17/06/2024
ለክረምቱ እነሆ መድኃኒቱ…
መልዕክታችንን በወዳጅ ጥያቄ እንጀምርና … "ዓመቱ እንዴት እያለፈ ነው?" እንበላችሁ! በርግጠኝነት ጥሩ እየተሸኘ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን!! ታዲያ ለእረፍት ጊዜያችሁስ "ምን አቀዳችሁ? የት ለማሳለፍስ አሰባችሁ?" ስንል ብንጠይቀና፤ በኛ በኩል ያዘጋጀነውን ግሩም አማራጭ ብንጠቁማችሁስ?
ሊንክና ኦስካር ትራቭሎች ነን!! ፋና ወጊ የሆንበትን የኅብረት የዑምራ ፓኬጆች በመልከ ብዙ የጉዞ አማራጭ አሰናድተን የበርካቶችን ናፍቆት ማስታገስ ተሳክቶልናል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ለክረምቱ የተጣመሩበትን ልዩ ፓኬጅ አዘጋጅተን፤ ካለፉት ጊዜያት በተለየ መልኩ የ13 ቀናት የመካና መዲና ቆይታችሁን መቼም የማይረሳ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናል፡፡
ሁልጊዜም አዳዲስ አማራጮችን ማስተዋወቅ መለያችን ነውና፤ ዘንድሮ ቁርኣንን ለሃፈዙ ልጆችዎና በያዝነው የትምህርት ዘመን አስደናቂ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለስኬታቸው የሚመጥን ሽልማት ካሰቡ፤ ሩቅ ሳይሄዱ ለውስን ሃፊዞችና ታታሪ ተማሪዎች ባዘጋጀነው ልዩ ቅናሽ በመጠቀም የልዩ ጉዞው አካል አድርገው ልጆችዎን ለተሻለ ውጤት ያዘጋጇቸው!!!!
በዘመነ አገልግሎትና በተቀላጠፈ መስተንግዶ በሚቆየው ልዩ የቤተሰብ ፓኬጃችን ዘጠኝ ቀናትን በመካና፤ ቀሪዎቹን አራት ቀናት ደግሞ በመዲና እንዲያሳልፉ ስንጋብዝዎ፤ የመጀመሪያው ዙር ምዝገባ እንደሚጠናቀቅ አስቀድመን በማሳወቅ ነው!!
ስለ ጉዞውና የፓኬጅ አማራጮቻችን የተሟላ መረጃ ለማግኘት በ 0911289096፣
በ 0952645262፣ እና በ 0118268788 ላይ ይደውሉልን!! jEDDA travel agency visa and ticket information !!