Tsadkane Mariam tours & car rent

Tsadkane Mariam tours & car rent Tsadkane Mariam tours & car rent will provides you,Any tayps of cars for long term and short term wi
(2)

Visit the steals filed in southern,Ethiopia.
21/03/2023

Visit the steals filed in southern,Ethiopia.

04/03/2023

የአድዋው ጦርነት አዋጊና የጦር አማካሪ የነበሩት
ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ

***
" የኢትዮጵያ ጦር የተዋጋው ሁዳዴን እየጾመ ነው"
" ታቦተ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ጦር መሃል ነበረ"
" አድዋ የተዋጋው የኢትዮጵያ ጦር አሰፋፈሩ የቤተ ክርስትያንን ፕላን ተከትሎ ነበር"
" አድዋ ጦርነት የተካሄደው በሁዳዴ ጾም ውስጥ ነው:: ጾም እንዳይሻር ጳጳሱ ገዘቱ"
" አቡነ ማቴዎስ ከዋናዎቹ የጦር አማካሪዎች አንዱ ነበሩ"
የአድዋ ዘመቻ ና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አስተዋጾ ብዙ ያልተወሳ ነገር አለ:: ጥቂቱን እንመልከት::

እየጾመ የተዋጋው የኢትዮጵያ ጦር

***
የአድዋ ጦርነት የተካሄደው በገና ጾምና በሁዳዴ ጾም ውስጥ ነው:: የአምባላጌ ና የመቀሌው ውጊያ የተካሄደው በገና ጾም ሲሆን - አድዋ ላይ በአሻሾ: ራዕዮና ሰማያታ ተራራና ሜዳ ላይ የካቲት 23 የተደረገው ዋናው የአድዋ ውጊያ ደግሞ የተደረገው በሁዳዴ ጾም ነው:: የያኔው ጾም ደግሞ እንዳሁኑ አልነበረም:: ክርስትያኑ ሁሉ ቀኑን ሙሉ ጾሞ የሚበላው ማታ ነበር::

በዚህ ምክንያት "ሰራዊቱ እንዳይደክምብኝ በማለት ንገሠ ነገሥቱ አጼ ምኒሊክ - ለጦርነቱ ሲባል የዘንድሮውን ጾም እንዳይጾም ዘማቹን ወታደር ይፍቱልኝ ::ጾሙ ለወታደሮቼ ይሻርልኝ" ብለው አቡኑን አቡነ ማቴዎስን ጠይቀው ነበር:: አቡነ ማቴዎስ ግን እምቢኝ አሉ:: "ወታደርም ቢሆን: ዘመቻም ቢሆን : ጾምን ሻሩ አልልም::" ብለው እምቢ አሉ::

ጳውሎስ ኞኞ " አጠ ምኒሊክ በሚለው መጽሓፉ ላይ ይህን አስገራሚ ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል ( ጳውሎስ ኞኞ ኣጤ ሚኒልክ ገጽ 172)

" የአድዋ ጦርነት የተካሄደው በገናና በሁዳዴ ጾም ነው::ክርስትያኑ ዘማች በዚያን ግዜ እንደነበረው አጿጿም ራቱን በልቶ እስከሚቀጥለው ጀምበር መጥለቅ ምንም አይቀምስም:: ውሃ እንኳን አይጠጣም ነበር:: ይሄን የተገነዘቡት አጤ ሚኒልክ ጳጳሱን አቡነ ማቴዎስን " ጦርነት ላይ መሆናችንን ያውቃሉ:: ሠራዊቱ በጦርነቱም : በጦሙም ተደራራቢ ጉዳት እንዳይደርስበት ያገኘውን እየበላ እንዲዋጋ ይፍቱት :: ቢያስፈልግ ከጦርነት መልስ ይጾማል " ቢሏቸው አቡኑ " አልፈታም " ብለው እምቢ አሉ:: ምኒሊክም በዚህ አዝነው " እግዚአብሔር የየዋህ አምላክ ይርዳው" አሉ:: " ይላል::

ሌላኛው ደራሲ ደግሞ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ አጼ ምኒሊክን " ስለ ኢትዮጵያ የሚዋጋው እግዚአብሔር ነው:: ሰልፉ የሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው:: ድሉም የኢትዮጵያ ይሆናል" ብለው መናገራቸውን ዘግቧል:: አቡኑ ተሳስተው ይሆን? ያነ የሆነውን እስኪ እንመልከት?

