባቸው በዓላት እየደረሱ ነው። በተለይ በውጭ አገር የምትገኙ ወገኖች በዚህ ወቅት አመቻችታችሁ ብትመጡ የህሊና እርካታ ታገኛላችሁ።

1) ተፈናቅለው የከረሙ የራያ፣ የጠለምት፣ የአበርገሌ እናቶች ወደ ቀያቸው ተመልሰው የጀበና ቡና፣ ልጆቻቸው ሊስትሮ ቢሰሩ የእናንተ መምጣት ገቢያቸው ነው። ዘመድ ጥየቃ የተለየ ነገር ይዛችሁላቸው እንድትሄዱ አይጠበቅም። አገልግሎቶቻቸውን ተጠቅማችሁ፣ አከራረማቸውን ጠይቃችሁ ብትመለሱ በቂያቸው ነው። ትልቅ ስጦታ ነው።

2) ህዝባችን ሀዘን ውስጥ ነው የከረመው። በተደጋጋሚ ለጥቃት የተጋለጠው የራያ ወገናችን ሀዘኑን አምቋል። አበርገሌና ጠለምት ስቃይ ውስጥ ነው የከረመው። ወገናችን በበደሉ ልክ አላስተዛዘንነውም። ስትመጡ ለቅሶ እንድትቀመጡ አይደለም። እንግዳው ሆናችሁ አክብራችሁ ስትመጡ ህዝባችን ያን ቁስሉን ረስቶ ሞቅ ደመቅ አድርጎ በዓላቱን ይውላል። የስነልቦና ጥቃት የደረሰበትን ህዝባችንን ዘመናዊ ህክምና ባናዘጋጅለት እንኳን በዓላቱን ሞቅ ደመቅ አድርገን መሪር ሀዘኑን እንዲረሳው እናደርጋለን። ከውጭ አገርም ሆነ ከቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል በመምጣታችሁ ህዝብ ለበዓሉ ልዩ ቦታ ሰጥቶ ይውላል። ቁስሉ ባይሽር እንዲያገግም ያግዛል። የእናንተ መምጣት በዘመናዊ ህክምና የሚያገኘውን የሚተካ የስነ ልቦና ጥንካሬ የሚሰጠው ከሆነ እርካታ ታገኙበታላችሁ። ያውም ተዝናንታችሁ።

3) ገንዘብ ለማውጣትም፣ በስነ ልቦና ለማበርታትም ብቻ አይደለም የምትመጡት። ህዝባችን ያን ሁሉ ወ*ረ*ራ ችሎ ተዋጊና ተጀን ሆኖ አሸንፏል። አሸናፊ ቤተሰብ፣ አሸናፊ ህዝብ ለመጎብኘት ነው የምትመጡት። ህዝባችን ዋጋ ከፍሎ አኩርቶናል። በግለሰብ ደረጃ የምናከብረው ሰውን "ባየሁት" ብለን እንኳ ረዥም መንገድ እንሄዳለን። ማስታወሻ እንዲኖረው እንፈልጋለን። በዚህ ወቅት አሸናፊው ህዝባችን ብቻ ሳይሆን ተራራና ሸለቆው ሳይቀር በአይናችን የምናየው ከተፈፀመ ወራት ያላለፉት እንዲሁ በጉልህ የሚታይ አኩሪ ታሪክ ታቅፏል። ለበዓላቱ ስትመጡ በአይናችሁ በብረቱ የጀግንነት ታሪክ አይታችሁ ትሄዳላችሁ።

ወገናችሁን ሰበብ ፈልጋችሁ ጎብኙት። ጊዜ ያላችሁ አያምልጣችሁ። ጊዜ ያለውን ገፋፍታችሁ ላኩት። መምጣት ባትችሉ በዓላት ደማቅ የሚሆኑበትን መንገድ አግዙ። ስትጨነቁለት የነበረው ህዝባችሁ በዓላቱን በደማቁ እንዲያሳልፍ አብራችሁት ዋሉ። በመምጣታችሁ ታደምቁለታላችሁ። መምጣታችሁን ይወደዋል። ወ*ራ*ሪ ይመጣበት የነበረው ህዝባችን ወገን መጣልኝ እንዲል የማድረግ አቅሙ አላችሁ። እንቅልፍ አጥታችሁ የነበራችሁት መጥታችሁ ለህሊናችሁ እረፍት የሚሰጥ ነገር አድርጋችሁ ተመለሱ።

