ሚስጢረኛው ጋዜጠኛ

  • Home
  • ሚስጢረኛው ጋዜጠኛ

ሚስጢረኛው ጋዜጠኛ ከዘረኝነት ነፃ የወጣ ማህበረሰብ መፍጠርና መገንባት ነው ከማ

08/12/2023

?

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓትን ከጥምረቱ አባልነት ሰረዘሰኔ 18፣ 2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኢትዮጵያ...
25/06/2020

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ህወሓትን ከጥምረቱ አባልነት ሰረዘ

ሰኔ 18፣ 2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት (ኢዴሕ)ን ከጥምረቱ መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ሆነው ተገኝተዋል በሚል ከአባልነት መሰረዙን አስታወቀ።

ጥምረቱ አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ አካሄዷል።

በዚሁ ጊዜ ጥምረቱ በአደረጃጀቱ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና የጥምረቱ ቀጣይ አቅጣጫ ላይም ተወያይቷል።

ጥምረቱ በአደረጃጀቱ ላይ ውይይት ሲያደርግ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጥምረቱ ውስጥ ወዥንብር እየፈጠረ ነው ብለዋል።

የጥምረቱ የአደረጃጀት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ “ፓርቲው የጥምረቱ አባላትን ለመከፋፈል የተለያዩ ጫናዎች እየፈጠረ ነው” ይላሉ።

“ይህ ብቻ ሳይሆን ህወሓት ጥምረቱን እንደ ሽፋን ተጠቅሞ አገርን ለማወክ እየተንቀሳቀሰ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፓርቲው በጥምረቱ ሰብሰባ ላይ እንደማይገኝና የጥምረቱ ስብሰባም መቀሌ ካልተካሄደ ተቀባይነት እንደሌለው እየገለጸ ነው ሲሉ ከስሰዋል።

አቶ ቶሎሳ “ህወሓት እኔ ያልኩት ካልሆነና እኛ ካልመራን ትክክል አይደለም የሚል” ግትር አቋም ያራምዳል ሲሉም ክሳቸውን ያቀርባሉ።

ህወሓት በቀጣይ ከጥምረቱ ጋር ‘ይቀጥል ወይስ ይሰረዝ’ በሚለው ጉዳይ ላይ የጥምረቱ አባላት ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የተወሰኑ አባላት ህወሓትን ጨምሮ ሌሎች መተዳደሪያ ደንቡን የማያከብሩ ከጥምረቱ ይሰረዙ ሲሉ፣ በቁጥር በርከት ያሉት ደግሞ ‘አንድ ዕድል’ ይሰጣቸው ብለዋል።

በመጨረሻም ጥምረቱ ህወሓት በቀጣዩ ጉባኤ እንዲሳተፍ ጥሪ ተደርጎ አቋሙን ግልጽ ያድርግ በማለት ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

ይሁንና የጥምረቱ አመራሮች ከጉባኤው በኋላ በኢዜአ ተገኝተው በጉባኤው የተደረሰበትን የውሳኔ ሀሳብ አሳውቀዋል።

የጥምረቱ ሊቀ-መንበር አቶ ደረጄ በቀለ እንደሚሉት ህወሓትና ኢዴሕ ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ ታግደዋል፤ ይህንንም ሁሉም የጥምረቱ አባላት የተስማሙበት ጉዳይ ነው ይላሉ።

በጉባኤው ወቅት ተገኝቶ መታዘብ እንደቻለው በጉዳዩ ላይ አባላቱ ለሁለት ተከፍለው ክርክር ተደርጎ፤ ይፋዊ የድምጽ አሰጣጥ ተካሂዶ ለፓርቲዎቹ አንድ ተጨማሪ እድል እንዲሰጠው ተስማምተው ነበር።

አቶ ደረጄ ”ሁሉም የጥምረቱ አባላት በሁለቱ ፓርቲዎች መሰረዝ ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል” በማለት ከጉባኤው በኋላ የደረሱበትን ስምምነት ገልጸዋል።

ጥምረቱ እዚህ ዉሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ምን አድርጓል የሚል ለቀረበው ጥያቄ “ጥምረቱ ግንቦት 6 ባካሄደው ስብስባ ፓርቲዎቹ ቀጥሎ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ካልተሳተፉ እንደሚታገዱ ተገልጾላቸው ነበር” ብለዋል።

ከዚያ በኋላም ሶስት ጊዜ በስልክ ፓርቲዎቹ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ እንደነበረ አስታውሰዋል።

“ለፓርቲዎቹም በነገው ዕለት መታገዳቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ይጽፋል” ሲሉም ገልፀዋል።

ሊቀመንበሩ “በተለይ ህወሓት 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ተራዝሞ ሳለ ለጥምረቱ ሳያሳውቅ ምርጫ አካሂዳለሁ ማለቱ የህገ ወጥነቱ ማሳያ ነው” ብለዋል።

ጥምረቱ 24 ፓርቲዎችን ያቀፈ ሲሆን በትናንቱ ጉባኤው 22 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገኝተዋል፤ ሌሎች አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ጥምረቱን መቀላቀላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የመንግሥት የሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ያደረገውን ጥናት ማጠናቀቁን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀአነስተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ጫናን የሚያ...
25/06/2020

የመንግሥት የሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ያደረገውን ጥናት ማጠናቀቁን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ

አነስተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞችን የመኖሪያ ቤት ጫናን የሚያቃልል ጥናት አስጠንቶ ለመንግሥት ሊያቀርብ መሆኑን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የመንግሥት ሠራተኞች ለረጅም ዓመታት በምሬት ከሚያነሷቸው ችግሮች አንዱና ዋነኛው የመኖሪያ ቤት ችግር ነው።

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኑሮ ውድነቱ ከቤት ኪራይ ዋጋ መናር ጋር ተዳምሮ የዜጎችን ኑሮ መፈታተን መጀመሩ ተገልጿል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ እንደገለጹት፣ በቤት ኪራይ ዋጋ መናር ቀጥተኛ ተጎጂ ከሚሆኑ ዜጎች መካከል ዝቅተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞች መሆናቸውን ይገልጻሉ።

ሠራተኞቹ ገቢያቸውን በሙሉ ለቤት ኪራይ ስለሚያውሉ ለምግብና ሌሎች አገልግሎት ለመሸፈን እንደሚቸገሩ ያስረዳሉ።

ችግሩን ይፈታል የተባለ ጥናት ኮሚሽኑ ከኮንስትራክሽንና ቤቶች ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጥናት ማስጠናቱንና ጥናቱም በቅርቡ ለመንግሥት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

”ጥናቱ በዋነኛነት ለረጅም ዓመታት በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሲሰሩ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ደሞዝ የሚኖሩ ሰዎች አሁን ላይ ከተፈጠረው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መናርና ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚበሉበትን እስከማጣት የሚደርሱ መሆናቸውን ጥናቶቻችን አሳይተውናል” በማለት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን እና ስምምነቶችን አፀደቀየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ...
25/06/2020

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን እና ስምምነቶችን አፀደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን እና ስምምነቶችን አፀደቀ።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው መርምሮ ያፀደቃቸው ረቂቅ አዋጆች፦

የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ኅብረት ሰንደቅ ዓላማ፣ መዝሙር እና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ፤

የገቢ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል መንግሥት ፕሮጀክቶች አስተዳደር እና አመራር ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ፤

የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኳታር መንግሥት የማዕድን ሥራዎች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ናቸው።

ምክር ቤቱ መርምሮ ያፀደቃቸው ስምምነቶች፦

በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለበረሃ አንበጣ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገው የብድር ስምምነት፤

ኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እንዲያግዝ ለሁለተኛው የኢትዮጵያ የዕድገትና ተወዳዳሪነት የልማት ፖሊሲ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት፤

በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት፤ በሁለቱ አገሮች መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት ስምምነት፤

በኢትዮጵያ እና በሩዋንዳ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት እና በሁለቱ አገራት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠት የሚያስችለው ስምምነት ናቸው።

በሌላ በኩል የተጓደሉ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላት ሹመት እንዲሁም የንግድ እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለመመደብ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።

የመረጃ መረብ ጥቃት ምን ያህል ያሳስባል? (ሳይበር ጥቃት) መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም ኢንተርኔት ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊዘልቁት...
25/06/2020

የመረጃ መረብ ጥቃት ምን ያህል ያሳስባል? (ሳይበር ጥቃት)

መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም ኢንተርኔት ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊዘልቁት ይችላሉ።

በግለሰብ ደረጃ ሲከወን ጉዳቱ አስደንጋጭ ላይሆን ይችላል። ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳት ሲያስከትል ነው።

አንድ አገር የፋይናንስ መረጃዎቹ ከተጠለፉበት በእንብርኩኩ ሊሄድ ይችላል።

ሠሞኑን ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች፡፡

አንድ አየር መንገድ መረጃዎቹ ቢጠለፉበት የአውሮፕላኖች መከስከስን ጨምሮ መላ ተግባሩ ሊስተጓጎል ይችላል። በዚህም በቀናት ውስጥ ቢሊዮኖችን ሊያሳጣው ይችላል።

አንድ አገር የመብራት ኃይል አቅራቢ ድርጅቱ በመረጃ ቦርቧሪዎች ቢገረሰስበት አገር በድቅድቅ ጨለማ ልትዋጥ ትችላለች።

ባንኮች በመረጃ ጠላፊዎች መረጃቸው ቢታወክ አለኝ የሚሉት ገንዘብ፣ ሰበሰብነው የሚሉት አዱኛ ሁሉ በአንድ ጀንበር እንደ ጉም ሊተንባቸው ይችላል።

ስለዚህ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማቶች ይህንን ችግር ቀድሞ ለመከላከል ሲባል በተቋሞቻቸው በሙያው የተማሩና ልምዱን ያዳበሩ ባለሙያዎችን በቅርበት በማማካር ሊጠቀሙባቸው ይገባል፡፡

ሚዛናዊነት ከራስ ቢጀምር ...የሚዛን መንሻፈፍ ግለሰብን ፣ ማህበረሰብንና ሀገርን እየቆየ እንደሚጎዳና ለማይጠገን ቀውስ እንደሚዳርግ የሚገነዘብ ሁሉ በዚህ ሀሳብ ይስማማል ፡፡ ችግሩ ዶ/ር አ...
25/06/2020

ሚዛናዊነት ከራስ ቢጀምር ...

