ኮረማሽ-Koremash

ኮረማሽ-Koremash የኢትዮጵያን ታሪክ ወግና ባህል ውብ በሆነ መልክ ይዳሰሳል ። አብረውን በመጓዝ የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽና ተፈጥራዊ ቦታዎች ይጎብኙ። ኮረማሽ የጉዞ ማህበር !
(4)

24/05/2024

ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም በሁለተኛው የፋሺስት ኢጣሊያን ወረራ ወቅት በሊግ ኦፍ ኔሽን ተገኝተው በእንግሊዝኛና ፈረንሳይኛ ያደረጉት ንግግር ፤

እ.ኤ.አ 1935

◆ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም    #ከ 115 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ለህዝባቸው በአዋጅ የዙፋናቸው ወራሽ ልጅ ኢያሱ ሚካኤል እንደሆነ እና ራስ ተሰማ ናደው ሞግ...
18/05/2024

◆ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም



#ከ 115 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ለህዝባቸው በአዋጅ የዙፋናቸው ወራሽ ልጅ ኢያሱ ሚካኤል እንደሆነ እና ራስ ተሰማ ናደው ሞግዚትና እንደራሴ አድርገው የሾሟቸው ዕለት ነበር።

Ethiopian History, Culture and Tourism

ዛሬ ሚያዝያ 30 የዓለም ዓቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ  ቀን ነው ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓመተ ምህረት የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የጄኔቫውን ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ዓለ...
08/05/2024

ዛሬ ሚያዝያ 30 የዓለም ዓቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ቀን ነው

ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓመተ ምህረት የተመሠረተው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የጄኔቫውን ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር አግኝቶ 38ኛው አባል ሆኗል።

ይህ ከመሆኑ ብዙ ዓመታት አስቀድሞ ከዓድዋ ጦርነት መንፈቅ ጊዜ ያህል በኋላ የሩሲያ የቀይ መስቀል አባላት በጄኔራል ሽዊደፍን መሪነት ወደ አገራችን መጥተው የሠጡትን የሕክምና ስራ ካዩ በኋላ ንጉሡና እቴጌይቱ የቀይ መስቀል ማህበር ዓላማና ተግባርን በሚገባ አውቀውታል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህ ማለትም በ1889 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የቀይ መስቀል ስም በአዲስ አበባ ከተማ የታወቀ ነበር።

በ1899 ንጉሥ ምኒልክ ጥቅምት 12,27 እና ኅዳር 18 ቀን ለሩሲያው ንጉሥና ባለቤታቸው የቀይ መስቀልን መመሥረታቸውን ሶስት ደብዳቤዎችን ፅፈው ነበር። እቴጌ ጣይቱም የማህበሩ የበላይ ጠባቂ ለመሆን መፍቀዳቸውንም ገልፀዋል።

ከእቴጌ ደብዳቤዎች አንዱም ......

እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ

ይህንን ደብዳቤ ለሚያይ ሕዝብ ሁሉ ሠላምታዬን እሠጣለሁ።

ለክርስቲያን ፥ ለተጎዱም ሕዝብ ለነዳያን ፥ ለቆሰሉም ብርቱ ሕመም ለታመሙም ሕዝብና ሠራዊት የፍቅር የመልካም ሥርዓትና የርኅራኄ ርዳታ ለማሳየት ስላሰብን ይህንንም የርኅራኄ መልካም ምግባር ለመፈፀም በመንግሥታችን በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ማኅበር ለመትከል ወደድን።

በእውነተኛ ልብ የተከልነው የቀይ መስቀል ማኅበር እግዚአብሔር ለመጠበቅ ስላበቃን ማኅበራችንን ለረዳ ለዶክተር ኩርት ሂርትሰቡርህ በከበረው ቀይ መስቀል ንሻኖች አክብረን ሸልመነዋል። ይህንንም ንሻን በደረቱ እንዲይዘው ፈቅደንለታል።

ሰኔ 9 ቀን 1899 ዓመተ ምሕረት አዲስ አበባ ከተማ ተጻፈ።

እንኳን ለ83ኛው የአርበኞች ቀን አደረሰን!"... በመቶ ሺህ የሚቆጠረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በየመንገዱ ዳር ተሰልፎ በናፍቆት ተውጦ ይታይ ነበር።... መንገዱ ሁሉ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና አ...
05/05/2024

እንኳን ለ83ኛው የአርበኞች ቀን አደረሰን!

"... በመቶ ሺህ የሚቆጠረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በየመንገዱ ዳር ተሰልፎ በናፍቆት ተውጦ ይታይ ነበር።... መንገዱ ሁሉ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና አበባ አጊጦ ነበር። የሕዝቡ ሁኔታና የከተማው ይዞታ ተለዋውጧል። ሕዝቡም ከናፍቆቱ ብዛት የተነሣ መሬት እየሳመ ደስታና ኅዘን የተቀላቀለበትን ልቅሶ እያለቀሰ ተቀበለን።
.. ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ስንሰቅል ፳፩ ግዜ መድፍ ተተኮሰ። በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም በዚሁ ዕለት ባዶሊዮ የኢጣሊያን ባንዲራ በዚሁ ቦታ ላይ የሰቀለበት ቀን ነበር። ቀጥሎም ወደ ቤተመንግስት ሰገነት ላይ ወጥተን በታላቅ በእልልታና ዘፈን፤ ፉከራና ሽለላ ደስታውን ይገልጥ የነበረውን ሕዝባችንን በአድናቆት ስንመለከት ቆይተን ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ንግግር ለሕዝባችን አሰማን።

".... ከማናቸውም አስቀድሞ ለሁላችሁ ልነግራችሁና ልትረዱት የምፈልገው ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ ያዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ መሆኑን ነው። በዚህ በአዲስ ዘመን ሁላችን መፈፀም ያለብን አዲስ ሥራ ይጀምራል።
..." ቀ.ኃ.ሥ. ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ፪ኛ መፅሐፍ።

ክብር ይችን ሀገር ጠብቀው ላቆዩ አርበኞቻችን!