ለህዝብም ለእናንተም ትልቅ እድል ነው። እንዳያመልጣችሁ። ህዝባችንም እንዳያመልጠው።
ጌታቸው ሺፈራው እንደከተበው

26/09/2022
18/09/2022

ዘማርያን የንስሐ ሕይወት ያላቸው፥ ሥጋ ወደሙ የሚቀበሉና እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚኖሩ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ።

መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ዘማርያን የንስሐ ሕይወት ያላቸው፥ ሥጋ ወደሙ የሚቀበሉና እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚኖሩ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ።

የሲሳይ በገና ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ልሳናት መምህር ሲሳይ ደምሴ ዛሬ ከሚዲያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት "እኛ እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነታችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ባለው የመዝሙር አገልግሎት ውስጥ ያለውን ክፍተት ለመሙላት እያገለገልን ነው ያለነው ብለዋል።

ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ ምንም መንፈሳዊ የዜማ መሣሪያዎችን እያስተማሩ ቢገኙም በቴክኒክና ሙያ ሥር የተካተቱ መሆኑን አንስተዋል። እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ነበር መግባት ያለብን በማለት ገልጸዋል ።

"የሰአታቱ ፥የማህሌቱ፥የቅዳሴው ፥የኪዳኑ ዜማ በቀኖና ቤተክርስቲያን የተወሰነ ነው ማንም ሊጨምር እና ሊቀንስ አይችልም በተለያዩ ሰዎች በካሴት የሚወጣው መዝሙር ግን እስካሁን ባለቤት የለውም እርሱ አሳሳቢ ነው" ሲሉ አክለዋል ።

"ዝማሬ ትልቅ ጸጋ ነው" ያሉት መምህሩ የዘማሪዎቹንም የአገልጋዮቹንም ሕይወት ከመታደግ አንጻር አንድ ሰው ድምፁ ስላማረ እና ግጥሙ ጥሩ ስለሆነ ብቻ የመዝሙር ካሴት በማውጣት ዘማሪ መሆን የለበትም ፡፡ ያሉ ሲሆን የንስሐ ሕይወት ያለው፥ ሥጋ ወደሙ የተቀበለ እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚኖር ሰው ሆኖ ነው መዘመር ያለበት ሲሉ ተናግረዋል ፡፡





ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channel/UCKqL7UekDOyp6q4j7ObVf9Q

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://t.me/tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/tewahedo_media

መስከረም 21 ግሸን ደብረ ከርቤ አይቀርም!
17/09/2022

መስከረም 21 ግሸን ደብረ ከርቤ አይቀርም!

