Getsemani Travel Agent

Getsemani  Travel Agent Travel to Jerusalem (Israel) with amazing price and package!!
(1)

3 ቀን፡ አርብ ሰኔ 07/2016 ዓ.ም  (ዕለተ እርገት)📍ጠዋት ተነስተን ወደ አይነከርም በመሄድ እመቤታችን ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት የሄደችበትን ፣የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ፅንስ የእመቤታችንን ...
15/06/2024

3 ቀን፡ አርብ ሰኔ 07/2016 ዓ.ም (ዕለተ እርገት)
📍ጠዋት ተነስተን ወደ አይነከርም በመሄድ እመቤታችን ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት የሄደችበትን ፣የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ፅንስ የእመቤታችንን ድምፅ በሰማ ግዜ የዘለለበትን እና የተወለደበትን አይነከርምን ተሳልመን
📍ወደ ቤተልሔም በመሄድ የወተት ዋሻን በዚያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ገዳመ እየሱስና ጌታችን የተወለደበትን በረት ተሳልመን
🍽 በቤተልሄም ቴንት ሬስቶራንት ምሳ ተመግበን
📍 የእረኞቹን መስክ ጎበኝተን
ወደ እየሩሳሌም ከተማ በመመለስ
🏩🍽 በሆቴላችን ኦሊቨ ደርሰን ረፍት ራትና አዳር በዝያው ሆኗል፡

ቀን 2: ሐሙስ ሰኔ 06/ 2016 ዓ. ም (ዕለተ እርገት)ከሌሊቱ 9:30 ሰዓት በመነሳት 📍ወደ ዴር ሱልጣን መድሐኒዓለም በመሄድ በስረዓተ ቅዳሴው እና በበዓሉ ስርዓት ላይ እንዲሳተፉ በማድረ...
15/06/2024

ቀን 2: ሐሙስ ሰኔ 06/ 2016 ዓ. ም (ዕለተ እርገት)
ከሌሊቱ 9:30 ሰዓት በመነሳት
📍ወደ ዴር ሱልጣን መድሐኒዓለም በመሄድ በስረዓተ ቅዳሴው እና በበዓሉ ስርዓት ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ አስቀድሰንና አስቆርበን ቁርሳችንንም በዚያው ተመግበን
📍ወደ ደብረዘይት ተራራ በመውጣት ይፀልይበት የነበረውንና አባታችን ሆይ የተባለውን ፀሎት ያስተማረበትን የኤሊዮን ዋሻን
📍አንዲሁም በእለተ ቀኑ የሚከበረውን ያረገበትን ቦታ አይተንና ተባርከን እየሩሳሌም ከተማን ከደ/ዘይት ተራራ ላይ ተመልክተን
🍽 ምሳችንን በእዚያው በሚገኝ እየሩሳሌም ሆቴል ተመግበን
ለበዓሉ ፣ለቆረቡት ሰዎች ክብር ከሰዓት በኋላ እረፍት እንዲሆን በማሰብ 8:00 ሰዓት ላይ
📍ወደ ሆቴላችን ኦሊቭ በመመለስ እረፍት፣ እራት እና አዳር በዝያው ሆኗል ::

ጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል
+251911607196
+251947414141

15/06/2024

የዕርገት በዓል ጉብኝት
መነሻ ቀንና 1ኛ ቀን ፦ ሰኔ 5-5 2016 ዓ.ም
✈️ ከቦሌ አወሮፕላን ማረፊያ እኩለ ሌሊት ላይ ተነሰተን ቴላቪቨ ቤንጎሪዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማታ ላይ ደርሰን የሀገሩን የጉሙሩክ ስረአት አጠናቀን
📍ማታ5 ፡00 ሰአት ላይ በአውቶቡሶቻችን ተሳፍረን
📍 እየሩሳሌም ወደሚገኘው ሆቴላችን ኦሊቭ ሆቴል አምርተን የክፍል ቁልፎቻችንን ተረክበን
🍽 በሆቴላችን አዳር አድርገናል፡፡