🙏🙏🙏

💚💛❤️

 # # # # የኢትዮጵያ አርበኞች  # # # #      (በ5 ዓመቱ የመከራ ዘመን)   ኢጣሊያ ዳግም ኢትዮጵያን ከወረረች በኋላ የንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴን የክተት አዋጅ ተከትሎ ሀገ...
04/05/2024

# # # # የኢትዮጵያ አርበኞች # # # #
(በ5 ዓመቱ የመከራ ዘመን)

ኢጣሊያ ዳግም ኢትዮጵያን ከወረረች በኋላ የንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴን የክተት አዋጅ ተከትሎ ሀገሩን ሊታደግ ሁሉም ባቅሙ አርበኛ ነበር። ከወራሪ ጋር ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ጠላት ባንዳዎች ጋር ጭምር እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ አድርገዋል። ከንጉሠ ነገሥቱ ስደት በኋላም ለሀገር ነፃነት እልፎች ተዋድቀዋል። ህይወታቸውን ገብረዋል። ከነፃነት ኋላም ንጉሣቸው ጠብቀው...በኦሜድላ ባንዲራቸዉን አዉለብልበዉ ሚያዝያ 27 መናገሻ ከተማቸዉ ገብተዋል።

እነ.....ባላምባራስ(ራስ) አበበ አረጋይ፣ ደጃዝማች ፍቅረማርያም፣ ደጃዝማች አውራሪስ፣ ደጃዝማች መንገሻ ወሰኔ፣ ደጃዝማች (ራስ) መስፍን ስለሺ፣ ደጃዝማች ሀብተ ሥላሴ፣ ደጃዝማች ኃይሉ ወልደ መድህን፣ ወ/ሮ ከበደች ስዩም፣ ባላምባራስ በሻህ ኃይሌ፣ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ፣ ደጃዝማች ተሾመ ሽንቁጥ፣ ደጃዝማች ዘውዴ አስፋው፣ ፊታውራሪ ተድላ መኮንን፣ ጄ/ል ጀጋማ ኬሎ

እነ.... ፊታውራሪ (ደጃች) ፀሐዩ እንቁ ሥላሴ፣ ፊታውራሪ ወልደ ፃድቅ፣ ፊታውራሪ ከበደ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ፊታውራሪ መኮንን ወልደ ጊዮርጊስ፣ ፊታውራሪ ተሰማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ፊታውራሪ ዳርጌ ጎርጅ፣ ፊታውራሪ ኃይለ ማርያም ቸሬ፣ ፊታውራሪ ደምሴ ወልደ አማኑኤል፣ ፊታውራሪ ከበደ ብዙነሽ ሜታ፣ ከንቲባ በከበረ ኃይለ ሥላሴ፣

እነ ልጅ ኃይለ ማርያም ማሞ፣ ቀኛዝማች ጎበዜ፣ ቀኛዝማች ደጋጋ ዲድኖ፣ ቀኛዝማች በቀለ ወልደ መድህን፣ ግራዝማች ኃይለ ሥላሴ በላይነህ፣ ባሻ ወልዴ፣ ባሻ ኤፍሬም፣ ልጅ ግዛቸው ኃይሌ፣ ልጅ ተኮላ ድል ነሳሁ ፣ ልጅ ሳህሌ እንቁ ሥላሴ፣ አቶ ተሰማ እርገጤ
እነ ደጃዝማች ገብረ ሕይወት፣ ደጃዝማች ኃይሉ ከበደ፣ ደጃዝማች ዓባይ ካሣ፣ ደጃዝማች ውብነህ ተሰማ፣ ፊታውራሪ መስፍን ረዳ ፣ ፊታውራሪ ኃይሉ ክብረት ፣ ደጃዝማች አስፋው፣ ደጃዝማች ዳኘው ተሰማ፣ ፊታውራሪ አስፋው ይግዛው፣ ፊታውራሪ በረደድ አስፋው፣ ፊታውራሪ ይማም ተሰማ፣ ልጅ ደስታ ፣ ደጃዝማች አዳነ
እነ ራስ ኃይሉ በለው፣ ቢትወደድ ነጋሽ በዛብህ፣ደጃዝማች መንገሻ ጀምበሬ፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ፣ ፊታውራሪ ኃይለ ኢየሱስ ፍላቴ፣ ፊታውራሪ ዘለቀ ደስታ ፣ ፊታውራሪ አያሌው፣ ፊታውራሪ ደረሰ ሽፈራው፣ ፊታውራሪ በቀለ አምባዬ፣ ፊታውራሪ ሽፈራው ረታ፣ ፊታውራሪ በየነ ቢሻው፣ ፊታውራሪ ካሳ ኃ/ማርያም ኮላሴ፤ ጓንጉል ኮላሴ፣ ደጃዝማች አፈወርቅ ወ/ሰማያት
እነ ራስ ደስታ ዳምጠው፣ ደጃዝማች በየነ መርእድ፣ ፊታውራሪ በዕደማርያም ፣ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ፣ ደጃዝማች ባልቻ፣ ደጃዝማች በቀለ ወያ፣ አቶ ከበደ አቦዝን ፣ ደጃዝማች ተስፋዬ ወልዴ፣ ፊታውራሪ ዮሐንስ፣ ፊታውራሪ ኃይለ አባ መርሳ፣ መላኩ በያን ፣ሀዲስ አለማየሁ፣አቋ ሰለባ፣ አቡነ ጴጥሮስ ፣ አቡነ ሚካኤል፣ የየካቲት 12 ሰማዕታት፣ የደብረ ሊባኖስ መስዋዕት መነኮሳት...

እና እልፍ በስም ያልተጠቀሳችሁ ...ታሪክ ያልመዘገባችሁ አርበኞች... ስንቅና ብልሃት አቀባይ ሴቶች... እንደነ ጀነራል ዊንጌት፤ ኮ/ል ሮቢንሰን. አዶልፍ እና ሌሎች በርካታ ለኢትዮጵያ የዘመታችሁ የውጭ አርበኞች ሁሉ ስለከፈላችሁት መስዋዕትነት... ስለሰጣችሁን ነፃነት... ስላስረከባችሁ ባንዲራ እናመሠግናለን!!!

ዘላለማዊ ክብር ለእናንተ!!!