የሚዛን መንሻፈፍ ግለሰብን ፣ ማህበረሰብንና ሀገርን እየቆየ እንደሚጎዳና ለማይጠገን ቀውስ እንደሚዳርግ የሚገነዘብ ሁሉ በዚህ ሀሳብ ይስማማል ፡፡

ችግሩ ዶ/ር አብይ እንዳሉት ሁሉም ቀድሞ ጣቱን የሚቀስረው ሌሎች ላይ የመሆኑ አባዜ ነው ፡፡

ይህ የጣት ቅሰራ ራሳቸው ዶ/ር አብይንም ይመለከታል ፡፡ አንዱን ትልቅ ጥፋት ሸፋፍነህ ሌላው ላይ ጣትህን ስትቀስር ሚዛናዊነት ይንጋደዳል ፡፡

አንዱን ትልቅ ጥፋት አላየሁም ብለህ አይንህን ከሸፈንክ ሌላኛው ጥፋት ላይ የአይንህን መጋረጃ ቀደህ ለመጣል ሞራል ታጣለህ ፡፡

24/06/2020

!! !!

 #አብቹ ሁሌም    እና  #ሞራል ያለው   ነው። ስለዚህ  #ለአብቹ ያለን   በማንኛውም ምክንያት  ........   መሆን አለበት።
23/06/2020

#አብቹ ሁሌም እና #ሞራል ያለው ነው። ስለዚህ #ለአብቹ ያለን በማንኛውም ምክንያት ........ መሆን አለበት።

 #ዶክርተር አብይ  #አብቹለዚህ ስብእናው ሚስጥር አሁን አወኩኝዶ/አ አብይ አባቱ እንዲህ ያሉት ይመስለኛል::፨ #ልጄ የግለሰብን ሆነ የመግስትን ገንዘብ አትሰረቅ። #ለሌሎችም ለራስህም ታማኝ...
23/06/2020

#ዶክርተር አብይ #አብቹ

ለዚህ ስብእናው ሚስጥር አሁን አወኩኝ
ዶ/አ አብይ አባቱ እንዲህ ያሉት ይመስለኛል::

፨ #ልጄ የግለሰብን ሆነ የመግስትን ገንዘብ አትሰረቅ።
#ለሌሎችም ለራስህም ታማኝ ሁን
#ከክፍዎችና ከክፍ ስራ ራቅ
#ከሌባ ጋር አትተባበር
#ሐገርህን ውደድ
#መልካሙን እንጁ ከክፍ ስራ እራስህን ጠብቅ
#ለሐብት አትሰገብገብ :: ለመልካም ነገር ትጋ ያሉት ይመስለኛል።
ተመልከት የልጅ አዋቂ ከአባቱ እግር ሰር ተቀምጦ ጥበብን ታሪክን እውቀትን ይቀስማል።

ታታሪ ንብ ሆኖ የቀሰመውን እውቀት ጋግሮ ለሌሎች ያደርሳል።
መልካም ቤተሰብ መልካም ዘር ይዘራል ፍሬውም ሌሎች ይተርፋል።

ዋሼሁ እነዴ

በቃ ትዝ አለኛ እኔ ምን ላድርግ ስል የማህበራዊ ሚዲያ ደንበኞቼ ትዝ አሉኝ ታዲያ ይህንን መረጃ ባካፍላቸው የነርሱን አዎንታ ለማገኘት ሳይሆን የእኔን መስጠት ብቻ በማሰብ ነው፡፡የጠቅላይ ሚኒ...
23/06/2020

በቃ ትዝ አለኛ እኔ ምን ላድርግ ስል የማህበራዊ ሚዲያ ደንበኞቼ ትዝ አሉኝ ታዲያ ይህንን መረጃ ባካፍላቸው የነርሱን አዎንታ ለማገኘት ሳይሆን የእኔን መስጠት ብቻ በማሰብ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በአንድ መድረክ ላይ ካነሷቸው አንኳር አንኳር ነጥቦች መካከል!

" #መንግስት እንደ ጎረምሳ የሚዝት የሚፎክር ሳይሆን እንደ ጎልማሳ የሚያስተውልና የሚታገስ ነው።"

#በድሮ አስተሳሰብ ጥሩ አባት ማለት ልጁን የሚገርፍ፣ የሚቆነጥጥና የሚሸነቁጥ ነበር፤ በዚህኛው ዘመን ግን ጥሩ አባት ማለት የሚመክርና የሚገስፅ ነው።"

የአገር እዳ ወደ 25 ቢልዬን ዶላር የGDP የእዳ ቅነሳ አድርገናል።

#የቆሙ የከሸፉ የመንግስት ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በዘንድሮ ብቻ 600 ሺ ሱኳር ተጨማሪ አስገብተናል። ሌሎችም ይቀጥላሉ።

#እንቦጭን ለመከላከል የሚረዳ የማሽን ግዢ ለማድረግ መንግስት ከአውሮፓ ሃገራት ጋር ድርድር ላይ ይገኛል!!

#የኢት GDP 86ቢልዮን የነበረ ሲሆን በሁለት አመት ወደ 100 ቢልዮን አድጓል ። ከ880 PCI ወደ ከ1000 በላይ ደርሷል።

#ጥንካሪችን በማቀድ፤ በመሥራት እና ጨርሶ ለስራ በማብቃት ላይ የሚያተኩር የመንግስት ብቃት እንጂ በማስር በመግረፍና መግደል የመንግስት ጥንካሬ መለኪያ የልምምድ ችግር ነው።

#ብልጽግና ምርጫ የሚያሰጋው ፖርቲ አይደለም!

#አብቹ

እስኪ ምን ተሰማችሁ

ፓዌ የምስራቅ አፍሪካን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ውጥን የተጀመረባት የልማት እርሾ ናት።ፓዌ ማለት በ34 ቀበሌ ውስጥ 34 አምፑላንስ ፣ 34 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ በየቀበሌው የ...
22/06/2020

ፓዌ የምስራቅ አፍሪካን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ውጥን የተጀመረባት የልማት እርሾ ናት።

ፓዌ ማለት በ34 ቀበሌ ውስጥ 34 አምፑላንስ ፣ 34 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ በየቀበሌው የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ ያውም በነፃ፣ ሩዝ በኤሊኮፍተር የሚዘራባት፣ በየቀበሌው ግዙፍ መጋዚኖች የነበሯት
በቀን ከአንድ እስከ ሶስት ጊዜ አውሮፕላን የሚመላለስባት
የመኪና መገጣጠሚያ የነበራት ፣

ገበሬው በትራክተር የሚያርስባት በኮምባይነር አጭዶ የሚወቃባት ፣ በዘመኑ በአፍሪካ ሁለተኛውን ጥራት ያለው የሕክምና ማዕከል ሆስፒታል ባለቤት የነበረች ።

በሁሉሙ ቀበሌዎቿ ጥራት ያለው መንገድ የተገነባላት ፣
የጣና በለስ ፕሮጀከት የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻ ሙዝ ፣ ፓፓዬ ሆምጣጤ ቦሮ ሎሚ መንደሪ .... ከሕዝቡ ተርፎ ሲደፋ አስታውሳለሁ ።

የዲጋ መዝናኛ ማዕከል እና የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ከነትዝታው አለ ፣ የዓልሙ አዳራሽ በሀገሪቱ የመጀመሪያ አስደማሚ ነበር በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የባሕል ማዕከል አቻ ሆኖ አዲስአበባ ላይ ተስርቷል ።

የእግርኳስ ሜዳው እስካሁን ከነ ሞገሱ አለ ፣ እያንዳንዱ ገበሬ ባለ 40 ዚንጎ የጣሊያን ቆርቆሮ ባለቤት ነበረ፣ በወር አንድ ጊዜ ሁሉም ሕዝብ የግዴታ ወባ ተመርምሮ በነፃ መድኃኒት ይወስድ ነበረ።

በነገራችን ላይ በወረዳው ሕክምና በነፃ ነበረ ፣ የመዋኛው ገንዳ የቅርጫት ኳስና የመረብ ኳስ ሜዳው እፁብ ድንቅ ነበረ፣
የትራንስፖርት ችግር አይታሰብም ይልቁንም በእግር መሔድ ይናፍቅ ነበረ፣ የመንደር 24 የእንስሳት ማድለቢያ አሁን ወና ሆኖ አለ ። ነበረ ነበረ ነበረ

እነሆ ዛሬ አየር መንገዱን ከሰላሳ ዓመት በኋላ በአቶ ወርቁ አይተነው በኩል እውን ሆኖ አየነው። ሀገርን ካላንዳች ፃድቅ አይተዋትምና መንግስት የረሳትን ግለሰብ አሰባት።

ይህ ሰው በራሱ ሀገር ነው፣ ዋርካ ነው፣ ከፓዌ ምንም ጥቅም አያገኝም ፣ ግን ፓዌን አሰባት። የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ አስር ዓመት ከሚያነክስ ለአቶ ወርቁ አይተነው ቢሰጠው ለወጣቱም ሰፊ የሥራ እድል ይፈጥራል።

የፓዌ ሕዝብ ጥያቄ ግን ከአየር መንገዱ መከፈት በጣም ይዘላልና ይታሰቡበት።

22/06/2020

ለዘመናት አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየው የጣና በለስ አየር ማረፊያ ዛሬ የሙከራ በረራውን አካሄድ።

ሰኔ 14/2012 ዓ/ም በሙከራ የበረራ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሳነ መስተዳደሮች ተገኝተዋል።

አካባቢው የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰላጫ በመሆኑ መደበኛ የበረራ ፕሮግራሙን ለማካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰሩ ርዕሳነ መስተዳድሮች ገልጸዋል።