15/06/2024

ሰላም የጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል ቤተሠቦች እንኳን ለጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እርገት በዓል አደረሳችሁ
እንደተለመደው ዛሬም የእርገት በአልን ለማክበር ቤተሠቦቻችንን ይዘን እየሩሳሌም ተገኝተናል ለተከታታይ ቀናቶች የምናደርገውን ጉብኝት እንድትከታተሉን እነጋብዛችኋለን

ጌተሰማኒ የጉዞ ወኪል
+251911607196
+251947414141
አዲስ አበባ

አስረኛ ቀን፡ አርብ ግንቦት 2 ቀን2016 ዓ.ም   📍 ጠዋት ተነስተን ወደ አላዛር ከተማ በማቅናት በዚያ የሚገኘውን✅ የአቡነ ተ/ሃይማኖት ገዳም ጎብኝተንና ተባርከን 📍 ከዝያም አይነከርም በ...
11/05/2024

አስረኛ ቀን፡ አርብ ግንቦት 2 ቀን2016 ዓ.ም
📍 ጠዋት ተነስተን ወደ አላዛር ከተማ በማቅናት በዚያ የሚገኘውን
✅ የአቡነ ተ/ሃይማኖት ገዳም ጎብኝተንና ተባርከን
📍 ከዝያም አይነከርም በመሄድ
✅ እመቤታችን ኤልሳቤጥን ለመጎብኘት የሄደችበትን
✅የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ፅንስ የእመቤታችንን ድምፅ በሰማ ግዜ
የዘለለበትን እና የተወለደበትን አይነከርምን ተሳልመን ወደ
📍 እየሩሳሌም ምሳና የግብይት ጊዜ እንዲኖረን ተደርጎ
🏨 ወደ ሆቴላችን ተመልሰን ራትና አዳር በዚያው ሆኗል፡፡

10/05/2024

ዘጠነኛ ቀን : ሐሙስ ግንቦት 01/2016 ዓ. ም
🏨 ከጠዋቱ 1:30 ላይ ከሆቴላችን Checkout አድርገን
📍የዕለቱ ጉዟችንን በጸሎት እና በአስተባባሪው የዕለቱ መርሐግብር ገለጻ ጀምረን
📍 በቀጥታ ወደ ቃና ዘ ገሊላ በመጓዝ ጌታችን የመጀመሪያ ተአምራቱን በይፋ የገልፀበትን ቅዱስ ስፍራ ጎብኝተንና ተሳልመን ጥንድ ሆነው መጥተው በቃና ዘገሊላ ለተገኙ በትዳር እየኖሩ ላሉ ባልና ሚስቶች መታሰቢያ በማድረግ
📍በዚያው ቦታ ለመታሰቢያ የሚሆን የወይን ግብይት ፈፅመንወደ ሀይፋ ከተማ በማምራት
📍 በቀርሜሎስ ተራራ የኤልያስን ዋሻ ተሳልመን
📍በሜድትራንያን የባህር ዳርቻ ረዥም ጉዞ አድርገን
📍ቴላቪቭ ገብተን የቆዳ ፋቂውን ሰማዖን ቤት እና የቅዱስ ጴጥሮስን ታላቅ ቤተክርስቲያን አይተን
📍በባህር ዳርቻ ረፍት አድርገን ምሳ በሴንት ጆርጅ ሬስቶራንት ተመግበን
📍በያፎ የቅዱስ ጴጥሮስን ቤተክርስቲያንና የሰማኦን ቆዳ ፋቂውን ቤት ጎብኝተንና ተሳልመን
📍 ወደ እየሩሳሌም አምርተን በኦሊቭ ሆቴላችን የመኝታ ክፍል ቁልፎቻችንን ተቀብለን እራት እና አዳር በዝያው ሆኗል ::

ስምንተኛ ቀን፡ እሮብ ሚያዝያ 30 ቀን 2016ዓ.ም📍 ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት የዕለቱ ጉብኝታችንን ጀምረን ወደ ገሊላ ባህር ዙሪያ መግደላን (የማርያም መግደላዊትን ሀገር )  የተራራው ስብከት ...
09/05/2024