 # # # # ዝክረ ሚያዝያ 27  # # # #             (ልጁ....አቢቹ)አቢቹ ነጋ ነጋ ቀሬራ መርማሪኒለቺቱ ነጋ ነጋ ቆሬን ሲንወራኒኒ(አቢቹ ሰላም ሰላም ከፍታው ላይ ምን ያንጎማ...
03/05/2024

# # # # ዝክረ ሚያዝያ 27 # # # #
(ልጁ....አቢቹ)

አቢቹ ነጋ ነጋ
ቀሬራ መርማሪኒ
ለቺቱ ነጋ ነጋ
ቆሬን ሲንወራኒኒ
(አቢቹ ሰላም ሰላም
ከፍታው ላይ ምን ያንጎማልልሃል
ሁሉም ሰላም ነው
እሾክ አንዳይወጋህ)

ስለ ልጁ ወይም አቢቹ ዝርዝር ታሪክ ተፅፎ ባይገኝም የቼክ ሪፐፕሊክ ተወላጅ የነበሩት ከራሥ ካሣ ጋር አብረው የዘመቱት ኦዶልፍ ፖርለሳክ ' ሃሰሽስካ ኦዴሳ' በሚለው እና በተጫነ ጆብሬ ' የሃበሻ ጀብዱ' በሚል ወደ አማርኛ በተመለሰው መፅሐፋቸው ስለ አቢቹ ካስነበቡን ድንቅ ታሪክ ቅንጫቢ እንሆ በረከት...
...ጃንሆይ... የንግግር መስመራቸውን ለውጠው ' ልጁን አይታችሁት ታውቃላችሁ?' ሲል ጠየቁ። ቆሞ የነበረው ኮሎኔል ኮናቫሎቭ ከአፋቸው ነጥቆ ' ጃንሆይ ሆይ ይቅርታ ያድርጉልኝና ስለ ልጁ ወዳጄ ካፒቴን ፖርለሳክ የበለጠ ስለሚያውቅና ከሁሉም በላይ የልጁ የጥብቅ ወዳጅ ስለሆነ የበለጠ ሊያብራራልዎታል ይችላል' አለ።

'ግድ የለም... እንደናንተም ባይሆን ይቺ አንድ ፍሬ ደጃዝማች ከኛም በላይ ትልቅ ጀብዱ እየሰራች እንደሆነ እንሰማለን። ይልቅ እርግጠኛ ነኝ ለረጅም ጊዜ ፍራፍሬ በልታችሁ አታውቁምና እንካችሁ' ብለው ለራሳቸው ከቀረበው ፍራፍሬ እንድንበላ ጋበዙን።... እኔም በሃሳብ ወደ አቢቹ ነጎድኩ። ...

ግን ስለ አቢቹ ጦር እንቅስቃሴ ጋይላ እያለን የከንባታ ልጆች እንዴት ከጠላት ጦር ላንቃ ውስጥ ፈልቅቆ እንዳወጣቸው ካወሩኝ ወሬ ውጪ ሌላ ወሬ ከሰማሁ ሰንብቻለሁ።

ወሬው ይኸውና...

የከንበታ ጦር በጣልያን ሰራዊት ተከቦ መውጫው ጠፍቶት አጥፍተህ ጥፋ አይነት ውጊያ ላይ እያለ ከየት መጡ ሳይባል እነዚያ የአቢቹ ፈጥኖ ደራሽ ደቦል አንበሶች ከጣልያኑ ጦር በብት ውስጥ ገብተው ሲክረኩሩት ደመሰስኩ ብሎ የሚኩራራው የጣልያኑ ጦር ሳያስብ አደጋ ደርሶበት በተራው ሲያፈገፍግ የከንባታውን ጦር ከዚያ ካለቀለት ውጊያ ውስጥ እነአቢቹ መንጥቀው አወጡት።....

የልጁ (አቢቹ) ጦር ከማይጨው ጦርነት በኋላ ፍፃሜ አግኝቷል።

#

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: ዒድ ሙባረክ።
09/04/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: ዒድ ሙባረክ።

በዛሬዋ_ዕለት መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ.ም ከ 83 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከስደት ዘመን በኋላ በኢትዮጵያ አርበኞች ትግል እና በብሪታኒያ ጦር መሪ ከጄነ...
06/04/2024

በዛሬዋ_ዕለት

መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ.ም

ከ 83 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከስደት ዘመን በኋላ በኢትዮጵያ አርበኞች ትግል እና በብሪታኒያ ጦር መሪ ከጄነራል ውንጌት ጋር የጣሊያንን ሠራዊት ድል እየመቱ በሱዳን (ኦሜድላ) በኩል ደብረ ማርቆስ የደረሱበት ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን ጦር እያገዘ በደቡብ አቅጣጫ በሱማሊያ በኩል የዘመተው የእንግሊዙ ጦር በመሪው ጄኔራል ካኒንግሀም አማካኝነት አዲስ አበባን በመቆጣጠር ጣሊያንን ከኢትዮጵያን መዲና ያስለቀቁበት ዕለት ነበር።

©ታሪክን_ወደኋላ

መጋቢት 13 ቀን 1898 ዓ.ም   ከ 118 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ልዑል ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል በተወለዱ በ 54 ዓመታቸው አርፈው ቀብራቸው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤ...
22/03/2024

መጋቢት 13 ቀን 1898 ዓ.ም



ከ 118 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ልዑል ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል በተወለዱ በ 54 ዓመታቸው አርፈው ቀብራቸው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተከናወነበት ዕለት ነበር።

በ 1894 ዓ.ም በመጀመሪ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር 4 ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር 9 ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኃላ ህመሙ ስለፀናባቸው ወደኀላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር።

እዚሁ ሲታከሙ ከቆዩ በኃላ መጋቢት 13 ቀን 1898 ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።

አፄ ምኒልክ የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን በአዲስ አበባ በዙሪያዋ ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተደርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ 23 ቀን 1898 ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ መኳንንቱና ሠራዊት ተሠብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውንና የራስ ወርቃቸውን ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸውን ተይዞ በፈረሰና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊት መካከል እየተመላለሱ ታላቅ ለቅሶ ተለቀሰላቸው።

ከአልቃሾቹም አንዱ ደግነታቸውን ለማስታወስ እንዲህ ብሎ አሟሸ

ስልከኛው ሲያረዳ ነገር ተሳሳተው
መኮንን አይደለም ድኃ ነው የሞተው

(ግንቦት 1 ቀን 1844 -- መጋቢት 13 ቀን 1898)

©ታሪክን ወደኋላ

ሠላም ቤተሠቦቻችን! ከ ቀጣይ የጉዞ ፕሮግራማችን ጋር ተመልሰናል 🌴 ጉለሌ ዕፅዋት ፓርክ   እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ወደ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ጀማሪ ተጓዦችን ያማከለ የ8 ኪሎ ሜትር የ...
12/03/2024

ሠላም ቤተሠቦቻችን!