የአካባቢውን ሰላም በአንጻራዊነት በማረጋጋት ቀጠናውን ወደ ልማት በሚደረገው ሂደትም የሁለቱ ክልል መንግስታት በትኩረት እንደሚሰሩ ተጠቁሟል።

ባለሃብቱ በራሳቸው ተነሳሽነት የአየር መንገዱን ለማስጀመር ያደረጉትን ተነሳሽነት በማመስገን በክልሉ ውስጥ ለሚያደርጉት የልማት እንቅስቃሴ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ አሻድሊ ሃሰን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ መንግስት ምላሽ ለመስጠት በሚደርገው ሂደት ውስጥ የባለሃብቱ ሚና የጎላ እንደሆነ ገልጸው ሌሎችም ለማገዝ መንግስት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ተቋርጦ የነበረውን የጣና በለስ አየር ማረፊያ በአዲስ መልክ ለማስጀመር በኢትዮጵያዊው ባለሃብት አቶ ወርቁ አይተነው እየተከናወነ ይገኛል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉሚያዚያ 4 ፣ 2012 ...
12/04/2020

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ሚያዚያ 4 ፣ 2012 ዓ.ም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በክልላችን ብሎም በመላው ዓለም እንዲሁም በኢትዮጵያ ለምትገኙና የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ የምታከብሩ ክርስቲያኖች ሁሉ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ” ብለዋል።

"በኮቪድ19 ወረርሽኝ የተነሣ በአካል መራራቅ ቢያጋጥምም፣ በመንፈስ አንድ ሆናችሁ ይህን በዓል ስታከብሩ፣ ብርታት እና መጽናናት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" ሲሉም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ምንጭ፡- https://www.facebook.com/ASHADLIHASEN/

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉሚያዚያ 4 ፣ 2012  ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የትን...
12/04/2020

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

ሚያዚያ 4 ፣ 2012 ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በመልዕክታቸው “በመላው ዓለም እንዲሁም በኢትዮጵያ ለምትገኙና የትንሣኤን በዓል በጎርጎርዮሳውያኑ የቀን አቆጣጠር ዛሬ የምታከብሩ ክርስቲያኖች ሁሉ መልካም የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ” ብለዋል።

"በኮቪድ19 ወረርሽኝ የተነሣ በአካል መራራቅ ቢያጋጥምም፣ በመንፈስ አንድ ሆናችሁ ይህን በዓል ስታከብሩ፣ ብርታት እና መጽናናት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" ሲሉም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

12/04/2020
============= ነፃ የጥቆማ ስልክ===============የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ ስለ ኮሮና ቫይረስ ነፃ የጥቆማ ስልክ  6016 መሆኑን አስታወቀ፡፡ስለ ኮሮ...
27/03/2020

============= ነፃ የጥቆማ ስልክ===============

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ ስለ ኮሮና ቫይረስ ነፃ የጥቆማ ስልክ 6016 መሆኑን አስታወቀ፡፡

ስለ ኮሮና ቫይረስ የሚያጠራጥር ማንኛውንም አይነት መረጃ በመጠየቅ ስለ ቫይረሱ በቂ መረጃ ኖሮን ለዜጎች ሠላምና ጤንነት የበኩላችንን እንወጣ፡፡

ማሳሰቢያ በዚህ የነፃ ስልክ ሲደውሉ ምንም አይነት ወጪ እንደሌለው ይወቁ፡፡ ለሌሎችም ያጋሩ

ምንጭ፡- ለብልፅግና አቶ አሻድሊ ሃሰን ደጋፊዎች أنصار السيد أسدلي حسن

አጫጭር መረጃዎች ኢትዮጵያ፦የሳምንቱ  በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ በኢትዮጵያ የተነገሩ መረጃዎች👉በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው International Community School (ICS) ከነገ ጀምሮ...
24/03/2020

አጫጭር መረጃዎች ኢትዮጵያ፦
የሳምንቱ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ በኢትዮጵያ የተነገሩ መረጃዎች

👉በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው International Community School (ICS) ከነገ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 11 ትምህርት ቤቱን በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት እንደሚዘጋ አስታውቋል።

👉የኮሮና ቫይረስ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል ትክክለኛውን መረጃ በመጠቀም ረገድ ከመንግስት ተቋማትና ግል ማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ጋር ውይይት ተደርጓል።

👉የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ከኢትዮዽያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ቤተ እምነቶች ጋር ምክክር አድርጓል።

👉የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ባለሙያዎች ለማሰልጠን፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለሟሟላት እና ለህክምና ማዕከላት የሚውል 30 ሚሊዮን ብር አፅድቋል።

👉ዛሬ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓለም የጤና ወረርሽኝ በሆነው የኮሮና ቫይረስ ላይ ምክክር አድርጓል። ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ዶክተር ኤባ አባተ በወቅታዊ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ ቫይረሱ እንዳይገባ እያደረገች ባለው ቅድመ ጥንቃቄ ዙሪያ ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

 #ኮሮና ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ተረጋግጧል።አሁን ከመደናገጥ  #መፍትሄውን እንወቅ።ይኼን መረጃ ለቤተሰብ፣ለጓደኛ፣ለዘመድ አዝማድ   and post በማድረግ አሳውቁ።*የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች...
15/03/2020

#ኮሮና ኢትዮጵያ ውስጥ መግባቱ ተረጋግጧል።አሁን ከመደናገጥ #መፍትሄውን እንወቅ።ይኼን መረጃ ለቤተሰብ፣ለጓደኛ፣ለዘመድ አዝማድ and post በማድረግ አሳውቁ።

*የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች በዋናነት 3 ናቸው።

1. ትኩሳት
2. የመተንፈስ ችግር
3. ሳል

*ኮሮና ቫይረስ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን
ሙቀት መቋቋም አይችልም።ስለዚህ

#ሻይ
#ሾርባ
#ትኩሳ ውሃ
#ስቲም...በየቀኑ በመጠቀም ቫይረሱን መገደብ እንችላለን።

*የቀዘቀዘ ውሃ፣ፍሪጅ ውስጥ የቀዘቀዘ ምግብ...አይመከርም።በአንጻሩ የፀሐይ ሙቀት በመቀበልና ትኩስ ነገሮችን በመውሰድ መግታት እንችላለን።

*ኮሮና ቫይረስ ከሚተላለፍባቸው መንገዶች መካከል
#ንክኪ ነው።ንክኪዎች፦

1.በሠላምታ
2.ብረትነት ባላቸው አካሎች
3.በልብስና በጨርቅ...ናቸው።

*ብረት ነክ በሆኑ አካሎች ላይ 12 ሰዓት ሊቆይ ይችላል።
*በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊቆይ ይችላል።

*ስለዚህም እጃችን በደምብ በሳሙና መታጠብ
*ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች በየቀኑ ማጠብ እና ፀሐይ ላይ ማስጣት ቫይረሱን እንዲሞት ያደርገዋል።

*የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች

1. ትኩሳት
2. የመተንፈስ ችግር
3. ሳል ሲሆኑ

ለበለጠ መረጃ 8335 ደውላችሁ መረጃ መጠየቅ ትችላላችሁ!! #ሼር

ወንዶች_ሆይመልክ ትዳር አይሆንም የተስተካከ ተክለ ሰውነቷ ቤትህን አያቆመውም፣ያትልቅ መቀመጫዋ ለቤትህ ሶፍ አይሆንህም ልብ በል ትዳር ማለት የህይወትን ጣዕም የምታውቅበት የምትደጋገፍበት በሳ...
15/03/2020

ወንዶች_ሆይ

መልክ ትዳር አይሆንም የተስተካከ ተክለ ሰውነቷ ቤትህን አያቆመውም፣ያትልቅ መቀመጫዋ ለቤትህ ሶፍ አይሆንህም ልብ በል ትዳር ማለት የህይወትን ጣዕም የምታውቅበት የምትደጋገፍበት በሳል የምትሆንበት አባት የምትሆንበት ከብቸኛነት ወተህ ሁለተኛ እናት የምታገኛበት፣ሀሳብህን የምትጋራልህ፣መፍትሄ የምስጥህ የህይወትህ ማጣፈጫ ደስታን የምሰጥህ ሴት ከፈለክ መልኳን ሳይሆን ከአስተሳሰቧ፣ከአለባበሷ ሳይሆን ከፈጣሪ ፈሪነቷ፣ ልብ ብለህ እያት በአሁኑ ስአት ፈጣሪዋን የምትፈራ ሴት ማገኛት መታደል ነውና ።

መልኳን ሳይሆን ለአንተ ያላትን አመለካከት አስብ ለዘላለም አብሮህ የሚኖርው ልቧ ላይ ያለው ላንተ ያላት ፍቅር እንጂ መልኳ አይደለም
ወንድሜ ሆይ ለህይወትህ ስኬትን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን ልብህ ያርፈባትን ሴት አግባ አይን ቀለዋጭ ነው ብዙ ያምርዋልና ልብህን አዳምጥ።

ያንተሚስት ላተ ብቻ ቆንጆና ውብ ናት ያንተ ሚስት ላተ ንግስት ናአት ወንድሜ ሆይ ሚስትህን ከማንም ጋር አተወዳድራት እራስን ሆኖ መኖር ጥበብ ነው እንደራስ መኖር ብስለት ነው ። ህይወትህን ከማንምጋር አተወዳድር ( ትዳርህን) እንደራስህ ሆነክ ከኖርክ እራስህን ከማንም ጋር ሳይሆን ከርስ ጋር ካወዳደርከው በህይወትህ ደስተኛ ነው የምትሆነ።

መልክ ትዳር አይሆንም ጎጆን አያቆምም ፈጣሪዋን ፈሪ ትዳሯን አክባሪ ታዛዥ ሚስት ከፈለክ አተም ፈጣሪህን ፈሪ ሁን ፈጣሪን የሚፈራ ፍቅርን ያውቃልና ለሁላችንም ፈጣሪውን የሚፈራ የተባርከና የተቀደሰ ፍቅርና ትዳር ይስጠን