ስምንተኛ ቀን፡ እሮብ ሚያዝያ 30 ቀን 2016ዓ.ም
📍 ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት የዕለቱ ጉብኝታችንን ጀምረን ወደ ገሊላ ባህር ዙሪያ መግደላን (የማርያም መግደላዊትን ሀገር ) የተራራው ስብከት ቦታን (ባትትዩድ ) ካየን በኃላ
📍 ጌታችን በሁለት አሳ እና በአምስት እንጀራ 5000 ሽ ህዝብ የመገብበትን ቦታ በረከት ወስደን
📍 የቅዱስ ጴጥሮስን መኖሪያ ጎብኝተን እንዲሁምን ታላቋን ቀፈርናሆምንና ጌታችን በርካታ ተዓምራት የሰራባቸውን ቦታዎችና የቅዱስ ጴጥሮስ የገነትን ቁልፍ የተቀበለበትን ቦታ ጎብኝተን
ከምሳ በኃላ ...
📍 በገሊላ ባህር ላይ የመርከብ መታሰቢያ ጉዞ ቆይታ አድርገን
📍 ራትና አዳር ቲቤሪያ ሪሴታል ሆቴል ሆኗል፡፡

ሰባተኛ ቀን፡ ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም (ኢየሩሳሌም - ናዝሬት - ቲቤሪያ)📍 በጠዋት በመነሳት  የሆቴል ክፍሎቻችንን ቁልፍ ካስረከብን በኋላ እቃችንን ጭነን 📍ወደ ደ/ታቦር ተራራ...
09/05/2024

ሰባተኛ ቀን፡ ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016ዓ.ም (ኢየሩሳሌም - ናዝሬት - ቲቤሪያ)
📍 በጠዋት በመነሳት የሆቴል ክፍሎቻችንን ቁልፍ ካስረከብን በኋላ እቃችንን ጭነን
📍ወደ ደ/ታቦር ተራራ በማቅናት
✅ ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበትን ቦታ ተሳልመን
✅ አንዲሁም የአካባቢውን መልካዓ ምድርና
✅ የአርማጌዲዮን ጦር የሚካሄድበትን ቦታ ቁልቁል አይተን
📍 ወደ ናዝሬት ገሊላ በመሄድ
✅ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብሥራት የተቀበለችበትን ፣
✅ ከምንጭ ውሃ ትቀዳበት የነበረበትንና ቤተ ዮሴፍ የተባለውን ቅዱሳት ሥፍራዎች በመሳለም
✅ ጎብኝተንና
✅ ተሳልመን
📍ወደ ትቤርያ ከተማ ተጉዘን
🏨 ሪሴታል ሆቴል ደርሰን የክፍል ቁልፎቻችንን ተረክበን ራትና አዳር በዝያው ሆኗል።

ስድስተኛ ቀን: ሰኞ ሚያዚያ 28/2016 ዓ. ም                                                                                          ...
07/05/2024

ስድስተኛ ቀን: ሰኞ ሚያዚያ 28/2016 ዓ. ም 📍ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት በመነሳት ወደ ባህረ ዮርዳኖስ በማምራት ተባርከን እና ተጠምቀን የጉዞ ቁርሳችንን በልተን
📍 ወደ ገዳመ ቆረንጦስ ሄደን
ቆይታችንን በኢያሪኮ አድርገን
📍 ምሳ በልተን እና ግብይት ፈፅመን
📍የኤልሳን ምንጭ ጠጥተን
📍በቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ገዳማችን ገብተን
✅ተሳልመንና
✅ተባርከን
✅አባቶቻችንን ጠይቀን
📍አንዲሁም የቀራጩ ዘኪዮስን ዛፍ አይተን 📍ወደ ሙት ባህር በማምራት ጥንታዊውን ✅የሶዶምና ገሞራ የጥፋት ቅሪት አይተን
📍 ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ ወደ ሆቴላችን ገብተን ራትና አዳር በዝያው ሆኗል ::

አምስተኛ ቀን : እሁድ 27/08/2016ዓ. ም እለተ ትንሣኤ📍ሌሊት ከቅዳሴ በሁዋላ የተዘጋጀውን ማስፈሰኪያ ቀምሰን 📍ሆቴላችን ገብተን አርፈን ✅ በድጋሜ ጠዋት በሆቴላችን ቁርስ ተመግበን ✅ ...
06/05/2024