ከ ቀጣይ የጉዞ ፕሮግራማችን ጋር ተመልሰናል

🌴 ጉለሌ ዕፅዋት ፓርክ

እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ወደ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ጀማሪ ተጓዦችን ያማከለ የ8 ኪሎ ሜትር የሚወስድ ቀለል ያለ የእግር ጉዞ (hiking) ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

የጉዞ አይነት

🌴ቀለል ያለ የእግር ጉዞ

የቦታው የመጨረሻ ከፍታ..1818 ሜትር
የጉዞው ክብደት..3/10
መነሻ ስዓት ...ጠዋት 1:30 ሰዓት

(ጀማሪ ተጓዦች ሊሳተፉበት የሚችል)
በመሆኑም የተፈጥሮና የእግር መንገድ ወዳጆች በዚህ ጉዞ ላይ አብራችሁን እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።
ጉዞው ውስን ሰዎችን የሚያሳትፍ ብቻ በመሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ለመገኘት ቀድመው እንዲመዘገቡ እንመክራለን ።

የጉዞ ዋጋ 600

ትራንስፖርት ከፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጉለሌ ዕፅዋት ፓርክ ደርሶ መልስ ትራንስፖርት ቀለል ያለ ቁርስ የታሸገ ውሃና የፓርክ መግቢያ እንዲሁም የአስጎብኚ ክፍያን ጨምሮ:

ለበለጠ መረጃ 👉 0913910270 ይደውሉ!

👉

ዛሬ ዛሬ ሃገራችን በምትከተለው የፖለቲካ መስመር የተነሳ ትውልድ በሙሉ “የኛ ጀግና ይሄ ነው”ብሎ የሚስማማበት አንድም ሰው የለንም:: የ3000 አመት (ምናልባትም ከዚያ በላይ)ታሪክ ያለን ህ...
09/03/2024

ዛሬ ዛሬ ሃገራችን በምትከተለው የፖለቲካ መስመር የተነሳ ትውልድ በሙሉ “የኛ ጀግና ይሄ ነው”ብሎ የሚስማማበት አንድም ሰው የለንም:: የ3000 አመት (ምናልባትም ከዚያ በላይ)ታሪክ ያለን ህዝብ ብንሆንም እንንኳ ነገስታቱንና አርበኞቹን በየጎሳው ተከፋፍለን "የኔ ነው" የለም "የኔ ነው" በሚል እየተጓተትን ለሀገር የሰሩትን ገድል ለተለየ ቡድን መኩሪያ ለማድረግ ስንታትር ይስተዋላል።

ቱርኮች ስለ ከማል አታ ቱርክ አውርተው አይጠግቡም፤ ጀርመኖች ስለ ቢስማርክ ክብር ድልድይ ሰርተው መንገድ ገንብተው ሃውልት አቁመው አይረኩም፤ ደቡብ አፍሪካ በኔልሰን ማንዴላ ቀልድ አያውቁም፤ ታንዛኒያዎች መሪያቸው ጁሊየስ ኔሬሬን ሟሊሙ (መምህር)እያሉ ሲያንቆለጳጵሷቸው በአንድ ድምጽ ነው።

የኛ ሃገር ግን ጉዳዩ ሌላ ነው። ብሄራዊ ጀግና የለንም። አሸንፎ የሚወጣው ኃይል የራሱን ጀግና ጀግናችን በሉ ብሎ ያውጅና በተራው ሲሸነፍ በሌላ የአሸናፊ ጀግና ይተካል።

“ከታሪክ ምድጃ ላይ አመዱን ተውና ፍም እሳቱን ጫሩ” ያሉትን የአንድ አዋቂ ሰው ንግግርን መስመር ተከትለን፤ ነገስታቶች የሰሩትን መጥፎ ይሁን ጥሩ ፍርድ ለታሪክ ባለሙያዎች በመተው፤ ለትውልድ ይጠቅማሉ፤ ትውልድን በኢትዮጵያዊነት ገመድ ያስተሳስራሉ፤ ያልናቸውንና አንድነታችንን ያደረጃሉ ያልናቸውን መሰረታዊ የታሪክ እውነቶች ማውሳት ነው።

የመተማ ውጊያና የአጼ ዮሃንስ ታሪክ የዚህ ሰሞን ዘመቻችን ማጠንጠኛ ነው::

በዚህ ሰሞን በምናደርገው ዘመቻም የአጼ ዮሃንስን የአገዛዝ ዘመናቸውንና የወቅቱን ክስተቶች እንዲሁም የመተማን ጦርነት መንስኤ ውጊያና የንጉሰ ነገስቱን ፍጻሜ እናያለን። ንጉሰ ነገስቱ ለኢትዮጵያ አንድነት ያበረከቱትን አስተዋፅኦ (እስከ ህይወት በመሰዋት የደረሰውን) ዝክረ ነገር እንዘክራለን::





#135

እንኳን ለ46ኛ የካራማራ የድል በዓል አደረሰን ። 46ኛ ዓመት የካራማራ የድል በዓል መታሠቢያ ፕሮግራማችን ላይ ጥሪያችንን አክብራችሁ ለመጣችሁ እንግዶቻችንና  በመታሠቢያ በዓሉ ላይ ለተገኛች...
05/03/2024

እንኳን ለ46ኛ የካራማራ የድል በዓል አደረሰን ።

46ኛ ዓመት የካራማራ የድል በዓል መታሠቢያ ፕሮግራማችን ላይ ጥሪያችንን አክብራችሁ ለመጣችሁ እንግዶቻችንና

በመታሠቢያ በዓሉ ላይ ለተገኛችሁ .....

* ሀገርና ታሪክ ወዳድ ኢትዮጵያውያን

* በጦርነቱ ወቅት በጦሩ ሜዳ ላይ ተሳትፎ ለነበራችሁ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ጀነራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛ መኮንኖች ፣ መሥመራዊ መኮንኖች እና ባለሌላ ማዕረግተኞችና ቤተሰቦቻቸው

* በዚያ አስከፊ ጦርነት ወቅት ቤተሠቦቻቸሁን ያጣችሁ የአብዮታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ሕፃናት አምባ ልጆች

* ለኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አባላት

* በፕሮግራሙ ለተሳተፋችሁ ሚዲያዎች በሙሉ

* በዚያ በክፉ ወቅት በዓለም አቀፋዊ ወንድማማችነት መርኅ መሠረት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለመስጠት በጦርነቱ ተሳታፊ ከነበሩ ሀገራት መካከል በፕሮግራማችን ላይ ለተገኙት በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደርና ለኤምባሲው ሠራተኞች በሙሉ

ምስጋናችንን እያቀረብን ...