የካቲት 22 ሌሊት የጣልያን ጦር ለውጊያ ከመነሳቱ በፊት ከባድ ድግስ ተዘጋጅቶለት በፌስታ ነበር:: የጣልያን ወታደሮችም የኢትዮጵያን ሰራዊ ለመውጋት ከሳውራ ተነስተው ገንዳብታ ሲደርሱ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ነበር:: ውጊያ ከመግባታቸው በፊት እረፍት እንዲያደርጉና በሚገባ እንዲመገቡ ታዘዙ:: በቆርቆሮ የታሸጉ ምግቦችን በልተው የሚበቃቸውን ያህል ውሃ ጠጥተው ለውጊያ ዝግጁ ሆነው የኢትዮጵያ ሰራዊት ወዳለበት መስመር በደፈጣ መግባት ጀመሩ::

የኢትዮጵያ ጦር መኮንኖች ደግሞ ቤተ ክርስትያን ጸሎት ላይ ነበሩ:: የጣልያኖች የተኩስ ድጽም እንደተሰማ ኢትዮጵያኖቹ የጳጳሱ አቡነ ማቴዎስን መስቀል እየተሳለሙ ወደ ውጊያ ገቡ:: እህል አልቀመሱም:: ውሃም አልጠጡም:: በጥድፊያ ወደ ሰልፋቸው አመሩ:: ውጊያው ተጀመረ:: የጣልያን ጦር በሶስት አቅጣጫ ተለጥጦ በመምጣቱ ጦርነቱ ከጠዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ አስራ አንድ ድረስ ቅልጥ ብሎ ዋለ::

የኢትዮጵያ ጦር ቀኑን ሙሉ የተዋጋው እህል ውሃ ሳይቀምስ ነበር:: ጦርነትን ምክንያት አድርጎ የገናን ጾም ሳይሽር : አሁንም ውጊያውን ምክንያት አድርጎ ሁዳዴን ጾም ሳይሽር እየጾመ ተዋግቶ የኢትዮጵያ ሰራዊት ደል አደረገ:: አቡነ ማቴዎስ አልተሳሳቱም ነበር:: ጳጳስ ይሉሃል እንዲህ ነው:: ሃሞተ ኮስታራ:: የእምነት ሰው::
አቡነ ማቴዎስ የአድዋን ጦርነት ከሚመሩት ሰዎች አንዱ ነበሩ

***
አቡነ ማቴዎስ በመንፈሳዊው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ጦር የበላይ ሆነው ከሚመሩትና ከሚያስተባብሩት አዝማች መሪዎች ውስጥ አንዱ ነበሩ:: የጦር እቅዱ ላይ ከጦር መሪዎቹ ጋር አብረው ይመክራሉ:: የጦር ውሎ ግምግማ ላይም ተሳታፊና ዋነኛ ተዋናይና ገምጋሚም ነበሩ:: ለምሳሌ የአምባላጌን የጣልያን ምሽግ የሰበሩትና ድል ያደረጉት ጀግናው ራስ መኮንን መቀሌ ላይ ያንን መድገም ባለመቻላቸው ራስ መኮንን ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ ካቀረቡት መሃል አንዱ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ::

The Battle of Adwa የሚለውን ግሩም መጽሓፍ የጻፉት ፕሮፌሰር ሬይመድ ጆናስ አቡነ ማቴዎስ ከኢትዮጵያ ጦር ዋና መሪዎች አንዱ እንደነበሩና እያንዳንዱን የውጊያ ውሎ ግምገማ ላይ እንደሚሳተፉ እንዲህ ሲሉ ይጠቅሱታል

Jonas, Raymond; Jonas, Raymond Anthony. Battle of Adwa : African Victory in the Age of Empire. ገጽ 139

" on the ninth, Ras Meconen forces launched a major assault on the fort ( Mekeles fort), taking heavy casualities. The loss of life pained Ras Meconnen, but the reaction from Ethiopian leadership was pitliess. Taitu, Menelik, Tekle Haymanot and Abune Matewos turned on Meconnen and accused Ras Meconeen."