አምስተኛ ቀን : እሁድ 27/08/2016ዓ. ም እለተ ትንሣኤ
📍ሌሊት ከቅዳሴ በሁዋላ የተዘጋጀውን ማስፈሰኪያ ቀምሰን
📍ሆቴላችን ገብተን አርፈን
✅ በድጋሜ ጠዋት በሆቴላችን ቁርስ ተመግበን
✅ ስለበዓሉ የግማሽ ቀን ረፍት ወስደን
✅ 6:30 ሰዓት ላይ በቀጥታ ወደ ተዘጋጀልን ልዩ የበዓል ምሳ በመሄድ በአስደሳች ሁኔታ አስከ 11:30 ሰዓት ቆይተን
በመቀጠል ምሽት 2:00 ላይ
📍የበዓል ራት ላይ ተሳትፈን በጥሩ ሁኔታ አስከ ምሽቱ 4:30 ሰዓት
✅ አምሽተን በዓሉን አሳልፈን አዳር በዝያው ሆኗል ::

መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልዎ
ጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል
+251911607196
+251947414141
+251910344587
አዲስ አበባ

አራተኛ ቀን - ቅዳሜ ሚያዚያ 26/2016 አ. ም 📍ጠዋት ተነስተን ወደ ደ/ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ገዳም ሄደን የሥዑር ቅዳሜ ስርዓተ ፀሎት ተሳትፈን 📍ወደ ቤተልሄም በመሄድ በ...
05/05/2024

አራተኛ ቀን - ቅዳሜ ሚያዚያ 26/2016 አ. ም
📍ጠዋት ተነስተን ወደ ደ/ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ገዳም ሄደን የሥዑር ቅዳሜ ስርዓተ ፀሎት ተሳትፈን
📍ወደ ቤተልሄም በመሄድ በገዳመ ኢየሱስ የኢትዮጵያ ገዳም ጥሩ ቆይታ አድርገን
📍እመቤታችን ወደ ግብፅ ስደት የጀመረችበትን የወተት ዋሻን ጎብኝተን
📍የተወለደበትን ቅዱስ ቦታ ተሳልመንና ተባርከን
📍የእረኞቹን ዋሻ ጎብኝተን ወደ እየሩሳሌም በመሄድ
📍 ሆቴላችን ኦሊቭ ደርሰን ለማታ የምንኩስና እና የቅዳሴ ስርዓት ዝግጅት አድርገን
📍ምሽት ላይ ወደ ደ/ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት በመሄድ
✅ የሚመነኩሱትን አስመንኩሰንና
✅ ሌሊቱን በትንሣዔው ብርሃን የቤተክርስቲያን ስርዓት ላይ ተሳትፈን
✅ በዝያው አስፈስከን
📍 ከንጋቱ 10:30 ላይ በሆቴላችን ደርሰን ረፍት አድርገናል፡፡

መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልዎት

3ኛ ቀን ስቅለትን በቀራንዩ የ14ቱ ምዕራፋት  ጉዞ ከጲላጦስ አደባባይ አስከ ጎሎጎታ                               25/8/16ጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል+251911607196+25...
04/05/2024

3ኛ ቀን ስቅለትን በቀራንዩ
የ14ቱ ምዕራፋት ጉዞ ከጲላጦስ አደባባይ አስከ ጎሎጎታ
25/8/16
ጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል
+251911607196
+251947414141
+251910344587

02/05/2024

ጤና ይስጥልን የጌተሠማኒ ቤተሠቦች እንደተለመደው
የትንሳኤን በአልን ለማክበር ጉዟችንን ወደ እየሩሳሌም አቅንተናል ረቡዕ ሚያዝያ 23/2016 ጡሀት ተነስተን ከሰአት በኋላ እስራኤል ቦሊንግርዩን አየር ማረፊያ ደርሰናል

29/02/2024

Watch, follow, and discover more trending content.