በተለይም .....

የዛሬው ፕሮግራማችን በስኬት ይጠናቀቅ ዘንድ እገዛችሁ ላልተለየን ....

👉 ለ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን

👉 ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ፅ/ቤት

👉 ለአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

👉 አዲስ አበባ ከተማ አስደዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን

👉 ይድኔ ፒክቸርስ

👉 ሲምፕሌክስ አድቨርታይዚይጅ

👉 ጌትሰን ኢንደስትሪ

👉 የቅርስና መፅሀፍት ሰብሳቢው አብዲ ነጋሽ ሀሠን

የተለየ ምስጋናችንን እናቀርባለን!!!

ክብረት ይስጥልን!!!

የበዓሉ አስተባባሪዎች

👉 ኮረማሽ የጉዞ ማህበር

👉 የኢትዮጵያ እና ኩባ ህዝቦች ወዳጅነት ማህበር

👉 ማይክ መላከ

ክብር ለካራማራ ጀግኖች ይሁን !

እናመሠግናለን !

በልዩ ሁኔታ ፎቶግራፈራችን Yidney Yidney በጣም እናመሰግናለን







ለሁሉም የሚዲያ አካላት! ኮረማሽ የጉዞ ማህበር ፤ የኢትዮጵያ እና የኩባ ህዝቦች ወዳጅነት ማህበር ፤ ማይክ መላከ ከአዲስ አበባ ባህል ፣ ቱሪዝምና ኪነጥበብ ቢሮ ጋር በመተባበር የ46 ኛውን ...
04/03/2024

ለሁሉም የሚዲያ አካላት!

ኮረማሽ የጉዞ ማህበር ፤ የኢትዮጵያ እና የኩባ ህዝቦች ወዳጅነት ማህበር ፤ ማይክ መላከ ከአዲስ አበባ ባህል ፣ ቱሪዝምና ኪነጥበብ ቢሮ ጋር በመተባበር የ46 ኛውን ዓመት የካራማራ የድል በዓል በጋራ ለማክበር አጠቃላይ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ።

ነገ ማክሰኞ የካቲት 26 ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ በኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ (ትግላችን ሐውልት) በሚደረገው የመታሠቢያ ፕሮግራም በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን የቆሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ፤ በጦርነቱ ተሳትፎ የነበራቸው ጀነራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛ መኮንኖች ፣ መስመራዊ መኮንኖች ፣ ባለ ሌላ ማዕረግተኞች ፣ አስደናቂ ጀብዱ የፈፀሙ ጀግኖች የሠራዊቱ አባላትና ቤተሰቦች በመታሠቢያ ፕሮግራሙ ላይ ይገኛሉ ።

በህይወት ያሉትን ስለውለታቸው እናመሠግናለን!
ሰማዕታቱንም እንዘክራለን!

ስለዚህ ይህን የድል መታሰቢያ ፕሮግራሙን ለመዘገብ ፍላጎቱ ያላችሁ የሚዲያ አካላት ነገ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ሁላችሁም በቦታው ላይ በመገኘት የመታሠቢያ በዓሉን ዝግጅት መዘገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

#ማሳሰቢያ : ሚዲያዎች ረጅም የማይክ ገመድ አሊያም ገመድ አልባ / wireless ማይክ ይዛችሁ እንድትገኙ ይሁን።






 ".... ሃያ ሺህ ያህል ወታደሮች ያሉበት የኤሮፓ ጦር በአፍሪካ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸነፈ::   በኔ እምነት መሠረት በዘመናችን ታሪክ ውስጥ እንደ ዓድዋው ያለ ጦርነት የለም:: በእልቂ...
02/03/2024



".... ሃያ ሺህ ያህል ወታደሮች ያሉበት የኤሮፓ ጦር በአፍሪካ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸነፈ::

በኔ እምነት መሠረት በዘመናችን ታሪክ ውስጥ እንደ ዓድዋው ያለ ጦርነት የለም:: በእልቂቱ በኩል 25000 ሰዎች በአንድ ቀን ጀምበር የሞቱበትና የቆሰሉበት ነው::

ፖለቲካና ታሪክ አበቃ::

በአፍሪካ ውስጥ ታላቅ የተወላጆች ሃይል መነሳቱ ታወቀ:: የአፍሪካ ተወላጆች ታሪክ ተለወጠ::

ጥቁሩ ዓለም በኤሮፓውያን ላይ ሲያምፅና ሲያሸንፍ የመጀመሪያው መሆኑ ነው:: አበሾች አደገኛ ህዝቦች መሆናቸው ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምሮ ተፅፎላቸዋል::

የኛ ዓለም ገና ቶር እና ኦዲዮን በሚባሉ አማልክት ሲያመልክ በነበረበት ጊዜ አበሾች የክርስትናን ሀይማኖት የተቀበሉ ናቸው::

".... አሁን የሁሉንም ፍላጎት ዓድዋ ዘጋው....."

ጆርጅ በርክሌይ

💚💛❤️

እንኳን ለ128ኛው የዓድዋ ድል መታሠቢያ ቀን አደረሰን

እንኳን አደረሳችሁ          📷 Yidney Yidney
01/03/2024

እንኳን አደረሳችሁ








📷 Yidney Yidney

የመጀመሪያው የዳግማዊ የአፄ ምኒልክ ፎቶግራፍ➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾ #አፄ ምኒልክ ፣ በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግስት ፣ ገና የሸዋ ንጉስ ሳሉ ከመኳንንቶቻቸዉ ጋር በወጣትነት ዘመናቸዉ የ...
20/02/2024

የመጀመሪያው የዳግማዊ የአፄ ምኒልክ ፎቶግራፍ
➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
#አፄ ምኒልክ ፣ በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግስት ፣ ገና የሸዋ ንጉስ ሳሉ ከመኳንንቶቻቸዉ ጋር በወጣትነት ዘመናቸዉ የተነሱት የመጀመሪያ ፎቶ
➠ ከግራ ወደ ቀኝ፦