"አምላክ ያገናኛውን ማንም አይለየውም"።

እስኪ ይህችን መፈክር (መሪ ቃል) መቼ እና ለምን ክብረ በዓል ነበር የተጠቀምናት መልስዎን ሲሰጡ በኢትዮጵያዊነትዎ እርግጠኛ መሆነዎን እንዳይዘነጉ፡፡ ምክንያቱም  ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ዘረኛ ...
23/12/2019

እስኪ ይህችን መፈክር (መሪ ቃል) መቼ እና ለምን ክብረ በዓል ነበር የተጠቀምናት

መልስዎን ሲሰጡ በኢትዮጵያዊነትዎ እርግጠኛ መሆነዎን እንዳይዘነጉ፡፡ ምክንያቱም ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ዘረኛ ወይም ብሄርተኛ አይደለምና ነው፡፡

እኔ ግን ጥርት ያልኩኝ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ሀቁ ይህንን መሪ ቃል ለምን ክብረ በዓል እንደተጠቀምንበት በደንብ አውቀዋለሁ፡፡

“ትልቅ ነበርን ትልቅም እንሆናለን “

እስኪ ይሞክሩ ይመልሱ ይሸለሙ

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ International Crisis Group የተሰዉ ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም የባላአደራዎች ቦርድ አባል ሆነዉ ተሾሙ።የግጭት ምክንያ...
18/12/2019

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ International Crisis Group የተሰዉ ዓለም አቀፍ አጥኚ ተቋም የባላአደራዎች ቦርድ አባል ሆነዉ ተሾሙ።

የግጭት ምክንያቶችን እና መከላከያዎችን የሚያጠናና መፍትሔዎችን የሚጠቁመዉ አጥኚ ተቋም እንዳስታወቀዉ ከቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በተጨማሪ፣ የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝደንትና የሕብረቱ የዉጪ ግንኙነት ኃላፊን ፍደሪካ ሞግሔረኒ የቦርዱ አባል ሆነዉ ተሾመዋል።

አጥኚዉ ተቋም እንዳለዉ ሁለቱ ፖለቲከኞች የዓለም አቀፉን ተቋም መርሕ፣ ሥራና አሰራርን የሚወስነዉ ከተፍኛ አካል አባላት ሆነዉ የተሾሙት ከዚሕ ቀደም በነበራችዉ የዳበረ ፖለቲካዊ ልምድ ነዉ።አጥኚዉ ተቋም አክሎ እንዳለዉ ኢትዮጵያዊዉና ኢጣሊያዊቱን ፖለቲከኛና ዲፕሎማቶች ለከፍተኛዉ ሥልጣን የሾመዉ ተቋሙ ለብዝሐነት የቆመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነዉ።

አቶ ኃይለማርያም እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2012 እስከ 2018 ድረስ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በነበሩበት ወቅት የአፍሪቃ ሕብረትንና ኢጋድን በሊቀመንበርነት መርተዋል።ኢጣሊያዊቱ ዲፕሎማት ደግሞ ከ2014-እስከ 2019 የዘለቀዉን አዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ምክንትል ፕሬዝደንትና የዉጪ ግንኙነት ኃላፊነትን ሥልጣን ከመያዛቸዉ በፊት ላጭር ጊዜ የኢጣሊያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነዉ አገልግለዋል።

የCrisis Group ፕሬዝደንትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሮበርት ሜሌይ እንዳሉት ድርጅታቸዉ ደም አፋሳሽ ግጭቶችን ለመከላከል በሚያደርገዉ ጥረት ከሁለቱ አዳዲስ ተሿሚዎች ጋር በቅርብ ተባብሮ እንደሚሰራ ተስፋ አላቸዉ።ሜሌይ የሚያስተዳድሩት ተቋም እነ አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ 47 የቦርድ አባላት አሉት።

በኢትዮጵያ ላለፉት 18 አመታት ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ይሰጥ የነበረው የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፈተና ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ መቅረቱን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ...
18/12/2019

በኢትዮጵያ ላለፉት 18 አመታት ለ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ይሰጥ የነበረው የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፈተና ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ መቅረቱን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረ እግዚአብሔር እንደገለፁት ይህ የተወሰነው አዲስ በተዘጋጀው የትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ በቀረበው ሃሳብ መሠረት ነው።

በዚሁ መሠረትም ዘንድሮ ለስምንተኛ ክፍልም በተለመዱ የትምህርት አይነቶች አጠቃላይ ፈተና እንደሚኖርም ገልጸዋል። ፈተናው ተመሳሳይ እና ተመጣጣኝ እንዲሆን የጋራ ምክክር መኖሩንም አስታውቀዋል።

ትምህርትን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናቶች መካሄዳቸውን እና ጥናቱን መሠረት በማድረግም የተዘጋጀ ፍኖተ ካርታ መኖሩን ያመለከቱት የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሩ ፈተናዎቹ በየደረጃው ተማሪዎቹ የተማሯቸውን ትምህርቶች ላይ በማተኮር አስፈላጊ ሂደቶችን ተከትሎ እንደሚዘጋጁ አስረድተዋል። ጥናቶቹ ሰፊ እንደመሆናቸውም በየጊዜ የሚታዩ ለውጦት እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።

የ10ኛ ክፍል ፈተና መቅረቱን ቀደም ብለው የትምህርት ሚኒስትሩም ይፋ ማድረጋቸውን ያስታወሱት የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር፤ በተለያዩ ምክንያቶች የመረጃ ክፍተት በተፈጠረባቸው አንዳንድ ቦታዎች የፈተና ዝግጅትን አስመልክቶ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ተከትሎ ፈተናው 12ኛ ክፍል ላይ መሆኑ አፅንኦት እንዲሰጥ መነገሩንም አብረው ገልጸዋል።

አሳሳቢዉ የመተከል ፀጥታ ሁኔታ   በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ አራት ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በዳንጉር እና ማንዱራ ወረዳዎች ...
17/12/2019

አሳሳቢዉ የመተከል ፀጥታ ሁኔታ

በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ አራት ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በዳንጉር እና ማንዱራ ወረዳዎች ከባለፈው ሚያዚያ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ በተከሰቱት ግጭቶች ምክንያት በጊዘያዊ ኮማንድ ፖስት መጠበቅ ከጀመሩ አምስት ወራትን አስቆጥሯል፡፡

ቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ አራት ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ ጃራ ዛሬ እንደተናገሩት ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ በዳንጉር ወረዳ አይፖፖ በተባለ ስፋራ ባልታወቁ ሰዎች አንድ ግለሰብ መገደሉን ተከትሎ በምቡክ ከተማ ዙሪያ በተከሰተዉ ጥቃት ሌሎች ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። የድርጊቱ ፍጻሚዎች ማንነት እስካሁን አልታወቀም ተብሎአል።

የፀጥታ ችግር አለባቸው ተብሎ በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ከሚጠበቁት ወረዳዎች ውስጥ አንዷ የሆነቸው ዳንጉር ወረዳ ባለፈው ዓመት በተለያየ ጊዜያት በተከሰቱት ተደጋጋሚ ግጭቶች የበርካታ የሰው ህይወት ማለፉ የሚታወስ ነዉ። ከሰሞኑም በወረዳዋ አንድ ቀበሌ እና ማንቡክ ከተማ በደረሰው ጥቃት የሰው ህይወት ማለፍን የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁ የሚታወቅ ነዉ። የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ጃራ እንደተናገሩት ባልታወቁ ሰዎች በዳንጉር ወረዳ በደረሰው ጥቃት የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከትናንት በስቲያ በዳንጉር አይፖፖ በተባለ ስፋራ አንድ ሰው መገደሉን ተከትሎ ወደ ወረዳዋ ከተማ ማምቡክ በመዛመት በሦስት ሰዎች ላይ በደረሰው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፍን ነው ኃላፈው የተናገሩት። በድርጊቱ የተሳተፍ ግለሶቦች ለጊዜ አለመታወቃቸውን የገለጹት አቶ ነጋ በሌሎች ወረዳዎች ግጭት እንዳይፈጠር ተጨማሪ የጸጥታ ሀይሎች ወደ ስፋራው መላካቸውን ገልጸዋል፡፡ የመተከል ዞን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ ከአካባቢው ማህረሰብ ጋር በመሆን ክትትል እያረደረገ ነው ብለዋል።

በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ለማድረግና ከዚህ ቀደም በዚው አካባቢው የነበረውን የጸጥታ መደፍረስ ለመቅረፍ ሁለቱ ክልሎች የአካባውን ማህረሰብ ከማቀራረብና በልማት ከማስተሰሰር ጀምሮ ወንጀለኞችን በጋራ ወደ ህግ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በዳንጉር የታጠቁ ኃይሎች መኖራቸውንም የጠቀሱት አቶ ነጋ በተለያዩ ጊዜያት ጥቃት በመፈጸም በኅብረሰተቡ መካከል መልካም ግንኙት እንዳይኖር ለማድፈግ ይሰራሉም ብለዋል። በዳንጉር እና ማንዱራ ወረዳዎች ከባለፈው ሚያዚያ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ በተከሰቱት ግጭቶች ምክንያት በጊዘያዊ ኮማንድ ፖስት መጠበቅ ከጀመሩ አምስት ወራትን አስቆጥሯል፡፡

ምንጭ፡- https://www.facebook.com/sharer/sharer.php?u=https%3A%2F%2Fp.dw.com%2Fp%2F3Uu8a%3Ffb

17/12/2019

እስኪ ሚስጢር ምንድነው ? ሚስጢርስ የሚያገለግለው ለማን እና መቼ ነው ? እኔ ግን ለረጅም ወራት የጠፋሁት ሚስጢር አለው፡፡

ምክር ቤቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ይወያያልጥቅምት 10፣ 2012 ዓ.ም የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል።ምክር ቤቱ ነ...
21/10/2019

ምክር ቤቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ይወያያል

ጥቅምት 10፣ 2012 ዓ.ም የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው ጉባዔው ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ይወያያል።

በጉባኤው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ላይ የቀረበ የድጋፍ ሞሽን የሚያጸድቅ ይሆናል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እንደሚሰጡም ይጠበቃል።

የነጥብ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናትየደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ-------------------------------------ትርጉም1. «የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ» ማለት የአንድን ...
18/10/2019