19/02/2024

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ እየሩሳሌም

የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ወደ ቅድስት ሀገር እየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ አዘጋጅተናል
መነሻ ቀን ሚያዝያ 23,2016/May 1,2024
መመለሻ ቀን ግንቦት 06,2016 May 14,2024
አሁኑኑ ይመዝገቡና ከኛ ጋ ተጉዘው ከበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ

ጌተሠማኔ የጉዞ ወኪል
ስልክ
+251947414141
+251911607196
+251910344587
+251118695756
አዲስ አበባ

ደውለው ያመልክቱ የተቀጣሪ ጾታ ሴት0947414141 / 0911607196
31/01/2024

ደውለው ያመልክቱ
የተቀጣሪ ጾታ ሴት
0947414141 / 0911607196

22/01/2024

የጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል ቤተሠቦች ለ2016 ዓም የጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዐል በቤተልሄም በመገኘት አክበረናል ቀጣዩን የእኩለ ጾም( ደብረዘይት ) እና የትንሳኤ በዐልንም በእየሩሳሌም ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀናል የምጡና ተመዝግበው ከኛ ጋር ጥሩ ግዜ በእየሩሳሌም ያሳልፋ
ስልክ
+251911607196
+251947414141
+251910344587
+251118695756
አዲሰ አበባ

09/01/2024

ክፍል 2

ለተከበራችሁ የጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል ቤተሠቦች እንኳን ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በአል እንኳን አደረሳችሁ

ዛሬ ቤተልሄም ነው ያለነው እግዛብሄር ፈቅዶልን ለአስራ ሶስተኛ ግዜ ለአስራ ሶስት አመት ያህል በዚች ቀን አዚህ ቦታ ተገኝተን ዘነድሮም በዐሉን እያከበርን ነው።
ሙሉን የክብረ በዐሉን ኘሮግራም በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ በነገው ቀን እቤተው ተቀምጠው ሙሉ ኘሮግራሙን ከዚሁ ከእየሩሳሌም እናስተላልፍለወታለን እንዲከታተሉን ጋብዘነወታል ።

ጌተሠማኔ የጉዞ ወኪል

09/01/2024

ለተከበራችሁ የጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል ቤተሠቦች እንኳን ለጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በአል እንኳን አደረሳችሁ

ዛሬ ቤተልሄም ነው ያለነው እግዛብሄር ፈቅዶልን ለአስራ ሶስተኛ ግዜ ለአስራ ሶስት አመት ያህል በዚች ቀን አዚህ ቦታ ተገኝተን ዘነድሮም በዐሉን እያከበርን ነው።
ሙሉን የክብረ በዐሉን ኘሮግራም በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ በነገው ቀን እቤተው ተቀምጠው ሙሉ ኘሮግራሙን ከዚሁ ከእየሩሳሌም እናስተላልፍለወታለን እንዲከታተሉን ጋብዘነወታል ።

ጌተሠማኔ የጉዞ ወኪል

ሀበሻ አስጎብኝ ድርጅት በአውሮፖሀበሻ አስጎብኝ ድርጅት በአውሮፖ የሻንጋይ ቪዛ ይዘው ለሚመጡ ኢትዮጵያኖች መልካም ዜና ይዞ መጥቷል የብዙ ቱሪስቶች መዳረሻ በሆኑት በአራት የአውሮፖ ከተሞች በ...
18/12/2023

ሀበሻ አስጎብኝ ድርጅት በአውሮፖ

ሀበሻ አስጎብኝ ድርጅት በአውሮፖ የሻንጋይ ቪዛ ይዘው ለሚመጡ ኢትዮጵያኖች መልካም ዜና ይዞ መጥቷል

የብዙ ቱሪስቶች መዳረሻ በሆኑት በአራት የአውሮፖ ከተሞች በፓሪስ ፣ በብራስል፣በአመስተርዳምና በሮም ለኢትዮጵያኖች የማስጎብኘት ስራ ጀምረናል።

ሀበሻ አስጎብኝ ድርጅት በነዚህ አራት ከተሞች እንግዳ ተቀብሎ በማስተናገድና በመሸኘት ረጅም ልምድ ባላቸው ኢትዮጵያውያኖች

# ከኤርፖርት ይቀበላል
# ሆቴል (አፖርትመንት)ያዘጋጃል
# ያስጎበኛል
# የባቡርና የባስ ትኬት ያመቻቻል
# ወደሚቀጥለው መዳረሻወት ይሸኛል
# ከልጆች ጋር ለሚመጡ የፖሪስ ዲስኒላንድ ትኬት እናዘጋጃለን

