01/03/2024
ቤዛ (ኅብረ ዝማሬ)
ይህቺ ሰንደቅ ዓላማ የክብር ምልክት
ሥፋት እና ምልዓት ርቀት አላት
በዓላማ አንድ ሆና ሦስት ናት በመልክ
ሆ …..
ላላ ….
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ብለን ተነስተናል ተስፋ አርገን ኹላችን
እኔ ለኔ ሳንል ቅድሚያ ለሀገራችን
እንደ ሐራሴቦን (ወጥተን ከሐራሴቦን) አንድ ዓላማ ይዘን
እንገባለን ከነዓን በፍቅር ተጉዘን
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን
የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን
በዘር በሃይማኖት በማሰብ አንሰናል
ይብቃ በኛ ዘመን ታሪክ ይወቅሰናል
እንቁም ተያይዘን በአንድነት
በኢትዮጵያዊነት
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (x2)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (x2)
የአንድነት ኃይል ጨለማን ድል ነሥቶ
ጨለማን ድል ነሥቶ (x2)
እናያለን አዲስ ፀሐይ ወቶ
አዲስ ፀሐይ ወቶ (x2)
በዝምታ ብንመስልም የተኛን
ብንመስልም የተኛን (x2)
ከተነሣን ማን ሊያቆመን እኛን
ማን ሊያቆመን እኛን (x2)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን (x2)
ቀልድ አናውቅም እኛ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን (x2)
ዓላማ ነው
ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (x2)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (x2)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን (x2)
አትምጡብን በቃ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን
―———————————————
ዜማ እና ግጥም — ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ)
ተጨማሪ የመግቢያ ዜማ — ቆየት ካለ ኅብረ ዝማሬ የተወሰደ
ሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግ እና ሊድ ጊታር — በረከት ተስፋዝጊ (ቤኪ)
ቴነር ሣክስ — ዘሪሁን በለጠ
ማስተሪንግ — ማሩ ዓለማየሁ (ማርቨን ስቱዲዮ)
ተቀባዮች ፤
1. ምኞት ኃይሉ (ዲጄ ዊሽ)
2. ልዑል ሲሳይ
3. ግሩም ታምራት
ምስጋና፥ ይህ ሥራ የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅዖፆ ላደረጋችሁ ወገኖች
በሙሉ
የሐራሴቦን ትርጓሜ
―――――――――
ሐራሴቦን የቦታ ስም ነው። እጅግ በረኃማ ነው።
ታሪክ : - እግዚአብሔር እሥራኤልን ከግብጽ ነጻ አውጥቶ መና ከሰማይ እያወረደ፣ ውኅ ከጭንጫ እያፈለቀ ሲመግባቸው ሰለቸን ብለው በእግዚአብሔር ላይ በማንጎራጎራቸው ሐራሴቦን ወደተባለው በረሃ እንዲወርዱ አዘዛቸው። በዚያም በእባብ እየተነደፉ አለቁ። በንስሐ ሲመለሱ ራርቶላቸው ሙሴን ከነሐስ የእባብ ምስል ሰርቶ በመስቀል ላይ እንዲሰቅለው ያን የሚያዩ እንዳይነደፉ፣ የተነደፉ እንዲድኑ፣ ማየት የማይችሉ የነሐሱ እባብ ሲደበደብ ድምፁን ሰምተው እንዲድኑ መድኃኒት ሠራላቸው።
ተምሳሌታዊ ትርጉም ፦
ሐራሴቦን = የሲዖል
ተናዳፊው እባብ = የሰይጣን