13/09/2022

አቡነ አሮን
የልደት ቦታ:- ገብያ በምትባል ሀገር ልዩ ስሟ ሰጎዳ በሚባል ስፍራ ነው። በዚያም ቦታ ገብረ መስቀል የተባለ እግዚአብሔርን የሚፈራ ለድኾችም ምፅዋትን መስጠት የሚያዘወትር አንድ ደግ ሰው ነበር።አመተ ማሪያም የምትባል ሚስት ነብረችው። እነዚህ ሁለቱም መልካምን ለመስራት የተዘጋጁ ነበሩ። ልጅም አልነብረቸውም። በዚህም ምክንያት ወደ እግዚአብሔር በሰዋች ሁሉም ዘንድ የተወደደ መልካምን ፍሬ እንዲሰጣቸው ይለምኑ ነበር። እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ አመተ ማሪያም ፀነሰች።ወንድ ልጅም ወለደች ።ስሙንም ፈረዳ ብላ ሰየመችው።እግዚአብሔር ፈረደልኝ የፀሎቴንም ዋጋ ሰጠኝ ስትል።የንፅሕናዋም ወራት በተፈፀመ ጊዜ ሕፃኑን በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሰረት ያጠምቁት ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዱት ።ካህኑም መንፈስ ቅዱስ እንዳናገረው ስሙን "አሮን" ሲል ሰየመው።ሕፃኑም አደገ መልአክም እግዚአብሔርም እየጠበቀው ከፍ ከፍ አለ። ገብረ መስቀልም ልጁ አሮንን ገብረ መሲሕ ወደሚባል ካህን ዘንድ ወሰደው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮም ገብረ ምሲሕ አሮንን መዝሙርንና የመፃህፋትን ያስተምረው ዘንድ ጀመረ። መንፈስ ቅዱስም ለአሮን የህሊውን መስኮቶች ሁሉ ከፈተለት። ዳዊትን ከጨረሰ በሁዋላ ልቡ በክርስቶስ ተነካ በፍቅሩም ተነደፈ።
ከዚህም በሁዋላ ዲቁና ይቀበል ዘንድ ወደ ጳጳስ ዘንድ ሄደ ። ዲያቆን አሮንም ሀገረ ገምብያን ተወ ወደ ሰጎዳም ሄደ። ያችም የጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት ። በዚያም በዲቁና አገልግሎት ለብዙ አመታት ተጠመደ።በማገልገል ላይም እያለ አንዲት ትንሽ የፍህም ፍንጣሪ ተነስታ አንዲቱ ጣቱ ላይ ዐረፈች። እዚያውም ተጣብቃ በጣም አቃጠለችው ። አሮ መንክራዊም እጅግ የመረረ ልቅሶን አለቀሰ። እንዲህም አለ ነፍሴ ሆይ ካዛሬ ጀምሮ እሳት አያገኝሽም። ከዚች ቀን በላይ በሀገሩ ላለማደር ለራሱ ቃል ገባ። ከዚያም አምሐራ ሀገርም ደረሰ ወደ አቡነ በፀሎተ ሚካኤል ደብረ ጎል ገባ። በንፅህናውና በተጋድሎው የተነሳ የምንኩስና ልብስን አለበሰው። አሮንም የደብሩ መጋቢና ሊቀ ዲያቆናት ሆነ ። ጳጳሱና ንጉስ አግዐዚና ጠብ ክርክር በሆነ ጊዜ ከአስራንዱ መምህራን ጋር አስራ ሁለተኛ ሆኖ ንጉሱን ግስፀዋል።
በሀገረ ሮሐ ዓይነ ስውር የሆነ አንድ ፃድቅ ሰው ነበረ። ሌሊትና ቀንም በፆምና በፀሎት የተጠመደ ነበረ። የሰውን ግብር ሁሉ በገሐድ ያይ ነበር። ይህ ዓይነ ስውሩ ፃድቅ አሮን መንክራዊን አብዝቶ ይወደው ነበር። መንፈስ ቅዱስም መካን እረፍቱን አመለከተው ። እንዲህም አለው መምህር ሆይ ና ወደ ውጭ ውሰደኝና ብቻችንን እንቀመጥ የእግዚአብሔርን የማዳኑን ነገር ይነጋገሩ ዘንድ ሁለቱ ለብቻቸው ወደ ውጭ ወጡ።እንዲህ ሲልም ይጠይቀው ጀመር ወንድሜ አሮን ሆይ በፀሐይ መግቢያ በኩል አህጉራት ይታዩሃል? አቡነ አሮንም ብዙ ገፅ ያላቸው የሀገሮችን ተራሮች አያለሁ አለው። ያም ፃድቅ መለሰ ቀኝ እጅህን ስጠኝ? የአቡነ አሮን እጅ ባገኘም ጊዜ በቀኙ በኩል እንደ ቀኝ ፍላፃ አድርጎ በጣቶቹ የዚያችን ደብር አቅጣጫ አመለከተው። እንደ ጋሻ ነጭ የሆነ ራሱም በሐረጋት በአትክልት ቅጠልና በሳር የተሞላ ተራራ እስክትመለከት ድረስ እስኪ አስተውል? ሲል መከረው። አሁን ዐወቅኩ የምትለውንም ተረዳሁ ሲል አባታችን መለሰለት። የማያየውም ለሚያየው እንዲህ አለው ከምታያቸው ከሁለቱ አድባራት የሁዋለኛው በመጀመርያ የምትኖርባት ናት ። ሁለተኛዋ ደግሞ በመጨረሻው ማረፊያህ ናት ። በሁለተኛዋ በደብረ ቀጢን መከራና ሐዘን ያገኝሃል። ከመከራው በሁዋላም በመጀመርያዋ ደብር በልምላሜ ትቀመጣለህ ።በዚያም ቦታ የተመረጡ ሰዋችና ቅዱሳን ሕዝብ መጥተው ያርፉበታል። ያም ዓይነ ስውር ወደ አባታችን ተመለስና ተነሳ ወደ እረፍትህ ። አንተና የታቦትህ መቅደስ አንተ ብፁዕ ነህ። ላንተም መልካም ይሆንልሃል።በፀሎትህ አስበኝ። በዚያችም ሌሊት መንፈስ ቅዱስ ስለ መንክራዊ አሮን የገለጠላቸውን ምስጢር ሁሉ ሲነጋገሩ አደሩ።
በማግስቱ አቡነ አሮን መንክራዊ ከማህበርተኞች ሁሉ ጋር ተነሳ ። የተከዜንም ወንዝ ተሻገሩ። አባታችንም ደብረ ዳሬትን በቀኝ በኩል ትቶ ወደ ምድረ ቀጢን ወጣ። ወድዚያች የሚሄድባት ጊዜ እስኪደርስ ደረስ።ማህበረ ቅዱሳንም ሁሉ ወደዚያ ገብተው ደብረ ቀጢንን ከበብዋት። በዚያም ታቦታቸውን የሚያኖሩበት ቦታ ፈለጉ።ከዐለት ወቅረው መቅደስን አሳምረ ሰሩ።ለበአት የሚሆኑ ዋሻዋቻቸውንም አዘጋጁ።በደብረ ቀጢንም 7 አመት ተቀመጡ።የአባታችን ነገሩ የተአምሩም ዜና በመቄት ፥ በአሳሳ ፥ በዋድላም አውራጃዎች በዳውንትም ሁሉ ተሰማ ። ፃዲቁም በሐዋርያት ስልጣንም ደቀ መዛሙርቱን