ከታች ባለው ዋትሳፕ፣ኢሚልና ቴሌግራም ያገኙናል

ለተሳካ የአውሮፖ ጉብኝትዎ ሀበሻ አስጎብኝ ምርጫዎ ይሁን

Tel=>0031686463105
[email protected]
Facebook=>Habesha.asgobegni

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ           ወደ ቅድስት ሀገር  እየሩሳሌም   2016 ዓ/ም የጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርሰቶስ ልደት በአል ምክንያት በማድረግ ወደ ቅድስት ሀገር እየሩሳሌም ተጉ...
09/12/2023

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ
ወደ ቅድስት ሀገር እየሩሳሌም
2016 ዓ/ም የጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርሰቶስ ልደት በአል ምክንያት በማድረግ ወደ ቅድስት ሀገር እየሩሳሌም ተጉዘን ጎብኝተን በረከት አግኝተን እንመለሳለን።
እርስዎም ከኛ ጋር ተጉዘው የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ
መነሻ ቀን ታህሳስ 23, 2016 ( JAN 2, 2023 )
መመለሻ ጥር 2, 2016( JAN 11, 2023 )
ምዝገባ ጀምረናል
ለበለጠ መረጃ
+251947414141
+251911607196
+251910344587
+251118695756
አዲስ አበባ

ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ. ም ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ላይ በመነሳት ወደ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ገዳም  በመሄድ በስርዓተ ቅዳሴው ተሳትፈንና የሚቆርቡትን አስቆ...
01/10/2023

ቅዳሜ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ. ም
ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ላይ በመነሳት ወደ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ገዳም በመሄድ በስርዓተ ቅዳሴው ተሳትፈንና የሚቆርቡትን አስቆርበን እስከ ምሳ ሰዓት በዚያው ቆይታ አድርገን ወደ ቤተልሔም በመሄድ በሳቫቫ ሬስቶራንት ምሳ ተመግበን ወደ ጽዮን ተራር በማምራት የፅዮን ተራራን ፣ የቅዱስ ዮሐንስ ቤት፣ የቅዱስ ዳዊትን መቃብር እና የአላዛር ቤትን/ የመጨረሻው እራት የተበላበትን / ፣ ጌታ ቅዱስ ጴጥርስን ዶሮ እስኪጮህ ሦስት ጊዜ ትከዳኛለህ ያለበትን ቤት ጎብኝተን ካጠናቀቅን በኋላ ወደሆቴላችን በመመለስ ረፍት አድርገን ለነገ ጉዞ እቃችንን በማዘጋጀት እራትና አዳር በቤተልሄም ማናጀር ስኩየር ሆቴል ሆኗል፡፡

26/09/2023

ጤና ይስጥልን የጌተሠማኒ ቤተሠቦች
እንደምን ሰነበታችሁ
የመስቀልን በአል በእየሩሳሌም ዴር ስሉጣን(ቀራንዮ) ለማክበር የተጓዙ ቤተሠቦቻችን የጉዞ መረሀ ግብር ምን ይመስላል በተከታታይ እናቀርብላችኋለን ተከታተሉን

በቀን 1፡ ማክሰኞ መስከረም 15/2016 ዓ. ም
ከ ቤንጎሪዮን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመነሳት ወደ ጋዛ ተጉዘን ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በቅዱስ ፊልፖስ የተጠመቀበትን ቦታ አይተንና ጠበል ተረጭተን ወደ ቤተልሄም በመሄድ በገዳመ ኢየሱስ የኢትዮጵያ ገዳም ጥሩ ቆይታ አድርገን እመቤታችን ወደ ግብፅ ስደት የጀመረችበትን የወተት ዋሻን ጎብኝተን ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበትን ቅዱስ ቦታ ተሳልመንና ተባርከን ምሳ በቤተልሄም ሳቫቫ ሬስቶራንት ተመግበን ወደ እየሩሳሌም በመሄድ ሆቴላችን ሻሎም ሬሞንየም ደርሰን የክፍል ቁልፎቻችንን ተረክበን በሆቴላችን ራትና አዳር አድርገናል፡፡