🔹ደጃዝማች ማሙዴ
🔹ራስ ዳርጌ (አጎታቸው)
🔹ደጃዝማች ሸዋረገድ
🔹ንጉስ ምኒልክ (በኃላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ)
🔹ደጃዝማች ናደው (የራስ ተሰማ አባት)
🔹ደጃዝማች ወልደሚካኤል (የቀ.ኃ.ሥ አያት)

🔸ምንጭ:- (አፄ ዮሐንስ የኢትዮጵያ አንድነት) ገፅ 77 ላይ በተክለፃዲቅ መኩሪያ 1982 ዓ.ም የተፃፈው

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም ( የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን) የደም ቀን (የካቲት 12፣ ባካፋው ሚካኤል)×××××××××××××××.. አገር ተቃጠለ!እሳተ ጎመራ ወረደ ከሰለ።ጭስ አመድ አዋራ ...
20/02/2024

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም
( የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን)

የደም ቀን (የካቲት 12፣ ባካፋው ሚካኤል)
×××××××××××××××
.. አገር ተቃጠለ!
እሳተ ጎመራ ወረደ ከሰለ።
ጭስ አመድ አዋራ ሰማዩን ሸፈነው
ጥቁር ሰማይ ጥቁር!....

የሰው ጭንቅላት ኳስ …........
አባቶች ታረዱ
እናቶች ታረዱ
ቤት ንብረት ፈረሰ ከብቶቹ ተነዱ።
ዓለም መና ቀረ ................
* ገብረ ክርስቶስ ደስታ

ስለ የካቲት 12 ቀን እልቂት ጳውሎስ ኞኞ የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት በተሰኘ መፅሐፉ እንዲህ ያስነብበናል
..የኔፕልስ ልዕልት በመወለዷ ግራዚያኒ የደስታ መግለጫ ገንዘብ እሰጣለሁ ብሎ ከዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከድሮው ቤተመንግስት ድሆች እንዲሰበሰቡ አዘዘ:: ከድሆቹም በስተቀር ታላላቅ የኢጣሊያ ሹማምንት የሜትሮፓሊታን ጳጳስ አቡነ ኪርልና ሌሎችም መኳንንት ነበሩ:: ለእያንዳንዱ ድሃም ሁለት ማርትሬዛ ብር እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር::

እኩለ ቀን ገደማ ላይ 3000 የሚሆኑ ድሆች ከቤተ መንግስቱ ገቡ:: ጓደኛማቾቹ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በዓሉ ከሚደረግበት ቦታ ቀደም ብለው ደርሰዋል:: ሁለቱም በኪሶቻቸው ቦንብ ይዘዋል::

ማርሻል ግራዚያኒ ለተሰበሰበው የአዲስ አበባ ሕዝብ ንግግር ሲያደርግ የያዙትን ቦንብ ወረወሩት:: ለ3ኛ ግዜ የተጣለው ቦንብ የፋሽስት ኢጣሊያ መኳንንት ካሉበት ቦታ ፈነዳ:: ግራዚያኒ በጀርባው ወደቀ::

በቀጠለው ጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሌሎች ቦንቦች ተከታትለው ተጣሉ:: ከጥቂት ግዜ በኋላ (ያለማቋረጥ ለ3ሰዓት ከተካሄደው ተኩስ በኋላ) ባለ ጥቁር ሸሚዞች የኢጣሊያ ሾፌሮች የቅኝ ግዛት ወታደሮች በአዲስ አበባ ከተማ እየዞሩ ሕዝቡን ይፈጁት ጀመር::

የካቲት 12 ቀን የጀመረው እልቂት በ3 ቀን 30,000 ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከተገደሉ በኋላ ሌላው እየታፈሰ ወደ በረሃ እስር ቤቶች ተላከ...

የተከፈለልንን አንረሳም!

ክብር ለሰማዕታት!

ተመስገን ገብሬ ስለ የካቲት እልቂት በአይኑ ያየውን ህይወቴ በሚለው መፅሐፉ እንዲህ ይተርካልዛሬ ቀኑ እሁድ ነበር።የተያዝንበትም ዓርብ በስምንት ሰዓት ነበር ።ከዚያ እስከዛሬ ውኃና እህል የሚ...
19/02/2024

ተመስገን ገብሬ ስለ የካቲት እልቂት በአይኑ ያየውን ህይወቴ በሚለው መፅሐፉ እንዲህ ይተርካል

ዛሬ ቀኑ እሁድ ነበር።የተያዝንበትም ዓርብ በስምንት ሰዓት ነበር ።ከዚያ እስከዛሬ ውኃና እህል የሚባል እንኳን ለመብል ማግኘት ፤ ያየም የለም ፤ ፀሀይ በዚህ ቀን ሲተኩስ ሰው ሁሉ ልብሱን እያወለቀ በራሱ ላይ ተከናነበው ። በዚህም መከናነብ የፀሀዮ ትኩሳት ሲበርድ ውሃውን ጥማት መከላከል የሚችሉ መስሏቸው ነበር ።

ከሌላው እስር ቤት በቀር በዚህም እስር ቤት ውስጥ የነበረው እስረኛ እነርሱ ጣሊያኖች እንደገመቱት 18,000 ነበር ። ከረሃቡና ከጥማቱ የተነሳ እስረኛውም ሁሉ መናገር አይችልም ነበር ።ነፍሱ ገና አለቀው እያለች ነው እንጂ ሁሉም ደክሞ ይጠራሞት ነበር ።ለመተላለፍ እስከማይቻል ድረስ ያ ትልቁ ሰፊ ሜዳ ጠቦ ነበር ፤ አንዱ እየተጋፋ መጣ ።ጠርሙስ በእጁ ነበር ።ፊቱ ክስመት ገብቶ ነበር ። ከአጠገባችን ቆሞ ሊነግረን ፈለገ ።ገና ከንፈሩን ማላቀቅ ግን አልቻለም ።ከውሃ ጥማት የተነሳ ረድዔት በሚፈልግ ዓይን በሚያሳዝን ተኩሮ ወደ እኛ ተመለከተ ።