የነጥብ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት
የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ
-------------------------------------
ትርጉም
1. «የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ» ማለት የአንድን ሠራተኛ ደመወዝ ወደ አዲሱ የደመወዝ ስኬል ለማሸጋገር ሲባል ቅርበቱ እየታየ የነበረውን ደመወዝ እንደሁኔታው ወደ አዲሱ የደመወዝ ስኬል የመነሻ፣ የእርከን ወይም የጣሪያ ደመወዝ ላይ ለማሳረፍ የሚፈቅድ የደመወዝ ማስተካከያ ነው።
2. የመሸጋገሪያ ደመወዝ» ማለት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 3 (ለ) መሠረት አንድ ሠራተኛ በደመወዝ ስኬል ሽግግሩ የሚያገኘውን የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ መጠን ለሶስት በማካፈል መደበኛ ደመወዙ ላይ ጨምሮ እስከ ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. ድረስ የሚከፈል ደመወዝ ነው፡፡

የመመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን
-----------------------------
ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረገው የሥራ መደቦቻቸው በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ ተመዝነው ደረጃ በወጣላቸው የሥራ መደቦች ላይ ለተደለደሉ ሠራተኞች ብቻ ነው፡፡

ልዩ ልዩ ውሳኔዎች
-----------------------
1) በሥራ ላይ የሚውለው የደመወዝ ስኬል
የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት እና የመንግስት የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ ገብቶ የተቀረጸውና በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተወሰነውና በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በፀደቀው መሰረት የደመወዝ ስኬል በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተግባራዊ ይሆናል፡፡ /የዚህ መመሪያ አባሪ ሆኖ ተያይዟል፡፡

2) ወደፊት ልዩ የደመወዝ ስኬል የማይፈቀድ ስለመሆኑ
የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ መተግበርን ተከትሎ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያሉ የደመወዝ ስኬሎችን ወደ አንድ የማሰባሰብ ተግባርና ሥርዓቱ ዘላቂነት ባለው ሁኔታ ጸንቶ መጠበቅ ስላለበት መንግሥት አገር አቀፍ የደመወዝ ስኬል መዘርጋት ሥርዓትን የልዩ የደመወዝ ስኬል ይፈቀድልኝ የሚሸረሽር ጥያቄን የማያስተናግድ ስለመሆኑ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የተላለፈው ውሳኔ የጸና ሆኖ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

3) ተጨማሪ ወጪውን በሶስት የበጀት ዓመታት ስለመሸፈን
 ከነባሩ የሥራዎች ምዘና ስርዓት ወደ ነጥብ የሥራዎች ምዘና ዘዴ የሚደረገው ሽግግር ዓላማ ለሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ወይም ጭማሪ ማድረግ አይደለም፡፡ ሆኖም ሽግግሩ በአንዳንድ የሥራ መደቦች ላይ የደመወዝ ለውጥ ስለሚያስከትል በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ የሚኖረውን የወጪ ጫና ከአስተዳደሩ የመክፈል አቅም ጋር ተገናዝቦ በመቋቋም የደመወዝ ስኬል ሽግግሩን ቀለል ባለ መንገድ ለመፈጸም ዝርዝር የአከፋፈል ሁኔታው፡-

ሀ) በተደለደሉበት የሥራ መደብ ብር 1,000 እና ከዚህ በታች የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ የሚያገኙ ሠራተኞች ሙሉ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያውን በአንድ ጊዜ እንዲያገኙ፣
ለ) ከብር 1,000 በላይ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ የሚያገኙ ሠራተኞች ልዩነቱን በሶስት እኩል ክፍያዎች እንዲጠናቀቅላቸው ይደረጋል፡፡

በዚህ ጥናት ያልተካተተ ተቋም
----------------------------

የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን ከደመወዝ ስኬል ሽግግር ውሳኔ በፊት ተፈቅዶላቸው በነበረው የደመወዝ ስኬል እየተጠቀሙ ይቆያሉ፡፡ ሆኖም ይህ የሽግግር ጊዜ የደመወዝ ስኬል በመንግሥት ውሳኔ መሠረት ወደፊት ሲሻሻል የተቋሙ የደመወዝ ስኬል የሚካተት ሆኖ ሲገኝ የተቋሙ የደመወዝ ስኬል እንደሌሎቹ የከተማው አስተዳደር ተቋማት በሀገር አቀፉ የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ስኬል ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡

 ከነባሩ የሥራዎች ምዘና ሥርዓት ወደ ነጥብ የሥራዎች ምዘና ዘዴ የሚደረገውን የደመወዝ ስኬል ሽግግር አፈጻጸም ከዚህ በታች በተመለከተው መሠረት ይሆናል፡፡
 የነባር የሥራ መደብ መጠሪያና ደረጃ በአዲስ መጠሪያና ደረጃ መቀየሩን የሚያረጋገጥ የመሸጋገሪያ ሠንጠረዥ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጸድቆ ያልደረሰው ተቋም የሠራተኛ ድልድል መፈጸምም ሆነ የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ አይችልም፡፡

 በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ በተመዘኑ የሥራ መደቦች ላይ የመጀመሪያ ድልድል ከተፈጸመ በኋላ በተካሄደ የአደረጃጀት ለውጥ ወይም ሌላ ምክንያት ዳግም መመዘን ባለበት የሥራ መደብ ላይ የተደለደለ ሠራተኛ ክፍያውን እንዲያገኝ የሚደረገው በቅድሚያ የሥራ መደቡ ምዘና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከጸደቀ በኋላ ነው፡፡

o የነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ የመንግስት ሠራተኞች ድልድል አፈጻጸም መመሪያ የሚጠይቀውን መስፈርት ማሟላታቸው ተረጋግጦ ድልድል የጸደቀላቸው ሠራተኞች፡-
ሀ) የመደበኛ የደመወዝ ጭማሪ ኡደት አይለወጥም፣
ለ) ለደረጃ እድገት የአንድ ዓመት መቆያ ጊዜ አይጠበቅበትም፣

o ከነባሩ የሥራዎች ምዘና ዘዴ ወደ ነጥብ የሥራዎች ምዘና የሚደረገውን ሽግግር ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገ የሠራተኞች ድልድል ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ በእንደገና ምደባ ከፍ ብሎ ከተመደበ የሥራ መደቡን የያዘው ሠራተኛ መስፈርቱን እስካሟላ ድረስ የሥራ መደቡ የሚያስገኘውን ደረጃና ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
o ከፍ ባለ የሥራ ደረጃ ላይ በተጠባባቂነት የተመደበ ሠራተኛ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ልዩነት የሚታሰብለት በድልድሉ በተመደበበት ደረጃ ላይ ነው፡፡
o በጥር ወር 2009 ዓ.ም. ተሻሽሎ በሥራ ላይ በዋለው የደመወዝ ስኬል ጣሪያ ላይ የደረሰና በአዲሱ የደመወዝ ስኬል ጣሪያው የሚነሳለት ሠራተኛ በተመደበበት የሥራ ደረጃ የአዲሱን የደመወዝ ስኬል ጣሪያ ሳያልፍ ማስተካከያውን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

 አንድ ሠራተኛ የሚከፈለው ደመወዝ በደመወዝ ስኬሉ ለተደለደለበት የሥራ መደብ ከተወሰነው የመነሻ ደመወዝ በታች ከሆነ፤ የሠራተኛው ደመወዝ ወደ መነሻ ደመወዝ ከፍ እንዲል ይደረጋል።
 የሠራተኛው ደመወዝ ከመነሻ በላይ ሆኖ፤ በመነሻና በአንደኛው የእርከን ደመወዝ መካከል ወይም በሁለት የእርከን ደመወዞች መካከል ከሆነ በአቅራቢያው ወደ አለው ከፍ ያለ የእርከን ደመወዝ ይስተካከላል።
 የሠራተኛው ደመወዝ ከደመወዝ ስኬሉ የመነሻ፣ የእርከን ወይም የጣሪያ ደመወዝ ጋር ከገጠመ ወይም ከጣሪያ በላይ ከሆነ የያዘውን ደመወዝ እንደያዘ ይቀጥላል።
 ቢሮው በአንድ ተቋም ከተፈጸሙ የሠራተኞች ድልድል መካከል በተለያዩ ሕግን ባልተከተሉ አሠራሮች ምክንያት ያልተቀበለው ካለ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ጭማሪው የሚሰጠው በድልድል አፈጻጸም መመሪያው መሠረት ሠራተኛው በሚያሟላበት ደረጃ ከተደለደለ በኋላ ነው፡፡

o ከፍ ካለ የሥራ ደረጃ ላይ በሚታሰብ ደመወዝ ተቀጥሮ እየተቀነሰ የሚከፈለው ሠራተኛ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ተጠቃሚ የሚሆነው በሚያሟላበት ደረጃ ላይ ተመሥርቶ ይሆናል፡፡
o በሙከራ ቅጥር ላይ የሚገኝ ሠራተኛ የዚህ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
o በዲሲፕሊን ጉድለት ምክንያት ከደረጃው ዝቅ ያለና ደመወዙ የተቀነሰበት ሠራተኛ ማስተካከያው የሚሰጠው በተቀነሰው ደረጃና ደመወዝ ላይ ታስቦ ነው፡፡ ሆኖም በተወሰነ የጊዜ ገደብ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ የተደረገ ሠራተኛ የጊዜ ገደቡ ደርሶ ወደ ቀድሞ ደረጃው ሲመለስ ከተመለሰበት ጊዜ ጀምሮ በአዲሱ የደመወዝ ስኬል ተገቢው ደመወዝ ይሰጠዋል፡፡