መልካም አዲስ አመት ለውድ የጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል ደንበኞች አዲሱ አመትየሠላም የጤና የፍቅርና ስኬት ዘመን ይሁንላችሁእንዲሁም አገራችንን ሠላም ያድርግልን+251911607196+251947414...
11/09/2023

መልካም አዲስ አመት ለውድ የጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል ደንበኞች
አዲሱ አመት
የሠላም የጤና
የፍቅርና ስኬት ዘመን ይሁንላችሁ
እንዲሁም አገራችንን ሠላም ያድርግልን
+251911607196
+251947414141
+251910344587
+2519118695756
አዲሰ አበባ

ጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል በዲጂታል ማርኬቲንግ እና የቤሮ ሪሲፕሽን ባለሙያ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ሆኖም በዚ መስክ ባለሙያ የሆናቹ ሰዋች በ 0911607196 / 0947414141 በመደወል የ...
28/08/2023

ጌተሠማኒ የጉዞ ወኪል በዲጂታል ማርኬቲንግ እና የቤሮ ሪሲፕሽን ባለሙያ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ሆኖም በዚ መስክ ባለሙያ የሆናቹ ሰዋች በ 0911607196 / 0947414141 በመደወል የበለጠ መርጃ ማግኘት ይችላሉ

ሰባተኛ ቀን - ማክሰኞ ነሐሴ 16 /2015  ዓ.ም. (እለተ ኪዳነምህረት ) እየሩሳሌም ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ላይ ከሆቴላችን በመነሳት ወደ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ገዳ...
24/08/2023

ሰባተኛ ቀን - ማክሰኞ ነሐሴ 16 /2015 ዓ.ም. (እለተ ኪዳነምህረት )
እየሩሳሌም
ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ላይ ከሆቴላችን በመነሳት ወደ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነምህረት የኢትዮጵያ ገዳም በመሄድ የበዓሉን ቅዳሴ አስቀድሰንና መቁረብ የፈለጉትን አቁርበን በቴክ አወይ የተያዘ ቁርስ ከተመገብን በኋላ ግዥ በገዳሙ ሱቅ አከናውነን ::
ወደ ፅዮን ተራራ በመሄድ ጥንታዊቷን የዳዊት መቃብር፣ጌታችን ሥጋውንና ደሙን በእለተ ሐሙስ የሰጠበትን ቦታ (የመጨረሻው ራት) የእመቤታችን የማርያምን መቃብር እና በክብር ያረገችበትን /ፍልሰታ ለማርያም/ ቦታ ጎብኝተንና ተሳልመን ምሳ ቤተልሔም ቴንት ሬስቶራንት ተመግበን ወደ ማረፊያ ሆቴላችን ሻሎም ሪሞንየም በመመለስ ለበዓሉ ክብር ቀሪውን ጊዜ ረፍት አድርገን ራትና አዳርም በዚያው ሆኗል::

ቀን 6: ሰኞ ነሐሴ 15/2015 ዓ. ም ከጠዋቱ 1:15 የዕለቱ ጉዟችንን በጸሎት እና በአስተባባሪው የዕለቱ መርሐግብር ገለጻ ጀምረን በቀጥታ ወደ ደብረ ታቦር በመሄድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢ...
23/08/2023

ቀን 6: ሰኞ ነሐሴ 15/2015 ዓ. ም ከጠዋቱ 1:15 የዕለቱ ጉዟችንን በጸሎት እና በአስተባባሪው የዕለቱ መርሐግብር ገለጻ ጀምረን በቀጥታ ወደ ደብረ ታቦር በመሄድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በገለፀበት ቦታ ላይ ተባርከንና ስለ ቦታው ሰፊ ገለፃ ተደርጎልን አንዲሁም ፀልየን ወደ ሀይፋ ከተማ በማምራት በቀርሜሎስ ተራራ የኤልያስን ዋሻ ተሳልመን በሜድትራንያን የባህር ዳርቻ ረዥም ጉዞ አድርገን ቴላቪቭ ገብተን ምሳ በአቡናስር ሬስቶራንት ተመግበን ልዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በመግባት ጎብኝተንና የሰማእትነት ተጋድሎ የፈፅመበትን ሰንሰለት አንደሁም አፅመ ቅዱሱን ተሳልመን ወደ ቴላቪቭ አምርተን በሻሎም ሪ ሞንየም ሆቴላችን የመኝታ ክፍል ቁልፎቻችንን ተቀብለን እራት እና አዳር በዝያው ሆኗል ::