በታላቅ ችግር በውኃ ጥማት የተያያዘውን ከንፈር አላቀቀው ።ደካማ በሆነ ድምጽ " እባካችሁ! እባካችሁ! " ሲል ሰማነው ፤ነገሩን የሚለውን አጥርተን አልሰማነውም ነበርና ልንሰማው እንድንችል ወደ እኛ በጣም ቀረበ ። "እባካችሁ ከእናንተ ጨብጦ የሌላችሁ ሽንቱን በዚህ ጠርሙስ ይስጠኝ ።ወንድሞቸ ሁለቱ በውሃ ጥማትአቶ ሞቱ ፤ እኔም ልሞት ነኝ ፤ እባክዎ ጨብጦ ባይኖርዎ ሽንትዎን እባክዎ ጌታ ይስጡኝ " ብሎ ልመናውን ወደ አቶ ገብረመድህን አወቀ አበረታው ።

ገብረመድህን አወቀም " እኔም እንደ አንተ ነኝ ውሃ ከጠጣሁ ሶስት ቀኔ ነው ፤ ከየት ሽንት አመጣለሁ " አለው ።እኛንም አልፎ እየዞረ ሲለምን አልቆየም ፤እስከተንተርሶ መጨረሻ ደክሞት ነበር ። መናገርም አቃተው ።እንደ ድንጋይም በአጠገባችን ጥጊት ጊዜ ተጋድሞ በሕይወት ቆየ ።በመጨረሻም ግን እንደ እንቅልፍ በሞት ያችን ድንጋይ እንደ ተንተራሰ አሸለበ ።በዚህ ቀን በውኃ ጥማት ብቻ ከመቶ በላይ እስረኛ ከጥዋት እስከ 7 ሰዓት ሞቱ ።

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዓለምን ያስደነቀው ኢትዮጵያዊ የታሪክ ክስተት... ታላቁ የአድዋ ድል!  የኢትዮጵያዊያንን አንድነት እና ጀግንነት ያስመሰከረ፣ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ጮራ የፈነጠቀ...
18/02/2024

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ

ዓለምን ያስደነቀው ኢትዮጵያዊ የታሪክ ክስተት... ታላቁ የአድዋ ድል! የኢትዮጵያዊያንን አንድነት እና ጀግንነት ያስመሰከረ፣ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ጮራ የፈነጠቀ ደማቅ ድል...አድዋ! ከ128 ዓመታት በፊት ፣ ድሉን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ የታተሙ ጋዜጦች ዜናውን በሰፊው ዘግበውት ነበር። በአሜሪካ፣ የአትላንታው ጋዜጣ "MENELIK VICTORIOUS" ብሎ ነበር ዜናውን በትልቁ ያበሰረው...

ክብርና ሞገስ ለጀግኖቻችን 💚💛❤️

#ወርሃየካቲት
#አድዋ128

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለዓለም አቀፍ የፖስታ ሕብረት ኢትዮጵያ ወደ ሕብረቱ እንድትገባ ደብዳቤ ፅፈው ጠየቁ።
13/02/2024

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለዓለም አቀፍ የፖስታ ሕብረት ኢትዮጵያ ወደ ሕብረቱ እንድትገባ ደብዳቤ ፅፈው ጠየቁ።

የ ዛሬ 58 ዓመት 👉 ጥር 27 ቀን 1957 ዓ.ም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተመርቆ ተከፈተመሀል አራዳ ላይ የሚገኘው የማዘጋጃ ቤት ህንፃ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገለት...
04/02/2024

የ ዛሬ 58 ዓመት 👉 ጥር 27 ቀን 1957 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ተመርቆ ተከፈተ

መሀል አራዳ ላይ የሚገኘው የማዘጋጃ ቤት ህንፃ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገለት በ8 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ህንፃ ነበር። ህንፃውን ዲዛይን ያደረገው አርክቴክት አርትሮ ሜዜዲሚ የሚባል ጣሊያናዊ ሲሆን ኢንጅነር መኮንን ሙላቱ የተባሉ ኢትዮጵያዊ የቁጥጥር ስራውን በመስራት ለአዲስ አበባ ከተማ ታላቅ ውለታ ውለዋል።

ግርማዊነታቸው ጥቅምት 23 ቀን 1942 ዓ.ም የሕንፃ ግንባታውን ለማስጀመር የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡ ሲሆን (ህንፃው ዲዛይን ሲደረግ 600 መቶ ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲኖሩትና የመኪና ማቆሚያና መናፈሻ ቦታ ጨምሮ በ75 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ እንዲያርፍ ነው) ተመርቆ የተከፈተው ግንባታው ከተጀመረ ከ 15 ዓመት በኋላ ጥር 27 ቀን 1957 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ ነበር።

ወደ ሕንፃው ሲገባ በሚታየው ሰሌዳ ላይ የሚከተለው ጽሁፍ ሰፍቶ ይታያል፦

«ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለመናገሻው ከተማ ለአዲስ አበባ ሕዝባቸው፣ ለማኅበራዊ ኑሮው፣ ለኤኮኖሜውና ለባህሉ ዕድገት አማካይ የአገልግሎት ቤት ይሆን ዘንድ ፈቅደው ያሠሩትን ይህን ሕንፃ፣ በሠላሳ አራተኛው ዘመነ መንግሥታቸው መርቀው ከፈቱ።»

©️ enkssm

የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ሐውልት በትውልድ ስፍራቸው ደብረ ታቦር ቆመላቸው።
03/02/2024

የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ ሐውልት በትውልድ ስፍራቸው ደብረ ታቦር ቆመላቸው።

ሮያል አርት አካዳሚ  ለንደን  ይህ  የጥበብ ውጤት በአርቲስት ታቫሬስ ስትራቻን በሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ 'የመጨረሻው እራት' አምሳያ የተሰራ ነው። አርቲስቱ ስያሜውን 'የመጀመሪያው ራት' ብሎታል...
01/02/2024

ሮያል አርት አካዳሚ

ለንደን

ይህ የጥበብ ውጤት በአርቲስት ታቫሬስ ስትራቻን በሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ 'የመጨረሻው እራት' አምሳያ የተሰራ ነው። አርቲስቱ ስያሜውን 'የመጀመሪያው ራት' ብሎታል።

ከ 17ኛው ክ/ዘመን እስከ ዛሬ ድረስ ታላቅ አስተዋፅዖ ላበረከቱ 12 ጥቁር ሰብዕናዎች የተሰራ መታሰቢያ ሐውልት ነው። ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በታቫረስ ስትራቻን “የመጀመሪያው እራት” ማዕከላዊ ቦታ ላይ ተመስለዋል።

Entangled Pasts 1768-now: Art, Colonialism and Change (3 February-28 April)

💚💛❤️

ዛሬ የድል በዓል መታሰቢያ ቀን ነው።ጥር 18, 1879ዓ.ም.የዶጋሊ ድል 137ኛ ዓመት!በታላቁ የኢትዮጵያ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳ (አባ ነጋ) ወራሪው የጣልያን ጦር 500 ወታደሮች ከነአዛዣ...
26/01/2024

ዛሬ የድል በዓል መታሰቢያ ቀን ነው።
ጥር 18, 1879ዓ.ም.
የዶጋሊ ድል 137ኛ ዓመት!

