30/08/2020
AT-MY TOUR AND TRAVEL AGENT
ዱባይ ለመሄድ የሚፈልጉ ከሆነ የሚከተሉትን ያስተውሉ።
1.ነጋዴ ሆነው ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ዱባይ የሚሄዱ ከሆነ ኤርፖርት ላይ በኢሚግሬሽን መ/ቤት የንግድ ፍቃድ ይጠየቃሉ።
2.ነጋዴ ሆነው ተመላላሽ እንደሆኑ የሚገልጽ ዱባይ ሲደርሱ ማህተም የተደረገበት ፖስፖርት ከሌሎት ደግሞ ንግድ ፍቃድና የባንክ መረጃ በኢሚግሬሽን መ/ቤት ሊጠየቁ ይችላሉ።
3.ንግድ ፍቃድ ከሌልዎት እና ለመጀመርያ ጊዜ የሚጓዙ ከሆነ የሚሄዱበትን ምክንያት በበቂ ማስረዳት ይጠበቃል። ለሥራ ተቀጥረው የሚሄዱ መሆኑን ከማህበራዊ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፍቃድ በኢሚግሬሽን መ/ቤት ሊጠየቁ ይችላሉ።
4.አረብ ኤምሬቶች ነዋሪ ሆነው ቪዛዎ ቢቃጠልም እስከ እዚህ አመት የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ ድረስ መመለስ ይችላሉ። ሆኖም ከሌሎቹ የኤምሬት ከተሞች ውጪ የመኖሪያ ቪዛ ያገኙት ከዱባይ ከተማ ከሆነ ተመልሶ ለመግባት የሚያስችል ፍቃድ ሊኖርዎት ይገባል።
5.ከ96 ሰአት ያልበለጠ ኮሮና ነጻ ማረጋገጫ ያስፈልጋል።
6.የጉዞ ኢንሹራንስ ያስፈልጋል
7.የታደሰ ወይም ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት ያስፈልጋል።
8.ጊዜው ያለፈበት ትኬት ከያዙ ለማስቀየር ኢትዮጵያ አየር መንገድ ስካይ ላይት ሆቴል ባለው ትኬት ቢሮ ያስቀይሩ ወይም የጉዞ ወኪሎን ያነጋግሩ።
9.,ስልክ መደወል ከፈለጉ 6787 ይጠይቁ።
10.ማስክ ያድርጉ ርቀት ይጠብቁ
ሳኒታዘር ኤርፖርት ውስጥ በየቦታው ስላለ ይጠቀሙ ።
መንገድዎ የተሳካ እነዲሆን እንመኛለን !!!
☎️☎️ 0910787979
0989641294
ኢሜይል: [email protected]
ቴሌግራም ቻናል:
እናመሰግናለን ::