ከዚህ ጽሁፍ መረዳት የምንችለው Ethiopian leadership ብሎ በአራተኛነት ያስቀመጣቸው አቡነ ማቴዎስን ነው:: አቡኑ ከሰራዊቱ ጋር ሆነው የሚያጽናኑ ብቻ አልነበሩም:: የኢትዩጵያ ጦር አመራር አካል ውስጥ አንዱ ነበሩ:: ውጊያ ሲበላሽ ይገስጹ ነበር:: ራስ መኮንን ከፍተኛ ባለስልጣን ቢሆኑም -ስልጣናቸውን ፈርተው አቡኑ ዝም አላሉም:: ስብሰባ (post combat evaluation) ላይ ተገኝተው ወቅሰዋቸዋል::

አጼ ምኒሊክ ራሳቸው ከባድ ውሳኔ ሲያጸኑ አቡነ ማቴዎስን አማክረው ነበር

***
ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ጣልያንን ድል ካደረጉ በኋላ ምርኮኞችን በተመለከተ በኢትዮጵያ አመራሮች መካከል ከፍተኛ ክርክር ተደርጎ ነበር:: የመጨረሻውን ውሳኔ ንጉሡ የወሰዱት የአቡነ ማቴዎስን አማክረው ነበር:: አሁንም ዝነኛው ፕሮፌሰር ሬይመድ ጆናስ ዘ ባትል ኦፍ አድዋ በሚለው መጽሓፋቸው ገስ 234 ላይ እንዲህ ይላሉ
" by all accounts, Menelik represented the voice of moderation. As Paul Lairbar put it, " his natural goodness inclined him toward forgivness. In the end Menelik took consel of ABUNE MATEWOS, who sides with Taitu, Alula, Mengesha and the others"

ጦርነቱ ላይ የተከናወኑ ሌሎችም በርካታ ውሳኔዎች ላይ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ::

እና ምን ለማለት ነው

***
የአድዋ ጦርነት ዲሎማሲ ዘመቻ ላይ አንዷ ዲፕሎማት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ነበረች( እነ ቄስ ወልደሚካኤል)

ዲፕሎማሲው ፈርሶ ጦር ሲታወጅ አንዷ ዘማች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ነበረች:: የቀረ የለም:: ጽላቱ: ካህኑ: መነኩሴው : ጳጳሱ ዘምቷል

ጦርነቱን በበላይ ሲመሩ ከነበሩ አካላት አንዷ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ
የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ ለዋና ዋና ውሳኔ ዋና አማካሪያቸው ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ

አቡነ ማቴዎስ የውጊያ ውሎን ይገመግሙ ነበር:: የተበላሸ ሲመስላቸውም የጦር መሪዎችን ይገስጹ ነበር
አረ ሰራዊቱን በዙር ቦታ እያስያዙ የሚያሰፍሩት መነኮሳቱ ነበሩ
ወዘተ ወዘተ

እናጠቃለው
***
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የነጻነታችን ባለውለታ ናት:: በባርነት ቀንበር ስር እንዳንማቅቅ ተጋድለውና ተሰውተው ለሀገራችን ነጻነትን የሰጧት ቅዱሳን መንፈሳዊ አባቶቻችንም ጭምር ናቸው:: አድዋ ላይ ጣልያንን ድል ያደረግነው -በቅዱሳን አባቶቻችን መንፈሳዊ ጸሎትና ስጋዊ ተጋድሎም ጭምር ነው::
አድዋ ሲነሳ ባለታሪኳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንም አትረሳ:: ስሟ ይነሳ:: ዋናዋ የድል መሀንዲስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ናትና!
(Ze Addis)

መምህር እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን ቃለሕይወትን ያሰማልን!!!
20/02/2023

መምህር እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን ቃለሕይወትን ያሰማልን!!!

Memehir Girma Wondimu||የዘመኑ መንፈስ ላልሰሙት አሰሙ መንፈሳዊነት ይብለጥ

14/02/2023
14/02/2023

Ethiopia News - Feta Daily News | Ethiopian Airlines | Abiy Ahmed Ali | Tewelede Gebremariam | EU on Ethiopia | Sileshi Bekele Tigrai | general Abebaw Tades...

የዩቱብ ቻናሌን ሰብስክራብ እያደረጋችሁ❤
17/11/2022

የዩቱብ ቻናሌን ሰብስክራብ እያደረጋችሁ❤

ክብር ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን

Address

Abenfitsum@yahoo. Com
Addis Ababa
26179

Telephone

+251912605503

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tsadkane Mariam tours & car rent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tsadkane Mariam tours & car rent:

Share