አምስተኛ ቀን - እሁድ ነሐሴ 14 /2015  ዓ.ም.ጥብርያዶስከጠዋቱ 1:00 የዕለቱ ጉዟችንን ጀምረን ወደ ገሊላ ባህር ዙሪያ መግደላን (የማርያም መግደላዊትን ሀገር )  የተራራው ስብከት ቦ...
23/08/2023

አምስተኛ ቀን - እሁድ ነሐሴ 14 /2015 ዓ.ም.
ጥብርያዶስ
ከጠዋቱ 1:00 የዕለቱ ጉዟችንን ጀምረን ወደ ገሊላ ባህር ዙሪያ መግደላን (የማርያም መግደላዊትን ሀገር ) የተራራው ስብከት ቦታን (ባትትዩድ ) ካየን በኃላ ምሳ በልተን የቅዱስ ጴጥሮስን መኖሪያ ጎብኝተን እንዲሁምን ታላቋን ቀፈርናሆምንና ጌታችን በርካታ ተዓምራት የሰራባቸውን ቦታዎችና የቅዱስ ጴጥሮስ የገነትን ቁልፍ የተቀበለበትን ቦታ ጎብኝተን በገሊላ ባህር ላይ የመታሰቢያ ቆይታ አድርገን ወደ ሆቴላችን ክርስታል በማምራት እራት እና አዳር በዝያው ሆኗል ::

ቀን 4- ቅዳሜ ነሐሴ  /2015  ዓ.ም.ቤተልሄም  -   -ናዝሬት - ቲቤርያ በጠዋት የክፍል ቁልፍ አስረክበን ጌታችን አምላካችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ የለወ...
23/08/2023

ቀን 4- ቅዳሜ ነሐሴ /2015 ዓ.ም.
ቤተልሄም - -ናዝሬት - ቲቤርያ
በጠዋት የክፍል ቁልፍ አስረክበን ጌታችን አምላካችን መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውሃውን ወደ ወይን ጠጅ የለወጠበት የቃና ዘገሊላ ቦታ እና አስቀድሞ ይኖርበት የነበረውን የዶኪማስ መኖሪያ ቤት እና የመታሰቢያው ቤተ መቅደስ በመሳለም ጉዞ ፈፅመን የተለየ ስርአት ለትዳር አጋሮች አከናውነን ወደ ናዝሬት በማምራት በናዝሬት ከተማ ላይ የሚገኘው የማርያም ምንጭ እና የመታሰቢያው ቤተ መቅደስ እንዲሁም ናዝሬት ከተማ ላይ የሚገኘው አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ አስቀድሞ ይኖርበት የነበረ መኖርያ ቤት እና የመታሰቢያው ቤተ መቅደስ ። በመቀጠል መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ያበሰረበት ቦታ እና የመታሰቢያው ቤተ መቅደስ ተሳልመን ምሳ በናዝሬት ከተማ በሚገኝ የቱሪስት ሬስቶራንት ተመግበን ወደ ወይራ ዘይት ፋብሪካ በመሄድ ግዥ አከናውነን የዛሬ መርሐ ግብርን አጠናቀን ወደ ቲቤርያ ከተማ በማምራት በሪሴታል ሆቴል የማረፊያ ክፍሎቻችንን ተረክበንና ራት በዚያው በልተን አዳር በዚያው አድርገናል።

Address

Kazanchis To Urael Road, Glory Building 3rd Floor Office # 301
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 13:30

Telephone

+251911607196

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getsemani Travel Agent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Getsemani Travel Agent:

Videos

Share

Category