በሰሜን ወሎ ካሉ አንዱና ታሪካዊ የአቡኑ አሮን የዋሻ ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን አቡነ አሮ ማናቸው የሚለውን ወደ በሁዋላ ይጠብቁን!
13/09/2022

በሰሜን ወሎ ካሉ አንዱና ታሪካዊ የአቡኑ አሮን የዋሻ ፍልፍል ቤተ ክርስቲያን አቡነ አሮ ማናቸው የሚለውን ወደ በሁዋላ ይጠብቁን!

12/09/2022

+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::

ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?

ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

11/09/2022

እየደሙ መዋብ !?!..
እንዲህ ናት ሀገሬ ...
ገነት ሆና ሳለ፣
የሲኦል አበጋዝ፣ ሚፈራረቅባት፤
የበቀል ቁርሾና፣
የተስፋ አበባ፣ አብሮ ሚፈካባት!
በጥላቻ ጦሮች፣
ልቧ እየተወጋ፣ በዓይኗ ስታነባ፤
ደስታዋን ሊመልስ፣
ምድሯ ያበቅላል፣ የተስፋ አበባ!
ደም እየፈሰሰ፣
ሀገር ተተብትባ፣ በሰማንያ ጣጣ፤
ይኸውና ደግሞ፣
አደይ ፍንድት ብሎ፣ አዲስ ዓመት መጣ !
ግሩም፣ አስደማሚ፣
የማትመረመር፣ ቅኔ ናት ምድሪቷ፤
አካሏ እየደማ፣
ለአልቃሽ ዓይኗ ደስታ፣ አበባ ነው ቤቷ።...
(አዲሱን ዓመት ሀገር ከመከራ የምታርፍበትና እኛም የሰላም አየር የምንተነፍስበት ያድርግልን!)
(((በዚሁ አጋጣሚ... ለአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫነት አደይ አበባን የምንጠቀም ኹሉ ትክክለኛዋና በዚህ በአዲስ ዓመት ወቅት የምትፈካዋ "ኢትዮጵያዊቷ" አደይ ባለ 8 (ስምት) ጆሮዋና ባለ ቢጫ ቀለሟ መኾኗን ልብ ልንል ይገባል:: ባለ 8 ጆሮዋ አደይ አበባ በዓለም የምትበቅለው በኢትዮጵያ ብቻ ሲኾን የምትፈካው/የምትፈነዳውም ልክ የኢትዮጵያ ዘመን ሲለወጥ ወቅቱን ጠብቃ ነው:: ፈክታ የምትቆየውም ለሦስት ወራት ያህል ነው:: በስምንቱ ጆሮዎቿ የአራቱን ዐበይት እና የአራቱን ንዑሳን አቅጣጫዎች ታመላክታለች:: (የስምንት አቅጣጫ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ ነገር ይያያዛል:: ዝርዝሩ ይቆየን::)