ልዩ ፈቃድ ተሰጥቶት በፕሮጀክት የአፈፃፀም መመሪያ መሠረት ወደ ፕሮጀክት የተዛወረ ሠራተኛ፡-
---------------------------------------
ሀ) መደበኛ ደመወዙ በነበረበት መሥሪያ ቤት የሚከፈለው ከሆነ ወደ ፕሮጀክት ከመዛወሩ በፊት የነበረ መደበኛ ደመወዙን መሠረት በማድረግ ለተደለደለበት የሥራ መደብ/ደረጃ/ የተወሰነው አዲሱ ደመወዝ ተጠቃሚ ይሆናል።
ለ) ደመወዙ ከፕሮጀክቱ እየተከፈለው የሚሠራ ከሆነ ወደ መደበኛ ሥራው ሲመለስ ለሚደለደልበት የሥራ መደብ/ደረጃ/ የተወሰነው አዲሱ ደመወዝ ተጠቃሚ ይሆናል።

 ይህ የደመወዝ ስኬል ማስተካከያ ጊዜያዊ ወይም የኮንትራት ሠራተኛን አይመለከትም፡፡ ሆኖም በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ ተመዝኖ ደረጃ በወጣለት ቋሚ የሥራ መደብ ላይ መመሪያውን ተከትሎ የተቀጠረ ጊዜያዊ ወይም የኮንትራት ሠራተኛ የደመወዝ ማስተካከያው ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
 በተለያዩ ምክንያቶች ከመደበኛ ሥራው ተለይቶ የቆየ ሠራተኛ ወደ ሥራው እንዲመለስ ሲደረግ በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ ተመዝኖ ደረጃ በወጣለት የሥራ መደብ ላይ እንዲመደብ ከተደረገ በኋላ ደመወዙ ወደ አዲሱ የደመወዝ ስኬል እንዲሸጋገር ይደረጋል፡፡
 ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከወጣበት ቀን ድረስ ከሥራ የለቀቀ ሠራተኛ ከሥራ እስከተለየበት ቀን ድረስ ያለው ደመወዙ በአዲሱ የደመወዝ ስኬል መሠረት ተሰልቶ ይከፈለዋል፡፡
 ከሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም. እስከ መስከረም ወር 2012 ዓ.ም. በሞት የተለየ ሠራተኛ በሞተበት ወር ደመወዙ በአዲሱ የደመወዝ ስኬል መሠረት ተሰልቶ ለወራሾቹ ይከፈላል፡፡

 ከሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከወጣበት ቀን ድረስ በሞት የተለየ ሠራተኛ ከብር 1000 በላይ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ልዩነት የሚያገኝ በመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 አንቀጽ 90 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የተመደበበት ደረጃ ሙሉ የሶስት ወር ደመወዝ በአንድ ጊዜ ለወራሾቹ ይከፈላል፡፡
 መሥሪያ ቤቱ ባወቀው በማናቸውም ምክንያት በድልድል ወቅት ሥራ ላይ ባለመኖሩ ያልተደለደለ ሠራተኛ ቅድሚያ በሥራ ላይ ባሉ መመሪያዎች መሠረት ወደ ምድብ ሥራው እንዲመለስ ሲደረግ፣ በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ ተመዝኖ ደረጃ በወጣለት ሥራ መደብ ላይ እንዲመደብ በማድረግ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

 “አንድ ሠራተኛ ለአንድ የሥራ መደብ የተቀመጠውን የሥራ ልምድ ለማሟላት እስከ አንድ ዓመት ከጐደለው እና ለሥራ መደቡ የተቀመጠውን የተፈላጊ ችሎታ የሚያሟላ ሌላ ሠራተኛ ከሌለ ሠራተኛውን ደልድሎ ማሠራት ይቻላል፡፡” በሚለው መሠረት ለተደለደለበት ደረጃ እስከ አንድ ዓመት የሚጎድለው ሠራተኛ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ጭማሪ ተጠቃሚ የሚሆነው የተደለደለበት የሥራ መደብ የሚጠይቀውን ቀሪ የሥራ ልምድ ሲያሟላ ነው፡፡

 በሥራው ልዩ ባህርይ ምክንያት እያስተማረ የህክምና አገልግሎት የሚያበረክት የጤና ባለሙያ የማስተማር ሥራው እንደተጠበቀ ሆኖ እንደሁኔታው በአካዳሚክ ወይም በጤና ሙያ /ከፍ ባለው/ ደረጃ ላይ ተደልድሎ ሊሠራ ይችላል፡፡
 በነባሩ የጤና ባለሙያዎች የእድገት መሰላል በሙያው የመጨረሻ የእድገት ተዋረድ ላይ ደርሰው ከነበሩ ሙያተኞች መካከል በያዙት ሙያ ከ10 ዓመት በላይ አገልግሎት ያለው ወይም ከጀማሪ ስፔሻሊስቶች በስተቀር በቀድሞው ምደባ ፕሣ-6/1 ደረጃ ላይ ደርሶ በሙያው አንድ ዓመትና በላይ በማገልገል ቢያንስ 11 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው የጤና ባለሙያ በአዲሱ የሙያው እድገት መሰላል የመጨረሻው ተዋረድ/ተዋረድ IV/ ላይ ተመድቦ በደረጃው 3ኛ እርከን ላይ የተመለከተውን ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

 የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ባለሙያዎች፣ የቴክኒካል ረዳቶች፣ ተመራማሪዎች፣ መደበኛ መምህራን፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሰልጣኞች፣ ኢንስትራክተሮች እና ሌሎች ለካርየር ዕድገት በተዘጋጁ ልዩ መስፈርቶች ይጠቀሙ በነበሩ ተቋማት ያሉ ሙያተኞቻቸው በነበሩበት ደረጃ ያለውድድር ከተደለደሉ በኋላ ወደ ቀጣዩ የእድገት መሰላል የሚሸጋገሩት ለደረጃው የተቀመጡ ነባር መስፈርቶችን ሲያሟሉ ነው፡፡

 የኮሌጅ የትምህርት ደረጃና በታች የትምህርት ዝግጅት በሚጠይቁ የሥራ መደቦች ላይ የሥራ መደቡ የሚጠይቀው የትምህርት ደረጃ ሳይኖረው በልዩ ሁኔታ ለአንድ ጊዜ እንዲደለደሉ ጳጉሜን 2 ቀን 2009 ዓ.ም. በቁጥር ፐሰሚ/30/ጠ10/91/17 በተጻፈ ደብዳቤ ሸኝነት በተላከው ሰርኩላር መሠረት የተደለደለ ሠራተኛ የተመደበበት ደረጃ የሚያስገኘውን የመሸጋገሪያ ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
 ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ከደረጃ I እስከ ደረጃ V ሠልጥነው የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ሳይኖረው ባለው የትምህርት ምስክር ወረቀት ለአንድ ጊዜ የተደለደለ ሠራተኛ የተመደበበት ደረጃ የሚያስገኝለትን የመሸጋገሪያ ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

 በደመወዝ ስኬል ሽግግር የሚያገኘው የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ መጠን ለሶስት ተካፍሎ የመሸጋገሪያ ደመወዝ እንዲከፈለው የተደረገ ሠራተኛ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. ድረስ ከደመወዙ ላይ ታክስ የሚቀነሰው ለበጀት ዓመቱ ከተፈቀደለት የመሸጋገሪያ ደመወዝ ላይ ነው፡፡

 ከ2012 እስከ 2014 የበጀት ዓመቶች ባለው ጊዜ ውስጥ በጡረታ ከሥራ ከሚገለሉ ሠራተኞች መካከል፡-
ሀ) ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በጡረታ ከሥራ የሚለይ ሠራተኛ ወደ አዲሱ የደመወዝ ስኬል ሲሸጋገር ሙሉ የደመወዝ መሸጋገሪያውን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
ለ) ከሐምሌ1 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በጡረታ ከሥራ የሚለይ ሠራተኛ ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ለተመደበበት ደረጃ የተወሰነውን የደመወዝ መሸጋገሪያ በዚህ መመሪያ ከተከፈለው በኋላ የ2013 የበጀት ዓመት ሙሉ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያውን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

ከላይ የተመለከተው የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ ዕድሜው 60 ዓመት ሳይሞላው በፈቃዱ በጡረታ ከሥራ የሚለይ ሠራተኛን አይመለከትም፡፡
የደረጃ ዕድገት የሚያገኙ ሠራተኞችን እና አዲስ ተቀጣሪን በሚመለከት፡-
 የነጥብ የሥራ ምዘና ሥርዓት ከክፍያ ጋር ከተሳሰረ በኋላ በቀጣይ ሙሉ ክፍያውን በሶስት እኩል መጠን እንዲከፈለው የተደረገ ሠራተኛ በያዘው ደረጃ ላይ ሌላ ሠራተኛ በደረጃ ዕድገት ወይም በቅጥር በአዲሱ የደመወዝ ስኬል ላይ ሲመደብ፣ የደመወዝ ስኬሉ ማስተካከያው ደረጃ በደረጃ እንዲከፈላቸው ከተደረጉ ሌሎች ነባር ሠራተኞች የክፍያ መጠን መብለጥ ስለሌለበት፡-

o የደረጃ ዕድገት የሚያገኙ ሠራተኞችን በሚመለከት፡-
-------------------------------------
• ይህ የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ አፈጻጸም መመሪያ ከጸደቀበት ወር ቀጥሎ እስከ ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. ድረስ የደረጃ ዕድገት ካገኙ ሠራተኞች መካከል በደረጃ ዕድገት ስም ያገኘው የገንዘብ መጠን፡-
• ሀ) እስከ ብር 1000 ከሆነ ሠራተኛው የደመወዝ ልዩነቱን የደረጃ ዕድገት ካገኘበት ወር መጀመሪያ ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
• ለ) ከብር 1000 በላይ ሆኖ በ2012 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የደረጃ ዕድገት ካገኘ የደረጃ ዕድገት የደመወዝ ልዩነቱን ለሶስት በማካፈል ወጤቱን እየተከፈለው ባለው የወር ደመወዝ ላይ፡-
• ካደገበት ወር እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም. ድረስ 1/3ኛ፣
• ከሀምሌ ወር 2012 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. ሁለተኛውን 1/3 እና
• ከሀምሌ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የመጨረሻውን 1/3ኛ፣
 የደመወዝ ማስተካከያ በመጨመር የሠራተኛው ደመወዝ እንደሁኔታው ወደ ተመደበበት ደረጃ የመነሻ ወይም የእርከን ደመወዝ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል፡፡
 ከብር 1000 በላይ ሆኖ በ2013 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የደረጃ ዕድገት ካገኘ የደረጃ ዕድገት የደመወዝ ልዩነቱን ለሁለት በማካፈል ወጤቱን እየተከፈለው ባለው የወር ደመወዝ ላይ፡-

