02/09/2020
🇩🇪🇫🇮🇫🇷🇬🇧ምን አዲስ ነገር አለ??🇬🇱🇮🇱🇵🇱🇺🇸
(ለትምህርት ፣ለንግድ፣በDV አድል፣ በጋብቻ ወይም በጉብኝት ከሀገር ለመውጣት እያሰቡ በመረጃ እጥረት ተቸግረዋል?)
02 Sep 2020
ውድ ቤተሰቦቻችን በስልክም በinboxም ምን አዲስ ነገር አለ? የት ኢምባሲ ተከፈተ? Covid ምርመራ ይጠየቃል ወይ? online አፕላይ ማድረግ ይቻላል ወይ? DV ደርሶኝ ነበር እድሌ ሊባክን ነው ወይ? የጋብቻ ፕሮሰስ ጀምሬ ነበር ምን ላድርግ? I-20, Acceptance Letter ቀኑ አለፈ ምን ይሻላል? የሚሉ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ እየደረሱን ስለሆነ አሁን ባለንበት ሰዓት ያሉትን ሁሉንም መረጃዎች በአንድ ላይ ጠቅለል አድርገን እንሆ ብለናል።
ነጋዴ ኖት?💵💵💵💸💸💸
:- ዱባይ ወደቀድሞ የንግድ ሁኔታ እየተመለሰች ሲሆን ከበፊቱ የተለየ ነገር ያለው ከቪዛ ጋር ተጨማሪ የጤና ኢንሹራንስ ማሰራት እና ሶስት ቀን ያላላፈው የኮቪድ ምርመራ ይዞ መሄድ ይኖርቦታል፤ የትኬት ዋጋም እስከ 35% ጭማሪ አሳይቷል።
:- ቻይና የአየር ድንበሮቿ ዝግ ሲሆኑ መች እነሚከፈት ለጊዜው የወጣ መግለጫ የለም።
:- ወደ ባንኮክ መብረር የሚቻል ሲሆን በፊት ይጠየቅ ከነበረው hotel booking በተጨማሪ 72 ሰዓት ያላለፈው የ covid ምርመራ ውጤት እና የጤና ኢንሹራንስ መያዝ ግዴታ ሆኗል፤ የትኬት ዋጋ በተመለከተ እስከ 20% ጭማሪ አሳይቷል።
፦ ወደ ቱርክ ለመግባት ፕሮሰስድ ቪዛ የሚያስፈልግ ሲሆን አዲስ አበባ የሚገኘው ኢምባሲ በወኪሉ በኩል የቪዛ ማመልከቻዎች መቀበል የጀመረ ሲሆን አዲስ የሚሰጡት ቪዛዎች የ1አመት ቆይታ ያላቸው ሆነዋል፤ የአየር ትኬት ዋጋ በአንፃሩ ያን ያህል ጭማሪ አላሳየም።
ተማሪ ኖት???👨🎓👩🎓👨🎓👩🎓
(Schengen Area) ፦ የሸንገን አባል ሀገራት ሙሉ በሚባል ሁኔታ የትምህርት አፕሊኬሽን በየኢምባሲያቸው እየተቀበሉ ሲሆን ቪዛ ያገኙ ተማሪዎች የኮቪድ ምርመራ ይዘው ወደ ትምህርት ሀገራቸው መብረር ይችላሉ።
: - አዲስም ሆነ ቀደም ብለው አመልክተው i-20 የመጣላቸው ተማሪዎች በሙሉ ኢምባሲ ዝግ ስለሆነ የመረጡትን ሴሚስተር ወደ January intake ቀይረው ኢምባሲ እስኪከፈት መጠበቅ ይኖርባቸዋል።
፦ የካናዳ ትምህርት ቤቶች የአካል ትምህርት ያልጀመሩ ሲሆን አዲስ አመልካቾችን ግን መቀበል ጀምረዎል፣ acceptance የመጣላችሁ ተማሪዎች እንደበፊቱ በVFS ሳይሆን በ online የቪዛ ማመልከቻ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ውጤቱ ሲመጣ ወደ VFS በማምራት passport እና Biometric የምትሰጡበት መንገድ ይመቻቻል ተብሎ ይጠበቃል።
ጎብኚ ኖት???🛳✈️🚉⛵️🚁🛶
አሁን ባለንበት ሰአት ወደ US፣ Australia፣ Europe (Schengen Area)፣ UK እንዲሁም ሌሎች ትልልቅ ሀገራት ጎብኚዎችን እየተቀበሉ ስላልሆነ የቪዛ ማመልከቻም ማስገባት አይቻልም። በአንፃሩ ቱርክ እና አንዳንድ ሀገራት በራቸውን ለጉብኝት ከፍተዋል።
የቋሚ ነዋሪነት ፕሮሰስ ላይ ኖት?📧📨📧
(Schengen Area) ፦ ሁሉም በሚባል ደረጃ የ family reunion/ National Visa አመልካቾችን በበፊቱ ፍጥነት ባይሆንም እያስተናዱ ይገኛሉ።
:- የጋብቻ ወይም የ family reunion ፕሮሰስ ጀምራችሁ ፍይላችሁ NVC ደርሶ ቀጠሮ ቀን ብቻ የቀራችሁ ኢምባሲ እስኪከፈት መጠበቅ የሚኖርባችሁ ሲሆን፤ አዲስ የምትጀምሩ ደግሞ ከpetition እስከ NVC ያለውን ፕሮሰስ መጀመር ትችላላችሁ ነገር ግን ቀጠሮ የሚሰጣችሁ ኢምባሲ ሲከፈት ይሆናል
እደለኞች እና ኬዝ ነምበራችሁ ከ 15,000 በላይ ሆኖ ኢንተርቪው ሳታደርጉ የቀራችሁ አመልካቾች የ DV 2020 መጨረሻ ቀን OCT 01 2020 ቀን ሲሆን እሱ ቀን ካለፈ በኃላ አዲስ ህግ ካልወጣ በስተቀር ኢንተርቪው የመጠራት እድል አይኖራቸውም።
እድኞችም ኢምባሲ Jan 01 2021 ይከፈታል ብለን ብናስብ እና በድሮ አሰራር ፍጥነት ልክ ከሆነ የሚሰራው መጀመር ከሚጠበቅበት ሰዓት ዘግይቶ በመጀመሩ ምክንያት ከኬዝ number 35,000 በኃላ ያሉ እድለኞች ኢንተርቪው ያለመጠራት እድል ሊኖራቸው ይችላል ተብሎ ይገመታል።
፦ የጋብቻ የGroup five እና የጥገኝነት ፕሮሰስ የጀመራችሁ ሰዎች እስከ ኢንርቪው ያለውን ፕሮሰስ Nairobi ከሚገኘው High Commission ጋር ጉዳያችሁን በemail መከታተል ትችላላችሁ።
ለተጨማሪ መረጃ ወደ
[email protected]
ጥያቄዎችን መላክ ይችላሉ።
ማማከር እና የኛን እገዛ የምትፈልጉ ደንበኞች
you can visit our office at,
22 Mazoria, Near Golagol Round About, Town Square Mall, Office 706 or call our office
TEL +251966698535
Addis Ababa, Ethiopia