የአደይ አበባን ባለ ስምንት ጆሮነትና ጥልቅ ኢትዮጵያዊ ትስስር መርምረው የደረሱበት አባቶቻችን በቅርሶች ላይም አትመዋት አልፈዋል:: ለምሳሌ በመርጡለ ማርያም ጥንታዊ ሕንፃ ላይ ያለው ጉልህ ምልክት የአደይ አበባ ምስል ነው::

አደይ አበባ በቢጫ ቀለሟ ዘመን በተለወጠ ቁጥር ተስፋ መኖሩን የምታበስር ናት:: ተስፋ የሕይወት መቀጠል ዋናው ምሥጢር ነው:: ተስፋ ባይኖር ውሎ ማደር አይቻልም:: በጦርነትም መሐል እንኳን ሰላምን ተስፋ ባናደርግ መኖር ትርጉም ይኖረዋልን? በእውነት አዲሱ ዓመት ተስፋችንን ያለልምልን::)))
ከመላኩ አላምረው ገፅ የተውሰድ

10/09/2022

+++ "የእኛ የጥፋት ውኃ የሚጎድለው መቼ ነው?" +++

በኖኅ ዘመን የነበሩት ሰዎች አመጸኞች ሆኑ። የእግዚአብሔርን የምሕረት ጥሪ እምቢ ብለው መንገዳቸውን በፊታቸው አበላሹ። ምድሪቱንም በግፋቸው ሞሏት። ስለዚህም እግዚአብሔር ከትውልዱ ጻድቅ የነበረው ኖኅና ቤተሰቡን አስቀርቶ ሌሎቹን ከምድር ጋር ያጠፋቸው ዘንድ የጥፋት ውኃን አዘነመ። የታላላቅ ቀላያት ምንጮች ሁሉ ተነደሉ። የሰማይ መስኮቶችም ከፈቱ። ምድር በአምላክ የቁጣ ውኃ ተጥለቀለቀች። በመርከቢቱ ከነበሩት በቀር ምድር አንዲት ነፍስ አልቀረላትም።

እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ ቁጣ በኋላ በመርከቡ የነበሩትን ኖኅንና እንስሳት አራዊቱን አሰበ። በምድርም ላይ ነፋስን አሳለፈ። የቀላያቱን ምንጮች የሰማዩንም መስኮቶች ደፈነ። ዝናሙንም ከሰማይ ከለከለ። ሞልቶ የነበረውም ውኃ ቀስ በቀስ እየጎደለ መጣ። በመጽሐፈ ኩፋሌ እንደ ተቀመጠው በውኃ ተጥለቅልቃ የነበረችው ምድር ግልጥ ሆና የታየችው በመጀመሪያው ወር መባቻ ላይ ነበር።(ኩፋ 7፥1)