• ካደገበት ወር እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. ድረስ ½ኛ የደረጃ እድገት ልዩነቱን በመጨመር እና
• ከሀምሌ ወር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የመጨረሻውን ½ኛ የደረጃ ዕድገት ልዩነቱን በመጨመር፣
 የሠራተኛው ደመወዝ ወደ ተመደበበት ደረጃ የመነሻ ወይም የእርከን ደመወዝ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል፡፡
 ከሀምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የደረጃ ዕድገት የሚያገኝ ሠራተኛ ለሚያድግበት ደረጃ የተወሰነውን የመነሻ ወይም የእርከን ደመወዝ ካደገበት ወር መጀመሪያ ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡

አዲስ ተቀጣሪን በሚመለከት፡-
------------------------------
ይህ መመሪያ ከፀደቀበት ቀን ማግስት ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ፡-
ሀ) ከደረጃ I እስከ ደረጃ VII ባሉ ደረጃዎች የተቀጠረ ሠራተኛ የተቀጠረበትን ደረጃ የመነሻ ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፣

ለ) ከደረጃ VII በላይ ባሉ ደረጃዎች የሚቀጠር ሠራተኛ በተቀጠረበት የሥራ ደረጃና ከተቀጠረበት ደረጃ በአንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ በሚገኝ ደረጃ መካከል ያሉ ሶስት የእርከን ልዩነቶችን በየበጀት ዓመቱ ዝቅ ባለው ደረጃ የመነሻ ደመወዝ ላይ አንድ አንድ እርከን በመጨመር የወር ደመወዝ እንዲከፈለው በማድረግ ከሀምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀጠረበትን ደረጃ የመነሻ ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡›

ምሳሌ 1 የደረጃ XV መነሻ ደመወዝ ብር 10150፣ የደረጃ XIV መነሻ ደመወዝ ደግሞ ብር 9056 ቢሆን፣ እንዲሁም የዚሁ ደረጃ 1ኛ እርከን ደመወዝ ብር 9420፣ የደረጃው የ2ኛ እርከን ደመወዝ ብር 9785 እና የ3ኛው እርከን ደመወዝ ብር 10150 ቢሆን አዲሱ የደመወዝ ስኬል ተግባራዊ ከሆነበት ቀን ማግስት ጀምሮ በደረጃ XV የተቀጠረ ሠራተኛ የተቀጠረበት ደረጃ እንደተጠበቀ ሆኖ፡-
እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም. ድረስ ከተቀጠረበት ደረጃ አንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ በሚገኘው የደረጃ XIV መነሻ ደመወዝ /ብር 9056/ ላይ አንድ እርከን በመጨመር የደረጃው 1ኛ እርከን ደመወዝ የሆነውን ብር 9420፣
በሁለተኛው የበጀት ዓመት /ከሀምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. /የደረጃ XIV 2ኛ እርከን ደመወዝ የሆነውን ብር 9785/፣
በሶስተኛው የበጀት ዓመት /ከሀምሌ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀጠረበት ደረጃ XV የመነሻ ደረጃ የመነሻ ደመወዝ የሆነውን ብር 10150፣እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

ሐ) ከሀምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ የሚቀጠር ሠራተኛ ከተቀጠረበት ደረጃ በአንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ የሚገኝ የሶስት እርከን የገንዘብ መጠንን ለሁለት በማካፈል ከተቀጠረበት ደረጃ በአንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ በሚገኝ የመነሻ ደመወዝ ላይ በመደመር የመጀመሪያው ዙር ደመወዙ በየወሩ የሚከፈለው ሲሆን፣ ከሀምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የቀረውን ገንዘብ በሚከፈለው ደመወዝ ላይ በመጨመር የተቀጠረበትን ደረጃ የመነሻ ደመወዝ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

ምሳሌ 2 ከላይ በምሳሌ አንድ ላይ በተጠቀሰው ደረጃ XV ላይ በ2013 ዓ.ም. የበጀት ዓመት /ከሀምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2ዐ13 ዓ.ም. /የተቀጠረ ሠራተኛ የተቀጠረበት ደረጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተቀጠረበት ደረጃ በአንድ ደረጃ ዝቅ ብሎ በሚገኘው የደረጃ XIV መነሻ ደመወዝን ከደረጃው የ3ኛ እርከን በመቀነስና ልዩነቱን ለሁለት በማካፈል /10150- 9056 = ብር 1094/ ስለሚሆን ብር 1094ን ለሁለት በማካፈል /1094/2/ የተገኘውን ብር 547 ደረጃ XIV መነሻ ደመወዝ በሆነው ብር 9056 ላይ በመደመር ብር /9056 + 547/ ብር 9603 እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም. ድረስ እንዲከፈለው ይደረጋል፡፡
ከሀምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ብር 9603 ላይ ቀሪውን 547 በመጨመር /9603 + 547 = ብር10150/ የሠራተኛው ደመወዝ የተቀጠረበት ደረጃ XV መነሻ ደመወዝ በሆነው ብር 10150 ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል፡፡

መ) ከሀምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የሚቀጠር ሠራተኛ የተቀጠረበትን ደረጃ የመነሻ ደመወዝ ከተቀጠረበት እለት ጀምሮ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ በዚህ መመሪያ ውስጥ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም።

መስከረም 2012 ዓ.ም

All crackers with limited capacity as you sit on the board of directors and team leaders in government institutions.What...
17/10/2019

All crackers with limited capacity as you sit on the board of directors and team leaders in government institutions.

What is Page Transparency ?

አረንጓዴ ቢጫ ሰንደቅ ዓላማ፤ የ600 ዓመት የታሪክ ማስረጃዎች( ክፍል አንድ)********************ከዛሬ 400 ዓመት ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና የኢትዮጵያውያን መለያ ( nati...
17/10/2019

አረንጓዴ ቢጫ ሰንደቅ ዓላማ፤ የ600 ዓመት የታሪክ ማስረጃዎች
( ክፍል አንድ)
********************
ከዛሬ 400 ዓመት ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና የኢትዮጵያውያን መለያ ( national banner) አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ነበረች፡፡ በዚያን ዘመን ዓለም ያውቀው የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማም ይሄንን ነበር፡፡ ማስረጃ ላቅርብ

በ16ኛው ክፍለዘመን የተወለደው ፣ ሆላንዳዊው ፒተር ቫንደር አ ( Pieter Vander) ፣ በዓለም ከታወቁ የካርታ ሥራ ባለሙያዎችና ጆግራፈሮች አንዱ ነበር፡፡ ይሄው ሰው 28 ቮልዩምና ከሶስት ሺህ በላይ ገጽ ያለውን የዓለም ካርታና አትላሶች አዘጋጅቷል፡፡ ይሄው ካርቶግራፈር ታድያ የያንዳንዱን ሀገር ካርታ ከሳለ በኋላ፣ የዛን ግዜ በነበረው አካዳሚካዊ ደንብ፣ ከካርታው ሥሩ የሀገሩን ሰዎች ማንነት ፣ ቀለምና የሚወክላቸው የሰንደቅ ዓላማ ቀለም ያስቀምጥ ነበር፡፡

ይሄ ምሁር የሳለውና ያሳትመው የኢትዪጵያ ካርታ ላይ ፣ ኢትዮጵያውያዊ እናትና አባትን አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ልብ አልብሶ ስሏቸዋል፡፡ ከደራሲው ኦርጅናል ሥራ ላይ የተወሰደው ኮፒ ካርታና ስዕል እዚህ ላይ ይገኛሉ፡፡

https://cdn.shopify.com/…/…/products/aq18957a_1024x1024.jpg…

ይህ ሰው ዜግነቱ ደች( ሆላንዳዊ) ነው፡፡ስራውም የካርታ ሥራ ባለሙያና ጆግራፈር ነው፡፡ በደች ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ሳይቀረ የካርታ ሥራን ያትም የነበረ ትልቅ ባለሙያ ነበር፡፡ በግዜውም ተወዳዳሪ ያልነበረው የካርታና የሀገራት ማንነት ሊቅ ነበር፡፡
ይህ ሊቅ ሀገራችንን ካርታው ላይ ሲጠቅሳት ስያሜዋን ያላት “ አቢሲንያ “ አይደለም፡፡ኢትዮጵያ ነው ብሎ የጠራት፡፡ ኢትዮጵያውያንንም ( መልካቸውን ጥቁር) ልብሳቸውን ግን አረንጓዴ፣ ቢጫ ፣ ቀይ አልብሶ ነው የሳለቸው፡፡

የመጽሃፍቶቹን ጥቁና ነጭ ኮፒ እዚህ ሊክ ላይ ያገኙታል

https://www.stolenhistory.org/…/1570-book-containing-a-dra…/

አሜሪካዊው ዋልት ዊትማን (1871)
************
እንግሊዞች ሼክስፒርን በባለቅኔነት እንደሚጠሩት ሁሉ፣ አሜሪካኖች አሉን ከሚሏቸው አንዱ ባለቅኔና ጸሐፊ በ1819 ዓ.ም የተወለደው ዋልት ዊትማን ነው፡፡
(https://whitmanarchive.org/biography/walt_whitman/index.html)
ዋልት ዊትማን እጅግ በርካታ ቅኔዎችንና ሌሎች መጻሕፍትን የጻፈ አሜሪካዊ ባለቅኔ ና ደርሲ ነው ፡፡ ከዛ ውስጥ አንዱ በ በ1860ዎቹ ተጽፎእ በ1871 የታተመው Ethiopia Saluting the Colors የሚለው ቅኔ ነው፡፡ ይህ ወቅት እንግሊዞች አጼ ቴዎድሮስን( 1855-1868) እየተተናኮሉ የነበረበት ወቅት ነበር፡፡ ለአሜሪካኖች ደግሞ ፣ እንግሊዝ ላይ የበላይነታቸውን እያሳዩ የነበረበት ውቅት ነበር፡፡ የተለያዩ የዓለም ሀገራትንም ፣ ከንግሊዝ ወጥተው ከአዲሷ ገናና ሀገር አሜሪካ ጋር እንዲወዳጁ ይሰብኩ ነበር፡፡ የቅኔ ደምቡ ሆኖ ይህ ቅኔም ሰምና ወርቅ ፣ ብዙ እማሬና ፍካሬ ቢኖረውም ፣ አንዱ ውትወታ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ትብብር ትፍጠር አይነት ነበር፡፡ ታድያ ዋልት በዚህ በ 1871 በታተመው Ethiopia Saluting the Colors የተሰኘው ቅኔው ላይ እንዲህ ይላል ( ዊትማን በ187አ ያሳተመውን መጽሃፍ ኮፒ እዚህ ላይ ያገኙታል

https://whitmanarchive.org/publ…/…/figures/ppp.00270.360.jpg

“What is it, fateful woman--so blear, hardly human?
Why wag your head, with turban bound--yellow, red and green?
Are the things so strange and marvelous, you see or have seen?”

