19/12/2024
ይድረስ ለቅዱስ ላሊበላ ነዋሪዎች እና በተለይ ለእጣቱ ትዉልድ። ቅርሳችን ለነገዉ ትዉልድ እንዲሸጋገር እና ለኛም ሆነ ለልጅ ልጆቻችን ኩራት ሆኖ እዲቀጥል ከኛው የወጡ ተቆርቋሪ ግለሰቦች እዉቀታቸዉን እና ያላቸዉን ግንኙነት ጠቅመዉ አካባቢን የሚጠቅም ሲራ ሲሰሩ ማበረታታት ይገባል። ነገር ግን በተለያዩ የፕሮጀክት ስም ዘረፋ የለመደ ትዉልድ አሁንም የናንተን የወጣቶቹን የወድፊት እድል ካልዘርፍኩ አትሰሩም በማለት “በዘላቂ የላሊበላ ልማት ማህበር” እየተሰሩ ያለዉን ስራ አስቁመዏታል። እኔ እንዳንድ ግለሰብ እና እንደ አካባቢው ተወላጂ መሪር የሆነ ሃዘን ዉስጥ ነው ያስገባኝ።
በአሁኑ ሰአት መንግስት መልማት አለባቸዉ ብሎ ለቱሪስት መዳረሻ ከሚያለማቸው ግዙፍ ፕሮጀችቶች እና እንዲለሙ ከተመረጡት ቦታዉች ላስታ (ቡግና፣ ግዳን እና መቄት) እንደሌሉበት ማንም የሚአዉቀው እዉነታ ነው። ይሁን እንጂ በኛው ልጆች አቅም፣ ፍላጎት እና እዉቅ የተጀመረን ስራ ለዘረፋ ስላልተመቻቸዉ ብቻ እናስተዳድራለን የሚሉት አካላት በተወሰኑ ቀሳጮች፣ ማእረግ ያላቸዉ አላዋቂዉች፣ ይህን አይነት በእዉቀት ላይ የሚሰራ ስራ ፈጽሞ የማይረዱ የማህረሰብ አንቂነን ባዮች፣ ታሪክን እያዛቡ የሚቸረችሩ እና ቅርስን በህገወጥ የሚዘዋዉሩ ካህን ነኝ ባዮች እናም ጽዳት የማይወድላቸ የቤተክርስቲያን ግቢን የሚያገሙ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ነኝ የሚሉ የነቀርሳ ጥርቅሞች እየተሰራ ያለን ሰራ አስቁመዋል። እኔ የምለዉ ከተማዋን አስተዳድራለሁ የሚለዉ የጽጥታ አካል እነዚህ ሰዎች እዛዉ ዉስጥ ሆነዉ ይህን ሲሰሩ ምን እያደረገ ነው። የከተማ ስተዳደሩስ እንደ ወርልድ ባንክ አይዘረፍም እኔ ምን አገባኝ ነው? ዶክተር ነኝ ባዩስ፣ እንዲያዉም ሞያየ ነዉ የሚል ሰው ይህን መረዳት አቅቶት የዘቀጠ ፖለቲካ ያደረገዋል እንዴ። ጎበዝ መንቃት ያለብን ይመሰለኛል መንቃት ካልቻልን ደግሞ የነቁት ማደናቀፍ ማቆም አለብን።
እኔ ዶክትሬት አለኝ እያሉ ለሚንጠራሩ የቅዱስ ላሊበላ ተወላጆች እባካችሁ እንደማትታወቁ አትሁኑ። “ጅብ ከማያዉቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልብኝ ይላል” እንደሚሉት አትሁኑ። በማህበረ ቅዱሳን ዉስጥ ተቀምጦ የ ጳዉሎስ እግር ስር ሲድሞነሞን መንደራችን በወርልድ ባንክ እና በወያኔ ተንኮል ስትፈርስ ትንፍሽ ያላለ፣ የገጠር ቤተክርስቲያናት በገንዘብ እጥረት እየተቆራመዱ፣ ግማሽ የሚደርሰው የቅዱስ ላሊበላ ገቢ ለሸዋ ቤተ ክህነት ግብር ሲሆን ያልተቆረቆረ አሁን ምን ይሁን ተብሎ ነው ያዙኝ ልቀቁኝ የሚባለዉ። ሌላዉ ደግሞ ቅድስቲቱን ከተማ ጵንጥጥና ያስተዋወቅ በሰራዉ መጥፎ ስራም ትዉልድ እንዲህ ተንሻፎ እንዲቀር ያደረገዉ ሁሉ አሁን አዉኢቅልሃለሁ ቢል ልንቀበለዉ አይገባ።
እኔ እንደ ግል ጥቃት ነው የማየው፣ እስከመጨረሻዉም እታገለዋለሁ
ግርማ ሞገስ