ባለ ዘመኖቹ እኛ ልክ በኖኅ ጊዜ እንደ ነበሩት የቀድሞ ሰዎች ክፋታችን ተካክሏል። መንገዳችንን በእግዚአብሔር ፊት አበላሽተናል። ምድርን በግፋችን ሞልተናታል። ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ያወረደው የጥፋት ውኃ ለእኛም ይገባን ነበር። እኛ ግን እርሱ እስኪቀጣንም አልጠበቅንም። እርስ በእርሳችን እየተጋደልን ምድራችንን በጥፋት ደም አጥለቀለቅናት። ወንድም ወንድሙን በጥይት ነደለ፣ በስለትም ሰውነቱን ከፈተ። የቁጣው ደም ከሰው እየመነጨ ምድርን ሸፈነ።

ታዲያ በዚህች ጎስቋላ ምድራችን ላይ የፈሰሰውን ደም የሚያደርቅ የይቅርታ ነፋስ መቼ ይነፍሳል? እንደ ውኃ ያጥለቀለቀንስ ደም መቼ ይጎድላል? የምንሰማው መጨካከንስ እያደር እያደር የሚቀለው መቼ ነው? አሁን እኮ የመጀመሪያው ወር (መስከረም) መባቻ ነው። ምድራችን የሸፈናት ጥላቻ እና መገዳደል ተገፍፎላት ዳግመኛ ግልጥ ሆና አናያትም?

የእኔ የአዲሱ ዓመት ስእለቴ ይህ ነው። የእናንተስ?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ጷጉሜን 5፣ 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

10/09/2022

ንጉሥ ፈርኦን ለ ያዕቆብ ሐበሻ በጣም የሚጠላውን ጥያቄ ጠየቀው:: "ዕድሜህ ስንት ነው?"

ከባሕላችን እጅግ ሊላቀቀን ያልቻለ ጥያቄ ቢኖር ዕድሜን መናገር መፍራት ነው:: "ኸረ ዕድሜዬን አልደብቅም" የምንል ሰዎች እንኳን ከመናገራችን በፊት "ዕድሜ ጸጋ ነው" የሚል ትንሽ የመግቢያ ንግግር እናደርጋለን:: በሰው ፊት ዕድሜ የጠየቁ ሕፃናትም “ዕድሜ አይጠየቅም እሺ ማሙሽዬ" የሚል ምክር ከትንሽ ቁንጥጫ ጋር ይቀምሳሉ::
ንጹሐኑ ሕፃናት ትምህርት ቤት "How old are you?”ን ሲያነቡ ስለሚውሉ ለምን እንደማይጠየቅ ግራ ግብት ይላቸዋል:: ብቻ በአጭሩ "ዕድሜህ ስንት ነው?" ተብለን ስንጠየቅ "ሰዓት ስንት ነው?" ስንባል በምንመልስበት ፍጥነት አንመልስም::

ያዕቆብ ግን ፈርኦን ሲጠይቀው የሐበሻ ደም የለበትምና "የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው" ብሎ ቀልጠፍ ብሎ መለሰ:: የሚገርመው በምድር ላይ የኖረበትን ዘመን "የእንግድነት ዘመን" አለው:: እውነትም ይህች ዓለም ሁላችንም ለጊዜው በእንግድነት የመጣንባት ናት እንጂ ሀገራችንስ በሰማይ ነው:: በእንግድነት መጥተን ዘላለም እንደሚኖር እንነካከሳለን እንጂ እንግዶች ነን:: እንደ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ግን "በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ" (ዕብ 11:13) ሁሉን ትተው የተከተሉት ሐዋርያቱም "በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ" ብለው አስተማሩ:: (1ኛ ጴጥ 1:17)

ያዕቆብ ዕድሜዬ 130 ነው ካለ በኁዋላ ጥቂትም ክፉም ሆነብኝ አለ:: እንግዲህ መቶ ሠላሳ አንሶት ነው:: እርግጥ ነው ሰው ዕድሜ አይጠግብም:: ማቱሳላንም ብንጠይቀው "ባጭር ተቀጨሁ" ማለቱ አይቀርም:: የተፈጠርነው ከዘላለማዊት ነፍስ ጋር ስለሆነ ለመኖር እንጂ ለመሞት መቼም ዝግጁ አንሆንም:: እንደ ያዕቆብ ያለ ብዙ ነገር ያየ ሰው ደግሞ ዕድሜህ ያንስብሃል:: ከእናትህ ሆድ ጀምረህ የሕይወት ትግል ከጀመርክ ለብኩርና ከተሽቀዳደምክ : ከፈጣሪህ ጋር ትግል ከገጠምክ : ድንጋይ ተንተርሰህ ሰማይ ድረስ ከተመለከትክ : ለራሔል ዓሥራ አራት ዓመት ደጅ ከጸናህ : በዮሴፍ ለዓመታት ካለቀስክ ዕድሜህ ቢያጥብርህ አይፈረድብህም::