https://whitmanarchive.org/published/LG/1871/poems/180

ዋልት በግጥሙ ኢትዮጵያን በአንዲት ወይዘሮ ነው የገለጣት፣ ራስዋ ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሪባን ሻሽ ያስረች ጥቁር ቆንጆ ሴት ብሎ ይገልጻታል፡፡ ዋልት አሜሪካዊ ነው፡፡ ይህንንም ግጥም የጻፈው በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ነበር ( ያሳተመው በአጼ ዮሃንስ ዘመን ቢሆንም) ፡፡ በአጼ ቴዎድሮስም ዘመን ፣ በአጼ ዮሃንስም ዘመን ፣ ኢትዮጵያ የምትታወቀው በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሟ ነበር፡፡ ይህችን ሰንደቅ መልበስ ፣ ራስ ላይ ማሰር የተጀመረውም አሁን ያለመሆኑንና ያኔም ኢትዮጵያ ስሟ በዓለም ዘንድ ኢትዮጵያ እንደነበር ያጤኗል፡፡መቀሌ በሚገኘው የአጼ ዮሃንስ ቤተ መንግስትም የሚታየው የአጼ ዮሃንስ ሰንደቅ ዓላማ ይሄው አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀዩ ነው፡፡

የትግራዩ ራስ ወልደሥላሴና አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማቸው ( 1736_1816)
*****************************************
በኢትዮጵያ ታሪክ ከሚጠቀሱት ጠንካራ መሳፍንት ውስጥ ፣ የትግራዩ ራስ ወልደሥላሴ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ትግራይን 25 ዓመት በገዙት ጠንካራው መስፍን ራስ ወልደሥላሴ ዘመን ፣ በርካታ የውጭ ዲፕሎማቶች ትግራይ ድረስ ሂደው በወቅቱ ስለነበረው የትግራይ ሕዝብ ባህልና ኑሮ ጽፈዋል፡፡ ከነሱ ውስጥ አንዱ በሳቸው ዘመን የትግራይ ሕዝብና የራስ ወልደሥላሴ ወታደሮች ራሳቸው ላይ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ [ጥለት ሻሽ] ያስሩ እንደነበር እንዲህ ሲል ይገልጠዋል Voyages and travels to India Ceylon, the Red Sea and Abyssinia and Egypt By George, Viscount Valencia pp 132

“ Round their heads, they wore bandages formed of Yellow , green red satin tied behind long and streaming loosely as they rode”
ከላይ እንዳየናቸው ፣ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ሆላንዳዊ የካርታና የጂኦግራፊ ሊቅ ኢትዮጵያውያን መለያቸው አረንጓዴ፣ ቢጫ ፣ ቀይ እንደሆነ ካርታው ላይ ስሎ ነግሮናል፡፡ አሜሪካዊው ባለቅኔ ዋልት ዊትማንም ኢትዮጵያን በሴት ወይዘሮ መስሎ ሲገልጣት ራስዋ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ያስረች ወይዘሮ አድርጎ ገልጿታል፡፡ ትግራይን በራስ ወልደ ሥላሲ ግዜ የጎበኘው ቪስካውንት ጆርጅ ደግሞ የትራዩ መስፍን የራስ ወልደ ሥላሴ ወታደሮች ራሳቸው ላይ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ና ቀይ ሪባን ያስሩ እንደነበር ግልጽ አድርጎ ይነገረናል፡፡

መጽሃፉን እዚህ ያገኙታል
https://books.google.com/books…

አጼ ሚኒሊክ ( 19ኛው ክፍለ ዘመን)
********************
በዘመነ አጼ ሚኒሊክም የተለየ ነገር አልነበረም፡፡ አረንጉዴ፣ ቢጫ ፣ ቀይ የሀገሪቱ አርማ ( national Banner) ነበረ፡፡ ይሄንንም ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ፣ ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ አጼ ምኒልክ በሚለው መጽሃፋቸው ብዙ ቦታ ላይ ገልጸውታል፡፡ ለምሳሌ በ1882 ዓ.ም ሥርዓተ መንግስት ሲያደርጉ የነበረውን ሁነት ጸሐፌ ት ዕዛዝ ከላይ በተጠቀሰው መጽሃፋቸው ገጽ 157 ላይ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል
“በዙፋኑም በኋላ፣ ወደ ትልቁ ሰገነት የሚያስወጣ ባለሟሎችና መኳንንቶች የሚመላለሱበት ያ ዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያየውን የመሰለ መሰላል ነበረ፡፡ መሰላሉም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ የተሸለመ ነው” ሲሉ ይገልጡታል፡፡
የአድዋ ጦርነት ሲደረግም ፣ የአክሱም ካህናት ይዘው ወደ አጼ ሚኒሊክ የመጡት ስዕለ ማርያምንና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማን ነበር፡፡( ገጽ 262) ፡፡ ዳግማዊ አጼ ምኒሊክም ከጣልያኖች ጋር የነበራቸው ጥያቄ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ነበር፡፡ ለምሳሌ ማጆር ሳልሳን እንዲህ ነበር ያሉት
https://ayamarushewa.blogspot.com/2018/02/blog-post.html

“ አጼ ምኒሊክም ሲመልሱ ፣ እኔም የመጣሁት የተተከለውን ባንዲራ ላስነሳ ነው፡፡ … ባገሬ በኢትዮጵያ መንግስት ባንዲራ እንጂ የሮማን ባንዲራ አላስተክልበትም ብለው መለሱለት” ገጽ 253
ይህንን ለግዜው እዚህ ላይ ገትተን እጅግ ወደኋላ ወደ 14ኛው ክፍለ ዘመን ስንጓዝ ደግሞ ፣ በዚያ ዘመንም የኢትዮጵያ መለያ ቀለም አረንጉዴ ቢጫ ቀይ መሆኑን በማስረጃ እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ በአስራ አራተኛው ክፍለዘመን የተጻፈውንና መጽሃፍ ስንመለከት ልክ አቡን እንደምናደርገው ያኔም በመጽሃፍት ዙርያ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለምን መሳል የተለመደ እንደነበረና በማስረጃ እናያለን፡፡

https://www.metmuseum.org/en/art/collection/search/317618 ( ከስምንተኛው ገጽ ጀምሮ ይመልከቱ)

እንግዲህ ከላይ በማስረጃ እንዳየናቸው፣ ከ14ኛው ክፍለዘመን የብራና መጽሃፍ ጀምሮ፣ የተለያዩ የውጭ ሊቃውንት የመሰከሩት ነገር ተመሳሳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው፡፡ ቢያንስ ለዚህ የስድስት መቶ አመት ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ትውፊታችን እንደሚለን ደግሞ ይህ ሰንደቅ ዓላማ ከኖህ ዘመን ጀምሮ እኛ ኢትዮጵያውያን ስንጠቀምበት የነበረው መለያችን ነው፡፡

ጣልያን ኢትዮጵያን ሁለተኛ ከመውረሩ በፊት፣ የጣልያን ወታደራዊ ሊቃውንት ስለ ኢትዮጵያ ብዙ ጥናት አስጠንተው ነበር፡፡ በተለይም የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ አድርገው የያዙት ነገሮች ማለትም ሃይማኖት ( ኦርቶዶክስ)፣ ሰንደቅ ዓላማ እና ዘውድ አስተዳደሩን ካላፈረሰ ኢትዮጵያን መያዝ ከባድ እንደሚሆን ና እነዚህ ነገሮች ከወደሙ ግን ኢትዮጵያን መቆጣጠር ቀላል እንደሆነ የጣልያን ሊቃውንት ባሳሰቡት መሰረት እነዚህ ሶስቱ የኢትዮጵያ እሴቶች ላይ የኮሎኖያሊስት ዘመቻ ተጀመረ፡፡ በዋነኛነትም ሚሲዮናውያን( በሃይማኖት ስብከት ሽፋን የገቡ ሰላዮች) የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ፣ ሰንደቅ ዓላማን እና አማራን ጥላሸት እየቀቡ በማስተማርና መጻሕፍትን በመጻፍ የህዝቡን ስነ ልቦና ማሸፈት ጀመሩ፡፡ ቀስ በቀስም ሙያ እናስተምራለን በሚል ሰበብ በከፈቷቸው ትምህርት ቤቶች ፣ አዳጊ ሕጻናትን ጸረ ሰንደቅ ዓላማ ሆነው እንዲወጡ ያስተማሯቸው ኢትዮጵያኖች የገዛ ሰንደቅ ዓላማቸውን ማዋረድ ጀመሩ፡፡ አልፎ ተርፎም እነዚሁ ወገኖች ስልጣን ሲይዙ የገዛ ሰንደቅ ዓላማቸውን “ ህጋዊ ያልሆነ “ እስከማለት ተደረሰ፡፡ Ephrem Ephrem
( ይቀጥላል)
share please .

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሚስጢረኛው ጋዜጠኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Travel Agency?

Share

ነፃ የጥቆማ ስልክ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ ስለ ኮሮና ቫይረስ

ነፃ የጥቆማ ስልክ 6016