በታላቁ የኢትዮጵያ ጀግና ራስ አሉላ እንግዳ (አባ ነጋ) ወራሪው የጣልያን ጦር 500 ወታደሮች ከነአዛዣቸው በዶጋሊ ተደምስሰዋል። ጣሊያን በሰው ሀገር ገብተው ለሞቱ ወታደሮቿ መታሰቢያ "ለዶጋሊ ጀግኖች" ብላ በሮም አደባባይ "ፒያዛ ዴ ቹክቼንቶ" የአምስት መቶዎቹ አደባባይ የሚል ትርጓሜ ያለው ሐውልት አቁማለች። ራስ አሉላ የጀግኖች ጀግና በመባል የሚታወቁ ታላቅ የኢትዮጵያ ባለውለታ ናቸው።

"መብቱን ዮሐንስ ላሉላ ቢሰጠው
እንደ ቀትር እሳት ክርክም ገላመጠው
ጣሊያንም ወደቀ እያንቀጠቀጠው
አጭዶና ክምሮ እንደገብስ አሰጣው።"

ታሪክን የኋሊት ....   ደጃች ካሳ ምርጫ በሥመ መንግሥታቸው " አፄ ዮሐንስ ራብዓይ (አራተኛ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ " ተብለው በጥር 13 ቀን 1864 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲ...
22/01/2024

ታሪክን የኋሊት ....

ደጃች ካሳ ምርጫ በሥመ መንግሥታቸው " አፄ ዮሐንስ ራብዓይ (አራተኛ) ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ " ተብለው በጥር 13 ቀን 1864 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን በአቡነ አትናቴዎስ እጅ ዘውድ ጫኑ።

ፎቶ፦ አጼ ዮሐንስ ልጃቸው ራስ አርአያሥላሴ

ታሪካዊ ኪነህንጻ፣ ጎንደር።ደብረብርሀን ስላሴ።ጎንደር የሚገኘው ታሪካዊው ደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስትያን ከ1930ዎቹ ጀምሮ ቀስ በቀስ ውጫዊ ምስሉ እየታደሰ የመጣ ታሪካዊ ቤተክርስትያን ነው...
22/01/2024

ታሪካዊ ኪነህንጻ፣ ጎንደር።

ደብረብርሀን ስላሴ።

ጎንደር የሚገኘው ታሪካዊው ደብረብርሀን ስላሴ ቤተክርስትያን ከ1930ዎቹ ጀምሮ ቀስ በቀስ ውጫዊ ምስሉ እየታደሰ የመጣ ታሪካዊ ቤተክርስትያን ነው። በተጨማሪም አውዳዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ውስጣዊ እድሳትም በየወቅቱ እየተካሄደለት ቆይቷል። ይሄ ታሪካዊ ቤተክርስትያን ከዚህ ቀደም ክብ በሆነና በፈረሰ የቤተክርስትያን መሰረት ላይ እንደተገነባም ይታወቃል።

እንኳን ለከተራ (ለጥምቀት) በዓል አደረሳችሁ ፎቶ Yidney Yidney 🙏
19/01/2024

እንኳን ለከተራ (ለጥምቀት) በዓል አደረሳችሁ

ፎቶ Yidney Yidney 🙏

** በብዙ ገዢዎች ተከፋፍላና ወድቃ የነበረች አገራቸውን ወደ ነበረችበት አንድነቷ ለመመለስ የደከሙት ....** የግል ዝና እንጂ የአገር ጉዳይ የማይሰማውን የዘመናቸውን መኳንንት ቢሾሙት እየ...
15/01/2024

** በብዙ ገዢዎች ተከፋፍላና ወድቃ የነበረች አገራቸውን ወደ ነበረችበት አንድነቷ ለመመለስ የደከሙት ....

** የግል ዝና እንጂ የአገር ጉዳይ የማይሰማውን የዘመናቸውን መኳንንት ቢሾሙት እየሸፈተ ቢሸልሙትና ቢያምኑት እየከዳ ያስቸገራቸውን መኳንንትና ህዝብ በጭካኔ በመቅጣት የታወቁት ....

** ኢትዮጵያን ከተለያዩ መኳንንት አገዛዝ አውጥተው በአንድ መንግሥት እንድትተዳደር ለማድረግ ለተከታዮቻቸው ለአጤ ዮሐንስና አጤ ምኒልክ መጓዣውን መንገድ በሕይወታቸው የከፈቱት .....

እናትና አባቱ ያለ አንድ አልወለዱ
አባ ታጠቅ ካሳ ያ ወንዱ ያ ወንዱ

የተባለላቸው ....

ካሣ ኃይሉ በሥመ መንግሥታቸው አጤ ቴዎድሮስ ሁለተኛ ከአባታቸው ከአቶ ኃይሉ ወልደጊዮርጊስ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አትጠገብ ወንድ በወሠን ልክ ከዛሬ 205 ዓመት በፊት በጥር 6 ቀን1811 ከጎንደር ከተማ 12 ኪሎሜትር ርቃ ከምትገኝ ዳዋ ከተባለች መንደር ተወለዱ።

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።በዓሉ የደስታ እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን:: 🌲 መልካም የገና በዓል! 🌲
07/01/2024

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የደስታ እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን::

🌲 መልካም የገና በዓል! 🌲

የዓመቱን የመጀመሪያ የአዳር (camping) መርሃ ግብር በታሪካዊው የመናገሻ ሱባ ጥብቅ ደን ውስጥ በቅርቡ የምናካሄድ ይሆናል
04/01/2024

የዓመቱን የመጀመሪያ የአዳር (camping) መርሃ ግብር በታሪካዊው የመናገሻ ሱባ ጥብቅ ደን ውስጥ በቅርቡ የምናካሄድ ይሆናል

Address

Mozambique Street, Tselere Building
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኮረማሽ-Koremash posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኮረማሽ-Koremash:

Videos

Share


Other Historical Tour Agencies in Addis Ababa

Show All

You may also like