ያልተኖረ ዕድሜ ግን ይሰለቻል:: ሰው ሥራ ሲኖረው ቀኑ እንዴት ይሮጣል? ይላል:: ሥራ የፈታ ደግሞ "ኸረ የዛሬው ቀን አልሔድ አለ እኮ" ይላል:: በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካቸው ከተጻፈ ሰዎች የሚያሳዝኑት "ኖረ ሞተም" የተባለላቸው ሰዎች ናቸው:: መኖርህ ካልፈየደ መሞትህ አይጎዳም ከመባል በላይ ምን አስከፊ ነገር አለ::

ወዳጄ አንተ ወደዚህች ምድር የመጣ አንተን የሚመስል ብቸኛው ሰው ነህ:: የማያልቅበት ፈጣሪ የአንተን ዓይነት ሰው ፈጥሮ አያውቅም ድጋሚም አይፈጥርም:: ምድርም የአንተ ዓይነት ሰው አይታ አታውቅም:: ዕድሜ የተሠጠህ ለአንተ ብቻ የተሠጠህን ነገር አበርክተህ እንድትሔድ ነው:: በአንተ ብቻ የሚፈታ ችግር በአንተ ብቻ የሚፈጠር ብዙ መፍትሔ አለ::

ሌሎች ከአንተ በሀብት በእውቀት በሥልጣን ወዘተ በልጠው ልታይ ትችላለህ:: ሕይወት ፍትሐዊ አይደለችም:: ፈጣሪ ያደላል ወይ ልትል ትችላለህ::
ከሀብታሙም ከአዋቂውም ከኃያሉም እኩል ለአንተ የተሠጠህ ፍትሐዊ ሥጦታ ግን ጊዜ ነው:: ለሁሉም ሰው ቀንና ሌሊቱ ሃያ አራት ሰዓት ነው:: በብራቸው ሰዓት ያስጨመሩ የሉም:: አጠቃቀምህ ነው እንጂ ጊዜ ለአንተም በእኩልነት ተሠጥቶሃል::

ዐዲስ ዓመት ሊገባ ነው:: ፀሐይ እያየችን ስታልፍ ሌላ አንድ ዓመት ሆናት:: 2012 አይቻልም እንጂ በድንጋይ ፈንክተን ብንሸኘው ደስ የሚለን ዓይነት ከባድ ዓመት ነበር:: አሁን ደግሞ ፈጣሪ በቸርነቱ ሌላ ዘመንን አቀዳጀን:: ፈጣሪ የሠጠን ያልተጻፈበት አዲስ ደብተር ነው:: ብዕሩ እጃችን ላይ ነው:: ምን እንጽፍበት ይሆን? ካለፈው ደብተር የቀጠለ ታሪክ እንጽፍ ይሆን? ወይስ አዲስ ነገር?

መልካም አዲስ ዓመት

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጳጉሜን 5 2012 ዓ ም

10/09/2022

#አሁን 4:30 #ወልድያ

የ2014 የመጨረሻዋ ቀን
የመጥፎ ነገሮች መጨረሻ ያድርግልን!!

አዲስ ዕሳቤ ለቱሪዝም
10/09/2022

አዲስ ዕሳቤ ለቱሪዝም

09/09/2022

>
(መላኩ አላምረው)
-----//-----
ንጉሥ ወይስ ቅዱስ? አይሉም አይሉም፤
ካህን ወይስ መሪ? አይሉም አይሉም፤
ላስታ ላሊበላ፣ አንዱ ሰው ነው ኹሉም።

ተዓምር ነው ምድሩ፣ ድንቅ ነው ስሪቱ፤
ንጉሥም ቅዱስም፣ ያበቅላል መሬቱ።
ቅዱስ ላሊበላ፣ ደብረ ሮሃ ላስታ፤
ምትናገርበት፣ ጥበብ አፍ አውጥታ፤

ምንኛ ድንቅ ነው፣ ጥበቡ ቅዱሱ፤
ምንኛ ግሩም ነው፣ እይታው ንጉሡ፤
የጥበብ እጆቹስ፣ እንደምን በረቱ፤
ሲነካው ታዘዘ፣ መቅደስ ኾነ አለቱ።
እንዴት ያለ ክብር፣ እንደምን ያለ ጽድቅ፤
ምድር ገና እያለች፣ በጨለማ ድቅድቅ፤
ያኔ በዚህች ምድር፣ ብርሃናት ነበሩ፤
አለት አንፀባርቀው፣ ለዓለም የሚያበሩ።
ካህኑ ላሊበላ፣ ንጉሡ ቅዱሱ፤
መስቀል እንደያዘ፣ ዘውድ ደፍቶ በራሱ፤
እንዴት ባለ ትጋት፣ እንደምን ከበረ፤
ሌት እየቀደሰ፣ ቀን ይፈርድ ነበረ።
ከሌሊትም ከፍሎ፣ ከቀንም ቀንሶ፤
ድንቅ ቅርስ አኖረ፣ አለቱን ቀልሶ።
አባቱ ይምርሃ፣ እንዴት ቢመርቀው፤
የእንጨቱን ሙያ፣ በአለት አጸደቀው።
በሄደበት ኹሉ፣ እግሩ በረገጠው፤
የቂም በቀልን ልብ፣ በእርቅ እየለወጠው፤
ታርቆ ስላደረ፣ ኹሉም እንደቃሉ፤
“አፍሮ አይገባ" ኾነ፣ ስሙ የእጅ መስቀሉ።
(የሰው ልጅ ከዚህ ሐቅ፣ ቢርቅም ባይርቅም፤
እውነት ያስታርቃል፣ ፍቅር አፍሮ አያውቅም።)
ቅዱስ የባረከው፣ ጠቢብ የዳሰሰው፤
ያስታውቃል ምድሩ፣ በረከት ሲደርሰው።
የላስታ እናቶች፣ ስለተመረቁ፤
ከውብ ከጀግና ውጭ፣ ወልደውም አያውቁ።
ቤዛ ኩሉ ቢባል፣ ቢዘመር ልደቱ፤
አሸንድዬ ቢባል፣ ሲሻገር ክረምቱ፤
ምሥጢር ስላዘለ፣ ትውፊት ሥርዓቱ፤
የሚታየው ኹሉ፣ ለዓይን ይማርካል፤
ንጉሥ ቅዱስ ሲኾን፣ እንዲህ ይባርካል።

22/08/2022

የእመቤታችን እረገቱዋ፥ ትንሳኤዋ እና ፍልሰቱዋ እርገቱዋና የሻደይ በዓል በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያ በተገኙብት በድምቀት ተከበረ።

አሸንደየን በዓል ለማክበር ወደቅድስቲቱ ከተማ አምሳለ እየሩሳሌም ደብረ ሮሃ/ላሊበላ በመግባት ላይ ያላቹህ እንግዶች እንኩዋን ደህና መጣቹህ እያልን ከዚህ በታች ያሉትን ጋይድ ቡኮች ከላሊበላ ...
20/08/2022

አሸንደየን በዓል ለማክበር ወደቅድስቲቱ ከተማ አምሳለ እየሩሳሌም ደብረ ሮሃ/ላሊበላ በመግባት ላይ ያላቹህ እንግዶች እንኩዋን ደህና መጣቹህ እያልን ከዚህ በታች ያሉትን ጋይድ ቡኮች ከላሊበላ ኤርፖርት የቱሪስት መረጃ ማእከል በነፃ ማግኘት ይችላሉ!

Address

Lalibela
888

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Laliebela Tour information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Laliebela Tour information:

Videos

Share

Category